September 28, 2022
32 mins read

የአማራ ዜጎች ከወለጋ የሰው ማረጃ ቄራ በሰላም እንዲወጡ የብልጽግና ፌዴራልና፣ የኦሮሚያና የአማራ ክልላዊ መንግሥቶች ግዴታና ተጠያቂነት አለባቸው

የማርያም መንገድ ይሠጣቸው!!!

 ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)

Untitled44444rrrr

‹‹ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር መብት አለው!!!›› በወለጋ፣ በመተከል፣ በቤኒሻንጉል የሚኖሩ አማሮች በህይወት የመኖር መብታቸው ተጥሶል፡፡ የህወኃት ኢህአዴግ የዘር ቨይረስ ወደ ኦነግ ብልፅግና የዘር አባ ሠንጋ ቨይረስ ከተላለፈ ቆይቶል፡፡ አራጆቹ!!!

በወለጋ የሰው ቄራ እርድ በጥበቃ ስር ያሉና ያለፍርድ የታገቱ ሰዎች መብት ስብዓዊ ክብራቸውን በማይጠብቁ ሁኔታዎችበኦህዴድ ብልፅግና መንግሥትና በኦነግ ሸኔ ያለፍርድ ለሰው ቄራ የደም መሥዋትነት እንዲቀርቡ የሚያደርጉ አንደኛ ነተጠያቂዎች የፌዴራል መንግሥቱን የሚመሩት ዶክተር አብይ አህመድና የኦሮሞ ክልላዊ መንግሥት  መሪ ሽመልስ አብዲሳ፣ የቤኒሻንጉሉ መሪ አሻድሊ ሃሰንና የአማራው ክልል መሪ ይልቃል ከፍያለ  ዋነኛ ተጠያቂነትን አቶ አንድአርራቸው ጽጌ ሲያስተባብሉ ታይተዋል፡፡ የእርሶ ልጆች በወለጋ ቄራ ውስጥ ቢሆሩ መጀመሪያ ከዚህ የእርድ ክልል ጣቢያ አስወጡን ብሎ የሚለምነውን ደሃ የአማራ ህዝብ ከመታደግ ሌላ ምን አለ፡፡ አሁንም ህዝቡ ነፃ የማርያም መንገድ ተከፍቶለት ከወለጋ ኦሮሚያና ከመተከል ቤኒሻንጉል ክልል መውጣት ነው የሚፈልገውና መፍትሔው ይሄ ብቻ ነውና ለዶክተር አብይ አህመድ እንዲወጣ ቢለምኑለት እንጠይቅዎታለን፡፡ ይሄ የሰው ደም ፈሶ አይቀርምና አንድ ቀን እንደሚያስጠይቅ ሊመክሩቸው ይገባል፡፡ ከዚህ በኃላ ስንት ዓመት ይኖራሉና በወለጋ የሰው ቄራ እርድ የመጀመሪያ ተጠያቂዎችን አብይ አህመድና ሽመልስ አብዲሳ፣ አሻድሊ ሃሰንና ይልቃል ከፍያለ መሆናቸውን ማድበስበስ የትም አያደርስዎትም እንላለን፡፡ በ1966ቱ አብዩት በግፍና ባልሰሩት ተግባር ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴና ካቢኔቸው በርሃብ ለረገፈው ህዝብ ተጠያቂ ሆነው መረሸናቸው የእርሷ የተማሪ ቤት ትዝታ መሆኑን የዘነጉት ይመስላሉ፡፡ ዛሬም ‹‹የአማራን ጥቃት ለማስቆም አንድ መፍትሔ አለኝ››……………(1) በአሉት ዲስኩርዎ ወለጋ ሂዱና ታስረው የጮህልዋትን ህዝቡ የሚልዎትን ብትሰሙ ሃቀኝንዎትን ያሳያሉ፡፡  ያለበለዛ በኢትዮጵያ የፍርድ ቀን ይመጣል!!! አንድ ቀን ይህን የዘር ጭፍጨፋ ወንጀል ለመደባበስ በመሞከርዎና፣ ህዝብን በማሳሳት የመጀመሪያ ተጠያቂዎች ሊህቁ/ ምሁራን ናቸው ብለው ማሳበብ አንድ ቀን ያስጠይቃል እንላለን፡፡ በህወሓት ኢህአዴግ መንግሥት ዘመን የተቀረጸው ህገ- መንግሥት ምን ይላል፡-

  • ‹‹ማንኛውም ሰው ስብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነትና፣ የነጻነት መብት አለው፡፡››አንቀጽ 14
  • ‹‹ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር መብት አለው፡፡ ማንኛውም ሰው በሕግ  በተደነገገ ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ሕይወቱን አያጣም፡፡›› አንቀጽ 15
  • ‹‹ማንኛውም ሰው በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት የመጠበቅ መብት አለው፡፡›› አንቀጽ 16

 

በዶክተር አብይ አህመድ አገዛዝ ዘመን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በኦነግ ሸኔ የተገደሉ አማራዎች ከሰባት ሽህ ቁጥር በላይ አሻቅቦል፣የቆሰሉ ሰዎች በሽህ ይቆጠራሉ፣ የተዘረፉ የቁም ከብቶች ሁለት መቶ ሽህ በላይ ይገመታል፣ የተቃጠሉ ቤቶች ብዙ ሽህ ይቆጠራል፣ 68 (ስልሳ ስምንት) ቤተክርስቲያኖች ተቃጥለዋል፣ 46 (አርባ ስድስት) መስጊዶች ተቃጥለዋል፣ 84 (ሰማንያ አራት) ወፍጮ ቤቶች 163 (መቶ ስልሳ ሦስት) ትምህርት ቤቶች ወድመዋል፣ ብዙ መኪኖች ተቃጥለዋል፣ 756 (ሰባት መቶ ሃምሳ ስድስት) ትምህርት ቤቶች ተዘርፈዋል የትምህርት ማስረጃዎች ተቃጥለዋል፡፡325 (ሦስት መቶ ሃያ አምስት) ሽህ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ 5227(አምስት ሽህ ሁለት መቶ ሃያ ሰባት) አስተማሪዎች ከስራ ውጪ ሆነዋል፡፡ በወለጋ 500 (አምስት መቶ) ሽህ ህዝብ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ በተመሳሳይ በምዕራብ ሸዋ ዞን የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች 647 ንፁሃን አማሮችን መግደላቸው ተገልፆል፡፡ 1252 (አንድ ሽህ ሁለት መቶ ሃምሳ ሁለት) የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ 85 (ሰማንያ አምስት) ሽህ ህዝብ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ 26.7 (ሃያ ስድስት ነጥብ ሰባት)  ሚሊዩን ብር የሚገመት ንብረት ወድሞል፡፡ የአማራ ክልል መንግሥት በጦርነቱ 11.6 (አስራአንድ ነጥብ ስድስት) ሚሊዮን ህዝብ አስቸኮይ የስብዓዊ እርዳታ ድጋፍ  እንደሚያስፈልጋቸው ተገልፆል፡፡ ከዚህ ውስጥ  9.3 (ዘጠኝ ነጥብ ሦስት) ሚሊዮን ህዝብ በሰሜኑ ጦርነት በእርሻ ዘርፍ እንዳያመርቱ የተገደዱ ገበሬዎች ናቸው፡፡ 2.3 (ሁለት ነጥብ ሦስት) ሚሊዮን ህዝብ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆኑ በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች የተጠለሉ የነፍስ አድን ድጋፍ ምግብ፣ መድኃኒት፣ መጠለያ ወዘተ የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡ የአማራ ህዝብ በተለይ በወለጋ ኦሮሚያና በመተከል ቤኒሻንጉል ክልሎች   ያሉት ህዝብ ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ቆስለዋል፣ ንብረታቸው ተዘርፎል  ምንም የቀረን ነገር የለምና ከነዚህ የሰዎች እርድ ቄራዎቸ ስቃይና መከራ ተላቀን ወደፈለግንበት በሰላም እንድንሄድ የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ድምፅ ተነስቶ ነፍሳችንን እንዲያድን በህፃናቶች፣ በእናቶችና በአረጋዊያኑ ስም እንጠይቃለን፡፡ አቶ አንዳርጋቸውም የህዝቡን ጥያቄ በኢሳት አማካኝነት ቦታው ድረስ በመሄድ ማረጋገጥ ሚዛናዊ ፍርድ ለመስጠት ይቻልዎታልና ጊዜውን ተጠቀሙበት እንላለን፡፡

ሰኞ ሰኔ 27/2014 . በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ዞን፣ ሃዋ ገላን ወረዳ ውስጥ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የዐይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ።የሟቾች አስክሬን ገና እየተሰበሰበ በመሆኑ የተገደሉትን ሰዎች ቁጥር በትክክል መግለጽ ያልቻሉት የዐይን ምስክሮቹ፣ “በቄለም ወለጋው ጥቃት ሕጻናት፣ ሴቶችና አረጋውያንን ጨምሮ በርካቶች ተገድለዋል” የዐይን ምስክሮች ሕጻናትን ጨምሮ ከ150 በላይ ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀረ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

  • ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትናንት ምሽት በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ በወለጋ በዜጎች ላይ ጭፍጨፋ መፈፀሙን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት ሸኔ የሚለው እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራው ቡድን በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ጭፍጨፋ ተፈፅሞባቸዋል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተፈፀመ ስላሉት ጭፍጨፋ ምንም ዓይነት ዝርዝር መረጃ አላሰፈሩም።
  • የኦሮሞነጻነት ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነት ኦዳ ተርቢ በበኩላቸው በቄለም ወለጋ፣ ማቻራ የተገደሉት ሰላማዊ ሰዎች “በአገዛዙ ታጣቂዎች ነው” ያሉ ሲሆን “ስፍራውን የተቆጣጠሩት የመከላከያ ሰራዊትና አጋር ኃይሎች ምንም አላደረጉም” በማለት በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። በተጨማሪም “ገዥው አካል ጣቶቹን በመቀሰር ከተጠያቂነት ለማምለጥ እየሞከረ ነው” ሲሉም ወቅሰዋል። ይህ መቀጠል የለበትም ሲሉ ያሰፈሩት ቃለ አቀባዩ የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ አካላት ገለልተኛ የሆነ ምርመራ እንዲደረግም አፅንኦት ሰጥተዋል ።
  • የተፈፀመውጥቃት፣ በምዕራብ ወለጋ፣ ጊምቢ ወረዳ፣ ቶሌ ቀበሌ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሔር አባላት ላይ ጭፍጨፋ ከተፈፀመ ከሁለት ሳምንት በኋላ የሆነ ነው። በዚህ ጥቃት ከተገደሉ ሰዎች አብዛኞቹ ህጻናትና ሴቶች መሆናቸውም ተገልጿል። መንግሥት በቶሌ ቀበሌው ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 338 መሆኑንና ምርመራ እየተካሄደ እንደሆነ ገልጿል። የዐይን እማኞች ቁጥሩ ከተገለጸው በላይ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን በአሜሪካ የአማራ ማኅበር የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ወደ 600 እንደሚጠጋ እና የ455 ሟቾችን ስም መለየት እንደቻለ አመልክቷል።
  • በቄለምወለጋ የተፈፀመው ጥቃት፣ በቄለም ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ ወረዳዎች በተቀናጀ የፀጥታ ኃይል ቁጥጥር ሥር ሙሉ በሙሉ መግባታቸውን የመንግሥት ኮሙኑኬሽን ካስታወቀ ከአምስት ቀናት በኋላ ነው። ቄለም ወለጋ ውስጥ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ትናንት ቢቢሲ ያናገራቸው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ፣ ስለ ጥቃቱ ዝርዝር መረጃ እንደሌላቸው  ገለጹ ሲሆን፣ የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናትን አግኝቶ ለማነጋገር የተደረገው ተደጋጋሚ ሙከራም አልተሳካም።
  • የኢትዮጵያሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑትን ዶክተር ዳንኤል በቀለ፣ተቋሙ ጥቃት ስለመፈጸሙ እንደሚያውቅ ተናግረዋል።ነገር ግን ስለተከሰተው አጠቃላይ ሁኔታ ዝርዝር ለማግኘት ከጥቃቱ ከሸሹ ሰዎች መረጃ እያሰባሰቡ እንደሆነ እና የተፈጸመውን ጥቃት ኮሚሽኑ እየተከታተለው እንደሆነ አመልክተዋል።  ጥቃቱ የተፈፀመበት አካባቢ በአገሪቷ በ1977 ዓ.ም. የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ በመንግሥት እንዲሰፍሩ በተደረጉ አነስተኛ ቁጥር ባላቸው የአማራ ብሔር ተወላጆች መኖሪያ መንደር ነው። ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ፣ የሚታረደው ህዝብ ነፍሱን ይዞ ከወለጋ፣ ከመተከል፣ ከቤኒሻንጉል መውጣትና ወደ አማራ ክልል መሄድ ስለሆነ የሚፈልገው ይህን መብቱንና ጥያቄውን ባለመመለስ በህይወት የመኖር መብቱን ችላ በማለት እያሳረዳችሁት ስላላችሁ በአስቸኮይ ተጨማሪ ሰዎች ሳይሞቱ ህዝቡ እንዲወጣ የማርያም መንገድ እንዲዘጋጅለት በህዝቡ ስም እንጠይቃለን፡፡ ዶክተር ዳንኤል የእርሶ ቤተሰቦች በዚህ ዓይነት አጣብቂኝ ውስጥ ቢገኙ ምን ያደርጋሉ?

ከዐይን እማኞች አንደበት ለቢቢሲ አማርኛ  ቃለ-መጠይቅ

ከጥቃቱ እንደተረፉ የሚናገሩት የዐይን ምሥክር “አስክሬን ገና ለቅመን አልጨረስንም። በረሃ ላይ ወስደው ሰው ጨፍጭፈዋል፤ መስጊድም የተሰበሰበ አስክሬን አለ። ሐኪሞች መጥተው ማድረቂያ አድር ውልን ሄደዋል። የሚታየውን ነገር ለመግለጽ ይከብዳል” ብለዋል። ጭፍጨፋው በቦምብ፣ በስለት እና በጥይት እንደተፈፀመም የዐይን እማኙ አክለዋል።

በጥቃቱ ከ45 በላይ ሰዎች ቆስለው ሆስፒታል መግባታቸውንና ሆስፒታል ከገቡት ውስጥ ሕይወታቸው ያለፈ እንዳለም የዐይን እማኙ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። ከዚህም በተጨማሪ በንብረት ላይ ዘረፋ እና ውድመት መፈፀሙን ገልጸው፣ ከ50 እስከ 70 የሚሆኑ ቤቶች መቃጠላቸውን ተናግረዋል። እርሱ እንደሚለው ብዙ ሰዎች አልቀዋል፤ከቤት ወደ ጫካ ተወስደው በአንድ ላይ ሕጻናትና ሴቶችን ተጨፍጭፈዋል። ገና የሟቾች አስክሬን እየተሰበሰበ መሆኑን የገለጸው የዐይን እማኙ፣ የተገደሉት ሰዎች ከ150 እስከ 160 እንደሚሆን ግምቱን ለቢቢሲ ገልጿል። “መንደሩ ውስጥ የተገደሉት ሽማግሌዎች፣ ሴቶች እና ሕጻናት ናቸው። ወጣቶችን ደግሞ አስገድደው ወደ ጫካ ይዘው ሄደዋል ተብሏል። ግን እስካሁን አልተመለሱም” ሲልም በታጣቂዎች ታግተው የተወሰዱ ሌሎች ሰዎች መኖራቸውንም ተናግሯል።

የዐይን እማኞቹ ጭፍጨፋውን የፈፀመው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እያለ የሚጠራው፣ ኦነግ-ሸኔ ነው ብለዋል። ከዚያም ከሰባት ሰዓት በኋላ የተወሰነ የመከላከያ ኃይል መግባቱንና ከ10 ሰዓት በኋላ በርካታ የመከላከያ ሠራዊት ኃይል ወደ ስፍራው መድረሱን፤ ነገር ግን ታጣቂዎቹ አካባቢውን ለቀው በመሄዳቸው ምንም የወሰዱት እርምጃ አለመኖሩን አስረድተዋል። “በጥቃቱ መንደር 20 እና መንደር 15 የሚኖሩ በርካታ የአማራ ተወላጆች በስለት፣ በቦምብ እና በጥይት በአስቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል” ብለዋል ነዋሪው። በተለይ ካላፉት አራት ዓመታት ወዲህ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ሲፈጸም ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉድሩ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ውስጥ በሚገኙ በተለይ የአማራ ብሔር ተወላጆች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች በታጣቂዎቹ በተፈፀመ ጥቃት ሕጻናትና ሴቶችን ጨምሮ በርካቶች ተገድለዋል።…………(2)

ከዐይን እማኞች አንደበት ለቢቢሲ አማርኛ  ቃለ-መጠይቅ

24 መስከረም 2022 በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ውስጥ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች በሰላማዊ ነዋሪዎች እና በአካባቢው የሚሊሻ አባላት ላይ ግድያ መፈጸማቸውን መንግሥት አስታወቀ። በሽብርተኝነት የተፈረጀውና መንግሥት ሸኔ በማለት የሚጠራው ይህ ቡድን በምዕራብ የኦሮሚያ አካባቢዎች በተከታታይ በሚፈጸሙ እና በመቶዎች በሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች ላይ በተፈጸሙ ግድያዎች ይከሰሳል። ባለፉት ቀናት በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ጃርደጋ ጃርቴ ውስጥ ታጣቂው ቡድን ጥቃት መፈጸሙን ነዋሪዎች ሲገልጹ የቆዩ ሲሆን፣ በተከታታይ ቀናት በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በዞኑ ውስጥ ነሐሴ መጨረሻ ላይ ከ20 ሺህ በላይ የተፈናቀሉበትና ከ60 በላይ ሰዎች የተገደሉበት ጥቃት ተፈጽሞ ነበር

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 14/2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ታጣቂው ቡድን በዞኑ ውስጥ “በንጹሃን ዜጎች እና በአካባቢው የሚሊሻ አባላት ላይ ግድያን ፈጽሟል” ያለ ሲሆን ስለተገደሉት ሰዎች ብዛት ግን ያለው ነገር የለም። የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ቡድኑ በስፋት በሚንቀሳቀስባቸው የምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች በፀጥታ ኃይሎችና በሕዝቡ ቅንጅት እርምጃ እንደተወሰደበት ያመለከተው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መግለጫ እየተበተነ ወደ ሆሮ ጉድሩ ጃርደጋ ጃርቴ አካባቢ ሲሸሽ ነበርብሏል። አሁን በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ተፈጽሞበታል የተባለውን የሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞንን ጨምሮ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ይንቀሳቀስባቸዋል በሚባሉት የምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች ባለፉት ዓመታት ሰላማዊ ነዋሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞችና ባለሥልጣንት እንዲሁም ተቋማት ጥቃት ሲፈጸምባቸው ቆይቷል።

በተለይ ካለፈው ዓመት አጋማሽ ወዲህ በአካባቢው ነዋሪ በሆኑ የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ተደጋጋሚ ጥቃቶች መፈጸማቸው ይታወሳል።በእነዚህ ጥቃቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሔር አባላት የተገደሉ ሲሆን በርካታ ኦሮሞዎችም በታጣቂዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች ተገድለዋል። መንግሥት እና ከጥቃቶቹ የተረፉ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች የበርካቶችን ሕይወት ለቀጠፉት ጥቃቶች የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ተጠያቂ ሲያደርጉ ቡድኑ ግን ድርጊቱን ሲያስተባብብል ቆይቷል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በምዕራብ ኦሮሚያ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ለበርካታ ነዋሪዎች ሞትና መፈናቀል ምክንያት የሆኑ በታጣቂዎች የተፈጸሙ ጥቃቶች በእጅጉ እንዳሰሳሰቡት ከሳምንታት በፊት ባወጣው መግለጫ ማመልከቱ ይታወሳል። ኮሚሽኑ እንዳለው ከነሐሴ 23 እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ በታጣቂዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ60 በላይ ሰዎች መገደላቸውን፤ ከ70 (ሰባ) በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን እና ከ20 (ሃያ) ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልጿ ነበር።  እንዲሁም ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪው ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ባወጣው መግለጫ ሰላማዊ ሰዎች በታጣቂዎች ሲገደሉ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ጥቃቱን ለመከላከል በቂ ጥበቃ አላደረጉም ሲል ወቅሶ ነበር።…………..(3)

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የጥቃቱ ሰለባዎችን ነፍስ እንዲያድንና ከአራጆቹ እጅ ነጻ እንዲያወጣቸው መጀመሪያ ‹‹ማንኛውም ሰው ስብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነትና፣ የነጻነት መብት አለው፡፡›› ስለዚህ የህጻናቱን፣ የሴቶቹንና የአረጋዊ ሰዎችን ወደሚፈልጉበት ክልል እንዲሄዱ በማድረግ ከአራጆች ቀንበር ነፃ እናውጣቸው እንላለን፡፡ ጉንጭ አልፋ መግለጫ ከማውጣትና ሙያን ከማርከስ ሥልጣንን ለቆ ለታረዱት ሰዎች ከለላና መከታ ሆኖ የአብይና የሽመልስን ፋሽስታዊ ሥራ ማጋለጥ የምሁራን ግዴታ ነው እንላለን፡፡ ነገም እንደሚታረዱ ታውቃላችሁና!!! ለወንጀሉ ተባባሪ ከመሆን ይሰውረን የጠየቁት የማርያም መንገድ ነው….. በየጫካው ተደብቀው የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ናቸው፡፡ የአማራ ክልል መንግሥትም ለዚህ ሞልቶ ለፈሰሰ ግፍ ዋና ተጠያቂ ነው፣ አብን ቃለማሃላውን አፍርሶ የአማራ ህዝብን ሸጦል፣ ኦፌኮ ከጁሃር ሜንጫ ጋር ገዳይና ተገዳይ ለድርድር ይቅረቡ ይላል፣ የኢዜማ ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ማስረጃ ሌብነት አስጨንቆታል፣ አስራሁለት ሚሊየን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለው መቅረታቸው ቁብም አልሰጠው፡፡ ብርሃኑ ተፈናቃዩቹን ሄዶ ቢያይ ተማሪዎቹን ከዛ ዘንድ ያገኛቸዋል፡፡

ፋኖ ተደራጅቶ የአማራ ህዝብ መመኪያና መከታ እንዳይሆን አንድ ሽህ አንድ ጠላቶች ተፈለፈሉበት፡፡ አቶ አንዳርጋቸው የፋኖአደራጅነት በመዘንጋት ይመስል አንድ ቃልም ስለ ፋኖ አደረጃጀት አልተነፈሰም አለቃህ ዘመነ ካሴ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነት አግኝቶል፡፡ የአማራ ህዝብ እንዳይደራጅ ኦህዴድ ብልጽግና፣ የኦሮሞ ብልፅግና፣ የአማራ ብልፅግና ቀን ከሌት ያሴራሉ፡፡  ከአስራ አምስት ሽህ በላይ የፋኖ ታጣቂዎች በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ሁኔታውን ያጋለጡ ጋዜጠኞች በእስር ዘብጥያ ወርደዋል፡፡   ኦነግ ሸኔ ከኦሮሚያ ምድር አማራን ያስወጣ የሚል የኦሮሙማ ፍኖተ ካርታ የተነሳ አማራ ዘር እንዲያልቅ ተፈርዶበታል፡፡ የአማራ ዜጎች ከወለጋ የሰው ማረጃ ቄራ በሰላም እንዲወጡ የብልጽግና ፌዴራልና፣ የኦሮሚያና የአማራ  ክልላዊ መንግሥቶች ግዴታና ተጠያቂነት አለባቸው!!!  የማርያም መንገድ ይሠጣቸው!!!  የታራጆቹ ጥያቄ ይሄ ብቻ ነው፣ ህዝብ ይጩህላቸው!!! የጠቅላዩ የአራት አመታት የመከራ ዘመን ከሰሜኑ ጦርነት ህወሓት ኢህአዴግን ካስተነፈስን በኃላ ኦነግ ሸኔን እንደርስበታለን ታገሱ ይላሉ፡፡ በማያልቀው የጦርነት አዙሪት ውስጥ አንድ ሚሊዮን ወጣቶች ሞተዋል፣ አንድ ትሪሊየን ብር የሚገመት መሰረተ-ልማቶች ወድመዋል፡፡ አካሉ የጎደለ ወጣቶችን ወላጆቻቸው ከየቤቱ ይቁጠሮቸው፡፡ ግን ይሄ ሁሉ እልቂትና ውድመት ለምን? አቶ አንዳርጋቸው ከጁሃር ጋር መከራከር መርጠዋል እንደኛ ምርጫ ከሆነማ ከእኩዬችህ አቻምየለህ ታምሩ፣ከፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው፣ ከሻለቃ ዳዊት ወልደጊርጊስ ወዘተ ጋር ቢወያዩ ይመረጣል፡፡ የኢሳት ሚዲያ የእርሷ ነውና ‹‹እኛም እንናገር ህዝብ አይደናገር!!!›› እኛ ሲሉ  እኔ? አይ ዘመን!

‹‹ሁሉም ሰዎች በህግ ፊት እኩል ናቸው፣በመካከላቸውም ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግ በሕግ እኩል ጥበቃ  ይደረግላቸዋል፡  በዚህ ረገድ በዘር፣ በብሔር፣ ብሔረሰብ፣ በቀለም፣ በፆታ፣ በቌንቌ፣ በኃይማኖት፣በፖለቲካ፣ በማህበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት በትውልድ ወይም በሌላ አቌም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግ ሰዎች ሁሉ እኩልና ተጨባጨ የህግ ፍህትን የማግኘት መብት አላቸው›› አንቀፅ 25

ምንጭ

(1) ‹‹የአማራን ጥቃት ለማስቆም አንድ መፍትሔ አለኝ/ ከጀዋር ጋር ፊት ለፊት መከራከር እፈልጋለሁ/ አንዳርጋቸው ፅጌ/ 27 ሴፕቴምበር 2022 ››

(2) “በቄለም ወለጋው ጥቃት ሕጻናት፣ ሴቶችና አረጋውያንን ጨምሮ በርካቶች ተገድለዋል” የዐይን ምስክሮች

(3) በሆሮ ጉድሩ ታጣቂዎች ነዋሪዎችን እና የሚሊሻ አባላትን መግደላቸውን መንግሥት ገለጸ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop