1. ብቃት አልባው ጠ/ሚ
2. የበሰበሰው በሙስና የዘቀጠው እና የመከነው ብልጽግና ፓርቲ የመንግሰትን የማስፈጸም አቅም ማሳጣቱ
3. በበቀል ስሜት ጠላቴ ያለውን የአማራን ህዝብ ሊፈጅ ከእነትጥቁ ገብቶ ዘር ማጥፋት በመንግሰት መዋቅራዊ ድጋፍ እየፈጸመ ያለው ኦነግ
4. በኦህዴድ ከሀዲነት እና ተረኝነት ምሬት ከፓርቲው የሚወጡ አንጃዎች እና ብሔሮች
5. በከፍተኛው ዘር ማጥፋት በእልህ እና ቁጭት እየጋመ ያለው የአማራ ብሔርተኝነት
6. በበቀል ስሜት የልቡን በልቡ ይዞ ወደ መንግሰት አስተዳደር እየመጣ ያለው ብርቱው ህወሓት
7. መለስ ዜናዊ ሊፈታው ያልቻለው እና ቀስ በቀስ ስር ወደ ሰደደ ጥላቻ እየተቀየረ ያለው የአዲስ አበባ ህዝብ ሊቀሰቅስ የሚችለው ከፍተኛ ህዝባዊ እምቢተኝነት እና አመጽ
8. በማድበስበስ በአሻጥር እና አለፍ ሲልም አፍ አውጥተው የኦሮሞን ጥቅም እስካልነካ ድረስ ወልቃይትም ራያም ወደ ትግራይ መመለስ ይችላሉ የሚለው የደካማው ጠ/ሚ አቋም አማራ እና ትግራይ ወደ ማይቀር ጦርነት ቢገቡ ይዳከሙልኛል የሚለው የተሳሳተ ስሌት
9. በሁለቱ አመት ጦርነት ውጤት ቀያሪ የነበረችው ኤርትራ ህልውናዋን ለማስጠበቅ በአማራ ኃይሎች በአፋሮች እና እንደአዲስ በአዳራጀችው የደካማዋ ሶማሊያ ጦር ልትፈጥር የምትችለው ጫና
10. የደቡብ አፍሪካው ስምምነት የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ ዘር ማጥፋትን ሴቶች እና ህጻናትን በበቀል ሲደፍሩ በነበሩ በሁለቱም ተፋላሚዎች ውስጥ ያሉ ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲቀርቡ ጉዳዩም በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ አለማድረጉ ወደ ዳግም ጦርነት ላለመመለስ ዋስትና አለመስጠቱ
11. የውጭ ኃይሎች የሚፈጥሩት እና እየፈጠሩ ያሉት ከፍተኛ ጫና
12. በብቃት አልባው በሙስና በዘቀጠው እና በዘር እየታመሰ ባለው ብልጽግና ችግር እየደረሱ ያሉት የኢኮኖሚ ቀውሶች አሁን ባለው ሁኔታ ሊሻሻሉ የማይችሉ በመሆናቸው…
.
የኢትዮጵያ ጉዳይ የጋራ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ምሁራን ወጣቶች የፖለቲካ ፓርቲዎች እና መላው ህዝብ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር እና ፍትሕ እንዲሰፍን ከጎሰኝነት እና ጠባብ ብሔረተኝነት ወጥተው ለሰብዓዊነት እና እኩል ተጠቃሚነት በሁሉም መድረክ ሰላማዊ ትግል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
PLEASE SHARE THIS MESSAGE FOR ALL ETHIOPIANS
ዮናስ