February 4, 2023
5 mins read

ሕዝብ ሆይ! ተይሁዳዊ ሽምግልና ፍትህና ሰላምን እየጠበክ መከራህን አታራዝመው!

Killers 1በላይነህ አባተ ([email protected])

እንደ ይህ አድግ ቁጥር አንድ ሁሉ በሕዝብ የቁጣ ማእበል የተጥለቀለቀው ይህ አድግ ቁጥር ሁለት ይሁዳዊ ሽምግልናን የወንበር ማስጠበቂያና የሕዝብ መጨፍጨፊያ መሳሪያ አድርጎ እየተጠቀምበት ነው፡፡ ክርስቶስ አእዋፍዋ የሆነውን ቅድስት ቤተክርስትያን ሳይቀር በይሁዳዊ የሽምግልና መሳሪያ ሊያጠፋ የይሁዳ ሽማግሌዎችን እያሰማራ ነው፡፡

በታሪካዊትና መንፈሳዊት ኢትዮጵያ ሽምግልና ከእውነተኛ ችሎት እጅግ የበለጠ ርትኡ ፍርድ የመስጥትና ዘላዊ ሰላምን የማስፈን መለኮታዊ ሀይል ነበረው፡፡ የኢትዮጵያን መንፈሳዊና ባህላዊ እሴቶች እየጠራረገ የሰይጣንን የቅጥፈት፣ የሌብነት፣ የአውሬነትና የጭራቅነት መንፈስ ሲሰራና ሲተክል የኖረው ይሁዳው ይህ አድግ ከመጣ ጀምሮ ሽምግልና ተበዳይን ከበዳይ እግር የሚያስደፋና የሕዝብ መጨፍጨፊያ መሳሪያ ሆኗል፡፡

ይህ አድግ ቁጥር አንድ ኤፍሬም ይስሀቅን የይሁዳዊ ሽምግልና መሪ ተዋናይ አድርጎ እደተጠቀመበት ሁሉ  በአራት ዓመታት ውስጥ ወድ ሶስት ሚሊዮን ሕዝብ የጨፈጨፈና ያስጨፈጨፈው ከአስር ሚሊዮን ሕህዝብ በላይ ስደተኛ ያደረገው ይህ አድግ ቁጥር ሁለት ደሞ ስለሽምግልና ምንም የማያውቁትን ሆደ ኣደሮች የሕዝብ መጨፍጨፊያ መሳሪያ አድርጎ መጠቀሙን እንደ ቀጠለ ነው፡፡ ከአለፈው መማር ያቃተው ልብ የለሽም በማያባራ ይሁዳዊ ሽምግልና እየተጠለፈ ታግሎ ማስወገድ ያለበትን መከራ እያራዘመው ነው፡፡

የውሸት እርቅና ምግልናን የማምታት አባዜ፦ ድርድር እንጅ ሽምግልናን የማያውቁት ምዕራባውያን ሰው ከተፈጠረበት ዘመን ጀምሮ የነበረውን የኢትዮጵያውያን እምነትና ባህል ተሸቀጣቸውና ተእርጥባናቸው ጋር በሚልኩት እንደ ጥንዚዛ በሚያፈናጥር የዳንስ ባህል ከተፈታተኑት በከፋ ሁኔታ ይህ አድግንና እንደ ኤፍሬም ይስሀቅ ያሉ ተላላኪዎች ተጠቅመው የኢትዮጵያን የሽምግልና ሥርዓት ማጥፋቱን አንደቀጠሉ ነው፡፡ ሽምግልናን ድርድር በሚባል ተበዳይን ከበዳይ እግር አስወድቆ ይቅርታ በሚያስጠይቅ ኤፍሬም ይሳቃዊ ወለፈንዲና ኢመለኮታዊ ተግባር ክፉኛ እያጠቁት ነው፡፡ የኢትዮጵያን ሽምግልና መለኮታዊ ሚዛንን፣ ፍርድንና ፍትህን ያካትታል፡፡ በአንፃሩ ይህ አድግና ኤፍሬም ይሳቅ እንደ ወረርሽኝ ጎትተው ያስገቡት ሳጥናኤላዊ ድርድር መለኮታዊ ሚዛንን፣ ትክክለኛ ፍርድንና ፍትህን በመዳመጫ ደፍጥጦ የተጎዳውን ደካማ ተጎጂው ጉልበታም በደም የከረፋ እግር ሥር ወድቆ ይቅርታ እንዲጠይቅ ያደርጋል፡፡

እምነት ቀርቶ የአውሬ ያህል እንኳ የደመነፍስ ባህሪ ካልፈጠረባቸው የይህ አድግ አረመኔዎች በሽምግልና በኩል እርቅን፣ ፍትህንና ሰላምን መጠበቅ ከሳጥናኤል በረከትን ተጭራቅ ርህራሄን እየጠበቁ ሲንዘላዘሉ እንደመኖር ነው፡፡

ሕዝብ ሆይ! ጭራቆች ለወንበር መጠበቂያና ለሕዝብ መጨፍጨፊያ ተሚጠቀሙበት ይሁዳዊ ሽምግልና ፍትህና ሰላምን ጠብቀህ መከራህን አታራዝመው፡፡ መፍትሔው  ጭራቅን ደጋግፎ ተወንበር አለማውጣት፤ ከወጣም ዥልጦ ማውረድ ነው፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

 

ጥር ሁለት ሺ አስራ አምስት ዓ.ም.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop