ያማራ ሕጻናት ቶሌ እየታረዱ
የብአዴን ጉዶች ቦሌ ሲቀልዱ፣
አማራ ካለፈ ዐይቶ አንዳላየ
ከሞቱት ሕጻናት በምኑ ተለየ?
ያማራ እናቶች ደረት እየመቱ
ደመቀና ግርማ ሻምፓኝ ከፈቱ፡፡
እንዲህ ያለ ውርደት እያዩ እየሰሙ
ኑሬያሉ ከማለት ሞት በስንት ጣሙ?
ባለፈው በወያኔ ዘመን መለስ ዜናዊ የብአዴን አባሎችን ይመለምል የነበረው በስም ብቻ ኣማራ የሆኑትን ወይም ደግሞ እሱ ራሱ አማራዊ ስም የሰጣቸውን፣ የአማራ ጥላቻቸው ከራሱ ከመለስ ዜናዊ በላይ የሆነውን ጉዶች ሥራየ ብሎ በማሾ እየፈለገ ነበር፡፡ ለዚህ ደግሞ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋልዋና ከበዴ ጫኔ ተጠቃሽ ምሳሌወች ናቸው፡፡
ባሁኑ በኦነግ ዘመን ደግሞ ጭራቅ አሕመድ ያስተማሪውን የመለስ ዜናዊን ተግባር ከመለስ ዜናዊ በበለጠ ሁኔታ እየተገበረው ይገኛል፣ ከመምሕሩ ደቀመዝሙሩ እንዲሉ፡፡ ባሁኑ በኦነግ ዘመን ጭራቅ አሕመድ ስልጣን የሚሰጣቸው ደመቀ መኮንንን፣ ተመስገን ጡሩነህን፣ ሰማ ጥሩነህን፣ አበባው ታደሰን፣ ግርማ የሽጥላንና እነሱን የመሳሰሉትን ቆንጆ አማራዊ ስም ቢኖራቸውም የአማራ ጥላቻቸው ግን ከራሱ ከጭራቅ አሕመድ የባሰውን ጉዶች ነው፡፡
መለስ ዜናዊን እንቅልፍ ይነሳው የነበረው የኦሮሞ ብሔርተኝነት ሳይሆን የአማራ ብሔርተኝነት ነበር፡፡ ማናቸውም የኦፒዲኦ አባል የፈለገውን ያህል ኦነጋዊ ቢሆንም መለስ ዜናዊ ግን ኦነጋዊነቱን ዐይቶ እንዳላየ ያልፍለት ነበር፡፡ ለዚህ ደግሞ አፒዲኦ ሲገልጡት ኦነግ ነው በማለት በይፋ መናገሩ በቂ ምስክር ነው፡፡ በሌላ በኩል ግን ማናቸውም የብአዴን አባል የሰናፍጭ ቅንጣት የምታህል አማራዊነት የሚሰማው ሆኖ ሲያገኘው ሳይውል ሳያድር ያስገድለው ነበር፡፡ የብአዴኑን ሙሉዓለምን ያስገደለውም በዚሁ ቋሚ መመርያው መሠረት ነበር፡፡
ጭራቅ አሕመድንም ልክ እንደ ጡት አባቱ እንደ መለስ ዜናዊ እንቅልፍ እየነሳው ያለው የትግሬ ብሔርተኝነት ሳይሆን የአማራ ብሔርተኝነት ነው፡፡ የትግሬ ብሔርተኛው ባይቶና የጠነክረውን ያህል ቢጠነክር፣ ወታደራዊ ክንፉ ሳምሪ ደግሞ እስካፍንጫው ቢታጠቅ ለጭራቅ አሕመድ ግድ ስለማይሰጠው ስማቸውን እንኳን አንስቶ አያውቅም፡፡ በሌላ በኩል ግን በቅጥረኛው በቀለጠ ሞላ አማካኝነት አብንን የኦነግ ቅጥቅጥ ለማድረግ፣ በብአዴናዊ አስመሳይ ፋኖወች አካማኝነት ደግሞ እውነተኛውን ፋኖን ለማጥፋት የማይቆፍረው ዲንጋ የለም፡፡
መለስ ዜናዊ አማራዊነት ስሜት ይሰማቸው የነበሩትን የብአዴን አባሎች እያፈነፈነ በማግኘት፣ ይቺ ባቄላ ካደረች እትቆረጠምም በሚል ስሜት ወዲያውኑ ያስገደላቸው እንደነበረ ሁሉ፣ ጭራቅ አሕመድም እነ ዶክተር አምባቸውንና ጀነራል አሳምነውን የገደላቸው በዚሁ መሠረት ነበር፡፡ መለስ ዜናዊን ቀጥ አድርጎ ይዞት የነበረው ወያኔ ሳይሆን በአዲሱ ለገሰ ይመራ የነበረው ብአዴን የሚባለው የጉዶች ስብስብ እንደነበረ ሁሉ፣ ጭራቅ አሕመድንም ቀጥ አድርጎ የያዘው ኦነግ ሳይሆን በደመቀ መኮንን የሚመራው ይሄው የጉዶች ስብስብ ነው፡፡
ጭራቅ አሕመድ የአማራን ሥጋ በልቶ የማይጠረቃ ኦነጋዊ አውሬ ቢሆንም፣ የአማራን ሥጋ የሚዘነጣጥልባቸው ጥርሶቹ ግን ሙሉ በሙሉ ብአዴኖች ናቸው፡፡ በተለይም ደግሞ የጭራቅ አሕመድ ክራንቻወች (ማለትም ረዝመው ያገጠጡት ሁለቱ የፊት ጥርሶቹ፣ canines) ደመቀ መኮንን እና ተመስገን ጡሩነህ ናቸው፡፡ በመሆናቸውም፣ ጭራቅ አሕመድ የአማራን ሕዝብ መብላት አቅቶት፣ የሰው ሥጋ ጠኔ ናላውን አዙሮት፣ ራሱን ስቶ እንዲወድቅ ብአዴናዊ ጥርሶቹን ማርገፍ የግድ ነው፡፡ ይልቁንም ደግሞ መንጋጋወቹን እነ ግርማ የሽጥላን እና ሰማ ጡሩነህን መንቀል፣ ክራንቻወቹን ደመቀ መኮንን እና ተመስገን ጡሩነህን መመንገል ይዋል ይደር የማይባል ነው፡፡
የየቀበሌው የደመላሽ ፋኖ ዋና ሚና መሆን ያለበት ደግሞ በየራሱ ቀበሌ ላይ የተተከሉትን የጭራቅ አሕመድን ብአዴናዊ ጥርሶች መንቀል፣ መመንገል፣ ማፍለስ ማወላለቅ ነው፡፡ የዘመነ ካሴ አረጋዊ እናት ሙሾ እያወረዱ፣ የደመቀ መኮንን ቤተሰቦች ውስኪ ሊቀዱ አይገባም፡፡ ነውር፣ የነውር ነውር ነው፡፡ ይህን ነውር አይቶ እንዳላየ የሚያልፍ አማራ ደግሞ ከደመቀ ቤተሰቦች በላይ ነውረኛ ነው፡፡
የአማራ ሕዝብ ደመቀ መኮንንን፣ ተመስገን ጡሩነህን፣ ሰማ ጡሩነህን፣ ግርማ የሽጥላን፣ አበባው ታደሰንና የመሳሰሉትን የበላኤ አማራውን የጭራቅ አሕመድን ብአዴናዊ ጥርሶች በማወላለቅ ጭራቅ አሕመድን ጨርቅ ካደረገ፣ ወያኔና ኦነግ እዳቸው ገብስ ነው፡፡
መስፍን አረጋ