መንግስት እኛን ካላወቀን፤ እኛ ለምን እሱን ማወቅ እንገደዳለን? – አሰፋ በድሉ

ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቁልፍ እየሰበረ (ይሄንን ሲሰሙ እንደ ጠባያቸው ፌክ ሊያዘጋጁ ይችላሉ) የቤተ ክህነት ቢሮ እየተቆጣጠረ የፖለቲካ ማስፈጸሚያ ለሚያደርግ መንግስት፤ በዚህ ቀን፤በዚህ ሰዓት ቢሮ ሰብረሃልና ፍርድ ስጠኝ ብሎ ራሱን መጠየቅ ለራስም ግራ ነው፡፡

በማርያም! ፍርድ ቤት፤ስራ አስፈጻሚ፤ ህግ አውጪ የተለያዩ ናቸው እያልን ራሳንን በራሳችን የማደንዘዣ ኪኒን የምንውጥበት ያ ደግ ዘመን አለፈ፡፡ አሁን ያለነው በሄሮድስ ዕጅ ነው፡፡ከሄሮድስ እንዲያመልጡ የረዳቸውን፤የመራቸውን፤ጥበብ፡ ኮከብ መፈለግ፤ይበጀናል፡፡ መንግስትንስ ምኑን እንፈትነዋለን? ምን የቀረው ነገር አለ? የራሱ ስራ አጋልጦት ራቁቱን ቆሟል፡፡ እንዲያውም እንደ ብልጠት ነው ዕያየው ያለ፤፤ ፍርድ ቤቱስ ፈረደ እንበል፤ማን ይፈጽመዋል? ፍርድ ቤቱ እንደ ፐሊሶቹ ለወንጀለኞቹ ቢወስንስ ወይም ቢያስገድዱትስ? ውሳኔውን አሜን ብለን ተቀብለን ቤተ-ክርስቲያንን ለመናፍቃን እናስረክባታለን?

ይህ አገር እንግሊዝ አይደለም፤፤በአንድ ወቅት የቀድሞው ጠ/ሚ/ር ቦሪስ አሳሪ ህግ እንዳይወጣባቸው ፓርላማውን ለሁለት ሳምንት ዕረፍት እንዲወጣ አድርገው፤ወደ ተባበሩት መንግስታት ስብሰባ ኒዮርክ አመሩ፡፤ ጥቂት ግለሰቦች ጉዳዩን እስከ ጠቅላይ ፍ/ቤት ወሰዱት፡፡ አስራ አንድ አባላት ያሉት ጠቅላይ ፍ/ቤትም በሙሉ ድምጽ ውሳኔውን   በጠቅላይ ፍ/ቤቱ ሰብሳቢ ወ/ሮ አንባቢነት የቦሪስን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አደረገው፡፡ ቦሪስም በደቅቃ ውስጥ ከኒውዮርክ ውሳኔውን እንደሚቀበል ገልጾ ስብሰባውን አቋርጦ ተመለሰ፤፤ በነገራችን ላይ ከስልጣን ለመባረር ምክንያት የሆነው በልደቱ ፓርቲ ምክንያት የኮቪድ ህግ ጥሰሃል ተብሎ ነው፡፡ ህግ የሚሰራው እንዲህ ባለ አገር ነው፡፡

አብይ አሸባሪ ብሎ፤የዕስር ማዘዣ ያወጣባቸውን ግለሰቦች ለይስሙላ እንኳን አንድ ቀን ፓርላማ መሰብሰብ ግድ ሳይሰጠው ፊቱ ቁጭ አርጎ ነገ ደግሞ ሌላ ጢባጢቤ እንዴት እንደሚጫወትባቸው እያሰብ ከሚሳለቅ መሪ ፍርድ መጠበቅ መቼም ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም የሚለውን አስበን እንለፈው፡፡ ምናልባትም የእስር ማዘዣ የያዘው ትዕዛዝ አከብረለሁ ባይ ኮንስታብል ጁንታ አየፈለገ ይሆናል ብለን እናስብ፤ መሪያችን አየት ያደርግና ምን አይነቱ ጀዝባ ነው ይልና ይሳለቅበታል፤፤ይህ ነው የኢትዮጵያ መሪ.፡፡ አፈ-አብይ ሺመልስ አብዲሳ አላማችንን ለማሳካት ህጋዊም፤ህገ-ወጥም አካሄድ እንከተላለን ያለውን ከመቼው ረሳናው? አዲስ አበባ ላይ የኦሮሚያን ባንዲራ፤ቋንቋ ወዘተ…የሚተገብረው ህግ ስለሚፈቅድ ነው? ሰው እያለቀ ነው፤ህይወት አድን ዛፍ ተከላው ይደርሳል ሲሉት፤ዛፍ አትትከሉ የሚሉ ጠላቶቻችን ናቸው፤አትስሟቸው አለ፡፡ምክንያትህ ሲባል ለአስከሬኑ ማረፊያ ስለሚሆን ያለንን መሪ መሪ ብለን ስንቀበል ነው ሁሉ ነገር የቀረው፡፡ህጉን እንተወውና ያደገበትን ባህል፤የመጣበትን አስተምህሮ፤ጤንነቱንም ማወቅ ነው የቸገረን፡፡ በጥብቅ ባህል፤በህግ ያደገው ጀግናው እሸቴ ሞገስ ስለ መንግስት የነበረው ዕምነት ገና ብዙ ጥናት የሚፈልግ ይመስለኛል፡፡ ልጆቹን ህይወቱን ከመሰዋቱ በፊት አደራ ያለው ለቤተ-ዘመድ፤በስልክ መልዕክቱን ለተቀበለው፤ወይም ደ/ር ለሆነው ለታናሽ ወንድሙ አልነበረም፡፡ አደራ ያለው ለመንግስት ነበር፡፡ወቅቱን ለመረዳት ትምህርት ቢገድበውም ያደገበት ባህል መንግስት ላይ ያለውን ጽኑ ዕምነት ይናገረል፡፡ ጠ/ሚ/ር ቀድሞ ወታደርም ቢሆን ሲቪል ነው፡፡አብይ ግን በል ሲለው ቀይ ቦኔት፤ሲያሻው የተራ ወታደር ወይ ደግሞ የኮለኔል ይለብሳል፤፤ማን ከልካይ አለው፤አሱ ህግም ፤ሞራልም አይመለከተውም፤እኛን ብቻ እንጂ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሕብር ራዲዮ ዕለታዊ ዜና | Hiber Radio Daily Ethiopia News Apr 02, 2023 | Ethiopia

ከህገ-ወጥ መንግስት ፍትህ እንደማናገኝ ብዙ መድከም ያለብኝ አይመስለኝም፡፡አሁን መፍትሄ ወደምለው ልለፍ፡፡ ትንሽ ስለ ኦነግ አቻ-በመፍጠር (dichotomy) አንድነትን መናድ የፖለቲካ ስትራቴጂ እና አብይ ሳይሸራርፍ እየፈጸመው የሚገኘውን ላንሳ፡፡ኦነግ ድርጅት ብቻ አይደለም፤አስተሳሰብ ጭምር ነው፡፡በአንድነት የሚያምኑት ውቦቹ ቆነጃጅት ቀሚሳቸው ላይ አረንጓዴ ፤ቢጫ፤ቀይ ከጨመሩበት፤ በዚያው ዲዛይን ግን ሌላ ቀለማት እንደተማሪ ዩኒፎርም ሁሉንም ያለብሳል፤ግንባራቸው ላይ ካሰሩ አንደዚው እንዲያስሩ ያደርጋል፤አደዋን በጋራ ካከበርን፤ለብቻ አቻ የኦሮሞ አድዋ ይፈጥራል፤ቢያደርሰን ዘንድሮ ደግሞ እንዴት እንደሚያከብሩት እናያለን፤የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ካልን፤የኦሮሚያ ዋና ከተማ ፊንፊኔ ይላል ኦነጋዊ አስተሳሰብ፤የጋራ ቤተ-መንግስት ካለን፤ሌላ ቤተ-መንግስት በመስራት ላይ ነው፡፡በዛ ያለው ኢትዮጵያዊ ኦርቶዶክስ ከሆነ(ስትጠመቅ አማራ ትሆናለሁ እንዳለው ምሁር)፤ኦሮሞ ደግሞ ሌላ ሃይማኖት መከትል አለበት ይላል ኦነጋዊው አስተሳሰብ፡፡ከድሮው ዘመን ይልቅ አሁን፤በኦሮምኛ ሰባኪያን ይሰበካል፡፡ከሰሞኑ ከሰማሁት እንኳን በጅማ ዞን ሃገረ ስብከት በሁሉም ወረዳወች ኦሮምኛ ሰባኪወች አሉ፡፡ይህ ግን ኦርቶዶክስን ከመተው አላስቀራቸውም፡፡ምክንያቱም ጉዳዩ የቋንቋ ስላልሆነ፡፡የተውት በፖለቲካ ምክንያት ነው፡፡ ምክንያቱም ስትጠመቁ አማራ ትሆናላችሁ ብለው ነው ያስተማሯቸው ኦነጋውያን፡፡ ይሄ የምናውቀው ነገር ነው፡፡ ህገ-ወጡ ሲኖዶስ ነኝ የሚለው ቋንቋን ይዞ ብቅ ያለው ለሽፋን ነው፡፡እኛና መንፈስ ቅዱስ መባል ቀረና፤በክርስቶስ ክርስቲያን መባል ቀረና፤የእግዚአብሔር ቤተሰቦች መባል ቀረና-እኛ ብሄር ብሄረሰቦች አሉን አስኬማ ደፍተው የኖሩት አባቶች፤እግዚኦ ነው፡፡ በክልሉ ያለው በሚሊዮን የሚቆጠር ሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ልጃቸው አይደለም? አምላካችን፤መምህራችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ጠፋው አንድ ልጅ ፍለጋ መሄዱን ነበር ያስተማረው፡፡ክርስቲያን በሰው አይታመንም፤፤ ወደ አቻ ስትራቴጂ ልመለስ፤ ቤተ-ክርስቲያን ዮናታንን ስትከስ፤አንተም ክሰስ ብለው አቻ ክስ፤ኢትዮጵያውያን የጋራ ፊደል ሲኖራቸው፤ከየትም ብለው፤ብቻ ከዚህ የተለየ ይሁን፤ አቻ ፊደል ፈጠሩ፤አቻ ታሪክም እንዲሁ ነው፡፡አንድም ነገር የጋራ ነገር እንዳይኖረን እየተሰራ ይገኛል፡፡ይሄ አብሮ መኖር የሚፈልግ ጠባይ ነው ወይ? አይደለም፡፡ግን ላሟን እኔ አስከ አለብኋት ድረስ፤ ላሟ የጋራችን ናት ነው ጉዳዩ፡፡መጨረሻ የቀረችው ቤተ-ክርስቲያን የአንድነታችን ምልክት ነበረች፡፡ ለእሷም አቻ ሲኖደስ ኦነጋዊው አስተሳሰብ ፈጠረላት፡፡ቤተ-ክርስቲያን ክስ ብትከስም አቻ ክስ ሊመሰርቱ ይችላሉ፡፡ከዚያ ኑ እንደራደር ይላሉ፡፡ስለዚህ እኛ የሰላም ሰወች፤የህግ ሰውች፤የፍቅር ሰወች መሆናችንን ለማስመስከር መድከም ያለብን አይመስለኝም፡፡የተዘረፈ ሰው ሲጀመር ራሱ እንዳልዘረፈ ማስረዳት መሞከር ትንሽ ግራ ይሆናል፡፡ይሄን ጉዳይ ጉዳዩን ለያዙት የህግ ባለሞያወች ትተን እኛ ምዕመናን ግን ለአባቶች የልጅነት ጥያቄ በማቅረብ ሌሎች ሰላማዊና ህጋዊ መንገዶች መከተል እና ህልውናቸችንን ማስከበር አለብን፡፡አብይ የሚፈራው አንድ ነገር ብቻ ነው፤ያም መገዳደር የሚችል ሃይል ብቻ ነው፡፡ እስከ አሁን አባቶቻችን በሚገርም ሁኔታ፤በሚስደምም ሁኔታ መርተውናል፡፡እውነት ለመናገር ልጆቻቸው እንኳን አናውቃቸውም፤፤ማስተዋል፤ዕውቀት፤ጥበብ፤ትህትና ሁሉንም አይተናል፡፡ በመጨረሻ የሚከተሉትን ስጋቶቼንና መፍትሄ የመሰሉኝን ጠቁሜ ጽሁፌን ልቋጭ፤

  1. ተጠባባቂ መሪ ስለ ማዘጋጀት – መንግስት በህገ-ወጥነቱ ከቀጠለ፤ፓትርያርኩን የሚረዱትን አባቶች ሊያስር ይችላል፤የማህበረ-ቅዱሳንንናየማህበራት መሪወችን፤እንዲሁም ብዙ በማህበራዊ ሚዲያ ተደማጭነት/ተከታይ ያላቸውን መሪወች ሊያስር ይችላል፡፡ያቺ ቀን ሳትደርስ ተተኪ በርከት ያለ አመራር በሁሉም ዘርፍ ያስፈልጋል፡፡ወጣቱን በየቀኑ ምን ማድረግ እንዳለበት የሚመሩ ተጠባባቂ መሪ አባቶች፤ወጣቶች ያስፈልጉናል፡፡
  2. አማራጭ መልዕክት ማስተላለፊያ መንገዶች ማዘጋጀት-ኢንተርኔት ሊቋረጥ ይችላል፡፡ብሮድካስት ባለ ስልጣን የቤተ-ክርስቲያንን ቴሌቨዠንን ጨምሮ ሌሎችንም ሊዘጋ ይችላል፡፡እናም በውጪ አማራጭ የሳተላይት ፕሮግራም ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ከዚህ በኋላ አብይን መውቀስ፤ማጋለጥ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ከአባቶች ጋር ተናቦ ነገ ይህን ስሩ፤ከነገ ወዲያ ደግሞ እያለ መንገድ የሚመራ ሚዲያ ያስፈልጋል፡፡ሁሌ መከራችንን ደግመን፤ደጋግመን ብናነሳም የባሰ እንጂ የተሻለ አልመጣም፡፡
  3. የትግሉ ማዕከል-አዲስ አበባ መሆን አለባት፡፡የአዲስ አበባ ከተፈታ የሁሉም ይፈታል፡፡የመከራችን ጠማቂ አራት ኪሎ ሆኖ ስለሚያፌዝብን፡፡ሌሎች አካባቢወች ተከታይ መሆን አለባቸው፡፡ቁልፍ ሰበራው ወደ አዲስ አበባ እየተጠጋ ነው፡፡ምስካየሃዝኑናን መድሃኒአለም የተጀመረውን አይተናል፡፡ወጣቶቹ በዕውነት እስከ መጨረሻው በዕምነት ያጽናችሁ፤ደጁን የምትጠብቁት መድሃኒአለም ጋሻ፤ከለላ ይሁናችሁ፡፡የባ/ዳር ሰልፍ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ለሁሉም ጥሪ ሲደረግ ቢሆን ዕላለሁ፡፡
  4. ሱዳኖች ከፈለጉ እንኳን ጎንደር፤እስከ ባ/ዳር ይምጡ፤፤እንዳትነኳቸው፡፡ለሁሉም ጊዜ አለው፡፡ለወደፊቱም የኢትዮጵያን ወዳጅ ማህበረሰብ ቀለበት ውስጥ መክተት ይፈልጋል፡፡ኢትዮጵያ መሪ ስታገኝ ሁሉም ይሆናል፡፡ልክ አንደ ኤርትራው ጊዜ ሁሉ ሱዳን በሮ የሄደው ሞትን ለመደገስ ነው፡፡ጥያቄ የለውም፡፡ኤርትራና ኢሳያስ ጊዜአቸውን ጨርሰዋል፡፡
  5. የአብይን ጣልቃ እንዳትገቡ ማስጠንቀቂያን በተመለከተ-ይሄንን አሁንም ለሴራው ስለሚጠቀምበት ደጋግመው የህግ ሰወች ቢያብራሩት ጥሩ ነው፡፡አብይ ገብተህ ቀድስ አልተባለም፡፡ማህበራት፤የሃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ ሲመዘገቡ መንግስት የሚያውቀው መተዳደሪያ ደንብ አላቸው፡፡ያንን ተከትሎ ህግ ያስከብራል ማለት ነው፡፡ምርጫ ቦርድ ፓርቲወችን እንዴት እንደሚዳኝ አንድ ምሁር ምሳሌ አድርገው ሲያነሱ ስለሰማሁ ጥሩ ማሳያ ነው፡፡
  6. ሌሎች ናቸው እንጂ አብይ የለበትም የሚል (እኔ የለሁበትም ፖለቲካ) አሳሳች ስልትን በተመለከተ- ይሄ አሁንም ብዙ ኦርቶዶክሳውያንና አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ያሳሳተ ነው፡፡አሁንም ኦሮምያ ክልል ብቻ እነ ሺመልስ እንዳስቸገሩ ተደገርጎ ሆን ተብሎ ይነገራል፡፡እውነቱ አጭር ነው፡፡ጃዋር በኦሮሞ ፖለቲካ ውስጥ ያለው ተጽኖ ይታወቃል፡፡ አብይ ግን ጃዋርን ሲያስር አንድ ቄሮ እንኳን ያንገራገረ አልነበረም፡፡መላው ኦሮምያ ጸጥ ነበር ያለው፡፡ሌላ ልጨምር፤ስንት የጸጥታ ችግር እንዳልነበር በምርጫ ወቅት ግን ኮሽ የሚል ነገር አልነበረም፡፡ እናም አብይ የሚፈልገው ኦነግ 50 ዓመት ታግሎ ያላሳካውን የኦነግ አላማ እኔ ይሄውና በአጭር ጊዜ ሰራሁት ብሎ ሃውልት እንዲያቆሙለት ስለሚፈልግ ነው፡፡በአናቱም ይላል ተመስገን – ለእነ ኦፌኮ የኦሮሞን ጥያቄ ይሄው ቆጥሬ መለስሁ እና ወንበሩን ስለምን ትሻላችሁ፤ተውኝ ልንገስበት ነው፡፡
  7. ይሄ ነጥብ አባቶችን አይመለከትም፡፡የሚመለከተው ኢትዮጵያን እንደ ዕጣ ፋንታቸው የሚያዩ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ነው፡፡ አብይ ከሱ በፊት ያሉት እንደሄዱት አሱም ይሸኛል፡፡የማናውቀው መቼ የሚለውን ነው፡፡ ከዳቦ አቅም እንኳን በየጊዜው ዕጨመረ ነው፡፡ ህዝቡ በአል እንደ ነገሩ ማሳለፍ ከጀመረ ቆይቷል፡፡የልጆቹን ልደት አያከብርም፡ወዘተ…የሞተውን፤የተፈናቀለውን ቤቱ ይቁጠረው፡፡ አሁንም ሌላ የሞት ድግስ በየቦታው እየደገሰ ነው፡፡ይሄንን ሁሉ ግን የደም እንባ እያነባ ችሏል፡፡ አሁን ግን ግፍ ሞልቶ እየፈሰሰ ነው፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ ግን አሁን እየገዛ ያለውን መገላገሉን እንጂ ስለ ቀጣዩ ማሰብ የሚፈልግ አይመስልም፤፤እንደ አለመታደል ሆኖ ታግሎ ያመጣውን ለውጥ ለሌላ የባሰ አስረክቦ፤ያው ሽክርክሪቱ እንዲቀጥል ያደርጋል፡፡ማሳያወችን ላንሳ፡፡የአጼ ሃይለ ስላሴን መንበር ያነቃነቀው ተማሪ ነው፡፡እነ ገርማሜ ንዋይ የሚሉም አሉ፡፡የሆነው ሆኖ ያስረከበው ለወታደሩ ነው፡፡ ደርግንም አሁንም ተማሪ ኢህአፐና መኢሶን ሆና ተደራጅታ አዳክማ በትንሽ ወጪ፤በአሜሪካም ድጋፍ፤ዛሬም ድረስ ቀጥሏል ለወያኔ አስረከበ፡፡ከዚያም ኦነገ 50 ዓመት የትጥቅ ትግል ታግሎ አንድ ቀበሌ ማስለቀቅ ያቃተውን ወያኔ፤ በቅንጅት ወንበሩን ነቅንቆ፤በብአዴን 100 ፐርሰንት የድምጽ ድጋፍ ከአራት ኪሎ ተባረረ፡፡በምትኩ የተካነው ግን ኢትዮጵያ በታሪኳ ሰምታው አይታው የማታውቀውን ጉድ አሳየን፡ሲኖዶስን-መስቀለቸውን እንኳን ለመሳለም ግርማቸው የሚያስፈሩትን አባቶች፤ በክላሽ እያዋከበ አገራችንንም ለማጣት በቋፍ ላይ እንገኛለን፡፡ ካለፈው ትምህርት የምንወስደው መቼ ነው? እንዴት የኢትዮጵያን ወዳጅ መለየት፤ማዘጋጀት አቃተን?
ተጨማሪ ያንብቡ:  ርዕዮት አለሙ በወህኒቤቱ አስተዳደር ክስ ቀረበባት

በጽሁፌ ውስጥ በስሜት የገለጽኁት ካለ በበጎ ተረዱልኝ፤፤

ከወገኖቼ፤ከሃይማኖቴ ጋር እንድቆም፤ ፈጣሪ ይርዳኝ! ምን ቀረን፤ሁሉን ተቀማን!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share