January 15, 2023
14 mins read

ሕገ-መንግሥቱ “የአንድነት ወይስ የመለያየት” የቃል-ኪዳን ሰነድ…?!

በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ለኢትዮጵያ “ውድቅትም ሆነ ትንሣኤ”፤ የሀገሪቱ የዕጣ ፈንታዋ የጽዋ ተርታዋ “አልፋና ኦሜጋ” አሁን በሥራ ላይ ያለው የኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት እንደሆነ ተደጋግሞ ይነሳል። አሁን ላለንበት ኁልቆ መሣፍርት ለሌለው ፖለቲካዊ ቀውሶቻችን አንዳንች መፍትሔ ይመጣ ዘንድም አሁን ሥራ ላይ ያለው ሕገ-መንግሥት፤ ሊከበር አሊያም ሊሻሻል ይገባዋል ከሚሉ ድምፅ ጀምሮ ይሄ ሕገ-መንግሥትማ የተጻፈበትን ወረቀት እንኳን ያህል ዋጋ የሌለው ሀገሪቱን ሲኦላዊ ቅርቃር ውስጥ የከተተ… የመፈራረስ፣ የመበታተን… ዓላማን ያነገበ የእርግማን/የጥፋት ሰነድ ነውና ተቀዳዶ መጣል፣ መቃጠል ነው ያለበት- የሚሉ ዋልታ ረገጥ ዓይነት ድምፆች እዚህም እዚያም ይሰማሉ።

የሆኖ ሆኖ የትኛውም ሕገ-መንግሥት የእግዜር ቃል/ መጽሐፍ ቅዱስ ወይም ቅዱስ ቁርዓን አይደለምና ሊሻሻል ሆነ ሊለወጥ የማይችልበት አንዳንች ምክንያት አይኖርም። ይህን ሐሳብ በመንደርደሪያነት ይዤ፤ ይህ አሁን በሥራ ላይ ያለውን የኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥትን በተመለከተ በዚህ በP2P መድረክ ላይ የሚነሱ የመከራከሪያ ሐሳቦች ላይ በመመርኮዝ ለውይይት መነሻ አሊያም ማዳበሪያ ይሆነን ዘንድ ጥቂት አስተያየት አከል ሐሳቦችን/መከራከሪያዎችን ለማንሳት ወደድኹ።
በመሠረቱ አሁን በሥራ ላይ ያለውን የኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት በተመለከተ በዚህ በP2P መድረክ የሚነሱ አንዳንድ የመከራከሪያ ሐሳቦች በግሌ እንዳስተዋልኩት- ይህ ሕገ- መንግሥት የመጣበትን/የተዋለደበትን ከገፊ ምክንያቶቹ አንፃር- ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለፈችባቸውን ታሪካዊ ጥያቄዎችና ውስብስብ ሂደቶቻቸውን በጥልቀት የመገምገም፣ የመፈተሽ ችግር/ክፍተት እንዳለበት የሚያሳይ ነው እላለኹ።
እንደ እውነቱ ከሆነ ዛሬ በሥራ ላይ ያለው ሕገ-መንግሥት እንደ ዱብዳ ከሆነ ቦታ መጥቶ በድንገት የተጫነብን ነገር አይደለም። የታሪክ ገጾቻችንን ስንፈትሽ፤ ለዚህ ሕገ-መንግሥት ዕውን መሆን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በተለያየ አቅጣጫና በመሰላቸው የፖለቲካ መስመር ክቡር ሕይወታቸውን ገብረዋል። መቼም ቢሆን ይህን የታሪክ እውነታ መካድ የምንችል አይመስለኝም። “ነጻነትን የማያውቁ ነጻ አውጪዎች” በሚለው መጽሐፉ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንደጠቀሰውም፤
“… በዘመናዊው ዓለም የፖለቲካ ትግል ታሪክ ውስጥ እንኳን የሚስተካከለውን ለማግኘት በሚያዳግት መልኩ፤ በርካታ ኢትዮጵያውያን ለፍትሕ፣ ለመብታቸውና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መስፈን እጅግ ግዙፍ የሆነ መሥዋዕትነትን ከፍለዋል…፤” ይለናል።
በርግጥ ይህ የሺዎች ደም የተገበረለት የዲሞክራሲ፣ የመብትና የፍትሕ ጥያቄ በትክክል ምላሽ አግኝቷል ወይ?! የሚለው ሌላ ትልቅ ጥያቄ ሆኖ ሳለ ግን ይህን ሀገራችን የምትተዳደርበትን ሕገ-መንግሥት ዕውን በማድረግ ረገድ ዛሬም ድረስ የተከፈለውንና የከፈሉትን መሥዋዕትነት ክቡርና ትልቅ ዋጋ ያለው እንደሆነ በትልቁ የሚያነሱና ይህን ሕገ-መንግሥት እንደ ዓይናቸው ብሌን የሚያዩት፣ የሚሳሱለት ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን መኖራቸው ግን መዘንጋት ያለብን አይመስለኝም።
እንደ አብነትም፤
ከሦስት ዓመት በፊት የምሠራበት ተቋም በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት ዙሪያ አንድ ሀገር አቀፍ ትልቅ የሕዝብ አስተያየት ጥናት/Public Opinion Survey አድርጎ ነበር። በዚህ ሀገር አቀፍ ጥናት ላይ ተሳታፊ ለመሆን ዕድሉን አግኝቼ ነበር።
ታዲያ ይህን በሕገ-መንግሥቱ ላይ የተደረገውን የሕዝብ አስተያየት ጥናት ስናካሂድ ለዚህ ጥናት ሲባል በሁሉም የሀገራችን ክልሎች ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች (የመንግሥትና የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ በወቅቱ ሕገ-መንግሥቱን በማርቀቅ ሂደት ከተሳተፉ ምሁራንና ሕገ-መንግሥቱ የማርቀቅና የማጽደቅ ሂደት ላይ በየቀበሌው ከተወያዩ የኅብረተሰብ አካላት፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የማኅበረሰብ ተወካዮች፣ ሴቶችና ወጣቶች… ጋር ያደርግናቸው የአትኩሮት የቡድን ውይይቶች/Focus Group Discussion እና በቁልፍ መረጃ ሰጪ ቃለ-መጠይቅ/Key Informat Interview ሂደት ላይ ያጋጠሙኝና ያስተዋልኳቸው እውነታዎች በሕገ-መንግሥቱ ዙሪያ ላይ ያለኝን ምልከታ በጥልቀት እንድፈትሽና እንድመረምር ያደረጉኝ አጋጣሚዎቹ ነበሩ።
እንደ አዲስ አበባ ባሉ ከተሞችና በተለይ አዳጊ ክልሎች በሚባሉት ሕዝቦች ዘንድ አሁን በሥራ ላይ ያለውን ሕገ-መንግሥት በተመለከተ ያለው የተራራቀ ምልከታ ያስገረመኝ ብቻ ሳይሆን ከእኔ ቅድመ-ግምት የራቀ በመሆኑም የደንገጥኩበትም ጭምር ነበር። በተለይ የአብዛኞቻችን ትኩረት በሆነው አንቀጽ- 39ን በተመለከተ። በርግጥም በቀጣይ ጽሑፌ ገጠመኞቼን መሠረት አድርጌ በሕገ-መንግሥታችን ዙሪያ የጀመርኩትን ሐሳብ በሰፊው እመለስበታለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
ሌላው እንደ አብነት የምጠቅሰው፤
በዘመነ ሕወሓት/ኢሕአዴግ፤ “የተጻፈበትን ወረቀት ዋጋ እንኳን የማይመጥን፣ ሕገ-አራዊት” የሚል ስያሜ ሰጥተውት ለበርካታ ከዓመታት ይህን ሕገ-መንግሥት ሲኮንኑትና ሲያወግዙት የነበሩት የመንግሥት ዋንኛ ተቃዋሚዎች በሂደት “ሕገ-መንግሥቱ ይከበር!!” ወደሚል U-turn አቋም የተሸጋገሩት እንዲሁ በድንገት አይመስለኝም። አንድም ሕገ-መንግሥቱ የመጣበትን ውስብስብ ታሪካዊ ሂደቱን/የተከፈለውን ግዙፍ ዋጋ፣ መሥዋዕትነት ከመፈተሽና አንድም ደግሞ ይህ ሕገ-መንግሥት በተባበሩት መንግሥታት፣ በአፍሪካና በሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ዘንድ የጸደቁትን የሰብአዊና የዲሞክራሲያዊ መብቶችንና ሙሉ በሙሉ ያካተተ ሰነድ ሆኖ በማገኝታቸው ይመስለኛል።
ዛሬ ደግሞ የሚገርም የታሪክ አጋጣሚ ብለን ልንጠራው በተገደድንበት ኹናቴ ይህ ሕገ-መንግሥት- በአፍሪካና በዓለም አቀፍ መድረክ ትልቅ እውቅና እንዲቸረው ያደረገ ክስተትን ለማስተናገድ በቅተናል። እንደምናውቀው የፌዴራል መንግሥቱና የሕወሓት ኃይሎች/እኛም ራሳችን ሳንቀር ጎራ ለይተን/ተቧድነን (በቃልም በጠመንጃም) ለሁለት ዓመታት የተዋጋንበት የእርስ በርስ ጦርነት/ዘግናኝ እልቂት በዕርቀ-ሰላም ይቋጭ ዘንድ ስምምነት ላይ ሲደርስ፤ በተደራዳሪዎችም ሆነ በአደራዳሪዎቻችን/በታዛቢዎች ዘንድ ከቀረቡት ምክረ-ሐሳቦች መካከል ቀዳሚውና ዋንኛው ይህ ነበር፤
“ሕገ-መንግሥቱን መሠረት አድርጋችሁ ተነጋገሩ፤ ተደራደሩ!! የድርድሩ ማዕቀፍም ሕገ-መንግሥቱና ሕገ-መንግሥቱ ብቻ ይሆናል!!” ይህ ምን ማለት እንደሆነ ለብዙዎቻችን ግልጽ ይመስለኛል።
ለማጠቃለል ያህል፤ ከዚህ በሻገር ግን ሕገ-መንግሥቱ፤ “ኢትዮጵያ ላይ የመበታተን፣ የመፈራረስ አደጋን የደቀነ… ሀገሪቱን በብሔር/በጎሳ የከፋፈለ፣ የዜግነት መብትን የደፈጠጠ፣ የመገንጠል/የመገነጣጠል መብትን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ዕውን እያደረገ… በአጠቃላይ የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያውያንን ህልውና ቅርቃር ውስጥ የከተተ፣ የአንድነታችን አደጋ… ወዘተ. የሚሉ አሉ።
በተቃራኒውም ደግሞ ይህ ሕገ-መንግሥት የህልውናችን መሠረት፣ በፈቃደኝነታችን ላይ የተመሠረተ የቃል-ኪዳን ሰነዳችን… ቋንቋችንን፣ ታሪካችንን፣ ቅርሳችንን፣ ባህላችንን ያስከበረ፣ ለማንነታችን ዕውቅና የቸረ፣ ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነታችን/ኢትዮጵያዊነታችን መሠረት የጣለ… የሚሉ አስተያየቶችንና እሳቤዎችን በብዛት እንሰማለን።
በሁለቱም ወገን የሚነሱ ሐሳቦችና መከራከሪያዎች በደንብና በቅጡ ሊፈተሹ ይገባቸዋል የሚል ሐሳብ ነው ያለኝ። በዚህ ረገድ መወያየትና መከራከር ካለብንም በምክንያት፣ በታሪካዊ ማስረጃ/በእውቀትና በመሬት ላይ ያለውን እውነታም ተመርኩዘን መሆን ይኖርበታል። የመከራከሪያ አጀንዳዎቻችንም ዘመንን የዋጁና ለትውልድ/ለሀገር የሚበጁ ይሆኑ ዘንድ ልንተጋ ያስፈልገናል።
አሁን በሥራ ላይ ባለው ሕገ-መንግሥት ዙሪያ ያነሳሁትን ሐሳብ በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ። እንግዲህ ሌሎቻችንም የዚህ መድረክ አባላት በእውቀት፣ በምክንያታዊነትና በቅንነት መንፈስ ሐሳብን በሐሳብ እንቃወም፣ ሐሳብን በሐሳብ እናዳብር፣ ሐሳብ ለሐሳብ እንፋጭ (ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ፤ “ብረት ብረትን ይስለዋል፤ ባልንጀራም ባልንጀራውን፤” እንዲል) እናም በዚህ መንፈስ እንወያይ፣ እንነጋገር፣ እንመካከር… ደግሞስ ሀገር አቀፍ የኾነ ምክክር ለመጀመር ኢትዮጵያ ሀገራችን መንገዱን ጀምራውም የለ… እናም መነጋገርሩ፣ መወያየቱ፣ መመካከሩ ነው የሚበጀን፣ የሚያባጀንም።
ሰላም ለኢትዮጵያ፤ ሰላም ለምድራችን!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop