April 15, 2023
6 mins read

የሁለት መነጽሮች ወግ – አስቻለው ከበደ አበበ ሜትሮ ቫንኩቨር ካናዳ

Isays and Meles were cousins
#image_title

Isays and Meles were cousins

የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ግዜ አንድ የተናገሩት ነገር ነበር፡፡ ይኸውም “ኤርትራውያን የአይናቸው ቀለም ካላማረን ማበረር እንችላለን” የሚል ነበር፡፡ ታዲያ ይህን የሳቸውን አባባል የሰማ ካድሬ የኤርትራውያን የአይን ቀለም ከኢትዮጵያውያን ይለያል ብሎ አራት ኪሎ ሰፈር ሲሞግተን ትዝ ይለኛል፡፡

አረ እባክህን የኤርትራውያን የአይን ቀለም እንደኛው  ጠቆር ያለ ቡናማ ወይንም ፈካ ያለ ቡናማ ነው ብንለው፡፡ አዎ ነው ግን ውስጡ ይለያል ብሎ ሊሞግተን ሞከረ፡፡ መቼም ሟቹ ጠ/ሚ ያንን ሲሉ አስተያታቸው ካለማረን ለማለት የፈለጉ ይመስለኛል፡፡

መቼም በሃገራችን ስለአይን የሚነገር ብዙ አባባል አለ፡፡ ለምሳሌ፣ “ነገር በአይን ይገባል” እና “ከፍትፍቱ ፊቱ” የሚለውን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ፊቱ የሚለውን ቃል አይንና አተያዩን ስለሚገልጽ የቁጣን፣ የሃዘኔታንና የደስታን አተያይ በአይናችን ላይ ሰለሚገለጽ፣ምንም እንኳን ፊት ላይ ከናፍርት የሚገልጹት ነገር ቢኖርም አይን ግን ዋነኛው ነው፡፡

ሰሞኑን በዋልታ ቲቪ፣ የትግራይ ክልል ግዚያዊ ር/መስተዳድር የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ከጋዜጠኛ ስሜነህ ባይፈርስ ጋር የደረጉትን ቃለ መጠየቅ ስንመለከት አንድ ነገር መታዘብ እንችላለን፡፡ ስሜነህ አይኑን የሚያሳይ ግን ቅርጹ ላይ ለውጥ ያደረገ መነጽር አድርጓል፡፡ አቶ ጌታቸው ደግሞ አይናቸውን የማያሳይ ጥቁር መነጽር አድርገዋል፡፡

በብዙ የአለማችን ባህሎች ውስጥ የሚባል አንድ አባባል አለ፡፡ ይኸውም አይናችን ነፍሳችንን የሚያሳይ መስኮት ነው” (The Eye is the window to the soul) ይህ አባባል ዝም ብሎ የተነገረ አይደለም፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክነያቱ አይናችን ላይ ፍርሃታችንና ጠሊቁ የውስጥ ስሜታችን ስለሚንፀባረቅ ነው፡፡

አቶ ጌታቸው በትግራይ ሰለደረሰው ውድመት፣ በአካባቢያቸው ከሉ ከአማራ፣ አፋርና ኤርትራ ህዝቦች ጋር ሊኖር ስለሚገባው ግንኙነት፣ ስለ መዓከላዊ መንግስት ግንኙነት፣ስለተጠያቂነት፣ ስለ ፖለቲካል ሚሰ ካልለኩሌሽን… አውርተዋል፡፡ ትግራይ፣ አማራና አፋር መውደማቸውንም ተናግረዋል፡፡ ከመዓከላዊ መንግስት ጋር የተደረገው ውይይትና ደርድር ከአማራና አፋሩ ጋር ሊደረግ እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡ እሰየው ባደረገው!!!

ታዲያ ይህን ሁሉ ሲናገሩ በጥቁር መነጽር ፊታቸውን ሸፍነው ነበር፡፡ ጋዜጠኛውም በእርግጥ ሙህር በሆኑበት በህግ ሞያና በ””ፈላስፋነት” አሞካሽቶ ነበር ያቀረባቸው፡፡ እውነት ለመናገር ግን ትግራይ ውስጥ ከጦርነቱ በኃላ የፍልስፍና እውቀቱን ያሳየን የቀድሞው ኢ.ን.ሳ ም/ዳይሬክተር የነበረው ቢኒያም ተወልደ ብቻ ነው፡፡

አቶ ጌታቸው ረዳ ፊታቸው በማስክ መጨንበላቸው ከእራሰቸው ፖለቲካዊ ጌም አንጸር ልክ ነው፡፡ ግን ነገራቸውን የሚያጋልጡባቸው የእጅ ገለጻ (Gesture) እና አካላዊ ገለጻ (Body Language)  ነበሩ፡፡

ከንፈራቸውን ይነክሱ ነበር፡፡ አንደ ህንዶቹ ነመስቴ የሁለት እጃቸውን መዳፍ ያጋጥሙ ነበር፡፡እጃቸውን ያጣምሩ ነበር፡፡ እጀቻቸውንም ያወራጩ ነበር፡፡ለምንድን ነው እሳቸው ቦዲ ጋርድ ይመስል ጥቁር መነጽር ያደረጉት ብለን እራሳችንን ብንጠይቅ፣ መልሱ በሳይንሳዊ መንገድ ሌላ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ማለትም የቀረጻው ቅንብር እንዳለ ሆኖ፡፡

አይን የሚጋልጠው ብዙ ነገር አለ፡፡ ለምሳሌ ከቀኘኝ ወደግራ የሚንቀሳቀስ አይን፣ አይንን ድንገት አተልቆ ማሳየት፣ የሚርገበገብ አይን፣ ወደ ላይ ቅንድብ ስር የሚወሸቅ አይን፣ ግራ ጥግ ወይንም ቀኝ ጥግ የሚወሸቅ አይን በስለላው አለም ውስጥ ትረጉም አላቸው፡፡

እንግዲህ አቶ ጌታቸው ሳይንሳዊ ሆነው ነው ቃለ መጠይቁን ያደረጉት፡፡ ሳይንሳዊ የሆነ ዲፐሎማሲ ስለተጠቀሙ ነው፣ ድቄት ሆነው ተበትነዋል የተባሉት ድፎ ዳቦ ሆነው ተመልሰው የመጡት፡፡ መንግስትስ (ዋልታዎችስ)?

 

አስቻለው ከበደ አበበ

ሜትሮ ቫንኩቨር ካናዳ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

341072451 932058051319883 406324785318022085 n
Previous Story

የመቃብር ጠባቂዎች ኃይል ትንሳዔውን አላስቀረውም፤ (ክርስቲያን ታደለ – የህ/ተ/ም/ቤት አባል)

abiy divider
Next Story

የጭራቅ ሽማግሎች-አዞ ሲውጥ ያለቅሳል፣ ዕባብ ሲነክስ ይለሰልሳል፣ በግ ያራጁን ቢላ ይልሳል

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop