ሥጋ ! ማስታወሻ ! –   መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ሥጋ ! !

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ሰዎች ሁላችን…
ሥጋን እንወዳለን…
ሥጋን እናፈቅራለን…
ለሥጋ እንሞታለን…
ለሥጋዬ ለዘመዴ…
ሁሌም እንላለን።
ግና …
ከቶ ምን ይሆን ይህ ሥጋ ማለት ?
በዘር፣በቋንቋ በጎሣ ተቧድኖ
በመግደል ና በማረድ ሠልጥኖ …
የሚሞትለት ?
…………………………….
አልገባኝም ?!
የከብት ሥጋ ታርዶ እንደሚበላ
ዘወትር ሰው ልጅ እንሥሣን እንደሚቀላ
ይህንን አውቃለሁ…
በሥጋ ቤት ማሃት ሰው የበሬን ጥሬ ሥጋ
በአዋዜ እያጠቀሰ ይበላል ፣ በቢላዋ እየወጋ
ግና የሰው ሥጋ ፣ ይለያል ከከብት
በአዋዜ አጥቅሰው ላይመገቡት
ለምንድነው የሚያርዱት ሰውን ላይበሉት ??
…………………………………..
ይህንን አውቃለሁ …
የእንስሳ ስጋ ነው የሰው ልጆች ምግብ
አውሬ ነው ይህንን የማይገነዘብ ፡፡
እርግጥ ማንም ያውቃል…
ከብት ታርዶ፣ በወግ ተሰናድቶ
እየተጠለጠለ በሜንጦ ተወግቶ
ሰው ሁሉ ይበላል ከሥጋ ቤት ገዝቶ ፡፡
……………………………
ይህንን አውቃለሁ ።
እርግጥ ነው፤አልተሰምቶም …
ከቶም አልታይቶም …
የሰው ሥጋ ታርዶ ሲቀርብ ለገበያ
ሲሆን ግን ይታያል ፣ ለየወገኑ መንጠላጠያ
ለማንም ይሆናል ሥጋ የቡና ላይ ቁርስ
እየተነሳ የሚጣል የሚታማ ፣
ሆኖ ጥንብ እርኩስ ፡፡
………………………..
ይህንን አውቃለሁ ።
ሰው ለእንሥሣ ሥጋ፣ በባልትናው ተራቆ
ሥጋውን ቆንጣ አድርጎ ና አድቅቆ
በፈጠራው_ ጣዕሙን አጣፍጦ
ይበላል “ የፆም ሽሮ “ ብሎ አድፍጦ ።
ክትፎ፤ጎረድ፣ጎረድ፤ቁርጥና ምላስ ሰንበር
ምንቸት፣ ቀይ ወጡ፣ አልጫ እየተባለ በየዓይነቱ ሲዘረዘር
ቅቅል፣ ጥብሥ፣ ክትፎ፣ ምላሥና ሰንበር
ሥጋ በየፈርጁ ፣ “ በሚኖ “ ላይ ሲደረደር …
ይህንን ማንም አይቷል ።
ማንም ሰው በልቷል ።
በግልፅ በአደባባይ …
ይህንን አውቃለሁ ።
ሥጋን ሺ ጊዜ በሆዴ ቀብሬያለሁ ።
……………………………
አሳምሬ እውቃለሁ …
የሥጋን ሥጋነት
የእንሥሣትን መሥዋትነት
የስጋን…ምግብነት ።
ይህንን ማንም ያውቃል …
እኔም አሣምሬ አውቃለሁ…
ግና ጥቂት ሰው ነው ፣
ሰው ሆኖ የስጋውን ክቡርነት
በወግ የሚረዳው ፡፡
……………………
ሰዎች ሆይ !
በጣም የምንወደው ይህ ሥጋ …
እያየን እኮ ነው ፣ነፍሳችንን ሲወጋ ።
በዘርና በጎሣ ሰውነታችንን እየለካ
ሰውን ከሚዛን ላይ አጉድሎ እንሥሣን እየተካ
ክቡሩን ሰውነት ቆጥሮ ፣ እንደ ከብት ሥጋ
ሰው በሰው ላይ የግፍ ካራውን በአንገቱ ያሳርፋል
ዛሬም ሰው ሰውን እንደ ከብት ያርዳል ።
………………………..
ህሊናውን አጥቶ በዘር ቫይረሥ ሰው ተለክፎ
በመንጋነት ተደራጅቶ በደመነፍሥ ለግድያ ተሰልፎ
በጭካኔ ሰው ያርዳል ፣ ሰው ያቃጥላል !
በሀገሬ በኢትዮጵያ ዛሬም ኡኡታው ጦፏል !
…………………………………………..
ይህንን ዘግናኝ ጩኸት አሰማለሁ !
በዚህም አዝናለሁ ።
ሁሌም በብዕሬ አቤቱታ አቀርባለሁ
ኡኡ! …የመንግሥት ያለህ
እላለሁ ።
በወግ የሚሰማ ግን አጥቻለሁ ።
ምንላድርግ ? …
ከዚህ በላይ አቅም ከቶም የለኝም
መንግስት ብቻ ነውና ያለው ጉልበትና አቅም
ዜጋማ ምን አቅም አለው ?
ለመታረድ ቀን ጠባቂ ነው ።
ግን ሰው ሰው ሆኖ ሳለ
ቢላን ሰው አንገት ላይ እንዴት አዋለ ?
ያውም ህፃን እና አቅመ ደካማ ሴት ላይ
ቢላዋውን አሳርፎ ሲያርድ ሲታይ
ይህ ሰው ሰው ይባላልን ?
እስቲ መንግስት ፍረደን
ዘወትር አታሳርደን ።
ሳይዘገንነው ሲያርድ ወንድሙን
አስመስክሯልና አውሬ መሆኑን
ፍፅሞ ከሰው ተርታ ወጥቷልና
በዘር ቫይረስ ህሊናው ተወሯልና
ልክ እንደ ተኩላ እና እንደ ጅብ ማሰብ ስለጀመረ
ማቆሚያ የለውም ጭካኔው በማያዳግም ቅጣት ካልተማረ ።
……………………………………………………….
ይህንን አውቀለሁ…
ሰው አብዝቶ ቢመገብ የከብት ሥጋ
አወፍሮ እንደሚያዳርገው ለህመም፣ለአደጋ ።
ጥቂቱንም በወጣትነቱ እንደሚገለው የሥጋ ጥጋብ
በማያገባው እየገባ ፣ በስጋው ተመክቶ ሲደባደብ ።
ይህንን መራራ እውነት ብዙ ጊዜ አስተውያለሁ …
ያለጊዜያቸው ለሞቱት ወንድምና እህቶቼም አዝኛለሁ ፡፡
ሆኖም …
የከብት ሥጋ መብላት ፣ ሰውን ከብት አያደርግም…
የከብት ሥጋ ሥለ በላ ፣ ሰው ህሊናው እኮ አይሞትም
የበግ ፣ የፍየል ፣ የበሬ ፣ የላም ፣ የጥጃ አእምሮን አይወርስም
ሥጋ ስለበላ እንደከብት አያሥብም ።
……………………………..
ይህንን አውቃለሁ…
ሰው መሆኑን ለዘነጋ…
ሰው መሆኑን እንዲረዳ
ከመፀለይ በቀር
ምን አደርጋለሁ ??

ተጨማሪ ያንብቡ:  ምን ይሉታል ! - (ዘ-ጌርሣም)

ህደር 5 ቀን 2015 ታደተ
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

 

እነዚህ ሁለት ግጥሞቼ ታህሣሥ 26/2013 ሌሊት፣8:30 ላይ ፈጣሪዬ ከእንቅልፊ ቀሥቅሶኝ የፃፍኳቸው ግጥሜ ነው ፡፡

ዛሬ ደግሞ በወጉ ተሰነደ ።

ይህንን አውቃለሁ !…

( የግጥሙ ደራሲ መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ )

ማስታወሻ !

ሰዎች ሁላችን…

ሥጋን እንወዳለን…

ሥጋን እናፈቅራለን…

ለሥጋ እንሞታለን…

ለሥጋዬ ለዘመዴ… ሁሌም እንላለን።

ከቶ ምን ይሆን ይህ ሥጋ ማለት ?

በዘር፣በቋንቋ በጎሣ ተቧድኖ

ነው ወይ ተቧድኖ …

የሚሞትለት ?

…………………………….

ሥጋ እንደሚበላ

ይህንን አውቃለሁ…

ከሉካንዳ ገዝቼ ሥጋ በልቻለሁ

ግና  የሰው ሥጋ ፣ ይለያል ከከብት

በአዋዜ አጥቅሰው ላይመገቡት

ለምንድነው የሚያርዱት ሰውን ላይበሉት ፡፡

የእንስሳ ስጋ ነው የሰው ልጆች ምግብ

አውሬ ነው ይህንን የማይገነዘን ፡፡

እርግጥ ማንም ያውቃል…

ከብት ታርዶ፣  በወግ ተሰናድቶ

እየተጠለጠለ በሜንጦ ተወግቶ

ሰው ሁሉ ይበላል ከሥጋ ቤት ገዝቶ ፡፡

……………………………

እርግጥ ነው፤አልተሰምቶም  …

ከቶም አልታይቶም …

የሰው ሥጋ ታርዶ ሲቀርብ  ለገበያ

ሲሆን ግን ይታያል ፣ ለወገን መጠልጠያ፡፡

ለባዳም  ይሆናል ሥጋ የቡና ላይ  ቁርስ

እየተነሳ የሚጣል  የሚሆን ፣ ጥንብ እርኩስ ፡፡

………………………..

ይህንን አውቃለሁ፣

ሰው ለእንሥሣ ሥጋ፣ ባልትናውን አስረግጦ

ጣፍጦ እንዲገባ በፈጠራው_ ጣዕሙን አጣፍጦ

ክትፎ፤ጎረድ፣ጎረድ፤ቁርጥና ምላስ ሰንበር

ምንቸት፣ ቀይ ወጡ፣ አልጫ  ፍትፍት ሳይቀር

ቅቅል፣ ጥብሥ፣ ክትፎ፣ ምላሥና ሰንበር

እየተባለ ሥጋ በየፈርጁ ፣ ሥሙ እንደሚዘረዘር …

ይህንን ማንም ያውቃል

እኔም ይህንን አውቃለሁ

ሥንት ጌዜ በሆዴ ሥጋን ቀብሬያለሁ ።

……………………………

ይህንን እውቃለሁ …

የስጋን ሥጋነት

የእንሥሣን … ከብትነት፡፡

የስጋን…ምግብነት።

ይህንን ማንም ያውቃል፣

እኔም ደግሞ  አውቃለሁ…

ግና ጥቂት ሰው ነው ፣

የስጋን ክቡርነት በወግ የሚረዳው ፡፡

ይህንን አውቃለሁ !

በጣም የምንወደው  ይህ ሥጋ …

እያየን እኮ ነው ፣ነፍሳችንን ሲወጋ ።

በዘርና በጎሣ ሰውነታችንን  እየለካ

ሰውን ከሚዛን ላይ ጥሎ ሥጋን እየተካ

ክቡሩን ሰውነት ቆጥሮ ፣ እንደ እንሥሣ ሥጋ

ሰው በሰው ላይ ግፍ ዛሬም ግፍ እየፈፀመነው …

የሚሰራውን ሳያውቀ እየተነዳ በመንጋ ።

…………………………………………..

ይህንን አውቃለሁ !

በዚህም አዝናለሁ

ምንላድርግ

እኔ መንግስት አይደለሁ

ህዝብ ነኝ እና ነገ እታረዳለሁ ፡።

ሰው ግን ለምን ያርዳል እንደ ከብት ሰውን

እንዴት አይዘገንነውም ሲርድ ወንድሙን ?

ግድ የላችሁም ይህ ሰው አውሬ ሆኗል

ተጨማሪ ያንብቡ:  ነፃነት - በ እንደሻው በርጃ

ፍፅሞ ከሰው ተርታ ወጥቷል

ልክ እንደ ተኩላ እና እንደ ጅብ ማሰብ ጀምሯል

እንጂ እንዴት ሰው ፣ ሰው ሆኖ ወድሙን ይቀላል ?

ሰው አርዶ  ቢመገብ የከብት ሥጋ

አወፍሮ እንደሚዳርገው ለህመም፣ለአደጋ ።

ጥቂቱንም በወጣትነቱ እንደሚገለው  የሥጋ ጥጋብ

በማያገባው እየገባ ፣ በስጋው ተመክቶ ሲደባደብ ።

እርግጥነው ይህንን እውነት ብዙ ጊዜ አስተውያለሁ …

ያለጊዜቸው ለሞቱት ወንድምና እህቶቼም አዝኛለሁ ፡፡

ሆኖም …

የከብት ሥጋ መብላት እኮ ፣ ሰውን  ከብት አያደርግም…

የከብት ሥጋ ሥለ በላ ፣ ሰው  ህሊናው እኮ  አይሞትም ፡፡

የበግ ፣ የፍየል ፣ የበሬ ፣ የላም ፣ የጥጃ ወዘተ ፡፡ አይሆንም ።

……………………………..

ይህንን አውቃለሁ…

ሰው መሆኑን ለዘነጋ…

ሰው መሆኑን እንዲረዳ ግን

ዛሬም እፀልያለሁ፡፡

 

ማስታወሻ

እነዚህ ሁለት ግጥሞቼ ታህሣሥ 26/2013 ሌሊት፣8:30 ላይ ፈጣሪዬ ከእንቅልፊ ቀሥቅሶኝ የፃፍኳቸው ግጥሜ ነው ፡፡

ዛሬ ደግሞ በወጉ ተሰነደ ።

 

 

ድጋሚ ህደር 4 ቀን 2015 ተፃፈ

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share