ቀደም ሲል በአገር ቤት የምትታመውንና በአሁኑ ጊዜ በገዥው ስርአት በነጻ ፕሬስ ላይ በሚደረገው ዘመቻ የመጨረሻው ሰለባ በመሆን ላይ ያለችውን ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣን ህይወት ለመስጠት እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወሳል።
ከእንቅስቃሴው አንዱ መገለጫ የህትመት መሳሪያ ግዥ ፕሮጀክት ሲሆን ለዚህ ፕሮጀክት መሳካት በሀገርም ሆነ በውጭ በርካታ ወገኖቻችን ለጥሪው ምላሽ በመስጠት ላይ መሆናቸው እጅግ አበረታቶናል ።በተለይ በውጭ የሚገኙ ወገኖቻችን ምላሽ ለዚህ ፕሮጄክት መሳካት ቀዳሚውን ስፍራ ይዞ ይገኛል ብለን እናምናለን።
ይህንኑ ጥረት ለማሳካትና እንዲሁም አገራችን የምትገኝበትን ወቅታዊ ሁኔታ ከኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው ጋር ለመወያየት አቶ ግርማ ሰይፉ የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀ መንበርና በፓርላማ ብቸኛው ተቃዋሚ በሰሜን አሜሪካ አንዳንድ ከተሞች ከወገኖቻቸው ጋር ውይይት የሚያደርጉ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በሚደረገው በዚህ ዙር የተካተቱት በሚከተሉት ከተሞችና ቀናት ይሆናል።
April 7/2013 Huston
April 10/2013 Lasvegas
April 10, 2013 —- Las Vegas
April 14/2013 Washington DC
April 20/2013 Los Angeles Via Skype
April 21/2013 Atlanta
April 27/2013 Minesota
April 28/2013 Boston
በመሆኑ በነዚህ ከተሞች የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በአስተባባሪዎች በሚዘጋጁ መድረኮች ተገኝታችሁ በሃገር ቤት ውስጥ ስለሚደረገው ትግል ውይይት እንድናደርግና በዚሁ አጋጣሚም ፍኖተ ነጻነት ተመልሳ ህያው መሆን አጋርነታችሁን እንድታረጋግጡልን በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን።
በዚህ ዙር በተዘጋጀ መድረክ ውይይት በማይካሄድባቸው ከተሞች ያላችሁ ወገኖቻችንም ያለንን የአቅም ውሱንነት ተገንዝባችሁ ቀደም ሲል በጀመራችሁት መሰረት በፍኖተ ነጻነት አካውንት በፔይፓል፤ በቼክ ፤ ወይም ቀጥታ በባንክ ሂሳብ ድጋፋችሁን እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
በተባበረ ክንድ የጀመርነውን ጥረት እናሳካለን
በሰሜን አሜሪካ የፍኖተ ነጻነት አስተባባሪ ኮሚቴ