የጭራቅ አሕመድ ኦነግ ሸኔ እና የሂትለር ኤስ ኤስ – መስፍን አረጋ

November 20, 2022
13 mins read

ጭራቅ አሕመድ ስልጣኔን ለመንካት ብታስቡ መቶ ሺወቻችሁ ባንድ ጀንበር ትታረዳላችሁ በማለት ባዲሳቤወች ላይ በግልጽ ዝቷል፡፡  ልብ በሉ፣ ጭራቅ አሕመድ ያለው ተቃውሞ ይነሳል ወይም ሁከት ይፈጠራል ሳይሆን፣ መቶ ሺወች ይታረዳሉ ነው፡፡  ቁጥሩን ደግሞ አስቡት፡፡  መቶ ሺወች ነው ያለው፡፡  ይህ ማለት ደግሞ ቢያንስ፣ ቢያንስ ሁለት መቶ ሺወች ማለት ነው፡፡ ስለዚህም ጭራቅ አሕመድ በግልጽ የዛተው በስልጣኔ ብትመጡብኝ ቢያንስ፣ ቢያንስ ሁለት መቶ ሺወቻችሁ ባንድ ጀንበር ትታረዳላችሁ በማለት ነው፡፡  በርግጥም ጭራቅ አሕመድ፣ ጭራቅ ብቻ ሳይሆን፣ ጭራቀ ጭራቅ (የጭራቆች ጭራቅ) ነው፡፡

አሁንም እንደገና ልብ በሉ፣ ጭራቅ አሕመድ ያለው ስልጣኔን ብትነኩ ሳይሆን ስልጣኔ ለመንካት ብታስቡ (ማለትም እኔን ተቃውማችሁ ሰላማዊ ሰልፍ ብትወጡ ወይም ድንጋይ ብትወረውሩ) ነው፡፡  ግራዚያኒ ቦንብ ተወረወረብኝ ብሎ ባንድ ጀንበር ሠላሳ ሺ ጨፈጨፈ ብለን ለዘመናት ጉድ ስንል፣ የኦነጉ ጭራቅ ደግሞ ድንጋይ ብትወረውሩብኝ መቶ ሺወቻችሁን ባንድ ጀንበር አርዳችኋለሁ ብሎ በግልጽ ዛተ፡፡  ዛቻውን የዛተው ደግሞ ትታረዳላችሁ የሚለውን ዘግናኝ ቃል ካንደበቱ ሲያወጣ ምንም ሳይሰቀጥጠውና፣ ዛቻውን እንደሚፈጸመው ፍጹም ርግጠኝነቱን በግልጽ በሚያመላክት ሁኔታ ፍጹም በተረጋጋ መንፈስ ነበር፡፡

ጭራቅ አሕመድ በርግጠኝነት መንፈስ ይህን ዓይነት ሰቅጣጭ ዛቻ ሊዝት የሚችለው ደግሞ፣ በቀጥታ የሚያዘውና ትዛዙን ለመቀበል በተጠንቀቅ የሚጠባበቅ፣ እረድ ያለውን ሁሉ ለማረድ ቅንጣት የማያቅማማ ተወርዋሪ አራጅ ሠራዊት አዘጋጅቶ ካስቀመጠ ብቻና ብቻ ነው፡፡  ጭራቁ ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ በየዕለቱ የሚከሰቱት ሁሉም ክስተቶች በማያሻማ ሁኔታ የሚያረጋግጡት ደግሞ፣ ይህ የጭራቅ አሕመድ ተወርዋሪ አራጅ ሠራዊት ሌላ ማንም ሳይሆን፣ ራሱ ጭራቅ አሕመድ ኦነግ ሸኔ የሚለው፣ የራሱ የጭራቅ አሕመድ ክብርዘብ (republican guard) የታጠቀውን ዘመናዊ መሣርያ እንዲታጠቅ ያደረገው አራጅ ሠራዊት ነው፡፡

የጭራቅ አሕመድ ኦነግ ሸኔ ሚና ከኤዶልፍ ሂትለር (Adolf Hitler) ኤስ ኤስ (Shutzstaffel, SS) ሚና ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡  ጭራቅ አሕመድ ኦነግ ሸኔን ፈጥሮ የሚጠቀመበት፣ ኤዶልፍ ሂትለር ኤስ ኤስን ፈጥሮ ይጠቀምበት በነበረው መንገድ ነው፣ ምንም እንኳን የጭራቅ አሕመድ ሸኔ ባውሬነቱ፣ የሂትለርን ኤስ ኤስ ቀርቶ የሃብያሪማናን (Habyarimana) ኢንትራሃምዌ (interahamwe) ሺ እጥፍ የሚያስከነዳ ወደር የለሽ ጭራቅ ቢሆንም፡፡

ኤዶልፍ ሂትለር ታላላቅ የጀርመን ጦር መሪወችን በተለያዩ ምክኒያቶች ገድሎ፣ አባሮና በጡረታ አሰናብቶ፣ በምትካቸው ዊሊያም ካይትልን (Wilhelm Keitel) የመሳሰሉ፣ በናዚ አስተሳሰብ የሰከሩ፣ ሲጠራቸው አቤት፣ ሲልካቸው ወዴት የሚሉ አሸርጋጆችን (yes men) በመሾም፣ የጀርመንን መከላከያ ሠራዊት (Wehrmacht) የናዚን የመስፋፋት አጀንዳ  የሚያስፈጽም የናዚ ሠራዊት አደረገው፡፡  በሌላ በኩል ደግሞ የጀርመን ሕዝብ ሰጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛለት ሽበር ለመልቀቅ፣ ጀርመናዊ ተቃዋሚወቹን ለመረሸንና፣ ይሁዳወችን በይሁዳነታቸው ብቻ ለመጨፍጨፍ ኤስ ኤስ የተሰኘውን ኢመደበኛ ሠራዊት (paramilitary force) መሠረተ፡፡

ኦነጋዊው ጭራቅ አሕመድ ደግሞ እሱ ራሱ ጠቅላይ አዛዥ በሆነበት በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ ቀንደኛወቹን አነጋውያን ብርሃኑ ጁላን ኢታማዦር ሹም፣ ቀንዓ ያደታን መከላከያ ሚኒስትር፣ ይልማ መርዳሳን አየር ኃይል አዛዥ በማድረግ በኦነጋውያን ቁጥጥር ሥር አውሎ፣ የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት የኦሮሙማን የመስፋፋት አጀንዳ የሚያስፈጽም የኦሮሙማ መደበኛ ሠራዊት አደረገው፡፡

ይህ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትነት ወደ ኦሮሙማ መደበኛ ሠራዊትነት የተለወጠ የኦሮሙማ ግዙፍ ጦር የኦሮሙማን የመስፋፋት አጀንዳ የሚያስፈጽመው ደግሞ ኦነግ ሸኔ ከሚባለው በጭራቅ አሕመድ በቀጥታ ከሚታዘዘው የኦሮሙማ ኢመደበኛ ሠራዊት ጋር በመናበብ እየተቀናበረ የተለያዩ ዘዴወችን በመጠቀም ነው፡፡  ከነዚህ ዘዴወች ውስጥ ደግሞ ዋና ዋናወቹ የሚከተሉት ሦስቱ ናቸው፡፡

ያንደኛው ዘዴ ዓላማ የኦሮሙማን አጀንዳ የሚቃወሙትን፣ የኦሮሙማ ጅብ በመጨረሻ የሚበላው ራሱን የኦሮሞን ሕዝብ መሆኑን የተረዱትን፣ ባንኮችን አላስዘርፍ፣ ጌድኦወችን አላፈናቅል፣ አማሮችን አላሳርድ፣ ጋሞወችን አላዋርድ የሚሉትን አገር ወዳድ ኦሮሞወችን ማስወገድ ነው፡፡  በዚህ ዘዴ መሠረት አገር ወዳድ ኦሮሞወች ባውራ ጎዳና ላይ በጠራራ ፀሐይ እየተረሸኑ፣ ለሌሎች አገር ወዳድ ኦሮሞወች መቀጣጫ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡  አያሌ ኦሮሞወች በተለያዩ የወለጋ ከተሞች ውስጥ ባደባባይ የተረሸኑት በዚህ ዘዴ መሠረት ነው፡፡

የሁለተኛው ዘዴ ዓላማ ኦሮምያ የሚባለውን፣ ወያኔ አማራን ለመጉዳት ሲል ብቻ አንቦራቆ የፈጠረውን ጊዜው ሲደርስ ሙሉ በሙሉ መፈራረስ ያለበትን ኢፍትሐዊ ክልል ሙሉ በሙሉ ካማሮች ማጽዳት ነው፡፡  በዚህ ዘዴ መሠረት የኦሮሙማ መደበኛ ሠራዊት አማሮች በብዛት በሚገኙባቸው ቀበሌወች ገብቶ በመስፈር አማሮች መከላከያ አለልን ብለው እንዲዘናጉ ካደረጋቸው በኋላ፣ በድንገት ለቆ ይወጣል፡፡  እሱ በድንገት ለቆ ሲወጣ ደግሞ የኦሮሙማ ኢመደበኛ ሠራዊት (ማለትም ኦነግ ሸኔ) እግር በግር ተከትሎ ይገባና የተዘናጉትን አማሮች ሴት፣ ወንድ፣ ሕፃን፣ አረጋዊ ሳይል በገጀራ ይቆራርጣቸዋል፡፡  ከጭፍጨፋው አምልጠው ጫካ የገቡት ደግሞ በረሐብ እንዲያልቁ ይደረጋሉ፡፡  ባቅራቢያ የሚገኙ አማሮች ደግሞ በጭፍጨፋው ዘግናኝነት በመሸበር ማቄን፣ ጨርቄን ሳይሉ ጣጥለው ይጠፋሉ፡፡ ቀበሌውና አቅራቢያወቹም ሙሉ በሙሉ ካማራ ይጸዳሉ፡፡

የሦስተኛው ዘዴ ዓላማ በሌሎቹ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ መሬቶችን ወደ ኦሮምያ ማጠቃለል ነው፡፡  በዚህ ዘዴ መሠረት አነግ ሸኔ (መከላከያ ከጀርባው ሁኖ በከባድ መሣርያ ከፍተኛ እገዛ እያደረገለት) ወደተወሰነ ቀጠና በተደጋጋሚ እየገባ ጅምላ ጭፍጨፋ እያካሄደ ከፍተኛ መፈናቀልን ያስከትላል፡፡  ጭራቅ አሕመድ ደግሞ ጭፍጨፋውና መፈናቀሉን ሰበብ አድርጎ በኦነጋዊ ጀነራል የሚመራ ኦነጋዊ ኮማንድ ፖስት ያቋቁምና፣ የቀጠናውን አስተዳደር ሙሉ በሙሉ በኦነጋውያን ቁጥጥር ሥር ያደርገዋል፡፡  በቀጠናው ውስጥ የተቋቋመው ኦነጋዊ ኮማንድ ፖስትና ኦነጋዊ አስተዳደር ደግሞ ከጭፍጨፋውና ከመፈናቀሉ የተረፉትን አማሮች በሽብርተኝነትና በሌሎች ምክኒያቶች እየነቀለ በምትካቸው ኦሮሞወችን በመትከል የሕዝብ አሰፋፈርን ቀይሮ ቀጠናውን የኦሮምያ አካል ያደርገዋል፡፡  በመተከል፣ በሰሜን ሸዋና በደቡብ ምሥራቅ ላኮመልዛ የተደረገውና እየተደረገ ያለውም ይሄውና ይሄው ብቻ ነው፡፡

ሂትለር ኤሰ ኤስን የመሠረተው፣ ውድቀታቸውን ሁሉ በይሁዳወች እያሳበቡ በይሁዳ ጥላቻ የተመረዙ እርነስት ሮምን (Ernst Rohm) የመሳሰሉ ውድቀታም (loser) ወታደሮችን በማሰባሰብ ነበር፡፡  ጭራቅ አሕመድ ደግሞ የኦነግ ሸኔን አስኳል የፈጠረው በኤርትራ በርሓ የሚሰቃዩትን ስቃይ በፀራማራ ትርክት እንዲያስታግሱ ይደረጉ ከነበሩት፣ ትጥቃቸውን ሳይፈቱ እንዲገቡ ካደረጋቸው የኦነግ መንጋወች ውስጥ ይበልጥ ጽንፈኛ የሆኑትን በመምረጥ ነው፡፡

ያይሁዶች ዋና ጠላት ናዚው ሂትለር እንደነበር ሁሉ፣ ያማራ ሕዝብ ዋና ጠላት ደግሞ ኦነጋዊው ጭራቅ አሕመድ ነው፡፡  ሂትለር ሲወገድ አይሁዶች ከናዚ እንደተገላገሉ ሁሉ፣ ጭራቅ አሕመድም ሲወገድ የአማራ ሕዝብም ከኦሮሙማ ይገላገላል፡፡  የአማራ ሕዝብ ዋና ትኩረቱን በዋና የሕልውና ጠላቱ በጭራቅ አሕመድ ላይ አድርጎ ጭራቁን ጨርቅ ካደረገ፣ ወያኔና ኦነግ እዳቸው ገብስ ነው፡፡

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

6 Comments

 1. ሰሞኑን ያቴውዽሮስ የተባለው የወያኔ ወኪል ደረጀ የሚባለውን የወያኔ ተቃዋሚ የወቅቱ ፖለቲካ ተቺ በማድረግ እንዳቀረበው ይህ መስፍን አረጋ የተባለውም ዘመቻ ጀምሯልአይሳካለትም:: የሰባተኛው ንጉስን ማታለል ባውቅም የሚፈጽማቸውን በጎ ነገሮች በማበረታታት ከለየላቸው ጽንፈኞች ጫና ይርቅ ዘንድ መገሰጽ መምከሩን ቀጥላለሁ::

 2. ይህ እብደት ነው። ለምን ይሆን አንድ የሚያረገን ወይም የሚያመሳስሉን ስንት ሃሳቦች እያሉ እንዲህ ያለ እጅግ ከእውነት የራቀ ጽሁፍ የሚረጨው? አሁን ማን ይሙት ጠ/ሚሩ ከሂትለር ጋር የሚወዳደሩ ናቸው? ችግራችን ምንድን ነው? ለምንስ እንዲህ ያለ ከልክ ያለፈና መረጃ አልባ ጽሁፍ በዘሃበሻ ላይ እንዲጸባረቅ ተፈቀደ? ይህ እጅግ በጣም ያሳዝናል።
  እንደ እውነቱ ከሆነ በዓለማችን ላይ በሥራው ሙሉዕ የሆነ መንግስት የለም። ሁሉም ከእነ ጉድለቱ ነው የሚተራመሰው። በመሆኑም የጠ/ሚሩ መንግስት ምጡቅ ነው ስህተት አልሰራም የሚል ሰው ያለ አይመስለኝም። ግን የመንግስት ችሎታም ሆነ ተግባር ተፈጻሚነቱ የህዝብ ተሳትፎ ሲኖረው ነው። የኢትዮጵያ ይበልጡ ችግር ከህዝቡ ከራሱ የሚመነጭ ነው። ሰው እያገተ ገንዘብ የሚጠይቅ፤ የራሱን ቤት እሳት ለኩሶ ተራብኩ ድረሱልኝ የሚል፤ በሃይማኖት ዙሪያ ራሱን ሸፍኖ በእምነቱ የማይኖር ባጭሩ ተንኮልን የተላበሰ ህዝብ ነው። ይህ ተንኮል ከከተማ እስከ ገጠር የታየና የሚታይ ድርጊት ነው። ስለሆነም ራሳችን የማየት፤ ምን ሰራሁ፤ ምን አጠፋሁ ብሎ ራስን መፈተሽ ሲገባ ሁሌ ከመንግስት ጋር ግብግብ መግጠም ፍሬአማናቱ አይታየኝም። ጽሁፉ አማራው ህዝብ ተጎዳ ተበደለ ነው። እሱን ሁሉም ያውቃል። ግን የታለ ሰዎች በወለጋና በሌሎች ቦታዎች ጭካኔ የተሞላበት ጭፍጨፋ ሲፈጸም የትኛው ክልል ነው ለተቃውሞ ሰልፍ የወጣው? አማራው እርስ በእርሱ የማይስማማ አልፎ ተርፎም በእርዳታ የተላከን ቁሳቁስ እንኳን በጊዜ ማከፋፈል የተሳነው እንደሆነ መሬት ላይ ያለው እውነት ያሳያል። ከአክራሪ ኦሮሞዎች ጋር ስርግብ የገጠሙ እውነተኛ ሰዎች ቢኖሩም በህዝቡ ላይ የሚደርሰውን ግፍ ግን ማስቆም አልቻለም። ይህን የአሰራር ዝንፈት እንዴት ባለመልኩ ልንቀይረው እንችላለን፤ ለሃገሪቱ ደህነንትስ ማድረግና አለማድረግ የሚገቡን ጉዳዮች ምንድን ናቸው ብለን ራሳችን መጠየቅ ነው። ከዚህ ውጭ ያለው ሁሉ የነገርን ቋጠሮ ይበልጥ የሚያጠብቅ እንጂ ለህዝባችን ሰላምና ደህንነት አይጠቅምም። ከልክ ያለፈ አክራሪነት ለማንም አይረባም። ያው ግን መርዘኛው የሃበሻ ፓለቲካ ሰውን ካልነከሰና ካላጠፋ ስኬት ያገኘ አይመስለውም። የጭራቅ አህመድ ኦነግ ሸኔ እና የሂትለር ኤስ ኤስ የሚለው የአቶ መስፍን አረጋ ጽሁፍ ከመንገድ የወጣና ሊታረም የሚገባው ነው እላለሁ። በመጨረሻም እውቁ ባለቅኔና ገጣሚ ገሞራው (ሃይሉ ገ/ዮሃንስ) ከዘመናት በፊት በገጠመው አንድ ስንኝ ሃሳቤን እዘጋለሁ።
  መርዝን በመርዝነት ስለ መርዝ መመረዝ
  የመርዝን ለመርዙ በመርዙ ማስመረዝ።

 3. ተስፋ ባንተ ተስፋ ባለው እሳቤ ከማን ጋር ታመሳስላቸዋለህ? ሁለቱ የሚለያዩበትስ ከምኑ ላይ ነው? በቀለም ማለቴ አይደለም።

 4. ተስፋን መሠል ሰዎች በፍጹም አይገቡኝም፡፡ ጭራቅ አቢይ አህመድ መባል ሲያንሰው ነው፡፡ እንደዚህ ያለ ሸለምጥማጥ ሰው ዓለማችን በሰው ቅርጽ እስካሁን አላየችም፡፡ ይህን ጭራቅ የሚደግፍ ሰው ራሱም ጭራቅ ነው፡፡ በሰው ቁስል ጨው መነስነስ ለካንስ ቀላል ነው፡፡ በመሠረቱ የማንንም ሃሣብንበነፃነትየመግለጽ መብት አልጋፋም፤ ግን ተስፋ የምትባለው የህልማለም ሰው እባክህን በምስኪን አማሮች ደምና አጥንት አታላግጥ፤ ካላወቅህ አርፈህ ተቀመጥ፡፡ አለዛ በጭራቁ ግራኝ አቢይ እየደረሰብን ያለው ግፍ አንተም ቅመሰውና ፈጣሪ እውነቱን ያሣይህ፡፡ አሽቃባጮች ዋጋቸውን ቢያገኙእንዲህ በሰው ስቃይ አይዘባበቱም ነበር፤ ግፈኞች፡፡

 5. ሃመረ መልካም ብለሃል ሰውየው ሸለምጥማጥ ነው አካሄዱ የሚገባህ ከወደቅህ በኋላ ነው አደገኛ ሰው ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የሕወሓት የዛሬ የጦርነት ዝግጅት አማራ አፋርና ኤርትራን አብሮ ያቆማል? | Hiber Radio Special Program

Next Story

ከታሪክ ማህደር – ኔልሰን ማንዴላ በኢትዮጵያ

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም

አቢይ አህመድ ታላቁን አሜሪካንና የተቀሩትን የምዕራብ ካፒታሊስት አገሮችን ማታለል ይችላል ወይ? የአሜሪካ “ብሄራዊ ጥቅምስ ኢትዮጵያ ውስጥ“ እንዴት ይጠበቃል? የአሜሪካ እሴቶችስ(Values) ምንድን ናቸው?

ለመሳይ መኮንና ለተጋባዡ የቀድሞ “ከፍተኛ  ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት” በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን የስቴት ዴፓርትሜንት ውስጥ ተቀጥሮ ለሚስራው ኢትዮጵያዊ ሰው የተሰጠ ምላሽ!   ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ግንቦት 19፣ 2016(ግንቦት 27፣ 2024) መሳይ መኮንን በአ.አ በ17.05.2024 ዓ.ም አንድ እሱ  የቀድሞው “ከፍተኛ የኢትዮጵያ

ጎንደር ሞርታሩን እስከ ጄነራሉ ተማረከ | ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | ብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን

ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | “ፋኖ ከተማውን ቢቆ-ጣ-ጠር ይሻላል” ከንቲባው |“አብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን” ኮ/ሉ |“በድ-ሮን እንመ-ታችኋለን እጅ እንዳትሰጡ” ጄ/ሉ
Go toTop