September 27, 2022
4 mins read

በዘመነ ሉቃስ ኢትዮጵያ የመከራ ቤተ ሙከራ ከመሆን መዳን አለባት

Meskel Ethiopiaኢትዮጵያ እና ህዝቧ ላለፉት ሶስት አስርተ ዓመታት በባርነት እና በዕስር መሆናቸዉን ከረጂም ዓመታት ያላሳለሰ ህዝባዊ ብሄራዊ እና ዓለም ዓቀፋዊ ያላሳለሰ ትግል በማድረግ በሁለት ሽ ስምንት ዓ.ም. የነፃነት ትግል ፍሬ አሽቷል፡፡

ይህም ኢህአዴግ በራሱ አልቃሽ እና ዘፋኝ ሆኖ በሚገኝ አድር ባይ የፖለቲካ አባላት አንዱ አሸባሪ እንዱ ተቆርቋሪ እንደነበር  እና ኢህአዴግ እና ስርዓቱን በመታደግ  የስርዓቱን ጨቋኝ ዕድሜ ማራዘም የተቻለዉ በኢትዮጵያዉያን እና በተለይም በዓማራ ህዝብ ወሳኝ ተጋድሎ ነዉ ፤ነበር ይህንም ያፈነገጠዉም ሆነ የተገላበጠዉ ኢህአዴግ  እና አመራሮች የመሰከሩት እናየሚመሰክሩት ነዉ ፡፡

ሆኖም የተናገሩትን ትተዉ በዕስር እና ከባርነት ያወጣቸዉን እና ከወደቁበት አንስቶ ወደ ስልጣን ማማ ዕርካብ ያወጣቸዉን ባለዉለታ ህዝብ የዓማራን ህዝብ በጠላትነት ፈርጀዉ ከዕስር ያወጣቸዉን ህዝብ ጣራ አልባ ዕስር ቤት ዉስጥ በአዲሱ ተያይዘዋል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ትህነግን እና ኢህዴን/ብአዴንን ከሞትበት አስትንፋስ ዘርቶ ፤ ከወደቀበት መቃብር ፈንቅሎ ፤  ከአፈር አንስቶ ፤ ከተደበቀበት ጎትቶ  ከጎንደር እና ከትግራይ በረኃ  አዉጥቶ ላለፉት ሠላሳ ዓመታት በራሱ የሞት እና የጭቆና ቋጥኝ ጭኖ ከዚህ መከራ ለመዉጣት ከፍተኛ ዋጋ ኢትዮጵያዉያን ከፍለዋል ፡፡

አገር ሲያረጂ ሜጭ ያበቅላል ፤ ዐድባር ሲጠፋ አምቧጮ  አድባር እንዲሆን  ላለፉት ሶስስት ዓመታት  በታሪክ ኢትዮጵያ እና ህዝቦች  በተለይም ዓማራ የመከራ መድብል እና የመከራ ቤተ ሙከራነታቸዉ ብሷል ፡፡

ስለ ነፃነት እና ህልዉና  ስንናገር  በመከራ እና ጭቆና ምድር ዉስጥ ጣራ እና በር ባላቸዉ ዕስር ቤት  ባቻ የሚገኙትን ብቻ ሳይሆን ለአንድ ክ/ዘመን አጋማሽ  ስደት ፣ ባርነት ፣ ሞት እና ዉርደት ዉስጥ ላሉት ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ከጣራ አልባ ዕስር ፤ ከምድር ሲኦል ለመዉጣት መነጋገር ፣መግባባት ፣መምከር እና ለአነድ ህዝብ እና አገር መተባበር የሚኖርበት ጊዜ አሁን ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ያሁኑ የኢትዮጵያ ሁነታ፤ ይመስላል የተምታታ – ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

“በዘመነ ሉቃስ ጥላቻ እና ክህደት ይደምሰስ ”

“ ኢትዮጵያ ከመከራ ወደ መድረ ፍስኃ ትሸጋገራለች  ፡፡”

“ተስፋችን  ከዘመናት መላቀስ ወደ ዘመነ ሉቃስ ዘመነ ድህነት እና ዘመነ ካሳ ነዉ ፡፡”

ነፃነት እና ህልዉና ዕዉን የሚሆነዉ  በአንድነት እና በዓላማ ፅናት በሚቆም ክንድ ነዉ ፡፡”

“አንድነት ኃይል ነዉ ”

Leave a Reply

Your email address will not be published.

የአቢይ አህመድ ጨለማ ጉዞ!
Previous Story

አቦይ ስብሃትን ፈቶ ፤ አርበኛ ዘመነ ካሴን ማሰር – አሰፋ በድሉ

madingo
Next Story

ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ አረፈ

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop