በሬ ካራጁ …እንዳይሆን መጠንቀቅ ደግ ነው – ሲና ዘ ሙሴ

የጠላቶቻችንን ሤራ ለማክሸፍ ነገሮችን በጥልቀት ፈትሾ መረዳት እጅግ አሥፈላጊ  የሆነበት ጋዜ ላይ ደርሰናል ።

“ ኢትዮጵያ በጦርነት ድል አትደረግም ። በሹመት ፣ በጥቅምና በመሣሠሉት እንጂ !  እናም ፣ ከፍተኛ   የመንግሥቷን ባለሥልጣናት በመደለል ፤ ግሪን ካርድ በመሥጠት ፤ ምሥጢራዊ አካውንት በአውሮፕና በአሜሪካ እንዲከፍቱ በማገዝ ፣ አገራቸውን እንዲሸጡ ልታደርጓቸው ካልቻላችሁ የኢትዮጵያን ህዝብ ተዋግታችሁ ማሸነፍ ከቶም አትችሉም    ።  ” በማለት  የኢጣሊያ የፋሺስቱ  ሞሶሎኒ ደቀመዝሙሮች ከአድዋ ሽፈንታቸው በኋላ ለመላው አውሮፖ ምክረ መለገሳቸውን ዞር ብለን ማሥታወሥ ይገባናል  ። አንዳንድ የዘመኑ ቅኝ ገዢ አገራት ምሁራንም ፣  የአድዋን ድል ተከትሎ በመጣው የኢትዮጵያውያኑ የልብ ኩራት የተነሣ ተበሣጭተው በየአጋጣሚው ይኽንኑ ሃሳብ በወቅቱ ለነበሩት ቅኝ ገዢዎች ማቅረባቸውንም አነሰዘንጋ  ። የእንግሊዝ ፣ የጀርመን ፣ የፈረንሣይ፣ የአሜሪካ ቅኝ ገዢ የልጅ ፣ልጆችም ዛሬም ይኽንን  መሠሪ ሃሳብ ወደ ተግባር ለመቀየር ፤ኢትዮጵያን ከዓለም ካርታ ላይ ለማጥፋት  በህቡ እና በይፋ  በብርቱ እየሰሩ ነው ። የላታን  ፊደልም አንዱ መሣሪያቸው ሆኖ እያገለገላቸው ነው ። በጀርመን ቅኝ ገዢዎች የተቀነባበረ የሤራ የላቲን ፊደል ፖለቲካ እጅግ አደገኛ እንደነበር ከ27 ዓመት የተገነዘቡት ጥቂት ጋዜጠኞችና በሣል ምሁራን ነበሩ  ። በበኩሌ በግእዙ ፊደል ወይም በራሳችን አማርኛ ፊደል መጠቀም ችግር አልነበረውም ። የቋንቋ ምሁራኑ ሃሳብም  አገረሰኛውን ንቆ በቀኝ ገዢው ፊደል መጠቀም የኋላ ኋላ የበሬ ካራጁ ይውላልን መሠሪ ገቢር ይከሥታል ደ በማለት አሣሥበዋል  ።

በመሠረቱ ፣ ቋንቋ ከመግባብያነት  ውጪ ፋይዳ የለውም ።ይኽ እየታወቀ ግን ከጀርመን ላቲንን  በመዋስ የኢትዮጵያን ቀለም ማጥፋት ተገቢ አይደለም ። ይኽ የላቲን ፊደል ፖለቲካ ፣  ፖለቲካውን ከሰው ፖለቲካ ተራ ከማውጣቱ በሻገር ዜጋውን በአገሩ ላይ እምነት እንዲያጣ በማድረግ በገመድ ጉተታ የፖለቲካ ትግል ውሥጥ ዘፍቆታል ። ተማሪዎች  ላይ ያሥከተለው ጦስ ና ጥንቡሣሥም ቀላል እና እንደዋዛ የሚታለፍ  አይደለም ። ደሞም የላቲን ፊደል አንዱ የከፋፍለህ ግዛ መንገድ መሆኑ በብዙ የቆንቋ እና የፖለቲካ ምሁራን በማሥረጃ እና በመረጃ የተረጋገጠ  እንደሆነ ልብ ማለት በዕወቅት ላይ ለተመሠረተ ክርክር ይጠቅማል  ።

ወደ ነገሬ ልመለሥ  ።ይህ ህቡ ሆኖ በአውሮፖና በአሜሪካ ቱጃሮች የሚሾር  ፣የከፋፍለህ ግዛ   እኩይ አሳብ ከቀዳማዊ ኃይለሥላሤ የንጉሠ ነገሥት መንግሥት አንስቶ እሥከዛሬ በረቀቀ ዘዴ  እየተተገበረ ያለ “ ኢያጓዊ መንገድ ነው ።” ይኽ መንገድ በሐሰተኛ ትርክትና ወሬ ህዝብ ማደናገር ፣ ማጣለት ፣ ቂምና ቁርሾ ማሥያዝ ላይ የተመሠረተ እርስ በእርስ የማጠፋፍያ መንገድ ነው ። ይኽን  መንገድ እሥከዛሬ በአራት ኪሎ ቤተመንግሥት የአገዛዝ  አልጋ ላይ  የተፈራረቁት  ባለሥልጣናት  ቀለምና መልክ ፍንትው አድርጎ ያሣየናል   ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሞትን በሕይወት፣ ጥላቻን በፍቅር የረታ ‹‹ይቅርታ!››

እንደሚታወቀው ከንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለሥላሤ   ውድቀት በኋላ ፤ የተከሰቱት ወታደር መር አገዛዞች  ናቸው ።ሁለቱም  ልምጭ ተኮር አመራሮች ነበሩ ።ይሁን እንጂ  ወታደራዊው ደርግ እጅግ የደመቀ የአርበኝነት መንፈሥ ነበረው ።በተግባር አገር ወደዳ  ነበር ። የወደቀውም በዓለም ላይ ከነበሩት ሁለት የፖለቲካ ጎራዎች አንዱ ሥለተንኮታኮተ ነው ።   በወቅቱ የነበረው  የሶሻሊስቱ ጎራ   ፣ በሩሲያዊው መሪ ጉርቫቾቭ  አማካኝነት  በአሜሪካ መንግሥት ተከታታይነት ባለው ሴራ ፣ በሩሲያ ምድር   ሲቀብሩት ፣ በቀላሉ   ዘረኛው ኃይል  ኢህአዴግ ብሎ ራሱን በመጥራት   ደርግን ከሥልጣኑ ገፍትሮ  ፤ ኢርትራ በቀላሉ ከእናት አገሯ ከኢትዮጵያ እንድትገነጠል በመተባበር ፤ የአራት ኪለውን አልጋ በቀላሉ ተረከበ  ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዐቢይ አሕመድ አሊ ለሥልጣን የበቃው በምርጫ ነው ወይ በቅርጫ (ኘሮፌሰር ኀይሌ ላሬ)

የዘረኛው ወያኔ ኢህአዴግ መንግሥት በተራው ፣ በሥልጣን እሥከ ጥግ ባለገ ። በብልግና ፣ ኤርትራን እንድትገነጠል ፣ መንገዱን ጨርቅ ያርግልሽ ብሎ ሲያበቃ ፣ ወደ ጥልቅ ብዝበዛ ጥቂት የእርሱ ሰዎች እንዲሰማሩ አደረገ ። አሜሪካኖቹ እና ምዕራብያዊያን ቱጃሮች ደግሞ ገንዘብን እንዲወድ ፣ የአገሩን ሰው ፣እንዲጠላ አደረጉት ።  የአገሪቱን ወርቅ እና ልዩ ፣ ልዩ ወድ ጌጥ ዘርፎ ፤   በየአገራቸው ባንኮች  ሀብት እንዲያከማች የሌባ ዋሻ ሰጡት ።

ተራው ዜጋ የበይ ተመልካች እንዲሆን ተደረገ ።  እንደነጮች ሁሉ ፣ በሠለጠነ መንገድ  በመርህ ደረጃ ፣ እርስ በእርስ እንዳይረዳ አገዛዙ በቋንቋ እና በዘውግ ከፋፈለው ። በአጭሩ “ ዘመነ ከፋፍልቲ “ ተጀመረ ። ወያኔ የተወሰኑ   ቋንቋዎች   የአትደረሱብኝ ግንብን እንዲያጥሩ አደረገ ።  አንዱ ለአንዱ እንዳይወግን በማደረግም “ የእኛ እና የእነሱ “ የሚል መናቆሪያ መድረክ ፈጠረ ። ጥቂቶችንም  ተጠቃሚ   በማድረግ ፣ በጥቅም እያባላ  በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ሥም ፣እና በክልል ሥም  ፣  የግል ሥርቆትን እያጧጧፈ ፣ ለ27 ዓመት ኢትዮጵያን በህገ አራዊት ሲገዛ ቆይቶ በድንገት ከወንበሩ ላይ እብሥ ብሎ መቀሌ መሸገ ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  “ላጉርስህ ሥትለው ልንከሥህ ካለህ ምን ትለዋለህ ??… “  መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ከዛስ  ፤ እንደምታውቁት ፤ ኢህአዴግ  ፣ ወደ ብልፅግና ተቀየረ ። ብልፅግናም ፣ ከወያኔ በሥተቀር ” አጋር ድርጅቶችን ” በሙሉ ወደ እራሱ አካቶ “ ብልፅግና “ የተሰኘ ፓርቲ መሠረተ   ። እናም በምርጫ መንግሥት ሆነ ። መሪውም አሻጋሪው አብይ አህመድ ሆኑ ። ( ጠቅላይ ሚኒሥቴር ዶ/ር  አብይ አህመድ ፤ የኢህአዴግ ጠቅላይ ሚኒሥቴር ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ፣ የሚኒሥትሮች ምክርቤት ሰብሳቢ … እንደሆኑ አትዘንጋ )

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራው መከራ ላገሩ ስለሠራ (በዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ)

ዶ/ር አብይ አህመድ ( ክ/ጠ/ሚ ) ፤ ለምዕራባውያን አልገዛም ባይ አፈንጋጭ መሪ ናቸው ። ይላሉ ብዙዎች  ። እርሳቸውም ይኽንን ባህሪያቸውን አልሸሸጉም ። እንደ ጥንቶቹ  ኢትዮጵያዊያን ጀግና አባቶቻችን   ለነጭ ተበርካኪ ወይም የበታችነት ሥሜት ያለማሳየታቸው አገርን ያኮራል ።በነጭ ማሥፈራርቾ የሚናጥ   መሪ ያለመሆን እጅግ የሚያኮራ ነው  ።  ይኽንን ባህሪያቸውን  ኢትዮጵያዊው ቢደግፈውም ፣ ተንበርካኪው እና ፈረንጅ አምላኪው ይጠላዋል ። ተበርካኪውና ፈረንጅ አምላኪው ፤ ሆድ አደር ፤ በብልፅግና ውስጥ ያለው ጭምር ፤  ይኽንን ኩሩነት ፈፅሞ አይወደውም    ። እናም ይኽ ሆዳም ቡድን ፣ ከምዕራባውያን ሰላዮች ጋር በህቡ ፣ በተደራጀ መልኩ  በእቅድ እየሰራ ሰውየውን ከኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል ተከታታይ ሤራዎች እየገነጎነ በህቡ እየተገበረ እንዳለ የሚያሳዩ ብዙ ጠቋሚ ምልክቶች ዛሬ በግልፅ እየታዩ ናቸው ።  የተመሥገን ደሣለኝም ሆነ የዘመነ ካሤ እሥር ከእነዚህ አስብቶ አራጆች ሤራ ጋር   የተሰናሰለ ነው ። ( ብዙ የፖለቲካ ተንታኞችና ፣ በዕውቀት ጭቅላቶየመጠቁ የደህነነት ባለሙያዎች   በዚህ አሣብ ይስማማሉ ። )

በዚህ  ወቅት ፣ ይኽቺን  አገር ወደፊት ለማራመድ ቅን ፍላጎት መሪው ቢኖረውም አብረው የሚሠሩት ምን ያህል ቁርጠኛ ና ፆመኛ ናቸው ? ምን ያህል ከብዝበዛ የነፁ ናቸው ? የሚል ጥያቄ አንስቶ የባለሥልጣናቱን ገበና መፈተሽም በዚህ ወቅት  እጅግ አሥፈላጊ  ይመሥለኛል ። በአሉባልታ ሳይሆን በተጨባጭ የባለሥልጣናቱን  ጨዋነትም ሆነ ያልተገባ በህሪና ተግበር የሚገመግሙ የቅርብ ሰዎች ወይም ውሥጥ አዋቂዎች ብቻ እንደሆኑም አንዘንጋ ። ከዚህ አንፃር የሚመሩትን ህዝብ የሚመጥን ንፁህ ህሊና ያላቸውን የብልፅግና ከፍተኛ ፣ መካከለኛና ዝቅተኛ  አመራሮች ፣ እነዚህ ውሥጥ አዋቂዎች ሊጠቁሙን ይችላሉ  ። እንደ ማንኛውም ህዝበ ፣ ከግል ኑሯቸው አኳያ ከመዘንናቸው  ግን  ሥልጣን ቢሊዮነር ያደረጋቸው በጣት የሚቆጠሩ ባለሥልጣናት የሉም ብለን መናገር አንችልም  ። …

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከመንግስት የቤቶች ግንባታ ጀርባ ያለው ትክክለኛ ዓለማ ሲገለጥ

ይኽንን አገር አውዳሚ የባለሥልጣናት  ብዝበዛ   ለማጋለጥ ደግሞ እንደ ባዓሉ ግርማ አይነት ደፋር  ጋዜጠኛ  ያሥፈልገናል ። ለሃቀኛ መንግሥት እና ለህዝቡ እንደ ተመሥገን ደሣለኝ እና እንደታዳዮስ ታንቱ አይነት ጋዜጠኞች እጅግ  አሥጸላጊ እንደሆነም መዘንጋት የለብንም ። “ሃቅን  ተናግሬ ና አሣውቄ ፣ ዛሬ ልሙት የሚሉ ጋዜጠኞች ይኽቺ አገር ከሌላት  ዴሞክራሲ እና የህግ የበላይነት በመላ አገሪቱ ሊንሰራፋ አይችልም ። የህግ የበላይነት እና ዴሞክራሲ ከሌለ ደግሞ አናርኪዝም ይሰፍናል ። የአናርኪዝም መሥፈን ደግሞ ለምዕራባውያን እና ለአሜሪካ በዝባዦች ጥርጊያ መንገድ ይከፍታል ። ለዚህም ነው የአውሮፖ  አንዳንድ ሚዲያዎች እና መንግሥታቱ ፣ ከአሜሪካ ሚዲያና መንግሥት ጋር ተቀናጅተው  ፣ የአገራችንን ገፅታ ለማበላሸት ፣ በትህነግ /ወያኔ አማካኝነት  proxy war የከፈቱብን ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  <> - በልጅግ ዓሊ

ይህ የውክልና ጦርነት በትህነግ አማካኝነት የተከፈተብን ፣ ኢትዮጵያውያን በጦርነት ማሸነፍ እንደማይቻል ከመቶ ዓመት በፊት በተጨባጭ በአደዋ ተራሮች  በማረጋገጣቸው  ነው ። እናም ይኽንን ጦርነት ልክ እንደ አደዋ  በድል ማጠናቀቅ ለአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እጅግ አሥፈላጊ ነው ። ለወደር የለሹ ና ህዝብን እፎይ ለሚያሥብለው ድል   መበሰረ  ደግሞ ፣ የአገሬ መንግሥት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ውሥጡን በዓይነ ቁራኛ መከታተል እና ራሱን ከጥፋት ኃይሎች መጠበቅ  ይኖርበታል  ።  ኃቀኛ ጋዜጠኞችም ፣   በቀኃሥ ዘመን እንደነበሩት የህዝብን ብሶት ለመንግሥት አቅራቢ እረኞች  መሆናቸውን መገንዘብ አለበት ። እረኛህን እንዴት ታሥራለህ ? ራስህን በራስኽ እንቀህ አሰንድታጠፋ በመሠሪ የውጪ ጠላቶቻችን ለምን በየዋህነትህ ትገደዳለህ ?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share