ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ አረፈ

ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ በዛሬው እለት ወደ ህክምና በሄደበት የጤና ተቋም ውስጥ ህይወቱ ማለፉን የቅርብ ወዳጆቹ ገልጸዋል። ማዲንጎን አፈወርቅ ትላንት ምሽት ክለብ ስራ ላይ ነበር። ዛሬ ጠዋትም ወደአንድ ክሊኒክ የሄደው መኪናውን እየነዳ ነው። ክሊኒኩ ውስጥ ከገባ በኋላ ግን እስትንፋሱ በመቆሙ በኦክስጂን ጭምር ለማትረፍ ተሞክሮ አልተሳካም።
ድምፆዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ዘመን የሚሻገር ሥራ ባለቤት ነው። ኢትዮጵያ በተፈተነችበት ወቅት እያመመው ግንባር ድረስ በመሔድና ማሰልጠኛም ምልምል ወታደሮችን በማነቃቃት የራሱ የሆነ ታሪክ የሠራ አርቲስት ነበር።ለመላው ቤተሰቦችና ለመላው የኢትየጵያ ሕዝብ መፅናናትን እንመኛለን!
ተጨማሪ ያንብቡ:  ኦነግ ሸኔ አዲስ ያሰለጠነውን የጦር ሰራዊት ያስመረቀ ሲሆን በኦሮሚያ የሰሜኑ ክልል ድል እየቀናኝ ነው አለ (የመረጃ ቪዲዮ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share