የመጨረሻው፣መጨረሻ April 2, 2023 ግጥም Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email ስንፈራው የነበረ፣ስንሰጋው የከረመ ግዘፍ ነስቶ፣ሥጋ ለብሶ ጥርሱን አግጦ፣ዐይኑን አፍጦ ክንዱን አፈርጥሞ፣ቀንዱን አሹሎ ሾተል ጦሩን፣ሰብቆ ስሎ ተገትሯል ከደጃችን:: የመጨረሻው፣መጨረሻ የዕውር ጉዞ መዳረሻ ድንበር ዳሩን፣ለመገመት ፍጻሜውን፣ለመተንበይ ብዙም አይከብድ:: ባይሆን ተብሎ የሚፈራው ሁሉን ነገር ተቆጣጥሮ መሪ ሲሆን፣ስፍራ ሲይዝ ጠፍቶ እርጋታ፣ሀገር ሲያብድ:: ቀድመው ላወቁ ለነቁ ላሳሰቡ፣ላስጠነቀቁ መዘከርያ ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, መጋቢት ፳፬/፳፻፲፭ ዓ.ም April 2/2023 እሁድ)2:01(ሚኪ.ላ/አ.አ ©ያመጌዕ Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ Previous Story የ አማራ ልዩ ሀይል – አዲስ የተሰጠን የአታካሮ አጀንዳ Next Story ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ – መላ መላ ብለው ኅሊናዎን አበርትተው ለንሥሃ ይብቁ! – ከበየነ