” ዐውደ ዓመት ና የሰው ተስፋ … ገ …ና ”  መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ዐውደ ዓመት በየዓመቱ የሚከሰት ማለት ነው ።ገ…ና የሚመጣ ። ሁሉም  ዓመት በዓሎች ገ…ና   በየዓመቱ የሚከሰቱ ናቸው ።  በተለምዶ አውደ ዓመት ይባላሉ ። ያው ዞረ   የሚከሰቱ ፣  ዑደታቸው የማያቋርጥ ገ…ና  ሥለሆኑ ። …

አውደ ዓመቶቻችን ብዙ ናቸው ።

በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ፣  ገና ( የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ቀን ) ፣ ጥምቀት ( መጥመቁ ዮሐንስ  ኢየሱስ ክርስቶስን ሲያጠምቀው የኢየሱስ  ዓምላክነት በግልፅ ከሰማይ የተመሠከረበት ቀን ።)  ፣  ሥቅለት ( ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል ለመንሣት በዕለተ ዓርብ የተሰቀለበት ቀን ) ፋሲካ ( የክርስቶስ ኢየሱስ ትንሣኤ ፤  ሞትን ድል አድርጎ ከሞት   የተነሳበት ቀን )

በሙስሊም እምነትም አውደ ፣  ዓመቶች አሉ ። ሥራ የማይሰራባቸው የፆም ፣ የልደትና ፣ የፈጣሪን ቸርነት ማሣያ በዓለት ፣ በየዓመቱ ይከበራሉ ። ግን ለምንድነው በየዓመቱ  ” የዓመት ባዓሎቹ ” ብርቅና አዲስ የሚሆኑብን ? ለምሣሌ ገና ፣ ታህሳስ 29 (በየአራት ዓመቱ በታህሳስ 28 ይከበራል ። ) ላለፉት 2015 ( በእኛ አቆጣጠር )  ዓመታት ደጋግሞ ገና መጥቷል ። ይምጣ እንጂ ዛሬ የምናከብረው ” ገና ” ካለፈው “ ገና “ ፈፅሞ አይመሣሠልም ።  አዲስ ቀን ነው ። በየዓመቱ ።

ገና በየዓመቱ ፣ አዲስ ቀን ነው ማለት ምን ማለት ነወ ?

አዲስ ቀን ትላንት ያልሆነ ያልተኖረ ፣ ያልኖርነው ቀን ማለት ነው ። በሩቅ የሚታሰበን በጊዜ መፈራረቅ የደረሰ አዲስ ቀን ሆኖም ከዕምነታችን  እና ከባህላዊ እሴታችን ጋር በብርቱ የተቆራኘ ቀን ማለት ነው ።  ለዚህ ለሰርክ አዳስ  አውደ አመት  ፤ በታሪክ ለየት ያለ ቀን ፣  ” ሽር ጉድ ” ብንልነት ፣ አይበዛበትም ። ካለን ፣  ኪሳችን ካበጠ ምን ችግር አለው ? ኪሳችንን  በሚገባው መጠን እናስተነፍሰዋለን ።  ከሌለንም   ተለቅተንም ሆነ ተበድረን በደመቀ ሁኔታ እናከብረዋለን ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አብይ አህመድ የስድስተኛ ክፍል ደረጃ ሙህር ዶ/ር ለካቢኔው የሰጠው ሁለተኛው ፈተና

ገና ( የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን ። )   ሥሙ ፣ ኃይማኖታዊ ትርጉሙ ከቶም ሳይለወጥ በየዓመቱ ያው እና አንድ ሆኖ ሣለ ፤ በየዓመቱ እንደ  አዲስ  ማክበራችን ግን ሁሌም ያሥገርመኛል  ።

አውቃለሁ ። ሰው ነገን ናፋቂ ነው ። ነገ ለሰው ሁሌም አዲስ ነው ።  ሰው ትላንትን ቶሎ የሚረሳ  ፍጡር ነው ። አብሶ መጥፎ መጥፎውን ለማስታወስ አይፈልግም ።  ነገ የተሻለ እንዲገጥመው ግን አጥብቆ ይሻል  ።  ሰው ተሰፋው በነገ ላይ የተመሠረተ ፍጡር ነው ።   እናም ሰው ነገን በጉጉት እና በናፍቆት ይጠባበቃል ። ነገ ያሥደስት ፣ ወይ ያስከፋ ግን አያቅም ።  ነገ ሁልጊዜ ነገ ነው ። መቋጫ የለውም ።  የሞተ ብቻ ነው ነገ የሚቋጭለት ። ሰው ከነገ ናፍቆት የሚገላገለው ሲሞት ብቻ ነው  እናም ፣ ሰው ህይወቱ እሥካለች ጊዜ ድረስ ነገን የሚጠብቅ አሳዛኝ ፍጡር ነው  ።

ለሰው ፣ ያልኖራቸው ፣ ከፊት ለፊቱ ያሉ የልነጉ  ቀናቶች ሁሉ ነገ  ይባላሉ ። ሰው ፣ ነገ መሽቶ _ እንደነጋ  የሚያያት ፀሐይ ፣ ያቺ ፤ የአህያ ሆድ የምትመስለው ፣ ሁሌም  አዲስ  ናት ። ፀሐይቱ ሥትጠልቅም ” በሰላም ያዋልከኝ በሰላም አሳድረኝ ። ” ብሎ የሚፀልየው አዲሷን ነገ ለማየት በብርቱ ሥለሚሻ ነው ።  እንግዲህ ከዚህ ነገን ያለማወቅ እና ” ዛሬን ኖሬ ለነገ እበቃ ይሆንን ? ”  በሚል ጥርጣሬ ሰው ልጅ ሥለሚኖር ፣ ፊቱ ያሉትን ፣ ያልኖራቸውን ቀናት በእጅጉ ይናፍቃል ።

ዛሬ በህይወት ያለ ሰው ፣ የዛሬውን የጌታችንን የመድኃኒታችንን የ 2015 ዓ/ም  የልደት ቀን እያከበረ ፤ ለ2016 ዓ/ም በሠላምና በጤና እንዲያደርሰው ይለምናል ። “ዓመት ከዓመት ያድርሰን ። እንዲሁ እንዳለን አይለየን ።  ” እያለ ይፀልያል ። እስከ መቃብር ። በተሰለፈው የሞት ሰልፍ መሠረት እየተጠራ ሥጋው ወደ አፈሩ እሥኪመለሠስ ድረሥ …

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሳዑዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 135 ሰዎችን በሽብርተኝነት ክስ አሰረች

 

መልካም የመዳኃኒዓለም የልደት ቀን ይሁንላችሁ ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share