የመቃብር ጠባቂዎች ኃይል ትንሳዔውን አላስቀረውም፤ (ክርስቲያን ታደለ – የህ/ተ/ም/ቤት አባል)

April 15, 2023
7 mins read
341072451 932058051319883 406324785318022085 n
#image_title

341072451 932058051319883 406324785318022085 n

በቅድሚያ በአገር ውስጥና በውጭ ለምትገኙ ለመላው ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያዊያት እንኳን ለ2015 ዓ.ም የስቅለትና የትንሳዔ በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ።

በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንዱ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለትና የትንሳዔ በዓል ነው፡፡ ትንሳዔ የሚለው ቃል በክርስትና ኃይማኖት አስተምኅሮ መሰረት «መነሳት» ማለት ሲሆን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፥ አዳም በሳተ ጊዜ፥ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ብሎ በገባለት ቃል መሰረት በቀራኒዮ ተሰቅሎ በ3ኛው ሌሊት «መግነዝ ፍቱልኝ፥ መቃብር ክፈቱልኝ» ሳይልና የመቃብር ጠባቂዎች ኃይል ሳያግደው ሞትን ድል አድርጎ መነሳቱን የምናበስርበትና የምናስብበት የፍቅር፣ የደስታና የድል በዓል ነው።

341254968 579488150943914 7404021278827696608 n

የትንሳዔ በዓል ኃቅንና እውነትን ወግነው ለቆሙ ሁሉ ከሞት አጠገብ ሕይወት፤ ከመቃብር አጠገብ ትንሳዔ መኖሩን የምናስብበት፤ ፈጣሪ ለሰው ልጆች ያለውን ጥልቅ ፍቅር በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞታችንን በሞቱ ድል አድርጎ የመዳንን ጸጋ ያገኘንበት፤ ስለ ፍቅር የሚከፈለውን መራራ መስዋእትነትን ያየንበት፤ ትኅትናንና ይቅር ባይነትን የምንማርበት ታላቅ በዓል ነው፡፡
ትንሳዔ የተስፋ መሟሸሽንና ሞትን የማሸነፍ በዓል ነው፤ በእለተ አርብ በጦር ጉልበታቸው የሚተማመኑ ሮማውያንና ሁሉን እናውቃለን በሚሉ ፈሪሳውያን የሀሰት ክስና ፍርድ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ መዋሉን ተከትሎ ፀሐይ የጨለመችበት፣ ጨረቃ ደም የለበሰችበት፣ ከዋክብት የረገፉበት እና ሞት የነገሰበት እንዲሁም ብዙዎች ተስፋ የቆረጡበት እለት ነበር፡፡ የጌታ ትንሳዔ በመከራና በጨለማ ውስጥም ሆነው ኃቅንና እውነትን ወግነው ለቆሙትና በጽናት ለጠበቁት ግን ከጨለመችው ፀሐይ ባሻገር አማናዊ ብርሃን፣ ደም ከለበሰችው ጨረቃ ባሻገር በደሙ የሚድኑ የሰው ልጆች መኖራቸውን፣ ከረግፉ ከዋክብት ባሻገር በሞቱ ሞትን ድል የሚነሳ አምላክ መኖሩን ያዩበት የድል እለት ነው፡፡
ዛሬ ላይ የዘመናችን መቃብር ጠባቂዎች የሕዝባችንን ፈተና በማብዛት እጅግ አስከፊ ለሆነ ሰቆቃ ዳርገውት ይገኛሉ። ይኼ ፈተና ትናንትም የነበረ፤ ዛሬም የቀጠለ፤…ነገ ግን በብርቱ የጋራ ትግላችን ወደ የሁሉም፥ በሁሉም የሆነች ፍትኅ የሰፈነባት፣ ነፃነት የለመለመባት፣ እኩልነት የተንሰራፋባትና ዴሞክራሲ የዳበረባት ኢትዮጵያን እውን በማድረግ በድል የምንደምቅበት ይሆናል። ነገ የሌላቸው አካላት ዛሬያችንን ቢያበላሹትም፤ ትናንት የሌላቸው ሰዎች ለትዝታ አልቦነት ደዌያቸው ፈውስ ዛሬያችንን ቢያጠለሹትም፥ ከአምላክ ጋር ወጀቡን በድል ተሻግረን በትንሳዔያችን እንደምቃለን። ይኼ ተጠየቅ የማይቀርብበት እውነታ ነው። በትናንታችን ብቻ ሳይሆን በነጋችንም ብሩኅ ተስፋ የሚቀኑ የጥፋት ማኅበርተኞች ከዚህም በላይ በብርቱ እንደሚፈትኑን ለኃቅ የቀረበ ግምት ነው። ፈተናው በበረታ ቁጥር ትንሳዔያችን እየቀረበ ለመሆኑ ማረጋገጫ ነውና፥ በጽናት እንበርታ።
የመቃብር ጠባቂዎች ኃይልና ብርታት የክርስቶስን ትንሳዔ እንዳላስቀረው ሁሉ፤ የዘመናችን መቃብር ጠባቂዎች የሕዝባችንን የፍትኅ፣ የነፃነት፣ የእኩልነትና የዴሞክራሲ ትንሳዔ የማርዘም ካልሆነ የማስቀረት አቅም ከቶውንም ሊኖራቸው አይችልም። ትንሳዔው እንደማይቀር፤ ያለስቅለትም ትንሳዔ እንደማይኖር እሙን ነው። ከተባበርን፣ ከተናበብን፣ ከተደማመጥንና በጋራ ጸንተን ቆመን የሕዝባችንን አቅም በሚገባ መጠቀም ከቻልን፥ በስቅለቱና በመከራው መጨረሻ ሕዝባችን ትንሳዔን ሲጎናፀፍ፥ የሕዝባችን ጠላቶች ደግሞ የኃፍረትን ማቅን ይለብሳሉ።
የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳዔ በዓልን ስናከብር አንድነታችንን በማጠናከር፤ ቤት ንብረት ወድሞባቸው የተፈናቀሉትን፣ ተንከባካቢ የሚሹ አረጋውያንን፣ የጎዳና ተዳዳሪዎችን፣ የኑሮ ሁኔታ ያልተሟላላቸውን እንዲሁም የታመሙና በእስር ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን በመጠየቅ እንዲሆን የአደራ መልእክቴን አስተላልፋለሁ።
መልካም የስቅለትና ትንሳዔ በዓል!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

336535470 924221495496660 2223212718077548013 n
Previous Story

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ

Isays and Meles were cousins
Next Story

የሁለት መነጽሮች ወግ – አስቻለው ከበደ አበበ ሜትሮ ቫንኩቨር ካናዳ

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም

አቢይ አህመድ ታላቁን አሜሪካንና የተቀሩትን የምዕራብ ካፒታሊስት አገሮችን ማታለል ይችላል ወይ? የአሜሪካ “ብሄራዊ ጥቅምስ ኢትዮጵያ ውስጥ“ እንዴት ይጠበቃል? የአሜሪካ እሴቶችስ(Values) ምንድን ናቸው?

ለመሳይ መኮንና ለተጋባዡ የቀድሞ “ከፍተኛ  ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት” በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን የስቴት ዴፓርትሜንት ውስጥ ተቀጥሮ ለሚስራው ኢትዮጵያዊ ሰው የተሰጠ ምላሽ!   ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ግንቦት 19፣ 2016(ግንቦት 27፣ 2024) መሳይ መኮንን በአ.አ በ17.05.2024 ዓ.ም አንድ እሱ  የቀድሞው “ከፍተኛ የኢትዮጵያ

ጎንደር ሞርታሩን እስከ ጄነራሉ ተማረከ | ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | ብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን

ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | “ፋኖ ከተማውን ቢቆ-ጣ-ጠር ይሻላል” ከንቲባው |“አብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን” ኮ/ሉ |“በድ-ሮን እንመ-ታችኋለን እጅ እንዳትሰጡ” ጄ/ሉ
Go toTop