የሌባ ዓይነ ደረቅ፣ መልሶ ልብ ያደርቅ
የአማራ ሕዝብ አጉል ጨዋነትና ጦሱ
ውድ አንባብያን ሆይ፡፡ ይህ ጦማር ከተለመደው አማራዊ ጨዋነት ወጣ ያለ ስለሆነ አስቀድሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ የአማራ ሕፃናት እንደ በግ እየታረዱና ደማቸውን ውሻ እየላሰው፣ አራጃቸውና አሳራጃቸው ጭራቅ አሕመድ ደግሞ ለቡድን ቀብራቸው (mass grave) ጥላ እንዲሆን ዛፍ እተክልላቸዋለሁ በማለት በአማራ ሕዝብ ቁስል ላይ እንጨት በመስደድ እያሾፈ፣ የኦሮሞ ወይም የትግሬ ጽንፈኛ፣ እንዲሁም የነሱን ፀራማራ አጀንዳ የሚያራምድ ሆዳደር ሎሌ ይቀየማል በማለት አጉል ጨዋ ለመሆን መሞከርና መባል ያለበትን ከማለት መቆጠብ፣ አሳፋሪ ፈሪነት ብቻ ሳይሆን ወንጀልም ጭምር ነው፡፡ በአማራ ሕጻናት ደም ከመታጠብ አልፈው የሚዋኙት እነዚህ ጽንፈኞችና ሎሌወቻቸው በማናለብኝ ስሜት እየተንቀባረሩ ባደባባይ ሲንጎባለሉ እጁን አጣጥፎ የሚመለከት አማራ ደግሞ፣ ሥጋቸው ከታረደው ሕጻነት በላይ መንፈሱ የታረደ፣ ወኔው የተሰለበ፣ ከሞቱት በላይ ከቆሙት በታች የሆነ ሙትቻ ብቻ ነው፡፡
ከአማራ ሕዝብ ዐብይ ድክመቶች ውስጥ አንዱና ዋናው አጉል ጨዋነት ነው፡፡ ጥድ አለቦታው ብሳና ይሆናል እንዲሉ፣ ጨዋነት ትርጉም የሚኖረው ለጨዋ ብቻ ነው፡፡ በኦሮሞና በትግሬ ጽንፈኞች ቋንቋ ውስጥ ደግሞ ጨዋነት የሚባለው ቃል ከናካቴው ስለሌለና ስለማያውቁት ጨዋነትን የሚቆጥሩት ከፈሪነት ነው፡፡ የአማራ ሕዝብ ደግሞ እነዚህን ጽንፈኞች በማያውቁት ቋንቋ በጨዋነት ሊያናግራቸው ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ቢደክምም ድካሙ መና ሁኗል፣ ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ ብሎ ቀረ እንዲሉ፡፡ ለድካሙ መና መሆን ደግሞ ሙሉ በሙሉ ተጠያቂው ሌላ ማንም ሳይሆን ራሱ የአማራ ሕዝብ ነው፡፡ ባላጋራህን በማያውቀው ቋንቋ አናግረኸው ካልገባው፣ ችግሩ የባላጋራህ ሳይሆን ያንተው የራስህ ነው፡፡
ስለዚህም ጨዋነትን ከፈሪነት ከሚቆጥሩት የኦሮሞና የትግሬ ጽንፈኞች፣ እንዲሁም ለነዚህ ጽንፈኞች ሎሌ በመሆን ኢጨዋ ባሕርያቸውን ከወረሱት ሆዳደሮች ጋር ተነጋግሮ ለመግባባት ከጨዋነት ዝቅ ማለት የውዴታ ግዴታ ሳይሆን የአልውዴታ ግዴታ ነው፡፡ እየየም ሲደላ ነውና፣ የአማራ ሕዝብ ሕልውና ጥያቄ ውስጥ በወደቀበት ወቅት ለአማራዊ ጨዋነት መጨነቅ ቅንጦት ነው፡፡ የአማራ ሕዝብ ሕልውናውን ለማስጠበቅ ለሚያደርገው መራራ ትግል የሚያስፈልጉት መሪር ቃሎች የሚያስቀይሙት ካለ ገደል ይግባ፣ ወይም ደግሞ አንድ ዩቲዩበኛ (youtuber) እንዳለው ባናቱ ይዘቅዘቅ፡፡
ጠላትን ሲለማመጡት፣ በጠላትነቱ ላይ ንቀት ይጨምርበትና ይበልጥ ይጠላል፡፡ ጠላትን ወግድ ሲሉት ግን ጥላቻው በከበሬታ ይለዝባል፡፡ ጠላትን የመለማመጥ ትርፉ መከራን ማባስ፣ ፍዳን ማብዛት ብቻ ነው፡፡ አብነቶቻችን (ምሳሌወቻችን) የሆኑት አብናቶቻችን (ማለትም አባቶቻችንና እናቶቻችን) ጠላት ወዳጅ ላይሆን አልለማመጥም የሚሉትም ይህን ትልቅ እውነታ ለማስገንዘብ ነው፡፡
ታላቁ የአማራ ሕዝብ ሆይ፡፡ የኦሮሞና የትግሬ ጽንፈኞችን በመለማመጥ ያተረፍከው፣ ከከብት ባነሰ ክብር አንገትህን እየተጠመዘዝክ መታረድን፣ አብናቶችህ ደማቸውን አፍስሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ባቆሟት አገር ላይ ከሁለተኛ ዜጋ መቆጠርን፣ የአሮሞ ጽንፈኞች ሣር እየነጩ ኩሬ ሲረጩ፣ አንተ ራስህ ወደ ቆረቆርካት አዲሳባ ዝር እንዳትል መከልከልን፣ የደቡብ አፍሪቃ ጥቁሮች በነጭ ከተዋረዱት በላይ በኦሮሞ ጽንፈኞች መዋረድን ነው፡፡ እጅጉን የሚያሳምመው ደግሞ በባሕልም፣ በትውፊትም፣ በጀግንነትም ከጥፍርህ የማይደርስ መንጋ በዚህ ደረጃ ሊያዋርድህ መቻሉ ነው፡፡ መንጋው በዚህ ደረጃ ሊያዋርድህ የቻለው ደግሞ ገና ፊጥ፣ ፊጥ ማለት ሲጀምር ይች ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም ብለህ አናቱን በርቅሰህ ባጭሩ ከማስቀረት ይልቅ ባጉል ጨዋነት አጉል እየተለማመጥክ ይበልጥና ይበልጥ እንዲንቅህ ስላደረከው ነው፡፡
ስለ አማራ ሕዝብ አጉል ጨዋነትና ጦሱ ይሄን ያህል ካልኩ ዘንዳ፣ ሕብረ ብሔራዊ ነኝ እያለ አማራ የሚባል ብሔር የለም የሚለው ያንዳርጋቸው ጽጌና፣ ዜግነትን አራምዳለሁ እያለ አማራ መጤ ነው የሚለው የብርሃኑ ነጋ ባልደረባ ወደሆነው፣ የሰሜን ፖለቲካን አምርሮ ስለሚጠላ የኦነግን ፀራማራ አጀንዳ ወደሚያራምደው ወደ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ልመለስና ለጻፈው ፀራማራ ጦማር፣ ለጨዋነት ሳልጨነቅ \በሚገባው\ እና /በሚገባው/ ቋንቋ መልስ ልስጠው፡፡
የኤፍሬም ማዴቦ መርዘኛ ብአዴናዊ መልዕክት
አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ሆይ፣ “የመስፍን አረጋ ድሪቶ” በሚል ርዕስ በጦመርከው ጦማር ላይ ያላልኩትን ብለሃል በሚል አጥብቀህ ወርፈኸኛል፡፡ ስለዚህም “የኤፍሬም ማዴቦ ሸፍጥ፤ ያይጥ ምስክሯ ድንቢጥ” በሚል ርዕስ በጦመርኩት ጦማር ላይ በግልጽ የገለጽኩትና ያብራራሁት አንተ ራስህ ያልከውን ብቻ ሳይሆን ለማለት የፈለከውን እንደሆነ ለጸሐፊው ላንተው ለራሰህ በድጋሚ ላብራራለህ የግድ ነው፡፡ እርግጥ ነው አብዛኛው አንባቢ የተጻፈለትን እንደወረደ የሚያነብ፣ በተለይም ደግሞ በመስመር መኻል ማንበብን (reading between the lines) እና ነጥቦችን ማገናኘትን (connecting the dots) የማይችል መናኛ አንባቢ ነው በሚል፣ ካጉል ንቀት በመነጨ እሳቤህ መሠረት፣ ለማስተላለፍ የፈለከውን ብአዴናዊ ፀራማራ መልዕክት፣ ለአማራ ሕዝብ የምታስብ በሚያስመስልህ ማማለያወች ልታድበሰብሰው ሞክረሃል፡፡ ሸፍጠኛ ያልኩህም በዚሁ ምክኒያት ነው፡፡ ሸፍጠኛ ማለት አሉተኛ፣ ዐባይ፣ ቀጣፊ ማለት ነው፡፡
ይሄው እንግዲህ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ፡፡ ሲንሲን (ስነአመክንዮ፣ logic) ሳታውቅ አትቀርም ብየ በማሰብ “ኦ-ብልፅግና … አ-ብልፅግና” በሚል ርዕስ በጦመርከው ጦማር ላይ ለማስተላለፍ የፈለከው ዋና መልዕክት ምን እንደሆነ ላንተው ለራስህ ባጭሩ እንድገልጽለህ በሲንሲን መንገድ አብረን እንጓዝ፡፡ በተራ ቁጥሮች የተዘረዘሩትን ነጥቦች እያያዝክ ተከተለኝ፡፡
- “በዛሬዋ ኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ ግልጽ የሆነ ልዩነት ያላቸው ሁለት ትልልቅ ቡድኖችአሉ፡፡ እነዚህ ሁለት ቡድኖች፣ ባቋማቸውም በፖለቲካ አሰላለፋቸውም አማራ ብልፅግና እና ኦሮሞ ብልፅግና ውስጥ ካሉ ኃይሎች ጋር በቅርብ የተሳሰሩ ናቸው … ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ የምናየው ምስቅልቅል እነዚህ ሁለት ኃይሎች የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለመቆጠጠርና የወደፊቷን ኢትዮጵያ ባምሳያቸው ለመቅረጽ የሚያደርጉት ትግል ውጤት ነው” ማለትህን መሸፈጥ አትችልም፣ የማይስተባበሉ ዋቢወች (references) አሉና፡፡
- በተራ ቁጥር (1) የተገለጸውን የጻፍከው የሌለውን ያለ አስመስለህየአማራን ሕዝብ ላም አለኝ በሰማይ ለማስባል እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ እዚህም ላይ ሸፍጠኻል፣ የሸፍጠኛ ሌላው ትርጉሙ የሌለውን አለ፣ ያልተደረገውን ተደረገ፣ ያልታየውን ታየ የሚል ማለት ነውና፡፡ ሐቁ ግን የአማራ ብልፅግና የሚባል ቡድን ከናካቴው የሌለ መሆኑ ነው፡፡ ያለው ብልፅግና አንድና አንድ ብቻ ሲሆን፣ እሱም የኦሮሞ ብልፅግና ነው፡፡ የአማራ ብልፅግና የሚባለው ስብስብ የኦሮሞ ብልፅግና፣ በተለይም ደግሞ የበላዔ አማራው የጭራቅ አሕመድ ጉዳይ አስፈጻሚ እንጅ ራሱን ችሎ የቆመ ቡድን አይደለም፡፡ የአማራ ብልጽግና መሪ ነው የሚባለው ደመቀ መኮንን በትምህርቱ ብዙም ያልገፋ ከመሆኑም በላይ ራሱን በራሱ የሚያስተምር ዓይነት ሰው አይደለም፡፡ ወያኔ የትምህርት ሚኒስቴር አድርጎት የነበረውም ትምህርትና እሱ በጭራሽ እንደማይተዋወቁ ስለሚያውቅ ነበር፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ የሚያውቃትን በደንብ መግለጽ የማይችል አንደበተ ግድር (challenged) ገመዳፍ ከመሆኑም በላይ በራስ መተማመን የሚባል ነገር ምናምኒትም እንደሌለው በግልጽ ያስታውቅበታል፡፡ ይባስ ብሎ ደግሞ ኃላፊነት መውሰድን እንደ ጦር የሚፈራ የጃግሬነት ሰብዕና (follower mentality) በጽኑ የተጠናወተው፣ ለጀሌነት እንጅ ለመሪነት ያልተፈጠረ ጃግሬ ግለሰብ ነው፡፡ ስለዚህም በዚህ ጃግሬ ግለሰብ የሚመራ ስብስብ የኦሮሞ ብልፅግና አሽከር እንጅ ተገዳዳሪ መሆን ቀርቶ አጋር ሊሆን አይችልም፡፡
- ለማንኛውም በተራ ቁጥር (1) የጻፍከው ዓይን ያወጣ ሐሰትቢሆንም እውነት ነው እንበልና፣ ከአማራ ብልፅግና እና ኦሮሞ ብልፅግና ጋር በቅርብ የተሳሰሩ ሁለት ትላልቅ ኃይሎች አሉ፣ ኢትዮጵያ የተመሰቃቀለችወም እነዚህ ሁለት ኃይሎች በሚያደርጉት ትግል ሳቢያ ነው እንበል፡፡
- በኢትዮጵያ መመሰቃቀል ከማንም በላይ የተጎዳው ደግሞ የአማራ ሕዝብ ነው፡፡ ስለዚህም ተራ ቁጥር (3) በቀጥታ የሚያመራው ወደ አንድና አንድ መደምደሚያ ብቻነው፡፡ እሱም የአማራ ሕዝብ ኢትዮጵያን ከምስቅልቅል በማውጣት ራሱን የሚታደገው ከአማራ ብልጽግና ጋር ወግኖ የኦሮሞን ብልጽግና ከታገለ ብቻ ነው የሚለው ነው፡፡ በሌላ አነጋገር፣ ባንተ ባቶ ኤፍሬም ማዴቦ ምክር መሠረት የአማራ ሕዝብ ለራሱ ሕልውና ሲል ሳይወድ በግዱም ቢሆን የአማራ ብልጽግናን (ማለትም ብአዴንን) መደገፍ አለበት ማለት ነው፡፡ በጦማርህ ማስተላለፍ የፈለካት ጭብጥ መልዕክት ይህችና ይህች ብቻ ናት፡፡ የመልዕክቷ ዓላማ ደግሞ የበላዔ አማራው የጭራቅ አሕመድ ጉዳይ አስፈጻሚ በመሆን የአማራን ሕዝብ ለሚያስጨፈጭፈው፣ የአማራ ለምድ በለበሰው በኦነጋዊው ተኩላ በደመቀ መኮንን ለሚመራው ለብአዴን ጥብቅና መቆም ነው፡፡ ያይጥ ምስክሯ ድንቢጥ ያልኩትም በዚሁ ምክኒያት ነው፣ ብአዴን ዐይጥ፣ አንተና መሰሎችህ ኢዜማውያን ደግሞ ድንቢጥ፡፡
- በጦማርህ ላይ ያተትከው የቀረው ሐተታ ሁሉ ዋና መልዕክትህን የመቀባቢያ እንቶ ፈንቶነው፡፡ ለምሳሌ ያህል በጦማርህ ላይ “የአማራ ክልል እንደ ክልልም እንደ ፖለቲካ ማሕበረሰብም ይህ ነው የሚባል መሪም አመራርም የሌለው፣ ባክቲቪስቶች፣ በባለሐብቶች፣ በዩቲዮብ አርበኞችና በተለያዩ የጎበዝ አለቆች የሚመራና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ መጫወት የሚገባውን ትልቅ ሚና የዘነጋ ክልል ነው” ብለሃል፡፡
- የታላቁ የአማራ ሕዝብ መሪና አመራር ማጣት በተራ ቁጥር 5 የገለጽከውን ያህል የሚከነክንህ ቢሆን ኖሮ፣ በኦሮሞ ጽንፈኛ ሚዲያወችላይ እየቀረብክ፣ ለታዳጊ የአማራ መሪወች መድረክ የሚሰጡትን፣ ድምጽ ለሌላቸው አማሮች ድምጽ የሆኑትን አማራ ተቆርቋሪ ሚዲያወች ባላወገዝክ፣ ባልወረፍክና ባልዘለፍክ ነበር፡፡ ባልደረባህ ብርሃኑ ነጋ ደግሞ የአማራ ሕዝብ የተማረ መሪ እንዳይኖረው፣ በትምህርት ሚኒስቴርነቱ እየፈጸመ ያለውን ከፍተኛ ደባ ባልፈጸመ ነበር፡፡ ሌላው ባልደረባህ አንዳርጋቸው ጽጌ ደግሞ የአማራ ሕዝብ መሪ እንዳይኖረው፣ አማራ የሚባል የለም እያለ፣ በእውቀት ያልተገራ፣ መረን የተለቀቀ፣ ስድ አፉን እየከፈተ፣ እንደ ዐመድ ወዳዷ እንስሳ ባላናፋ ነበር፡፡ አንተ፣ ብርሃኑ ነጋ፣ አንዳርጋቸው ጽጌና መሰሎቻችሁ ይህን ሁሉ ነውር በአማራ ሕዝብ ላይ የምትፈጽሙት ደግሞ መሪ እንዳይኖረው ያደረጋችሁት የአማራ ሕዝብ ለነውራችሁ አጸፋውን በሚመልስላችሁ ደረጃ ላይ አለመሆኑን ስለምታውቁ ብቻ ነው፡፡ አንተና ባልደረቦችህ በታላቁ ባማራ ሕዝብ ላይ የታሳለቃችሁትን ያህል ሕዳጣን በሚባሉት አናሳ ብሔረሰቦች ላይ እንኳን አልተሳለቃችሁም፡፡ እሱም ቢሆን የጊዜ ጉዳይ ነው፣ አይነጋ መስሏት እቆጥ አራች እንዲሉ፡፡
- የአማራ ሕዝብ አማራዊ መሪ የሌለው መሆኑ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ሐቅ ነው፡፡ ዋና መልዕክትህ ይህን መናገር የማያስፈልገውን ሐቅ መናገር ከሆነ፣ በተራ ቁጥር (1) ላይ የተገለጸውን፣ የአማራ ሕዝብ ካማራ ብልጽግና (ብአዴን) ጋር ይሰለፍ የሚል አንደምታ ያለውንመልዕክትህን መጻፍ ባላስፈለገህ ነበር፡፡ ስለዚህም፣ ይህን ገሐድ ሐቅ የጻፍከው፣ በተራ ቁጥር (1) የተገለጸውን መርዘኛውን ብአዴናዊ መልዕክትህን ለአማራ ሕዝብ የምታስብ በሚያስመስልህ ማር ለመለወስ ስትል ብቻ ነው፡፡
- የአማራ ሕዝብ ይህ ነው የሚባል ሁነኛ አማራዊ መሪየሌለው መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ አጠያያቀው ግን ለምን የለውም የሚለው ነው፡፡ መልሱ ደግሞ ግልጽ ነው፡፡
- የአማራ ሕዝብ ይህ ነው የሚባል ሁነኛ አማራዊ መሪ የሌለው፣ አንተን አቶ ኤፍሬም ማዴቦን፣ ብርሃኑ ነጋን፣ አንዳርጋቸው ጽጌንና መሰሎቻችሁን መሪወቸ ናችሁ ብሎ በማመኑና በሙሉ ልቡ በመከተሉ ብቻና ብቻ ነው፡፡ እናንተ ግን የአማራን ሕዝብ እስኪበቃችሁ ጋጣችሁትና፣ የበለጠ ለምለም መስክ(greener pasture) የታያችሁ ሲመስላችሁ፣ አውላላ ሜዳ ላይ ጥላችሁት ዘወር አላችሁ፡፡ ለኦነጋዊው አውሬ ለጭራቅ አሕመድ ሎሌ በመሆን አማራን ይመሩብናል ብላችሁ በምትፈሯቸው ወጣት ፋኖወች ላይ ዘመቻ ከፈታችሁ፣ አስከፈታችሁ፡፡ ላማራ ተቆርቋሪ የሆኑትን የተለያዩ ሚዲያወች ካየር ላይ ለማውረድ መፈንቀል የምትችሉትን ዲንጋ ሁሉ ፈነቀላችሁ፣ ባብዛኛውም ተሳካላችሁ፡፡ የአማራ ሕዝብ በወያኔና በኦነግ የሚደርስበትን ሰቆቃ የሚዘግቡትን እንደ ጎበዜ ሲሳይ ያሉትን ዘጋቢወች ከሥራ ማባረራችሁ ሳያንሳችሁ፣ አሳስራችሁ አሰቃያችሁ፡፡ የአማራ ሕዝብ በጭራቅ አሕመድ መንጋወች እየታረደ እንደ ቅጠል ሲረግፍ ድምጻቸሁን አጥፍታችሁ፣ መታረዱን ለማስቆም መነሳሳት ሲጀምር ደግሞ ጅማሮውን ለማጨናገፍ መሯሯጥ ጀመራችሁ፡፡
- አቶ ኤፍሬም ማዴቦ፣ እስኪ አጭር ጥያቄወች ልጠይቅህ፡፡ መሪወቹ ሙሉ በሙሉ አልአማሮችቢሆኑም፣ የሚደገፈው ግን ከሞላ ጎደል በአማራ ብቻ ስለነበር ወያኔወችና ኦነጎች የአማራ ድርጅት ይሉት በነበረው በግንቦት ሰባት ውስጥ አንተና ባልደረቦችህ ያደረጋችሁትና ድርጅቱን ያስደረጋችሁትን እያወክ፣ አማራ መሪም፣ አመራርም የለውም ስትል ትንሽ አታፍርም? ዓይንህ በጨው ያጠብከው እስከዚህ ድረስ ነው? አብዛኞቹ ሠራተኞቹ አልአማሮች ቢሆኑም፣ የሚደገፈው ግን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በአማራ ብቻ በመሆኑ፣ ወያኔወችና ኦነጎች የአማራ ሚዲያ ይሉት በነበረው በኢሳት (ESAT) ውስጥ አንተና ባልደረቦችህ ያደረጋችሁትንና ኢሳትን ያስደረጋችሁትን እያወክ፣ የአማራ ትግል የሚመራው በዩቲዩብ አርበኞች ነው ስትል ሸፍጠኛ ብትባል አያንስብህም? አሁንሳ ገባህ፣ የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ ለምን እንዳልኩህ?
- የአማራ ሕዝብ ለዚህ ሁሉ ውርደት የተዳረገው፣ አማራዊነት የሌላቸውን፣ አልፎ ተርፎም አማራዊነትን አምረረው የሚጠሉትንእንደ ብርሃኑ ነጋና እንደ አንዳርጋቸው ጽጌ የመሳሰሉ ፀራማራ ተኩላወችን መሪወቹ በማድረጉ ነው፡፡ የአማራ ሕዝብ መሐንዲስ ቅጣው እጅጉን በመሰሉ አማራዊ መሪወች ቢመራ ኖሮ፣ ወያኔና ኦነግ ገና ድሮ ሙተው ተቀበረው ባሁኑ ጊዜ ከናካቴው ተረስተው ነበር፡፡ ቢሆንም ያለፈው አልፏል:: ለመጭው እንጅ ላለፈው ክረምት ቤት አይሠራም፡፡ ካሁን በኋላ የአማራ ሕዝብ መመራት ያለበት፣ አማራዊነቱን ያለ ምንም ይሉኝታ በግልጽና በተግባር ባስመሰከረ፣ ቆራጥና ቆፍጣና አማራዊ መሪ ብቻ ነው፡፡ መሪው ደግሞ የተማረ ቢሆንና፣ የተማረውም በቃላት ከመጫወትና ፀጉር ከመሰንጠቅ ያለፈ ምንም ጥረት የማይጠይቁትን እንቶ ፈንቶ ትምህርቶች ሳይሆን፣ ከፍተኛ ክሂሎትንና ትጋትን የሚጠይቁትን ሕክምናን ፣ ምንድስናን (engineering) እና ሰገልን (science) ቢሆን ይመረጣል፡፡ ቻይናን ምዕራባውያን ከሚያዋርዷት የተናቀች አገር ወደሚያጎበድዱላት የተከበረች አገር ባጭር ጊዜ ውስጥ የለወጧት፣ ወሬ ማውራትን ሳይሆን ንድፍ መንደፍንና የነደፉትን መተግበርን የተማሩት ማንዲስ መሪወቿ ናቸው፡፡ የአማራ ሕዝብም በንደዚህ ዓይነት አማራዊ መሪወች ከተመራ፣ ወያኔና ኦነግ ያለበሱትን የወርደት ማቅ ባጭር ጊዜ ውስጥ አውልቆ እንደሚጥልና፣ ሁለተኛ ሊያለብሱት መሞከር ቀርቶ እንዳያስቡ አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣቸው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ደም የሚጠራው በደም ነው፡፡
- በመጨረሻም፣ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ፣ አውቀህ ስለተኛህ ቢቀሰቅሱህ አትሰማም፡፡ የኔ ጽኑ ፍላጎት ደግሞ የአማራ ሕዝብ ሙሉ ትኩረቱን በዋና የሕልውና ጠላቱ በጭራቅ አሕመድ ላይ አውሎ፣ ጭራቁን ጨርቅ አድርጎ፣ ሕልውናውን ለዘለቄታው እንዲያስከብር የሰናፍጭ ቅንጣትየምታክል ብትሆንም የምችለውን ያህል አስተዋጽኦ ማድረግ እንጅ፣ አውቆ ከተኛ ዳተኛ ጋር አተካራ ገጥሜ እየተነታረኩ ጊዜየንና ጉልበቴን ማጥፋት አይደለም፡፡ ስለዚህም፣ ካሁን በኋላ የጻፍከውን ብትጽፍም መልስ አልሰጥህም፡፡ ይህን ሁሉ የጻፍኩትም አንተንና ባልደረቦችህን ከቁም ነገር ቆጥሬ ሳይሆን፣ ሸፍጠኝነታችሁን ያላወቀ አማራ ያለ ባይመስለኝም ምናልባት ካለ ብየ ነው፡፡
መስፍን አረጋ