September 24, 2022
13 mins read

ጋኖች አለቁና ምንቸቶች ጋን ሆኑ ድራንዝ – ጴጥሮስ ከባህር ዳር

zemene 1
ይህን ጀግና ያሰረው ይፈር ያፈነው ይፈር የካደው ይፈር።

ቀዝቃዛ በሆነ ምሽት አንድ ቢሊየነር ከቤት ውጭ አንድ ድሃ ሽማግሌ አገኘ። ‹በዚ ቅዝቃዜ ውጪ ላይ ኮት እንኳን አለበስክም አይበርድህም እንዴ› ብሎ ጠየቀው። አዛውንቱም “ኮት የለኝም ነገር ግን ለምጄዋለሁ ሲል መለሰለት። ቢሊየነሩም “ቆይ ጠብቀኝ ወደ ቤቴ ሄጄ ኮት አመጣልሀለው” ብሎት ሄደ።

ድሃው ሰውም በጣም ተደስቶ እጠብቅሀለው አለው። ቢሊየነሩ ወደ ቤቱ ደረሰ ግን በስራ ተጠምዶ ስለ ምስኪኑ ሰው ረሳ። በማግስቱ ጠዋት ድነገት ምስኪኑን አዛውንት አስታወሰና ሊፈልገው ወጣ ነገር ግን ምስኪኑን አዛውንት በቅዝቃዜው ሞቶ አገኘው።

ምስኪኑ አዛውንትም እንዲህ የሚል ደብዳቤ አስቀምጦለት ነበር “ሞቅ ያለ ልብስ ሳላገኝ ቅዝቃዜውን ለመቋቋም የሚያስችል የአእምሮ ጥንካሬ ነበረኝ, ነገር ግን እንደምትረዳኝ ቃል ስትገባ, ቃልህ የአእምሮ ኃይሌን ገደለው”

ቃል መፈጸም ካልቻልን ምንም ቃል አንግባ እያልኩ በቁርጡ ቀን ጀግና በዘመነ ካሴ መታሰር የዘቀዘኩት ብዕር እንዳነሳ ተግድጃለሁ፡፡ ግን ለምን@

“ይች ምድር ክርስቶስን ሰቅላለች። ሶቅራጥስን መርዝ ግታ ገድላለች። ጆርዳኖ ብሩኖን በእሳት ጧፍ ውስጥ ከታ አቃጥላ ገድላለች። አለም እውነትን መሼከም አትችልም።እውነት ያቅራታል።…..”

“በላይ ዘለቀን አንቃ ገላ፣ ልጁን የሻሽ ወርቅን ተራ አረቂ ሻጭ አድርጋ የልጅ ልጁን ለግርድና አረብ ሃገር የምትልከው ኢትዮጲያ ዛሬም ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህን አጣች/ገደለች/እናታለም ኢትዮጲያ ግን ምን አደረግን!? አንችን ብለን ለቁም ስለሞትን ምን አደረግን!?. ..እኛ እኮ የእሱን ታሪክ እየሰማን አድገን ነው ኢትዮጲያዊ የሆንን።….ይብላኝ ለመጭው ጊዜ።” ሲል ዘመነ ካሴ የዛሬ 4 ዓመት የጻፈው እያስታወስኩ ባሳለፍነው ሳምንት ስለ ዘመነ ካሴ በሕግ ጥላ ሥር መዋሉን ስሰማ  ለጽሁፌ በርዕስ የተጠቀምኩበትን ሀሳብ ማውጠንጠን ጀምርኩ፡፡

“የአማራ ጠላቱ አማራ ነው|፡፡ ” እንዳሉት ታላቁ   ምሁር ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ  ዛሬም ዘመነ ካሴ በመያዝ አሸሸ ገዳሜ የሚሉትን የብአዴን ተላላኪ  የብልጽግና አጎንባሽ ለተመለከተ የምሁሩ አባባል  እውነትነት እንዳለው ማረጋገጥ ሩቅ አያስኬድም፡፡

ስለ ዘመነ ካሴ ምንም ብየ አላውቅም ምክንያት በሚገባ ስለእርሱ መረጃ ስላልነበረኝ ነው።ሰሞኑን ዘመነ ካሴ ባህርዳር ከተማ ውስጥ በፖሊስ መያዙን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከገለፀ በኋላ ስለእርሱ የተለያዩ እርሱን የሚያውቁ ሰዎችን ጠይቂያለው።

ዘመነካሴ ምሁራዊ አቅም ያለው እንደሆነም ተረድቻለሁ።ዘመነ የመጀመሪያ ድግሪውን ከሐረማያ ዩንቨርስቲ ሁለተኛ ድግሪውን ደግሞ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በከፍተኛ ማዕረግ አጠናቅቋል።

ይህን ያህል አካዳሚክ አቅም ያለው ሰው ራሱንና ቤተሰቡን ለመምራት የሚገደው ነገር እንደማይኖር እሙን ነው።ዘመነን ወደ ትግል ሜዳ እንድገባ ያደረገው ወገኑ የአማራ ሕዝብ የደረሰበት መከራ አንገሽግሾት ነው።

ዘመነ እንኳን አልሞተ፤ በወንጀል ተጠርጥሮ መታሰር በእርሱ አልተጀመረም።ዜጎች በወንጀል ይጠረጠራሉ ሆኖም ነፃ የመውጣት ዕድላቸው ክፍ ያለ ነው።

ስለሆነም እንደ ዘመነ ካሴ ዓይነትን ምሁራን መልካም ጎን እንደሌላቸው አድርገው ስም የሚያጠለሹ በአማራ ስም የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ግለሰቦች ለአማራ የሚጠቅመውንና የሚጎዳውን አሰላስለው ቢያስቡ መልካም ነው።

ጫካ ለጫካ እየተርመጠመጠ ንፁሀንን ሲገድል ሲያርድ አታገኘውም ወይም የንፁሀንን ጎጆ እያቃጠለ ሴት ሲደፍር አታየውም በታላቅ ስብዕና የተገታ ማንነት ለአገር የተሰጠ ትልቅ የፍቅር ልብ ባለቤትነትን በዚህ ጀግና ልብ ብቻ ታያለህ። አገሬ ተደፈረች ስትለው ያሰርከኝ የጎዳሀኝ ገዥ መንግስት ነህ እንኳን አላለም ከጎንህ ቆሞ በክፉ ቀንህ እኔ ልቅደም ብሎ የዘመተ ቆራጥ የወንዶች ቁና ነው። “በክፉ ጊዜ እና ወቅት የበቀሉ እንክርዳዶች በደህና ጊዜ ታርሶ በተዘራው እርሻ ላይ ገዘፉ” እንዳለው ነው ፀሀፊው ታሪኩ። ይህን ጀግና ስታስረው የአገርህ ባንዲራ ክብር ከእጅግ እንደወደቀች ታውቃለህ በተለይም ደግሞ ለአገሪቱ ወታደር ዩኒፎርሟን ለለበስ ይህ የሀፍረቶች ሁሉ ሀፍረት ነው ለዛውም ፊት አውራሪ ጀግና የአገር ትንታግ። ለአገር ክብር ለሞራልህ ትልቅ የሰብአዊነት ርህራሄ ሲኖርህ የምታደርገው የጀግና ወታደር ክብር ይሄ ነው። ይሄን ጀግና በማሰር የምታሸማቀው የምታሳፍረው ማንም የለም የአገሪቱን ሙሉ ወታደር እንጅ። ዛሬ ፍም ላይ ጥደህ ሂወቱን ለአገር የምታሰዋው ወታደር ጊዜ መጣ ብለህ ነገ ምን ላይ እንደምትጥለው ጥሩ ማሳያ ነው። ከጅምሩ ጀምሮ እያንዳንዷን እንቅስቃሴ በዚህ ሰው ላይ እከታተል ነበር አንዲት ጥፋት እንኳን አላጠፋም አንዲት የፈለገው ታምር ይመጣታል እንጅ እኔ ልጅ አቤል ለማንም እንደማልዋሽ እንደማላሸረግድ የማያውቅ የለም ስለዚህ ጀግና በከፋው ቀን በዛ ቀውጢ ጊዜ ፊት አውራሪ ሆኖ ሲፋለም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጀግና ሲለው ነበር የብሄር ፖለቲከኞች ህሊና የሚባል ልጓም እንኳን የሌላቸው ከቆይታ በሁዋላ ሌላ አጀንዳ ፈጠሩ የአገሪቱ መሪ ፓርቲ ያለምንም ሀላፊነት የስህተቱ ሰለባ ሆነ ይህን ጀግና መንግስት ከዳው። ዘመነ ካሴ ጀግና ነው ለዛውም ታሪክ በክንዱ የፃፈ ስታሳድዱት እንኳን እንደሌሎቹ ንፁሀን ላይ እጁን ያላነሳ በናንተ ክፋት ንፁሀንን ያልጎዳ ጀግና። እንደሌሎቹ ክብሩን ዝቅ አርጎ ተራነትን ቢመርጥ ኖሮ እንኳን ዘመነ ስንት የጦርነት ልምድ ያለው ጀግና ቀርቶ ዛሬ በየጥሻው አመታት ሙሉ መያዝ አቅቶት ንፁሀንን የሚቀጥፉ ስንት ወንበዴወች ከነሱ መሀል አንዱ ሆኖ እስከወዲያኛው ሳይገኝ ህልም ሆኖ በቀረ ነበር ። ደጋግማችሁ ስትይዙት ስትለቁት ስታፍኑት ስታግቱት ስታንገላቱት ግፋችሁን ያልፈራ የእውነትም የእምነትም ሰው ነው።

ለአገር ክብር የተዋደቀን ማሳደድ ለዛውም አንድ ወንጀል ላይ እንኳን ስሙ የሌለን ማንገላታት የአገሪቱን ክብር ዝቅ ያደርጋል።

ከበርካታ እሱን የሚያውቁ ከፍተኛ መአረግ ላይ ያሉ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮችን የክፍለ ጦር አመራሮችን ለማናገር ሞከርኩ ሁሉም የሰጡኝ መልስ “ዘመነ ካሴ ጀግና ነው በክፉ ቀን ለአገሩ የተፋለመ በሱ ላይ የተደረገውን ወንጀል እናውቃለን” ነው ያሉኝ።

ዘመነ ካሴን አሰራችሁት አንገላታችሁት ምንም አደረጋችሁት የሱ ጀግንነት እናንተ ከማሰራቸው በፊት በቀይ ቀለም የተፃፈ በፊት ስለሆነ አትሰርዙትም ከዚህ በሁዋላም በዘመነ ላይ ምንም ብታደርጉ አይለውጠውም ስለ አገራችሁ ለአገሩ እየተዋደቀ ያለ ከዚህ ጀግና ጋር ለአንድ አገር ህልውና የዘመተ ምን ይላችሁዋል ?

ዘመንን አስረህ ልትፎክር አትችልም ዘመነን አንገላታሁ ብለህ ልትጨፍር አትችልም በታሪክ ሰሪ ብዕር በተፃፈ ምንጣፍ ማጥፊያ ላጲስ የለም። ብዙ ኢትዮጵያውያን ግን ከምርም መንጋ ነው ያልነው ወደን አይደለም ትናንት ለአገሩ ዘመነ ካሴ ሲፋለም የሱን ፎቶ ፕሮፋይል አድርገው የጀግኖች ጀግና ሲሉት የነበሩት ያን ድል ረስተው በተራ የብሄረተኞች ጩኽት ባንዴ ሲለወጡ ይደንቃል። ተለወጣችሁ አልተለወጣችሁ ስለሱ የፖሰታችሁት ፅሁፍ ሁለት አመት እንኳን ሳይሞላው እስካሁን እያየነው ከክህደታችሁ ብዙ ተምረናል። አንዴ ተራራ ገባ ሌላ ጊዜ ገዳም ገባ ደስ ሲላቸው ጫካ ገባ ይላሉ እና የገበሬ ንፁህ ቤት ገብቶ ንፁሀንን እያረደ እየዘረፈ እየገደለ እንደሌሎቹ ቢቀመጥ ነበር ለእናንተ ትክክል? እሱ ጀግና ነው የንፁሀንን ደም ለማፍሰስ አይደለም ደማቸው እንዳይፈስ ነብሱን የሰጠላቸው። መረጃውን አንሰጥም በሚል እንጅ አሁን ጦርነቱ እየተደረገ ያለው በምን ሆነና ጥሻ ለጥሻ ጫካ ለጫካ ተራራ ለተራራ ከተማ ለከተማ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ከዛ ውጭ የትኛውም የሀይፐርሶኒክ ጦርነት ኖሮ ነው ወገኖቼ ዳሩ ጋኖች አለቁና… ነው ነገሩ፡፡

 

307869215 1142681926343574 5381103325803230409 n

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop