የሚመጣው እየሆነ ካለው ይብሳል (እውነቱ ቢሆን)

ወያኔ አማራን ጠላት ብሎ ሰይሞና ለ27 አመታት አሰቃይቶ አፈናቅሎና ጨፍጭፎ ከቆየ በኋላ በህዝብ መራር ትግል ወንበሩን ለኦሮሙማ አስረክቦ የራሱን ታላቋን ትግራይን (እነርሱ አባይ ትግራይ ይሏታል) እንደአገር ለመመስረት ወደ መቀሌ ሸመጠጠ፡፡ወያኔወች  በሀብት ምንጭም ሆነ በመውጭያና መግቢያ በር የሰፋችንና የተለጠጠችን ትግራይ ግዛትን በካርታ ጭምር ሰርተውና በህልማቸውም ቃዥተው ላሰቧትታላቋ ትግራይ ብዙ ስራወችን ሰርተዋል፡፡ለዚሁ ስኬትም ብዙ  አስበውበትም ተዘጋጅተውበትም ስለነበረ ትጥቅም ስንቅም በበቂ ሰብስበው ነበር፡፡ በተለይ እስካሁን ድረስ ፈረንጆቹን የሚያስጮሁበት ቢሊዮኖች ዶላሮችን ከኢትዮጵያ ዘርፈው በውጭ አገራት ባንኮች አከማችተው ስለነበረ በውጭ አገራት  የተወሰኑ የውጭ ዜጎችና ታላላቅ የዜና ማእከላት ጭምር ከደሀዋ ኢትዮጵያ 27 አመታት ሙሉ ተዘርፎ የተከማቸን  ዶላር እየበሉ ብዙ  ጮሀዋል፡፡

ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓም ወያኔ የኢትዮጵያን  ሰራዊት ሰሜን  እዝን አድብቶና በዘር ለይቶ  በጨለማ በማረድ ወደአዲስ አበባ ያደረገውን ግስጋሴ በወኔና በቁጭት ሀያል በቁጥር ግን ጥቂት የነበሩት ጀግኖቹ የአማራ ልዩ ሀይል አባላት ቅራቅር ላይ የወያኔን ግትልትል ጦር ብትንትኑን አውጥተው ወደኋላ እንዲያፈገፍግ ባያደርጉት ኖሮ አሁን ያለው ታሪክ መልኩን በቀየረ ነበር፡፡

ምን ያደርጋል ብዙም ሳይቆይ በኦሮሙማ ኢትዮጵያ ጠል ዘረኛ አመራር የሚመራው ዉጊያ  በ”አፈግፍጉ” የሴራ ትእዛዛት እየተሸነፈ መጣ፡፡ ወያኔም ድል በድል እየሆነ እስከ ደብረ በርሀን ድረስ ዘልቆ ለመግባት ቻለ፡፤ ወያኔምአቅሙ የቻለውን ዘረፈ አጋዘ ጨፈጨፈ፡፡ እውነትን አጥብቆ ለሚከተል ሰብአዊ ፍጡር ያ ጦርነት በፈጸማቸው ሰቅጣጭ ድርጊቶቹና የወያኔ ወራሪ ሰራዊት እግረኛና ዘራፊ ቡድን እየተቀናጀና እየተናበበ በአማራና አፋር ላይ ባካሄደው አሳዛኝ  ወረራ፣ጥቃትና የህዝብ እልቂት ከውስጥ የኦሮሙማ መመሳጠር አልነበረበትም ለማለት ይከብዳል፡፡

ጊዜው ደርሶና በስኬትም ይሁን በስሌት ነገሮች ተቀያይረው “ጠላቶች ነን” ይባባሉ የነበሩት ኦሮሙማና ወያኔ  የህዝቡን ደም ተረማምደው አሁን በመላላስ ላይ ይገኛሉ፡፡እርቅና የሰላም ስምምነት በሚሉት ማሞኛ ህዝቡንና አገሪቱን የቁማራቸው መለማመጃ አድርገዋቸዋል፡፡ ህዝቡ አሁንም እዚያው በጨለማ፣ በስቃይና በፍርሀት ኑሮ ውስጥ ነው ያለው፡፡

ኦሮሙማ ይባስ ብሎ ሰሜኑን በማውደምና ደቡቡን በመሸንሽን የኦሮሞ ኢምፓየርን በኢትዮጵያዊነት መቃብር ላይ ለመትከል ባቀደው የፖለቲካ ስሌቱ መሰረት ቀዳሚውን የወቅቱ አጀንዳው ያደረገው ወልቃይትንና ራያን ፊት ለፊት አውጥቶ ለጦር ውድማነት እንድመቻቹ ማድረግን ነው፡፡ ለዚህ የኦሮሙማ ርኩስ አላማ ስኬት የአማራ ሆዳም ምስለኔወች ተልእኮ ምትክ የለሽ ነው፡፡

ከራሱ ከአማራው በወጡ ሆዳም ልጆቹ የተከዳውና አማራ ነን በሚሉ ነገር ግን አማራ ባልሆኑ የአውሬው አብይ አህመድ አሽከሮች የሚበወዘው የአማራ ህዝብ ህይወቱ ተመሰቃቅሎና ነገው ጨልሞ ይገኛል፡፡  በኦሮምያ ክልል ውስጥ አማራው በአማራነቱ  እየተለየ  በየሰአቱ እየታረደና እያለቀ ነው፡፡ አዲስ አበባን ሳይጨምር ቁጥሩ ከአስር ሚሊዮን የማያንስ አማራ ኢትዮጵያ አገሬ ናት ብሎስለሚያምን ወያኔ ኦሮምያ ብሎ በከለለው ግዝት ውስጥ ይኖራል፡፤

ተረኞቹና ያለልክ ያበጡት ኦሮሙማወች ደግሞ ይህንን ሁሉ የአማራ  ተወላጅ ከቻሉ በማባረር፣ በማረድና በመጭፍጨፍ ቁጥሩን ለመቀነስ ተግተው እየሰሩ ነው፡፡ ይህም አልበቃቸው ብሎ ህዝቡ አማራነቱን እየካደ ክልሏ የኦሮሞወች ብቻ ነች በሚሏት የኦሮምያ ክልል ውስጥ ለመኖር አማራነቱን ክዶና ኦሮሞነትን በግዴታ ተቀብሎ ሁለተኛ ዜጋ እንዲሆን ለማድረግ አስፈላጊውን እቅድ አውጥተው እየሰሩ ነው፡፡ ወያኔ ስልጣን እንደያዘ  ለአማራ  ክልልህ ነው ብለው በከለለት የአማራ ክልልም ውስጥ ያለውን አማራም የወያኔንና የኦሮሙማ የተጣመረ የፖለቲካ ሴራን ይቀናቀናሉ ብለው የሚያስቧቸውን አማራወችና የአውሬውን አብይ አህመድ አገዛዝ ይቃወማሉ ብለው የሚያስቧቸውን አማራወች ገድለዋቸውል፡፡ አስረዋቸዋል፡፡ አሁንም እየገደሏቸውና  እያሰሯቸው ነው፡፤

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለፋኖ አደረጃጀት የቀረበ መነሻ ሐሳብ - መስፍን አረጋ

በአሁኑ ሰአት በአብይ አህመድ ምስለኔወች በአስር ሽህወች የሚቆጠሩ አማራወች በእስር ቤት እየማቀቁ ይገኛሉ፡፡ የአማራ ክልል አመራር የሚባለው የአብይ አህመድ ምስለኔ የሆነው የሆዳሞች ስብስብም ይህንኑ በክልሉ የታሰሩ ከአስር ሽህወች የሚበልጡ ንቁና ግንባር ቀደም የአማራ ነጻነት ታጋዮችን ማሰሩን እንደ ስኬት ቅንጣት ሳያፍር በይፋ ወጥቶ በአማራ ቴሌቪዥን ጭምር እየተናገረው ነው፡፡  እነዚህን ምስለኔወችና ለሆዳቸው የተሸጡ አጋሰሶች እነማን እንደሆኑና የት የት ቦታም ላይ እንደሚገኙ የአማራ ህዝብ በነቂስ ያውቃቸዋል፡፡ ህዝቡ በአይነ ቁራኛ እያያቸው ነው፡፤ በአብይ አህመድ ደህንነቶች ከላይ እስከታች ታፍኖና ተወጥሮ የሚገኘው የአማራ ህዝብ የሚጠብቀው የአንዲት ክብሪት የመለኮስን ክስተት ብቻ ነው፡፤

ወያኔ ስልጣን ላይ ከወጣ ከ1983 ዓም ጀምሮ በክልሉ ውስጥ ብቻ የሚገኘው ከ30 ሚሊዮን ባላይ የሚቆጠረው የአማራ ህዝብ  በምስለኔወች እንጅ በራሱ ሀቀኛ ልጆች ተዳድሮ አያውቅም፡፤ ይህም ወያኔ ትግሉን “ሀ” ብሎ ሲጀምር ያቀደው ጸረ አማራ ስትራቴጅ ግቡን መታለት፡፡ ይሄዉና አሁንም  ኦሮሙማ ይህንኑ ተቀብሎ አማራን በምስለኔወች መግዛቱን ቀጠለበት፡፡

ወያኔ የኦሮሞ ህዝብን ለመግዛት ይመቸው ዘንድ ራሱ የጠፈጠፈው ኦህዴድ የተሰኘ  የኦሮሞ ድርጅት ከመፈጠሩ በፊት እነአባዱላ ገመዳን ጨምሮ ብዙ የኦሮሞ ምርኮኞች መጀመሪያ ላይ የተማረኩ መኮንኖች ድርጅት ውስጥ ከመመደባቸው ጥቂት ቀደም ብሎ ኢህአፓ (የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ) ውስጥ ነበሩ፡፡ ኢህአፓ በደርግ ክፉኛ በመታቱ ተፈረካከሰ፡፡ ከዚያም እነታምራት ላይኔን የያዘው አንደኛው የኢህአፓ ፍርካሽ  ወደወያኔ ገብቶ ስሙን  ወደ ኢህዲን (የኢትዮጵያ ህዝብ ድሞክራቲክ ንቅናቄ) እንድቀይር ሲደረግ የተወሰኑት የአብዮታዊ መኮንኖች ድርጅት አባላት በዚህ ድርጅት ውስጥ ነበሩ፡፡ ከዚያም ወያኔ የኦሮሞን ሰፊ ህዝብ በኦህዴድና የአማራን ሰፊ ህዝብ ደግሞ  በኢህዲን በስውር አደረጃጀት ተደላድሎ  መግዛት ጀመረ፡፤ ኦህዴድ ብዙም ስለማይጎረብጥ ስሙንም ግብሩንም ይዞ ዘለቀ፡፡ በተቃራኒው የአማራን ህዝብ ታሪክ ስለሚያውቅና   ክፉኛም  ስለሚፈራው ስለሚጠራጥረውም ስሙንም አደረጃጀቱንም አመራሩንም ወያኔ በየወቅቱ እየበወዘ የአማራን ህዝብ ትግል ዉሉ እንዲጠፋ ለማድረግ የቻለውን ሁሉ አደረገ፡፡

የየወቅቱ የዘር ፖለቲከኞች መቀለጃ የሆነው ሰፊውና በአገሪቱ ውስጥ ትልቁን የዘር ግንድ ይዞ በቁጥር በአንደኛ ደረጃ  የነበረውንና  በኢትዮጵያዊንቱ የማይደራደረውን አማራን የህዝቡን ቁጥር ከአመት ወደአመት “ቀነሰ” በማለት ቁማር ተጫወቱበት፡፡ የአማራው ትክክለኛ ቁጥር ከኦሮሞው ቁጥር በብዙ ሚሊዮኖች ይበልጥ እንደነበረ ምስክር የሚሆኑት አሁንም በህይወት ያሉትና ያኔ (በ1983 ዓም) ወያኔ ውድቅ ያደረገውን ትክክለኛውን የህዝብ ቆጠራ በበላይነት የመሩት የዚያው ወቅት የፍርድ ሚንስትር የነበሩት አቶ ማህተመ ሰሎሞን በህይወት ስላሉ ካልታፈኑ በስተቀር አሁንም ሊመሰክሩት የሚችሉት ሀቅ ነው፡፡

ወያኔ አማራን በራሱ ሀቀኛ ልጆች እንዲተዳደር እንደልፈቀደ ሁሉ ተረኛው ኦሮሙማም ይህንኑ አልፈቀደም፡፡ አማራ ሳይሆኑ በአማራ  ክልል ውስጥ አማራን እንደፈለጉ ሲገዙግዙት የነበሩት አማራ ያልሆኑት እነ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋሉዋና በረከት ስምኦን አይነቶቹ  ነበሩ፡፡ እነዚህ የባንዳው መለስ ዜናዊ ታማኞች ኢህዲን ይባል የነበረውን የአማራ አሻንጉሊቶች ጥርቅም ስሙንም ከኢህድን ወደ ብአዴን እንዲለውጥ ሲያደረርጉት ተግባሩንም ይበልጥ ጸረ አማራና ይበልጥ የሚጭኑትን የሚሸከም አህያ አድርገው አደራጁት፡፤ የወቅቱ የዚህ አዲስ  አወቃቀር  መገለጫም ወያኔ ጋር ሲፋለም የነብረውን ፋኖን ሰብስቦ ያሰረው የይልቃል ከፋለ የክልሉ “የስም” ፕሬዝዳንትነት፣ የግርማ የሽጥላ(የጅብጥላ) አድራጊ ፈጣሪነትና የከሀዲው የአብኑ በለጠ ሞላ (ቀለጠ ሞላ) ጭልጥ ብሎ ለአብይ አህመድ ታማኝ ሎሌ መሆን በቂ ማረጋገጫወች ናቸው፡፡ ሲጀመር አንስቶ በድርጅቱ የቆየውና በሰፈራ ኦሮምያ ክልል ያደገው ለሸክም የማያቅማማው የደመቀ መኮንን ጉዳይ አይነሳ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አባይን ለመንከባከብ የጎሰኛነት አገዛዝ በዲሞክራሳዊ አገዛዝ መተካት አለበት አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ይህ ሁሉ ባለበት ሁኔታ  አሁን ላይ አውሬው አብይ አህመድ የሚያጣድፋቸው ሁለት አበይት ችግሮች በአማራው ህልውና ላይ ትንፋሽ አይሰጤ ሆነዋል፡፡ አንዱ ለም የአማራ መሬቶችን ለወያኔ አሳልፎ የመስጠት የፖለቲካ ቁመራ ሲሆን ሌላው መላው አማራን ስሩን ነቅሎ የሚጥል የሽወዳ ህዝብ ቆጠራ አዲሱ የኦሮሙማ ፕሮጀክት ናቸው፡፡

በዚህ ቁማር መነሻነት  የወልቃይትና ራያ ዙሪያ አብይ አህመድ ምንም አሰወሰነ አላስወሰነ የአማራህዝብ ትግል ሊቆም አይችልም፡፡ ወያኔም ወልቃይትንና ራያን በተዘዋዋሪ መንገድም ቢሆን የትግራይ አካል የሚያደርጋቸው ቢመስለውም ታላቋ ትግራይን የመመስረት እቅዱ ለጊዜው  ሊቀዘቅዝ ይችል ይሆናል እንጅ ጨርሶ ሊዳፈን አይችልም፡፡

ይህ ለኦሮሙማ አጣብቂኝ  ቢመስልም እውን እየሆነ ባለው  የኦሮሙማ ስሌትና እቅድ መሰረት በድርጊቱ  አማራን በመጨፈጨፍ የታጀበ ድልን ለመቀዳጀት ጫፍ ላይ ደርሷል፡፡  የህዝብ ቆጠራ ዉጤቱም ወያኔ ጀምሮት እንደነበረውፕሮጀክት ሁሉ አሁንም በቀጣይነት  የአማራውን ህዝብ ብዛት ቁጥር አስንሶ በተቃራኒው የኦሮሞን ህዝብ ቁጥር አስድጎ የሚከናወን እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው፡፤ ኦሮሙማ በዚህ የሽወዳ ህዝብ ቆጠራ ዉጤት ባለ ብዙ ዘርፍ ጥቅምን ያገኛል፡፡ዉጤቱን በድምጽ አስጣጥ፣ በበጅት ምደባና ’በጥቅለላ’ በሁሉም ዘርፍ ኦሮሙማ የባላይነቱን የሚያረጋጋጥበት መሳሪያው ያደርገዋል፡፡ ደቡቡን በታትኖና ሸንሽኖ ጨርሷል፡፡ ከወያኔ ጋር ያለውን ችግርም ወልቃይትንና ራያን ከተቻለ በፌደራል ስም ራሱ ኦሮሙማ ገዥ በመሆን ካልተቻለም ለወያኔ አስልፎ በመስጠት ከወያኔ ጋር ያለውን ችግር ይፈታል ማለት ነው፡፡ ይህ ነው የኦሮሙማ ስሌት፡፡

መቼም ቢሆን ኦሮሙማ አርቆ አያስብምና በቶሎ ይረካል፡፡በቶሎ ወደዘረፋም ይገባል፡፡ኬናንም ያውጃል፡፡ተስፋፍቶም  ይዘርፋል፡፤ ሲዘርፍም ሲረካም ጥጋቡንም አይችልም፡፡ ኦሮሙማ በብዙ ድርጊቶቹ ከከብትነት ያልተላቀቀ የመንጋወች ስብስብ መሆኑን ድርጊቶቹ ምስክሮች ናቸው፡፤

ሰው ጥሮ ግሮና በባንክ ቆጥቦ በብድር የሰራውን ቤትና አፓርትማ በመነግስት ተብየው በራሱ ሰራር መንጠቅ፡፡ በጠራራ ጸሀይ በይፋ የመንግስት ባንኮችን መዝረፍ፣ ሴት ተማሪወችን ከዩኒቨርሲቲ  በዘር ለይቶ ወስዶ ዱካቸውን ማጥፋትና ለልጆቹ ለቤተሰቦች በህይወት  አሉ ወይንም የሉም የሚለውን አድበስብሶ ማለፍ፣ ስውን ከገደሉ በኋላ  ዘቅዝቆ መስቀል፡፤ እርጉዝ ሴትን አርዶና ሆዷን ቀድዶ ሽሉን በማውጣት የሞተቸውን ሴት እጅዋን ስቦ ከሆዷ ቀድዶ ያወጣውን ሽል ለሟቿ ማስታቀፍ፣ ወዘተ ወዘተ ብዙ እዚህ ላይ ሊነገሩና ሊሰሙ የሚቀፍፉና ሰው መሆንን የሚያስጠሉ እንሰሳዊ ስራወችንና ድርጊቶችን ኦሮሙማ ፈጽሟል ፈቅዶም ተባብሮም አስፈጽሟል፡፡

በእውን ወያኔ ምንም ሰውን ያለስራውና ያለወንጀሉ ቢያስርም፣ ቢዘርፍም ቢገድልምና የከፋ ዘረኛ ቢሆንም ይህንን መሰል ነውርና ዘግናኝ ነገሮችን ህዝቡ እያየና እያወቀ በይፋ ፈጽሟልን??  ህዝቡ ይፍረድ፡፡ ኦሮሙማ  አሁን ላለበት ደረጃም የደረሰው የሆዳም አማራወችን ምርኩዝነት ይዞ እንጅ በራሱ ብቻውን ራሱን ችሎ  መቆም ስለማይችል ወይ ፈንድቶ ወይ ተንፍሶ እስካሁን ለይቶለት ነበር፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰማህ ወይ የነፍጠኛ ልጅ! - በላይነህ አባተ

በአመራር ደረጃም ቢሆን አውሬው አብይ አህመድ ከባንዳው መለስ ዜናዊ ጋር ሊወዳደር አይችልም፡፤ መለስ ተግባሩ  ለክፋትም ቢሆን ትንሽ ያመዛዝናል፡፡ ዘረኛ ስርአት የነበረው የወያኔ ስርአት  እስከነ አመራሩ በጅቦችና በከብቶች ከተከበበው የኦሮሙማ ስርአት ጋር ሲነጻጸር ትንሽም ቢሆን  አንጻራዊ የመሻል ልዩነት ነበረው፡፤ በአጭሩ ከእባቡ ወያኔ ምንም የማያስተነትነው ጅቡ ኦሮሙማ የባሰ ህዝቡንም አገሪቱንም እየጎዳ ያለ አገዛዝ ነው፡፡ ይህ እንዴት ሆነ ብለን ምስጢሩን ብንመረምር እውነቱን  የሚያዉቁት አንድም የአሩሲዋ እመቤታቸው ነች ፡፤ አለበለዚያም የመንጋወቹን  መሪወችን   የከተበው የ666 ማህበራቸው ነው፡፡ እውነቱን እግዚአብሄር ይወቅ፡፤ መፍትሄም በአፋጣኝ ይስጥ፡፡

ወደተነሳሁበት ርእስ መቋጫ ልመለስ፡፤ የዚህችን አጭር መጣጥፌን ርእስ “የሚመጣው እየሆነ ካለው ይብሳል” ያልኩበት ዋና ምክንያት የአገሪቱና የህዝቡ ተስፋ እየጨለመና እየባሰበት በመሄድ ላይ ስለሆነ ነው፡፤ አብይ አህመድ የሚባል ከችሎታ ችሎታ የሌለውና ለሰው መጎሳቆልና ሞት ቅንጣት ርህራሄ የሌለው እቡይ ሰው በመጥፎ የታሪክ አጋጣሚ   የአገር አመራርሀላፊነትን  በሽወዳ በመውሰዱና ተረኝነትንብሎም  ዘረፋንና ጭፍጨፋን በማስፋፋት ስለተጠመደ በእነዚህ ድርጊቶቹም ደስተኛ መሆኑን ሳያፍር ህዝቡን በመናቅ ስለሚደሰኩር ነው፡፡ አብይ ሙልጭ ያለ ውሸታም ከእውቀት የጸዳና ፍጹም አታላይ የሆነ እርጉም ሰው ነው፡፡ ሰውየው እንደዚህ አይነት ሰው ባይሆን ኖሮ ሰውን ከፋፍሎ በሆዱ እየገዛህዝቡን  ሲጋድልና ሲያጨፋጭፍ አይታይም ነበር፡፤ በታሪክ ወደርየለስ ትንሽ ሰው ነው፡፡

ይታያችሁ እስኪ፦  አማራንና ትግሬን በወልቃይትና ራያ ጉዳይ ዳግም ጦር እንዲማዘዙ፤ እርሱ ግን በስላም ኦሮሚያን እንዲያበለጽግ ይህን እኩይ አላማ ያለ እርሱና ያለተከታይ መንጋወቹ  ማን ያስባል??

እንደገናም ሌላውን አደጋደግመን  እንይ ፦ ደቡቡ ተሸንሽኖ፣ ተቆላልፎና ተክፋፍፈሎ ሲወዳድቅ ክፍልፋዮቹ ቀስ በቀስ በኦሮሚያ ጥገኝነት ስር እንዲጠቃለሉ ታስቦና ታቅዶ እየተሰራ ነው፡፡ እምቢተኛው አማራም ታርዶና ተጨፍጭፎ እከሚያልቅ ድረስ ይበልጥ ሞትና እልቂት እየተደገሰለት ሲሆን ቁጥሩም ሆን ተብሎ እንድቀንስ ለማድረግ ሰሞኑን አዲስ የተሾሙት  የስታትስቲኪስ ባልስልጣን ተረኛ የኦሮሙማ ሹሞች  ታሪካቸው ያደፈ መሆኑ ሳያንስ ገና እግራቸው ባልስልጣኑ ጋር እንደደረሰ በሀለፊነት በቦታው ለብዙ አመታት በሀለፊነት ይሰሩ የነበሩትን አማራወች ጠራርገው አባረዋቸዋል፡፡ ይህ የአብይ አህመድ ተዛዝ ነው፡፡ ይህ አማራን ድባቅ ለመታት የታቀደ የመጀመሪያ እርምጃ ነው፡፡ ለአማራው ህዝብ ቁጥር አናሳ ሪፖርት ይህ የኦሮሙማ ቁማር ስኬታማነት የመጀመሪያው እርምጃ ነው፡፡

አሁንስ ህዝቤ ሆይ መጩው ጊዜ ይበልጥ አልቸለመብህምን?? ዝም ብለህ ወደ ጨለማና ወደ ጉድጓድ ትነዳለህልን?? ስለዚህ ይህንን ጨለማና የከፋ መጪ ጊዜን አስበህ ለማይቀረው የነጻነት ትግል ተደራጅ”ተዘጋጅ”!!

በሰንሰለት የታሰረ ባሪያ ሰንሰለቱን ቢበጥስ ከተሳካለት ነጻነቱን ይጎናጸፋል፡፤ ካልተሳካለትም ያንኑ ሰንሰለት አያጣውም እንደሚባለው ብሂል ሁሉ  አንተም አሁን በቁም ከምትሞት ታገልና ጠላትህን አስወግድ፡፤ በዚህ ድርጊትህም ነጻነትህን ልትጎናጸፍ ትችላለህ፡፤ ካልተሳካልህም እስከሚሳካልህ ድረስ ያሁኑን አይነት የቁም ሞት ኑሮህን መቼም ቢሆን አታጣውምና ጨርሶ ሳይጨልምብህ ዛሬዉኑ ተነሳ!!!፡፡

 

 

5 Comments

 1. እውነቱ ፦ በትትክልም እውነት ብለሀል፡፤
  እየመጣ ያለው በእውነትም እስካሁን ካየነው ከኖርነውናን ካሳለፍንረው የመከራ ጊዜ በእጅጉ ይብሳል፡፤ አብይ አህመድ ለህዝብ እልቂትና ለአገር መዋረድ ደንታ የሊለው ሰው ነው፡፤ በዙሪያው ያሉት ሆዳሞች እስካጀቡት ድረስና ኣገሪቱ አንድ ሆና እንዳትጠነክር የሚፈልጉ የውጭ ሀይሎች የሚያዙትን እስከፈጸመ ድረስ ለህዝብም ለአገርም ግድ የለውም፡፤ ምክንያቱም ሰውየው ጭቃ አንጎል ስለሆነ ነው፡፡ ያሳፍራል!!

 2. ይገርማል እፍርት የሚባል ነገር ቀረ 80% የመከላከያ ስራዊትን ያረደ ኢትዮጵያ በብድር የገዛችውን የጦር መሳሪያ ተጠቅሞ ኢትዮጵያን የወጋ አካል የሚፈልገውን አደራዳሪ መርጦ የአብይን መንግስት አፍንጫውን ይዞ በሚፈልገው መንገድ ስምምነቱን የቋጨ ወንጀለኛ ድርጅት መሪዎች ጋር ብርሃኑ ጁላና ሬድዋን ሁሴን ፊት ለፊት ቀርበው ተሸማቅቀው ፎቶ ሲለቁልን ትንሽ እፍረት የለም? ጤናም ሰው ቢሆን ደብቁኝ ይላል ወታደራዊ ስሜት ያለው ዜጋ ቢኖር አጠገባቸው ቁሞ መታየት አይፈልግም እንዚህ ግ ን በኩራት የሚቀመጡበትን ወምበር ያመቻቻሉ፡፡ ምን አይነት ሹመኞች ላይ ወደቅን ምንስ አጠፋን አምላክ በዚህ ልክ የቀጣን ከብልጽግና ተሿሚዎች አንድ ለጥሩ እድር ሰብሳቢ የሚበቃ ሰው ይኖራል? ነገሩስ ሆነ ታረቁ ተቃቀፉ የኢትዮጵያ መንግስት ብዙ ዶላሮችን ልኮ ተገባበዙ የሚቀጥለው ምንድነው? ህወአት ኤርትራን እወጋለሁ ብሏል ትግሬ ለጊዜው ኢትዮጵያ ክልል ነኝ ብሏል ከኤርትራ ጋር ጦርነትና ትንኮሳ መጀመሩ የማይቀር ነው የብርሃኑ ጁላ ወታደር ትላንት ነብሱን ካዳነው ከኤርትራ ጦር ሁኖ ኤርትራን ሊወጋ ነው ማለት ነው? የጉድ አገር ፡፡ አማራ አርፈህ ቁጭ በል ቢፈልግ ትግሬንና ቄሮን ይላክ

 3. ሶስት ጉዳዮች፦
  1ኛ) ሸኔ በሉት ኦነግ አብይ አህመድ የማያወቅውና የማይፈቅደው አንዲት ቅንጣት ነገር አትፈጸምም፡፡ ሁሉም የሆነውና እየሆነ ያለው በአውሬው አብይ አህመድ ስሌትና ስለት ነው፡፡
  2ኛ) ከጸረ ኮሎኒያሊስት ትግሉ ጀምሮ አማራን አምርረው የሚጠሉት ምእራባዊያን አንድ ጊዜ ጠበቅ አንድ ጊዜ ላላ እያደረጉ አውሬውን አብይ አህመድን በremote control ይቆጣጠሩታል፡፡ ቃልም ተገብቶለታል፡፡ በዚህ ድርጊቶቻቸውም ኢትዮጵያ በታሪኳ እንደምትታውቀው ጠንካራ አገር እንዳትሆን ይሻሉ፡፤ አማራውም እንደገና አንገቱን ቀና እንዳያደርግም አጥብቀው ይሻሉ፡፤ አማራውን በታሪክ ያዉቁታላ!፡ ለዚህ እቅዳቸው ስኬታማነት የሚስማማቸው ሰው ደግሞ አብይ አህመድ አሊ ብቻ ነው፡፡
  3ኛ) ታሪክ እንደሚመሰክረው መሪወች ድክታተርም፣ ለተቀናቃኞቻቸው ምህረት የለሽም፣ ለስልጣናቸው ቀናኢም፣ ሀብትና ገንዘብ ዘራፊም ወዘተ ወዘተ ይሆናሉ፡፡ነገር ግን እነዚህን ሁሉ ሆነው በተጨማሪነት አብይ አህመድን ያህል አገራቸውን የሚያዋርዱና በህዝቦቻቸው ስቃይ የሚደሰቱ ፈጽሞ አልነበሩም፡፡ አብይ ግን ሁሉንም ነው፡፡
  ምሳሌ፦ ስምምነቱ መረኢት ላይ ሳይወርና አንድም ነገር መስመር ሳይዝ ከላይ እስከታች በኦሮሙማወች የሚዘረፈው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቢሮውን ከአማራ ወልቃይት አውጥቶ በትግራይ በሽሬ ከተማ እንዲሆን መወሰኑ ምንን ያመላክታል? ይህንን አብይ አያውቀውምን? እርምጃው ሰራ አልሰራ ተሳካ አልተሳካ ከዚህ በኋላ ገንዘቡን በማስቀመጥም ሆነ በሌላ አግባብ በዚህ ባንክ የሚገለገል የአማራ ተወላጅ ይኖራልን??

 4. አይ ፊልድ ማርሻል መመሪያ ከነሱ ሆነ የምትወስደው? ታደሰ ወረደ ነው ፊልድ ማርሻል የመሰለው፡፡ ጌታቸው ረዳ ባጫ ደበሌ እኛ ስናውቀው እስክሳ ወራጅ ነው ካለ ረጅም ጊዜ አልነበረም ዛሬ ባጫ ደበሌ አልጋ አንጥፎ እግር. እራት አብልቶ ጌታቸው ረዳን ያስተኛል እነ ብርሃኑም እንቅልፍ ሲወስዳቸው ወደሚሄዱበት ይሄዳሉ እንዲህ ነው የኢትዮጵያ ነገር፡፡ ዛሬ ዛሬማ ህወአትን አትናገሩብን ማለት አምጥተዋል ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያ በአብይና ብርሃኑ ጁላ የሚመራ የመከላከያ ሃይል ይኖራታልን? የመከላከያ ሚኒስቴሩ የህወአቱ አብረሃ በላይ ነው ለምን እሱን ወደ ናይሮቢ አልላኩትም? ምስጢሩን ታሪክና ጊዜ ያወጣዋል፡፡ የመከላከያ ሃይሉስ በነዚህ ሰዎች ስር ካሁን በኋዋላ ይዋጋል? ትእዛዝ ይቀበላልን? እነዚህ ሃይሎች ባለቁት የኢትዮጵያ ልጆች መች ነው ተጠያቂ የሚሆኑት? ኤርትራስ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ባይ ባይ መባሏ ደስ ይላታልን? የምናየው ይሆናል

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share