“የአድዋን 127ኛ በዓል የዐብይ ብልጽግና ሲያኮላሸው ዝም ልንል አንችልም” አክሎግ ቢራራ (ዶር)

“ ከሲኦል ተመልሰንም ቢኾን ኢትዮጵያን እንበታትናታለን”! ህወሃት የአማራውን ሕዝብ ለማስፈራራትና ወልቃይትን ለማጠቃለል የሰጠን ማስጠንቀቂያ “ጠንካራ ሕዝብ አንድነቱንና ክብሩን በደሙ ያፀናል”

የአማራ ክልል ፕሬዝደንት ዶር ይልቃል ከፋለ
“ሞት ሰለቸኝ፤ ውሸት ሰለቸኝ”
ኦባንግ ሜቶ፤ የሰብአዊ መብት ጠበቃ
“ዛሬ የውርደት ቀን ነው”
አንዳርጋቸው ጽጌ፤ የአድዋን የድል በዓል ብልፅግናዎች ሲያቃውሱት ተመልክቶ የተናገረው

“የፋሺስት ጣሊያን ጀነራል ግራዚያኒ ከሙታን ተነስቶ እንደገና አዲስ አበባን ይዞ የየካቲትን ፍጅት ሊድግም ነው? ይኽ ምን ይባላል? አቢይ አሕመድ እንደ ሮማዊው ቄሳር እንደ ኔሮ እንጦጦ ላይ ተሰይሞ ክራር እየተጫወተ በተድላ ደስታ እየተዝናና ይሆን?”

ፕሮፌሰር ጳውሎስ ሚልኪያስ

“He (Abiy Ahmad) intentionally closed his eyes to the TPLF’s maneuver to keep its modern weaponry and its professional defense forces. It seems that Abiy and the TPLF have silently agreed that the handing over of old weapons and the disbanding of TPLF recruits is enough to fool Ethiopians into believing that the TPLF has disarmed. “

 

Journalist Leo Okere, “Abiy Ahmad’s Machinations for Amharafrei,” February 22, 2023 ( https://zehabesha.com/abiy-ahmads-machinations-for-amharafrei-ethiopia/)

የዚህ ሃተታና ምክረ ሃሳብ ዋና ምክንያት ህወሃታዊያን፤ ኦህዴዳዊያን/ ኦነጋዊያንና የኦሮሞ ብልጽግና የዘውግ አክራሪዎች፤ ተተኪዎችና መሪዎች በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት በሚያምኑ አካላት፤ በተለይ በወጣቱ ትውልድ አባላት ለይ የሚያካሄዱትን ዘርፈ ብዙ ግፍና በደል የሚፈጽሙት በታቀደና ስልት ባለው ደረጃ እንጅ በዘፈቀደ አለማሆኑን ለማሳየት ነው።

ለዚህ መረጃ ካስፈለገ የዐብይ ብልጽግና መንግሥት የአድዋን በዓል ፍጹምና አደገኛ ወደ ሆነ ጠባብ ብሄርተኝነት ለመቀየር መሞከሩ ነው። ይህ የፖለቲካ ቁማር አብዛኛውን የኦሮሞን ሕዝብ ይወክላል የሚል እምነት የለኝም። የሚያጠናክረው ክስተት ግን የማዘናጋትና አጀንዳዎችን የመቀያየር ጥበበኛ የሆኑት ጠቅላይ ሚንስትር (The Prime Minister who excels in the art of deception) ኢትዮጵያን ከአንድ ግጭት ወደ ሌላ ግጭት፤ ከአንድ ቀውስ ወደ ሌላ ቀውስ እያሸጋገሯት መሆኑን ለማሳየት ነው። ህወሃት እኔ ካልገዛኋት ኢትዮጵያን እበታትናታለሁ ብሎ ፎከረ። ኦህዴድ/ኦነግ/የኦሮሞ ብልጽግና እኔ ኢትዮጵያን አፈራርሸና አድሸ ሙሉ በሙሉ የበላይ ሆኘ ካልገዛኋት ብዙ ሚሊየን ሕዝብ ቢጨፈጨፍ አልጠየቅም የሚል መርህ ይከተላል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የመጨረሻው ደወል - አንዱ ዓለም ተፈራ

የበላይነት የፖለቲካ ዘዴው ከፈረንጆች የተቀዳ ከፋፍለህ ግዝው መሆኑን መገንዘብና እኛ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት የምናምን ግለሰቦችና ስብስቦች ከጎጥ፤ ከመንደር፤ ከብሄር፤ ከኃይማኖት መለያ በላይ መጥቆ በመውጣት፤ ያለ ምንም ማመነታታት የምንሰበሰብበት፤ የምንደረጃበትና አማራጮችን የምንቃርብበት ወቅት ነው። ይህ ለነገ የሚተው አይደለም።

ዛሬ ኢትዮጵያ በፖለቲካ ሥልጣን ፍላጎት የሰከሩ ብሄርተኞች የሚገዟት አገር እንጅ፤ በሕግ የበላይነት፤ በሕዝብ እህትማማችነት/ወንድማማችነት/አንድነት፤ በእውነተኛ እክሉልነትና በፍትህ የሚያምን የመንግሥት አመራር የላትም። መንግሥት አለ ብሎ ለመናገር የሚያስችል ሁኔታም የለም። ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ ተንቃለች ብል አልሳሳትም።

ለምሳሌ፤ እስከ አፍንጫው የታጠቀው የኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል የሱዳንና የደቡብ ሱዳንን ወረራና ሰፊ መሬት ነጠቃ ሊከላከል አልቻለም። በተጻራሪው ግን ሕዝብን ለማስፈራራት ሲባል በአዲስ አበባ የጦር ጀቶችና ሄሊክፕተሮች ሰማይና ምድሩን ሲቆጣጠሩና ሕዝቡን ሲያስፈራሩ ታይተዋል። ሕዝብ እንደ ጠላት የሚታይባትን አገር በሃያኛ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ማየት ያማል፤ ያሳፍራል፤ ያዋርዳል። ጠላቱ ማነው? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው።

የፖለቲካ ጠበብቱ አንዳርጋቸው ጽጌ ባለፈው የአድዋን 2023 የድል በዓል ለማየት በአዲስ አበባ እየተዘዋወረ የአይን ምስክር ሆኖ የተናገረውን ታሪክ ሲጠቅሰው ይኖራል። “ዛሬ የውርደት ቀን ነው” ያለው ወዶ አይደለም። የተናገረው ሃቁን ነው። በኦሮሞ ብልጽግና አቀነባባሪነትና አመቻችነት ኢትዮጵያን የሚገዙት ኦህዴዶች/ኦነጋዊያን ጽንፈኞችና እብሪተኞች ናቸው።

በሌላ አነጋገር፤ ህወሃትን ተክቶ ኢትዮጵያን በበላይነትና በአምባገነንነት በሚገዛው የኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲና በህወሃት መካከል ያለው ልዩነት ለይስሙላ ነው። በጋራ ጠላታቸው ላይ ይስማማሉ። የጋራ ጠላታቸው የአማራው ብሄር ለመሆኑ ተጨማሪ መረጃ አያስፈልገውም።

ግን፤ በአማራው ሕዝብ ላይ የሚካሄደው ግፍና በደል፤ የዱር አራዊት የመሰለ (barbaric) ግድያ፤ ማፈናቀል፤ ማሳደድና ማዋረድ ቀስ በቀስ በአፋሩ፤ በሶማሌው፤ በወላይታው፤ በጉራጌው፤ በትግራዩና በሌላው ኢትዮጵያዊ ላይ ሁሉ እንደሚደርስ አንጠራጠር። የሚካሄደው ፍጹም የሆነ ሁሉን አቀፍ የበላይነት ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዐማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል ርዕዮታዊ ዘርፍ - መስፍን አረጋ

ዋናው ብሄር ተኮር ጭካኔ በአማራው ላይ መሆኑን በተለያዩ ትንተናዎቸ ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ አሳይቻለሁ። አማራውን ከእልቂት እንዲድን ተከላክሎ ኢትዮጵያን ለመታደግ የሚቻለው ግን ሌላውንም በኢትዮጵያ የሚኖር ሕዝብ በመቀስቀስና በማበረታት እንጅ በመለያየት ሊሆን አይችልል የሚል እምነት አለኝ። ከፋፋዩን የኦሮሞ ብልፅግናን መንግሥት ካላጋለጥንና ከብሄር ባሻገር ካልተባበርን ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ልትቀጥል አትችልም።

እኛ የለት የለቱን አጀንዳ ብቻ ስለምናይ ነው እንጅ፤ ለዚህ አማራ ጠልነት ስር እየሰደደ መሄድ መሰረት የሆነው በ60ዎቹ ዓመታት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲና በውጭ ስለ የብሄረሰቦች ጥያቄ (The national question) ተብሎ ስለሚጠራው ጉዳይ በሰፊው ንትርክ የተካሄ ትርክት መኖሩንና የተማሪውን እንቅስቃሴ ከሁለት እንደ ከፈለው መርሳት የለብንም። ዛሬ “ከአማራ በላይ አማራ ነን” የሚሉት የአማራው ምሁራን፤ ግራ ክንፍ አባላትና ስብስቦች ይህንን ከስታሊን የተወረሰ ትርክት እንዳስተጋቡትና እንዳጠናከሩት የረሱት ይመስለኛል። ስንት ወጣቶች በፖለቲካ ልዩነት ተጨፍጭፈዋል? በኢትዮጵያ ፋይዳቢስ ንትርክ ምክንያት ያሸነፉት የብሄር ነጻ አውጭ ግንባሮች ናቸው—በተለይ ህወሃትና ኦነግ። ብአዴን እኮ የህወሃት ልጅ ነው።

በሌላ አነጋገር ህወሃት፤ ኦነግ፤ የኤርትራ ነጻ አውጭ ግንባርና ሌሎች ግንባሮች ይህንን የኢትዮጵያ ወጣቶች እንቅስቃሴና የብሄር ፖለቲካ ግብዓት ተጠቅመውበታል። በወቅቱ “ነጻ የምትወጡት ከማን ነው?” ብለን የጠየቅን ጥቂቶች ነን። ይህ ያለፈ ታሪክ ስለሆነ ወደ ጎን እተወዋለሁ።

የዐብይ ብልጽግና ዛሬ የሚከተለው የፖለቲካ መስመር መሰረት የብሄር፤ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ጥያቄ ነው። እኔ የምገነዘበው፤ ሰሜነኞች (አቢሲኒያዎች) ለሶስት ሽህ ዓመታት ገዝተዋል፤ መዝብረዋል፤ ጨቁነዋል ወዘተ እና አሁን ጊዜው የኦሮሞ ብልጽግና የበላይነት መሆኑን በውድ ሆነ በግድ ተቀበሉ የሚለውን ሃቅ ነው። ጠቅላይ ሚንስትሩ የዚህ ስር ነቀል ለውጥ ወገንተኛ ናቸው (Abiy is partisan to this tectonic shift).

በአንድ የዋሽንግተን ስብሰባ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን እኔና የኔ ጓደኛ ለመሆኑ “የአንተ ኢትዮጵያዊ ጀግና ማነው?” ብየ የኔ አጼ ቴዎድሮስና አፄ ምንኒልክ እንደሆኑ ነገርኩት። “እኔ ጀግና የለኝ” ያለው ትዝ ይለኛል።

ስላ ወቅቱ ተደራራቢ ቀውስ ምሳሌዎች ልስጥ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮ ቴሌኮም ለውጪ ሀገር ድርጅት ይሸጥ ወይስ አይሸጥ ? (መላኩ ከአትላንታ)

አማራው ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ ማገብ

በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ የሚካሄደው የአማራ ብሄር ጠልነትን በግልጽ በሚያሳይ ደረጃ አማራውን በብሄሩ እየለዩ ልክ በበረት እንደታጎረ እንስሳ “መጤ ነህ፤ ነፍጠኛ ነህ፤ የዱሮውን ናፋቂ ነህ፤ ውጣና አትገባም” ወዘተ እያሉ ከቤትና ከንብረቱ እያባረሩት ነው። ከዚህ የባሰ ግፍና በደል፤ ጭካኔና ዘረኛነት አለ? የለም።

በውጭ የሚኖረው ግዙፍ አማራ የተከፋፈለና ለዓላማ አንድነት በጋራ ለመቆም ያልቻለ ስለሆነ፤ ይህንን የህልውና ጉዳይ እንኳን ለማስቆም በኣንድ ላይ ሆኖ ጠንካራ አቤቱታ ለተባበሩት መንግሥታት ሰብአዊ ኮሚሽን፤ ለአሜሪካና አውሮፓ ባለሥልጣናት፤ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት፤ ለሂውማን ራይትስ ዎች፤ ለአምነስቲ ኢንተርናሺናል ለማቅረብ አልቻለም። ባጭሩ፤ ከግራ ክንፉ የወረስነው የእርስ በእርስ ጥላቻ፤ መነታረክና መከፋፈል አማራውን እየጎዳው ነው።

የኦሮሞ ብልጽግና መንግሥት አማራውን እንደ እንስሳ ማጎር፤ ማሳደድ፤ ማዋረድ፤ መጨፍጨፍና ከቀየው በገፍ ማስወገድ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ነው። በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ህግጋት መስፈርት ሲታይ ይህ ተደጋጋሚ ድርጊት የዐብይን ብልጽግና መንግሥት በሕግ ያስጠይቀዋል። ክስ መቅረብ አለበት። ለዚህ ባለሞያዎችን ለይቶ እንዲሳተፉ ማድረግና ገንዘብ መሰብሰብ ወሳኝ ነው።

 

ችግሩ ይህ ብቻ አይደለም።

አዲስ አበባ ወይንስ ሸገር?

ባለፈው “Is Abiy a liability or an asset?” በሚለው ድርሰቴ እንዳሳየሁት፤ አዲስ አበባን ለማዳከም፤ ፋይዳ ቢስ ለማድረግና በምትኳ “የሸገር ከተማን” ግንባታ በአስቸኳይ ስኪታማ ለማድረግ የሚደረገው የተቀነባበረ እንቅስቃሴ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን ይጎዳል። አዲስ አበባ ስትዳከም የሚጎዳው ማነው? ሸገርን ለመገንባት ፈሰስ የሚሆነውን ወደ አንድ ትሪልየን ብር የሚገመት መዋእለንዋይ ማን ይሸከመዋል? ሸገር የማን ከተማ ይሆናል? የሸገር የመጨረሻ ግብ ምንድን ነው? የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ ያስፈልጋል። ይህ መሰረታዊ ችግር ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን ይመለከታል።

 

የኢትዮጵያን ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በብሄር መክፋፈል ለምን?

የኢትዮጵያን ተዋህዶ ቤተክርስትያን በዘውግ ለመከፋፈል የሚደረገው ሴራ፤ የአድዋን አገራዊና ዓለም አቀፋዊ በዓል ታሪክና ገጽታ በማናጋት፤ በማዛባትና የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ በማድረግ ለኦነጋዊያን/ኦህዴዳዊያን/የኦሮሞ ብልጽግና መንግሥት አይን ያወጣ የበላይነት አመች ሁኔታዎችን የመፍጠር ሂደት አፍራሽ ነው። ዘረኝነት ነው።

 

https://zehabesha.com/the-abiy-ahmed-shimelis-abdissa-lawless-regime-and-amharafrei/

 

https://zehabesha.com/open-letter-to-the-norwegian-nobel-committee-3/

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share