ዝናሽ ታያቸው እንደ ክላራ ፒታቺ 

የጭራቅ አሕመድ ባልተቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው የወንጌል ዘማሪ ነኝ ትላለች፡፡  ስለዚህም ጥያቄው ስለ ወንጌል ታውቃለች ወይስ የገጠሙላትን ሁሉ እንደ በቀቀን (parrot) እየበቀቀነች ታንጎራጉራለች የሚለው ነው፡፡  ሁኔታዋ ሁሉ የሚያሳብቅባት ግን ስለ ወንጌል ማወቅ ቀርቶ ፍንጭም እንደሌላት ነው፡፡  ፍንጭ ቢኖራት ኖሮ በመጽሐፈ አስቴር ውስጥ በሰፊው የተወሳውን የመጽሐፍ ቅዱሷን የአስቴርን ታሪክ በትንሹም ቢሆን ባስታወሰች ነበር፡፡

የመጽሐፍ ቅዱሷ ንግሥት አስቴር ባሏ ንጉሥ አርጤክስስ (Ahasuerus, Xerxes) አይሁዳውያንን በገፍና በገፍ ሊጨፈጭፍ በተነሳ ጊዜ፣ እኔም ሚስትህ አይሁዳዊ ነኝና ጭፍጨፋህን ከኔ ጀምር የሚል ጽኑ አቋም በመውሰድ ሕዝቧን ከጭፍጨፋ ማዳን ብቻ ሳይሆን፣ የባሏ እኩይ አማካሪ የነበረውን ፀረይሁዳውን ሐማንን በስቅላት አስቀጣችው፡፡

የኦሮሙማ “ቀዳማዊ እመቤት” የሆነቸው ዝናሽ ታያቸው ግን ባሏ ጭራቅ አሕመድ አማሮችን በጨፈጨፈና ባስጨፈጨፈ ቁጥር “እየሱሴ የኔ ጌታ፣ ያረገልኝ ትልቅ ውለታ” እያለች በመዘመር፣ በጭፍጨፋው እንዲቀጥልበት ታበረታታዋለች፡፡  አማራን ይበልጥ አዳክማ ለባሏ ለጭራቅ አሕመድ ጭፍጨፋ ይበልጥ ምቹ ለማድረግ ደግሞ ጎንደርን ካማራ ለመነጠል ከነ አገኘሁ ተሻገርና መላኩ አለበል ጋር ትመሳጠራለች፡፡  አጋሮቿ ዮናታን አክሊሉንና ሶፍያ ሽባባውን የመሳሰሉ ፀረተዋሕዶ ጴንጤወች ናቸው፡፡  አማካሪወቿ ደግሞ ሌንጮ ለታንና ሌንጮ ባቲን የመሳስሉ የባሏ ፀራማራ አማካሪወች እንደሆኑ ያደባባይ ንግግሮቿ በግላጭ ይመሰክሩባታል፡፡  እሷ ልጇን ትድር ይመስል በጥበብ ተሽሞንሙና በጠያራ ጎንደር ስለምትሄድ ብቻ፣ ልጆቻቸውን ለመቅበር አዲሳባ እንዳይገቡ የተከለከሉትን ያማራ እናቶች፣ ሰላም የምታገኙት ዳቧችሁን በልታችሁ አርፋችሁ ከተቀምጣችሁ ብቻ ነው በማለት በቁስላቸው ላይ እንጨት እየሰደደች ትሳለቅባቸዋለች፡፡

ስለዚህም ይህች እኩይ ሴት ከባሏ ከጭራቅ አሕመድ ባልተናነሰ ሁኔታ ያማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላት ናት፡፡  በመሆኗም ያማራ ሕዝብ ሊመለከታት የሚገባው ጭራቅ አሕመድን በሚመለከትበት አይን ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰላማዊ ሰልፉ ቢታገትም ፣ የተሳካ ሕዝባዊ ንቅናቄ ነበር! -ከአንድነት ፓርቲና ከ 33ቱ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ

ጣልያኖች ጭራቁን ቤኒቶ ሞሶሎኒን (Benito Mussolini) ዋጋውን ሲሰጡት፣ የሞሶሎኒ ቀንደኛ አበረታታች የነበረችውን ጭራቂቷን ውሽማውን ክላራ ፒታችንም (Clara Petacci) በተመሳሳይ መንገድ ዋጋዋን ሰጧት፡፡  ጭራቅ አሕመድ አማራ እጅ ሲወድቅ ደግሞ (እንደሚወድቅ ምንም ጥርጥር የለኝም) እሱ የሞሶሎኒን (Benito Mussolini)፣ ጭራቂቷ ዝናሽ ታያቸው ደግሞ የክላራ ፒታችን (Clara Petacci) ጽዋ መቅመስ አለባቸው፡፡  ያማራ ሕዝብ የጭራቅ አሕመድ ዓይነት ዳግም እንዳይነሳ ማድረግ የሚችለው፣ ጭራቅ አሕመድንና ግብራበሮቹን ለሌሎች ማስተማርያ በሚሆን መንገድ አይቀጡ ቅጣት ሲቀጣቸው ብቻ ነው፡፡

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

5 Comments

  1. Bread without flour and wheat. Is that manna?
    ያለ ውሃ የሚቦካው የጎንደር ዳቦ?
    ጎንደር ከፍተኛ የውሃ ችግር እንዳለ ይታወቃል።
    የጎንደር የውሃ ችግር አዲስ ባይሆንም በተከታታይ ለውሃው ችግር መፍትሔ ተብለው የመጡት ፕሮጄክቶች ወጪ በሙሰኞች በመዘረፉ ከሰው ቁጥር መጨመር ጋር እጅግ እየተባባሰ መጥቷል።
    ዝናሽ ታያቸው ከባሏ ዝናብ ማዝነብም የላቀ ተአምር በመሥራት ለጎንደር ሕዝብ መና ልታወርድለት ነው። ውሃም ዱቄትም ሳይኖር ዳቦ ጋግራ ልታበላው። የብልጽግና ወንጌሎቹ ባልና ሚስት ለሁለት ተጋግዘው የሙሴን ተአምራት እያሳዩ ነው ማለት ነው።
    እርግጥ የጎንደር የውሃ ችግር እንዳልነው በአቢይ ዘመን የተባባሰ እንጂ የተጀመረ አይደለም። እንዲያውም ከነዘፈኑ
    አይ አገር አይ አገር አይ አገር ጎንደር
    ውሃ የለም እንጂ ውሃማ ቢኖር
    ብሎ ይዘፈን ነበር። እርግጥ ውሃ ከሌለ ምኑን አገር ሆነ ብሎ ያሰበና የተከፋ ጎንደሬ ዘፈኑ በካሴት በተቀረጸበት ዘመን “ቡና የለም እንጂ” በምትል የደንቆሮ ሐረግ ተክቷት ዘፈኑ ለብዙው የዛሬ ትውልድ አባል እንደዚህ ይመስለዋል
    ቡና የለም እንጂ ቡናማ ቢኖር
    አይ አገር አይ አገር አይ አገር ጎንደር
    ይህ ግን “የደንቆሮ ኤዲት” ነው የተባለበት ጎንደር ክፍለ ሀገር በአርማጭሆ ቆላ ቡና አምራች የነበረ መሆኑ ነው። ይሁንና የውሃ ችግር በመንግሥቱ ኃይለማርያም ጊዜም ስለነበር ይህንኑ ለመንጌ ነግረውት ጎሐ ሆቴል ላይ ሆኖ ጣናን እያየ በመብሸቅ ችግር የለም ከኦጋዴን እንስብላችኋለን ብሎ ተሳልቆ ነበር አሉ።
    ዞሮ ዞሮ አቢይ አህመድ ሲዳብስህ፤ ሲደባብስህ፤ ሣር ሲያግጥህ፣ ጨው ሲያስልስህ ቀጣዩ ምን እንደሆነ ታውቃለህና ጎንደር አርብ ማልዳ መሆኑን አውቀህ ለመስቀልና ለትንሣኤ መዘጋጀቱ ይበጅሃል።

  2. ቅዱስ ቃሉ ከአፋችሁ ክፉ ቃል አይውጣ የሚለውን ጠብቄ እንጅ ለዚህ ነውረኛ ሃተታ ብዙ ነበረኝ::
    መሪዎቹ ከምኒሊክ ጀምሮ በሴራ ፓለቲካ ቢታሙም ሚስቶቻቸው ግን ከጣይቱ ብጡል እስከ መነን ውባንችና ዝናሽ ይህን ያህል የከፋ ነገር ያልተነገረባቸው መልካሞች በመሆናቸው ይህ ክስ ድንቅ ዘማሪዋን የወቅቱን ክብርት እመቤት መንቀፍ ነውር ነው::
    የ7ኛ ተብዬ ንጉስን ታይታ ማስፈጸሙን ባልቀበልም እቴጌ መነን የጀመረችውን በጎ ስራ እቴጌ እጀጥበብን ደግማለች ክርስቶስ ይባርካት ባልዋ ሚዛናዊ እንዲሆን ከጎሳ ፓለቲካ እርሾ ይነጻ ዘንድ በጸሎት ደግፋታለሁ::
    ፓስተር ዲጎኔ ሞረቴው

    • ሞረቴው ተበሳጩ እንጅ እሱም መጽሀፍ ጠቅሶ እንደ አስቴር ሰውን ከመታረድ ታድነው ግፍ ሞልቶ ሲፈስ ዋጋው ብዙ ነው ያለ መሰለኝ። እናንተም ሳታውቁት ፈረንጅ የሰጣችሁን የቤት ስራ ከመተግበር ክርስቶስን ለማያውቁ ለህብረተሰብ ክፍል ሂዳችሁ ወንጌልን ስበኩ። የእናንተ የውጊያ ሜዳ ኦርቶዶክስ ነው ቄስ ግርማ የተባለው ሙሉ ጊዜውን ፖለቲካ ያደረገ ጸረ ኦርቶዶክስ ለህግ መቅረብ ሲገባው እንደፈለገው ሚዲያ ላይ ቀርቦ እስኪያልበው ድረስ ተሳድቦ ይመለሳል። እስቲ ይምከሩት አሁን እስራኤል ዳንሳን፣እዩ ጩፋን፣ዮናታን አክሊሉ፣ ከፍያለው ምናምንን የመሰሉትን ጩሉሌዎች ያየ እንኳን ጴንጤ ነኝ ሊል ጴንጤን አውቃለሁ ይላል? ፓስተር ሞረቴው በኔ በኩል በቃኝ አይበሳጩ እድሜ ይቀንሳል ቶሎ ለመሄድ ካሰቡ ምክንያቱን እርሶ ነው የሚያውቁት። በተረፈ ቀዳማይት እመቤት፣ሶፍያ ሽባባውን የመሳሰሉ ቀላቀላያሉ ሴቶች ኮንሰርት ነገር ካሰቡ ስፖንሰር ማድረግ ይቻላል እርሱም እንደሚገኙ እገምታለሁ

  3. ፕሮፍ እንደሚመስለኝ ያ ወይጦ አገኘሁ ተሻገር ነው የሚያሳስታት ሴትዮዋ ደህና ነበረች፡፡ ባልየው አኪሩ ሲወድቅ በሷ በኩል ልሞክረው ብሎ ነው አሁን አሁን አዜብን እየመሰለች ሄደች ይህ እብደቱን ትታ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጋ እንደ ዉብአንች ብሻው በክብር ብትቀመጥ መልካም ነበር ፡፡ አለፍ ሲል ለህክምና ብላ በወጣችበት ብትቀርም መልካም ሃሳብ ነው፡፡ይህ እዩኝ እዩኝ ማለት አዜብ መስፍንን ምን እንዳደረጋት ቋሚ ሁነን አይተናል፡፡ ባለፈው እንደ ባሏ ሳት ብሏት የተናገረችው የአገኘሁ ተሻገር እንጅ የእሷ ሊሆን አይችልም ” ዳቦ መጋገሪያ አሰርቻለሁ ዝም ብላቸሁ ዳቦ ብሉ” ማለት ከምን የመጣ እብሪት ነው ?ውሃ ሳይኖር ዳቦው በምን ይቦካ? የሚያሳዝነው አዜብ መስፍንም አማራ ሁና የአማራውን መምቻ ዱላ አቀባይ እሷ ነበረች ይችኛዋ እርጋታ አላት ስንል መስመር እየሳተች ነው፡፡ እስቲ ልብ ይስጣት ብትችል ከአዜብ መስፍን ሳይሆን ከወ/ሮ ውብአንች ብሻው ብትማር ስሟ ሳይነሳ ተከብራ ትኖር ነበር የኛ ሰው ክፉ ነው ምን እንደሚያስብ የሚያውቀው እራሱ ብቻ ነው ነገር ሲለወጥ እኔን አያድርገኝ ነው፡፡

  4. ሶፍያ ሽባባው ብትል እህቷ ባህር ዳር የአንድ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር እንደሆነችና ባለፈው ጥቁር ለነሳችሁ ብላ ከባድ ውሳኔ ማስተላለፍ ተሰምቷል። ከተረኞችና ከተራማጆች (ተራጋጮች) አፍ የማይጠፋው ስር እርስ ከዚህ በላይ ምን አደረገ። ይሄ ቤተ ሰብ ክብር የተሰጠው ጅጅ የተባለችው እህታቸው ኢትዮጵያን ከፍ ስላደረገች እንጅ በሌላ አይደለም። እንዲህ ሰማይን በእርግጫ መምታት ልክ አይሆንም በሁሀላ ደብቁኝ ያመጣል። ሶፍያም ስለግል ህይወትሽ መስማት ይበቃናል ሀይማኖትም ከእናንተ የቀደመ ስላለን ያላመኑትን ፈልጉ እንጅ በብሽሽቅ መልኩ ሳታውቁት ፈረንጅ የሰጣችሁን ተልእኮ ተቀብላችሁ ጤና አትንሱ። ሂዱ ወደ አለም ያላመኑትን ስበኩ እንጅ ያመኑትን ጤና ንሱ የሚል አልተጻፈም። ከዶክተር ወዳጄነህም መማር መልካም ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share