ኢትዮጵያና የእርዳታ ታሪኳ
ብዙዎቻችን ሰፋ ያለ ትንታኔ ለማንበብ ፈቃደኛ አይደለንም። ወደ ኋላ ዞር ብሎ ማየት ግን የአሁኑንና የወደፊቱን ሁኔታ ለመቃኘት ይረዳናል። የዚህ ወቅታዊ ትንተና ዋና ምክንያት ኢትዮጵያን ከድህነት አሮንቃ ለማውጣት የሚቻለው አገርንና መላውን ሕዝቧን በማፍቀርና በማሰቢ ባለቤትና ኢላማ አድርጎ የሚሰራ የመንግሥት አመራር ከሌለ የውጭ ድጎማና እርዳታ የጅቦችን ኪሶች ይሞላል፤ ጡንቻ ይሰጣል እንጂ ተራውን ሕዝብ ሊረዳ አይችልም የሚል ነው።
የውጭ ድጎማ፤ ብድር ታሪክና ሂደት
ኢትዮጵያ የጣልያንን ፋሽስት ኃይል እንደገና አሸንፋ ነጻነቷን ከተጎናጸፈች በኋላ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት አጋር የነበረችው ዩናይትድ ኪንግደም ለኢትዮጵያ እርዳታ መስጠት ጀመረች። እንግሊዝ እርዳታዋን በ 1952 አቋረጠች፤ አሜሪካ ተካቻት። ከ 1950-1970 ባለው ጊዜ መካከል ኢትዮጵያ ከአሜሪካ፤ ከዓለም ባንክና ከሌሎች ለጋሶች ያገኘችው የእርዳታ መጠን $600 ሚሊየን ይገመታል። አንድ ሶስተኛ የሚሆነውን የለገሱት አሜሪካኖች ናቸው። የሶቭየት ህብረት $100 ሚሊየን፤ ዓለም ባንክ $121 ሚሊየን ለግሰዋል። የእርዳታው መጠን በዓመት ሶስት ሚሊየን ዶላር ይገመታል። በአሁኑ ወቅት፤ አሜሪካ ብቻ በያመቱ ለኢትዮጵያ የምትለግሰው አንድ ቢሊየን ዶላር ነው። አሜሪካ ለደርግ