የብአዴንን ስሪት ታሪካችን፤ባህላችን፤ማንነታችን ውስጥ ፈልጌ አጣሁት – አሰፋ በድሉ

አጭር ነገር ስለ እስክንድር ነጋ፡፡በቃ ጀግናው ዕየተጋደለ ነው፡፡ እኛስ? ስርዐቱ እንደ ትልቅ ግዳይ ስለሚያየው ይህንን አብረን ከማጮህ ተቆጥበን ይልቅ አሁንም ከፊታችን ስለተደቀነው አደጋ፤ዕለት ዕለት እየኖርነው ስለላ ህይወት ስለ ራሳችን አብዝተን እንደ እስክንድር እንኳን ባይሆን የተቻለንን እናድርግ፤፤ ታቅፈን ወንበር ላይ ያወጣናቸው ኦነጋውያን በትዕቢት ሰክረዋልና ከምድረ ገጽ ሊያጠፋን ከባድ ኦፐረሽን ላይ ናቸው!

የብአዴንን መግለጫ ተከትሎ ሁላችንም ባልተለመደ ሁናቴ በግማሽ ልብ ሆነን ግን ደግሞ ካለ በቂ ዝግጅት ህዝብ እንዳይጎዳ፤ውርደት እንዳይከተል በማለት ከዚህም፤ከዚያም አንዳንድ ነገር መወርወራችን አልቀረም፡፡ከፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ እንዲል መጽሃፍ ድርጊታቸውን መከታተል ይገባ ነበርና ለአብይም፤ለብአዴንም ቅርብ የሆኑ ሚዲያወች ተከታትለን እንደታዘብነው ብአዴን ከጌታው የተማረውን ኮንፍውዝ ነው መግለጫ ብሎ ያወጣው ለማለት እገደዳለሁ፡፡ካልሆነ በአጭር ጊዜ አቋሙን ቁልጭ እድርጎ ይውጣ፡፡ ለዚህ ማሳያ ሁለት ነገሮችን ላንሳ፡፡

1ኛ፡ አብይ ደውሎ የልዩ ሃይል ስልጠና እንዲያቆሙ በስልክ እንደነገራቸው ሰማን፡፡ ይህንን የዘገቡት ለአብይና ለብአዴን ቅርብ የሆኑ የሚታወቁ ሚዲያወች ከውሥጥ የመረጃ ምንጭ የተገኘ ስለሆኑ ለመቀበል እገደዳለሁ፡፡ በወቅቱ አናቆምም የሚል ምላሽ እንደሰጡ ነበር የተዘገበው፡፡እንዲያውም ለመግለጫው መውጣት እንደ አንድ ገፊ ምክንያት ተደርጎ ተዘገበ፡፡ይሁንና ትናንትና ማለትም በ17/06/2015 አንድ ሚዲያ ለክልሉ የጸጥታ ሃላፊ ደውሎ እንዳረጋገጠው የልዩ ሃይል ስልጠናው እንዲቆም ተደርጓል፡፡እንዲቆም የሆነበትን ምክንያት ያሉትን ሚዲያው ጨምሮ ጠቅሷል፡፡ዋናው ነገር ስልጠናው መቆሙ ተረጋግጧል፡፡ ብአዴን ማለት ይሄ ነው፡፡ማን እንዲጠብቀን ካላችሁ ብአዴንን ጠይቁት!

2ኛ፡የብአዴን አቋም ወይም መግለጫ ከ complaint ያለፈ ቢሆን ኖሮ ከፌደራል አካባቢ በተለይም ከእነ አብይ አካባቢ የሆነ እንቅስቃሴ ይታይ ነበር፡፡ወፍ የለም ይላሉ የዘመኑ ወጣቶች፡፡ እንደዚያ ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ ምናልባት እስኪረጋገጥ መጠበቅ ቢኖርብንም የት እንዳለ ሳይታወቅ የቆየው ለኢትዮጵያ በቂ ዋጋ የከፈለው፤አይበገሬው፤ ጀግናው እስክንድር ነጋ መጨረሻውን ያሳምርለት ባ/ዳር በፖሊስ ወደ ሰባታሚት ማረሚያ ሲወስዱት ታይቷል የሚል ዜና እየወጣ ነው፡፡ ዘመነ ካሴ ይቀበለዋል፡፡ብአዴን በቀደመ ግብሩ ነው ማለት እንግዴህ ይሄ ነው፡፡የአማራ ገዳይ፤አሳዳጅ፤ቤት አፍራሽ እስክንድር ነው እንዴ? እሱማ ለወገኑ፤ለአገሩ ያማረ ኑሮውን ትቶ ዋጋ እየከፈለ ነው፡፡ ጦር እያስጠጋ ያለው እስክንድር ነው? እና አማራ ዘሩ ቢጠፋ ምን ይደንቃል፡፡ በንጉሳቸው ፊት ግዳይ ጥሎ፤ሞገስ፤ሽልማት ማግኘት ነው ህልማቸው፡፡ደደቢታዊ የባንዳ አስተምሮ ነፍሱን ሳይቀር ሰጦ ሁሌም በጌታው ፊት ሞገስን እንደሚያገኝ ያስባል፡፡ ይህንን ነው እንግዲህ ብአዴናውያን ከወዴስ ተገኙ? እንደምንስ ባለ ባህል አደጉ ብለን እንጠይቃለን የምንለው፤፤ ምክንያቱስ እኛ የምናውቀው ባህል እንኳነስ ወንድሙን ባዕድ እንኳን ቢሆን ከአመነው አብሮት ይሰዋል፡፡ደም የመመለስ ባህል ዕኮ ጥቃትን ላለመቀበል የሚደረግ የክብር ዕዳ ነው፡፡መቅረት ያለበት ነው በዕውነቱ፡፡ መቼም በዘመነ አብይ ህግ ማስከበር ብለው ደግሞ ቆመው እንዳይቀሩ እንደፈረደብን እንመክራለን፡፡አብይ በርቱ እኛም ሸኔን ልክ እናስገባዋለን ብሎ ያንን ስድብ ይሰድባቸዋል፡፡ይህንን እየጻፍሁ እንኳን የሰሜን ሸዋ አዋሳኝ ከተሞች በኦነግ እየተደበደቡ ነው፡፡እኔ አነግ ስል ብልጽግናንና ኦፌኮን ጨምሮ ሁሉንም የኦነግ ክፍልፋዮች ማለታቸን ነው፡፡ እንዴት ወገንህ ሁለት እጅህን አስሮ ያስደበድብሃል፡፡ብአዴን የበረከት ስምዖን ዕጣ ሊደርሰው ይገባል በተለይም ከፍተኛው አመራር፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አገራችንን ከጥፋት፤ ሕዝባችንን ከመከራ ለመሰወር፤ በጌታ ፍቃድ - ከዶ/ር በቀለ ገሠሠ

እስቲ ስለ ጉደኛው ብአዴን የአቋም ፓርቲነት ትንሽ ማሳያ እናንሳ፤

1ኛ፡ የአያቱን ቤተ-መንግስት አፍረሶ ስሙን ቀይሮ ወደ ፓርክነት አውርዶ አያምርም  ሲለው ተኩላው፤ የጅል ሳቅ እየሳቀ በጣም በጣም ያምራል ክቡር ጠ/ሚ/ር በተለይ ስሙ አነድነት መሆኑ ለብልጽግና ህብረ-ብሄራዊነታችን ስኬት ነው ይላል

2ኛ፡ ደግሞም ኦነጋዊ ቤተ-መንግስት  እንሰራለን ሲለው፤ ከአርሶ አደሩ መዋጮ እንሰበስባለን ይላል ይቀጥሉ፤ግን ፒኮክ ይኖረዋል ይልና ጥያቄ ያክላል

3ኛ፡ አድዋን ሰርዞ የራሱን ፎቶ ሰቅሎ የውሸት ኦነጋዊ የትያቲር ታሪክ ሲፈጥር ብአዴን ትንፍሽ የማይል ለማዳ ውሻ ይመስላል

4ኛ፡ እናቱ ለህክምና አዲስ አበባ  ስትሄድ ጎሃ ጽዮን ስትታገት እንድ ለሚያውቀው ተረኛ ደውሎ እባካችሁ እገሊት የምትባል የእኔ እናት ስለሆነች አሳልፋልኝ ይላል ብአዴን-የዜጎች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር መብት መኖሩን ማወቁንም በዕውነቱ እጠራጠራለሁ

5ኛ፡ ብአዴናዊው የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ አዲስ አበባ የማን ናት ተብሎ ሲጠየቅ ስሩ ሁሉ መስመር መስመር ይሰራል፤ላብ ያጠምቀዋል፡፡

ስንቱን እናነሳዋለን ይቆየን

አሁን ወደ ዋናው ጉዳይ  ወደ እነ ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ልመለስ፡፡ አቋማቸውን ትናንትና በ17/06/2015 ጎንደር ባካሄዱት ስብሰባ ግልጽ አድርገዋል፡፡ ብዙ ነጥቦች የተጠቀሱ ቢሆንም ዋናው ፍሬ ነገር ህወሃት በሃይል አስፍሯቸው የነበሩት ወንጀለኞች ወልቃይት መምጣት የሚችሉት ለፍርድ ብቻ ነው፡ያሉት፡፡ይህ ማለት ሪፈረንደም አንቀበልም ነው፡፡ ትክክለኛ ውሳኔ ነው፡፡ሪፈረንደም እንዲካሄድ መፍቀድ ማለት ህወሃት በጉልበት የወሰደውን በማህተም ህጋዊነቱን ማረጋገጥ ማለት ነው፡፡ከቻልን መታገል ካልሆነ ያው ከአብይ ጋር ሆነው በጉልበት ይውሰዱት፡፡ኢትዮጵያና አማራ መሪ ሲያገኙ ይመለሰል፡፡አሁንስ ከ27 ዓመት በኋላ አይደል የተመለሰው፡፡ለልጅ ልጆቻቸው ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ ቦንብ ከሚቀብሩ የትግራይ ህዝብ አብዝቶ ቢያስብበት መልካም ነው፡፡ የደ/አፍሪካው የሠላም ስምምነት በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው የጎንደሩ ስብሰባ አንዱ ማሳያ ነው፡፡የአማራ መንግስት እንደ መንግስት በታዛቢነት ተገኘ ማለት የአማራ ህዝብ ወይም ምክር ቤት ተጠይቆ ይሁንታ የሰጠበት ተሳትፎ አልነበረም፡፡ስለሆነም ስምምነቱ በአማራ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት የለውም ማለት ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  እኛ ስናደርገው ትክክል ሌላው ሲያደርገው ወንጀል - ይገረም አለሙ

ወልቃይትና የአመራ ህዝብ ውሳኔ ይህ ከሆነ የብአዴንና አብይ እንዲሁም ህወሃት እና አሜሪካ ውሳኔ የሚታወቀ ቢሆንም ብአዴን ግን በመግለጫው ሊያምታታ እንደ ሞከረው ማለቃቀሱ አይቀርም፡፡እዚህ ላይ ለኦሮሞ ብልጽግና ሰወች አንድ ነገር እናስታውሳቸው፡፡በጣም ደጋግመው የሚናገሩት እኛ ርስት ለማስመለስ አልተዋጋንም ይላሉ፡፡በማያውቁት ነገር ሲዘባርቁ ከርመዋል፡፡በከብት ዕርባታ የሚተዳደር ማሃበረሰብ ሳርና ውሃ ባለበት ሁሉ መጓዝ እንጂ ርስት ምን ማለት እንደ ሆነ ላያውቅ ይችላል፡፡ በአፍሪካም ከብት አርቢወች አንዳንዴ አገራትን ሳይቀር አቆራርጠው ሳርና ውሃ ባለበት ይጓዛሉ፡፡በምዕራብ አፍሪካ የሚገኙ ፉላኒ የሚባሉት ከብት አርቢወች በዚህ በጣም ይታወቃሉ፡፡ከዚህ በተለየ የሰሜኑ የአራችን ክፍል ደግሞ ከጥንት ጀምሮ የተረጋጋና በታወቀ ቦታ ሰፍሮ የሚኖር፤በባላባት ወይም በርስት ስርዐት ሲተዳደር የነበረ ማህበረሰብ፡ነበር ደርግ እስከሚያፈርሰው፡፡ ርስት ማለት በቋንቋ፤ በባህል ብቻ የሚገናኝ ሳይሆን በዘር ሃረግም የሚዣመድ ነው፡፡ አነግ አገሩን ሁሉ የእኔ ነው የሚለው በጣም በተራራቀ ማንነት አንዳንዴ የዳቦ ስም በማውጣትም ጭምር ነው፡፡ርስት ግን የስጋ ዝምድና ጭምር ነው፡፡እናም ኦነግ እና ወያኔ ራሳቸው በቀረጹት ህገ-መንስት እንኳን የወልቃት የማንነት ጥያቄ ርስት የማስመለስ እያሉ ለማጣጣል የሚደረገው ሙከራ ተቀባይነት የለውም፡፡

የድርድር የሠላም ሃሳብ ለትግራይ ህዝብ

የሰሜን ሰወች ኤርትራውያንን ጨምሮ ኢትዮጵያን በመመሥረት እና የብዙ ዕሴቶች ባለቤቶች ቢሆኑም መሪ ማፍራት ላይ ግን ርግማን እስኪመስል ድረስ ቀኝ ገዥ ያይደለ ከእኛው መሓል የወጡ መሪወች እስከ አሁን ድረስ መከራ አጽንተውብናል፡፡በቅርብ ከቅኝ ግዛት የተላቀቁ አገሮች ወደ ሰላምና ዴሞክራሲ ሲሸጋገሩ እኛ ግን እንደ አለመታደል ሆኖ እንደ አገር መቀጠል እንኳን አቅቶን መስቀለኛ መንገድ ላይ እንገኛለን፡፡ኤርትራዊያን ሲገነጠሉ ችጋር ሀሉ ብን ብሎ እንደሚጠፋ፤በወደብ ኪራይ ብቻ ተንደላቀው አንደሚኖሩ ተለፈፈ፤፤የሆነው ግን የኤርትራ ልጆች የሻርክ ሲሣይ፤በየአገሩ ስደተኛ ሲሆኑ ነው ያየነው፡፡ህወሃትም ለትግራያ ህዝብ ያተረፈለትን እናንተ መርምሩት፡፡ የትግራይ ህዝብ በደርግ ወቅት በጦርነት ቆዮ፤ከዚያም ከኤርትራውያን ጋር አሁን ደግሞ ከአብይ ጋር ተዋጋ፡፡ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ ከአማራ ጋር ይዋጋል ወይ? ከዘረኝነት ሁላችንስ ምን አተረፍን? ምናለ ይሄ ነገር በዕርቅ ቢቋጭ፡፡የፈሪ ሃሳብ አይደለም እያቀረብሁ ያለሁት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሕዝብን ሊያፋጁ የተነሱ የጉግ ማንጉጉ መንግስታት ተላላኪዎች!! - ተዘራ አሰጉ

የዘረኝነትን ግንብ ምናለ ቢፈርስ-ዕጣ ፋንታችን እኮ የተሳሰረ ነው፡፡ እንኳን ትግራይና አማራ በአንድ አገር የሚኖሩት ቀርቶ ኤርትራ እንኳን ከኢትዮጵያ ፖለቲካ መለየት አልቻለችም፡፡ይሄው አብራ እያቦካች ነው፡፡ እናም ተለያተን ላንለያይ ነገር በእርቅ ቢፈታ፡፡ማንኛውም ሰው ጥረህ ግረህ በላብህ ሰርተህ ዕደር ተባለ እንጂ ጓሮህን እንቶኔ እንዳይወስድብህ በመጠበቅ ያልፍልሃል አልተባለም፡፡ጥላቻና ዘረኝነት እስከ ጥግ ሄድንበት ምን አተረፍን? አንደኛ እንደ አገር አብሮ መኖር አያስችልም ሁለተኛ ኑሮንም እንደታሰበው አይቀይርም፤፤ለዘህ ምስክር ሩቅ መሄድ አያስፈልግም፡፡ህወሃት በያዘው የዘረኝነት መንገድ የትግይ ህዝብም ሆነ ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ትርፋን እያየነው ነው፡፡ግን ፖለቲከኞች አይሰሙም፤፤

ዕጣ ፋንታችን የተሳሰረ ነው፡፡ ጥላቻው ይቅር በመባባል ይለዝባል፡፡ለዚህም አባቶች ፤ሽማግሎች አሉ፡፡ስለሆነም የዘረኝነትን ግንብ ለማፍረስ የሚከተለውን ሃሳብ አቀርባለሁ፡፡ ሌላም አማራጭ ሃሳብ ይኖራል፡፡ሁሌ ፈረንጅ በቀደደልን ፈሰን ምን አተረፍን? ሃሳቦቼ እነሆ፤

1ኛ፡ህወሃት በጉልበት የከለለው ወሰን ከህወሃት በፊት ወደ ነበረው ይመለስ፤የተፈናቀሉት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን ከዚህ ዘረኝነት በፊት በጋራ እንደኖርባት አሁንም በሁለቱ ክልሎች ያንን መመለስ

2ኛ፡ አማርኛ እና ትግርኛ በሁለቱም ክልሎች የስራ ቋንቋ እንዲሆኑ ማድረግ

3ኛ፡ ሁለቱንም ቋንቋወች በሁለቱም ክልሎች በት/ቤት እንዲሰጡ ማድረግ

4ኛ፡ የስራ ቅጥርን በተመለከተ በቋንቋ ምክንያት ምንም ክልከላ ሳይደረግ ቅጥር እንዲፈጸም ሆኖ ተቀጣሪው/ዋ የማይችሉትን ቋንቋ በመንግስት ወጪ በቅጥር ሙከራ ወቅት ለ 6 ወር ወይም እንደ አስፈላጉነቱ የቋንቋ ማሰልጠኛ ተቋማትን በመክፈት አንዲሰለጥኑ ማድረግ፡፡ይህ በግል ድርጅቶችም በመንግስት ወጪ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ

ይህ ስምምነት በህዝባዊ ውይይት ከዳበረ በኋላ በሁለቱ የክልል ም/ቤቶች ጸድቆ ህግ እንዲሆን ቢደረግ ዘላቂ ሰላም ይገኛል፡፡

ካልሆነ ግን የጦርነት አዙሪት ውስጥ እንኖራለን፡፡ ምርጫው የራሳችን ነው፡፡

ስለ ትግራይ ወዳጆቼ፤በግልም ውለታ ስላለብኝ፤ዘላቂ ስላምም ስለሚያስፈልግ ከህሊና ዕዳ ነጻ ለመዳን ይህን ሃሳብ ሰንዝሬአለሁ፡፡ ለራሴም በሠላም መኖር ስለምፈልግ!

እግዚአብሄር ይርዳን!

 

2 Comments

  1. አሰፋ በድሉ ብአዴንን ፈልጌ አጣሁት ላልከው ፈጣሪው እፍ ብሎ ነብስ የዘራበት ክትፎ ሲያመላልሱለት የከረሙት ስሙን ሲሰሙት የሚደነብሩት በድን ብሎ ስም ከመስጠቱም ባሻገር በተለያየ ቃለ ምልልስ ሰው የለባቸውም ብሎ ነግሮናል ይህን በዚህ ከቋጨን ትግርኛ በምን ሂሳብና ምን ሊያደርግለት ነው የገዳዩን ቋንቋ ሰው እንዲኖረው ማሳሰቢያ የምትሰጠው? የክፉ ምሳሌዎች ስለሆኑ ከሰው ተገልለው መቀመጥ እንጅ ከህዝብ እንዲቀላቀሉ የሚበረታቱ አይሆንም ባይሆን መንገድ ካለ ከጥልያን ከየመን እንጅ ወደዚህ ማምጣት ጥፋቱ ያመዝናል።በነሱም አትፈርድም የባንዳ ታሪካቸው አንገት ያስደፋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share