November 15, 2022
6 mins read

ሜዳ ሲቃጠል ተራራ ከሳቀ ያ ተራራ ከሜዳው የበለጠ በእሳት መጎዳቱ አይቀርም – መኮንን ሻውል ልደጊዮርጊስ

127489623 gettyimages 1244430199.jpgበኢትዮጵያ አንድ መንግስት እንዳለ ነው በበኩሌ የማውቀው ። እንደ ህገ መንግስቱ ከሆነ የፌደራሉ መንግስት የኢትዮጵያ መንግስት ነው ፡  ለአስተዳደር ተብሎ የተከለሉ አስተዳደር አገልግሎት የሚሰጡ መንግስታት እንዳሉም አውቃለሁ ፡፡ ፖሊሶችም አሏቸው ፡፡ ልዩ ሃይልና ሚሊሻም ( ህገ መንግስቱ ባይፈቅድላቸውም  እስከ አፍንጫው የታጠቀ ልዩ ኃይል አለቸው ) ፡፡ እነዚህ ጦር መሳሪ የታጠቁ ኃይሎች ግን ህገመንግስቱን መጠበቅ እንጂ ማፍረስ አይገባቸውም ። ይሁን እንጂ በህገ መንግስቱ የተዘረዘሩት ሰብኣዊና ተፈጥሯዊ መብቶች በየክልሉ ሲጣሱ ለብዙ ጊዜ ታይተዋል ። ዛሬም ይህ አልተቋረጠም ፡፡ የሰው በህይወት የመኖር መብቱ በእጅጉ እየተጣሰ ሰው አይኑ እያየ በቢላዋ አንገቱ እየተቀላ ነው ። ይህ አረመኒያዊ ድርጊት የኢትዮጵያዊን መገለጫ አይደለም ። ይህ ድርጊት የታሪካዊ ጠላቶቻችን መገለጫ ነው ፡፡ ትላንት ልጆቻቸው የአፄ ዮሐንስን አንገት ቆርጠው ሲጨፍሩ ነበር ፡፡ ዛሬም ይህንኑ ድርጊት በህቡ እየፈጸሙት ነው ፡፡ ህዝብን ከህዝብ ለመለያየትና የማይታረቅ ቅራኔ ፤ የማያባራ እልቂት በአገራችን ለማምጣት ፡፡

ይህንን መንግስት አያውቅም ።ማለት ስህተት ነው ፡፡ ይሁን እንጂ መንግስት በህገመንግስቱ ያልተገባ አንቀፅ የታሰረ ይመስላል ፡፡ ይሁን እንጂ የክልሎችን ፍቃድ ሳይጠይቅ በየክልሎቹ ጸጥታን ለማረጋጋት እንዳይገባ የሚከለክለው የለም ፡፡ የተጠናከረ ጦርም በየክልሉ ማዋቀር ህገ መንግስቱን የመጠበቀ መብት አለው ፡፡

በእርግጥ አገራችን ደሃ ናት ። ደሃ ያደረግናትም እርስ በእርሳችን እየተጋደልን ነው ። የሚያጋድሉንም አውቀናል የሚሉ ያላወቂዎች ናቸው ። እነዚህ ያለዋቂዎች ሆድ እንጂ ጭቅላት የላቸውም ። ህሊና የላቸውም ። ግን እናወቃለን ብቻ ሳይሆን እናውቅልሃለን ባዮችና በአንደበታቸው እሳትነት ጎሳዬ ወይም ዘሬ ነው የሚሉትን ወደ ጥፋት ፣ ወደስርቆት እና ዘረፋ የሚመሩ ናቸው ። ሰርቶ ለመበልጸግ ሳይሆን እንዴት ዘርፎ መበልጸግ እንደሚቻል በማስተማር የዜጎችን አንጡራ ሀብት ለማዘረፍ አስታጥቀው የሚያሰማሩ እና ከአገር ጠላቶች ጋር በህቡ የሚሰሩ ናቸው ።

ይህንን እየተገነዘበ ፣ መንግስት የተለሳለሰ እና ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከህግ በላይ የሆኑ የጥፋት እና አገርን ደሃ ለማድረግ ተግተው የሚሰሩ ኃይሎችን ለማጥፋት ፣ ስውርና ረቂቅ ዕቅድ የለማውጣቱ  ተገቢ ብቻ ሳሆን ፍጹም ስህተት ነው ። ይህ ቀፋፊ እና በኢትዮጵያውያን ላይ ሊፈጸም የማይገባው ድርጊት መሆኑን በቅጡ ያለመረዳትም ነው ፡፡ ይህ የምር  ከሆነ ደግሞ ፣ ነገ እሳቱ ወደ ባለስልጣናቱ  ሲደርስ ነገ የመንግስት ባለስልጣን ሁሉ ማድረግ የሚገባውን የትክክለኛ ፍትህ ድርጊት ባለማድረጉ እጅግ ይቋጨዋል ።″ እኛ በሚያስፈሩ እና በሚፈሩ ጠባቂዎች ተከበናል ። የሚደርስብን የለም ። ማለትም ሞኝነት ነው ። ″ ቀኃሥም ሆነ ደርግ የሚፈሩ እና የሚያስፈሩ ጠባቂዎች ነበሯቸው ፡  ይሁን እንጂ ከፈጣሪ ቁጣ ምድራዊ ኃይል አላዳናቸውም ። ፍትህን የሚረግጥ ፣ በህግ የበላይነት የማይመራ እና  የዜጋን ተፈጥሯዊ መብት የሚያፍን መንግስት ሁሉ የሚጣላው ከፈጣሪ ጋር ነው ፡፡ እናም የፈጣሪ ቁጣ ደጃቸው እንደለ አውቀው ለንስሃ ቢዘጋጅ ይበጃቸዋል ።

አውቅ በአስተዳደርም ሆነ በሰባዓዊ መብት ጥበቃ ረገድ  ከህግ የበላይነት አሰራር ውጪ  በየክልሉ የባለስልጣን እና የህግ አስፈጻሚ አካላት ከህግ በላይ መሆን ጎልቶ ይታያል ። …

 

ያም ሆነ ይህ ፣ መንግስት ህዝብን እያቃጠለ ያለውን እሳት ተራራ ላይ ነኝ ብሎ ቀዝቀዝ ብሎ ጉዳዩን ማየት የለበትም ። ዝም ካለ ግን ነገ እሳቱ ሜዳውን ጨርሶ ወደተራራው መዝለቁን ከወዲሁ ይገንዘብ ። መንግስት መንግስት  በመሆኑ የተሰጠውን ኃይል በበቂ መጠን  ቢጠቀም ለአገር ሰላም እና ብልጽግና ይጠቅማል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው እና አሁን ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የሁለተኛ (ተፈራ ) ክፍለጦር ሰብሳቢ የነበረው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በክብር ተሰዋ። የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህሎና አደጋ ለመቀልበስ ያለ

ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል !

January 22, 2025
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

Go toTop