ነፃነት እና ህልዉና ዕዉን ለማድረግ ከማንም አንጠብቅ!  

ኢትዮጵያን እንደ አገር ኢትዮጵያዉያንን እንደ ሠዉ ፣ ህዝብ ፣ዜጋ  እና ባለአገር በማይቆጥር ህገ- ኢህአዴግ እሾህ ስር ሆኖ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ሠላም እና አንድነት ይሰፍናል ብለን ማሰባችን ወይም አለመጠርጠር ዛሬም በለቅሶ እና መላልሶ መከራ አዙሪት ዉስጥ ወድቀናል፡፡

ለመሆኑ የትኛዉ የኣለማችን ክፍል ነበር በአንድ አገር ህዝብ መካከከል  ወዳጂ እና ጠላት በማለት  ጨቃኞች ፣ጨካኞች ፣ከኃዴወች እና የናት ጡት ነካሾች የጥላቻ እንክርዳድ መዝራት እና ማባዛት ጀምረዋል ፡፡

ይህም ኢትዮጵያን ከስሯ ለመንቀል ፣ኢትዮጵያዉያንን መግደል ፣ ማፈናቀል ፣ ማግለል እና መጠነ ሠፊ በደል ለማድረስ  በመሳሪያነት በዋነኝነት ህገ-ኢኃዴግ  እና የኢትዮጵያን ጥንታዊ ታላቅነት እና የግዛት አንድነት ለማፍረስ ይቻል ዘንድ ምንም አይነት ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ዕዉነትነት እና ይዘት የማይታይበት የክልል አስተዳደር እንዲቆቋም ሆኗል፡፡

እንግዲህ ኢትዮጵያዉያን ነን የሚል እና ሠባዊነት ያለዉ  ሠባዊ ፍጡርነት የሚሰማዉ ሁሉ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን በተለይም ዓማራ ላይ የተሸረበዉ የጅምላ ጥላቻ፣ ማሳደድ፣ ማግለል እና መግደል አሜኬላ  ህገ- ጥፋት እና ሞት  እና ፍርደ ገምድል የክልል አወቃቀር የአገርን ሉዓላዊነት እና ብዙኃኑ -ዓማራ  ፍላጎት እና መብት ያላካተተ እንደነበር ሳይጀመር  የታወቀ ነበር ፡፡

ይህ ህገ -ኢህአዴግ (ህገ-ፖለቲካ) እና የክልል  አወቃቀር ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉያንን የማግለል ሴራ  በወቅቱ የሽግግር መንግስት ምስረታ ወቅት ኢትዮጵያን ሆነ ኢትዮጵያዉያንን በተለይም ዓማራ የሚዉክል ድርጂት ባለመኖሩ ባለቤት ያገለለ  ክህደት እና ጥፋት ሀ…ሁ… ያኔ ተጀምሮ ዛሬ ላይ ዙሩ ቀጥሏል፡፡

ሆኖም ክቡር ፕ/ር አስራት ወልደየስ  የዚህችን አገር የጥፋት ሴራ እና በኢትዮጵያዉያን  ላይ የተደገሠዉን የጠላት ሴራ አስቀድመዉ በመረዳታቸዉ እና ዕዉነተኛም የጥበብ ሠዉ ስለነበሩ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከፀረ-ኢትዮጵያዉያን ጋር አልስማማም ብለዉ ለአንድያ ነፍሳቸዉ እና ለጠፊዉ ዓለም ጥቅም ሳይበገሩ በኢትዮጵያ ታሪክ እምቢኝ ለአገሬ፣ ለነፃነቴ እና ለማንነቴ ብለዉ የክፉዎችን ዱለታ ረግጠዉ ወጥተዋል ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ህውሃት እያዘናጋን አንዳይሆን! ለህወሃት መዘናጋት በትውልድ ላይ መፍረድ ነው፤ - ገብረ አማኑእል፤

ይህ ብቻ አይደለም አይበገሬዉ የነፃነት እና የማንነት  የንጋት ኮከከብ ዕንቁዉ የጥበብ ቀንድ ፕ/ር አስራት ወልደየስ የጥፋት ስምምነቱን ረግጠዉ የወጡበት ምክነያት ከዓመታት በኋላ ዕዉን ሆኖ ተመለከቱ ፡፡

ይኸዉም ኢትዮጵያ በታሪኳ ሆኖ የማያዉቅ  የኤርትራ ከእናት አገሯ ኢትዮጵያ ያለምን ህዝበ ዉሳኔ እንድትለይ ሆነ ፣ ኢትዮጵያ የራሰሷን የተፈጥሮ ባህር በር  በክህደት እንድታጣ ተደረገ ፣ የዓማራ ህዝብ እና ኢትዮጵያ የሚል ሁሉ አገሬ ድንበሬ የሚለዉን በግፍ እና በጥላቻ እንዲነጠቅ ፤እንዲያጣ ሆነ ፣ ዓማራ በራሱ አገር ፣ በሚኖርበት እና ወልዶ ከብዶ በኖረበት ኢትዮጵያ ግዛት ሁሉ መጣተኛ፣ ችግረኛ ፣ ስደተኛ ….በማለት ማጥላላት፣ ማሳደድ  እና ማስወገድ ፣ መግደል… በስፋት እና በይፋ ሆነ ፡፡

ኢትዮጵያዊነትን ለማደብዘዝ የተለያዩ ዕንቅፋቶች እና ማሳደጃወች ተግባራዊ ሆኑ ከነዚህም የኢትዮጵያን ህዝባዊ ኃይል (ምድር ጦር ፣ አየር ኃይል፣ ባህር ኃይል….) በዓለም የአገራት ምስረታ ታሪክ ሆኖ የማያዉቅ ሁኔታ እንዲፈርስ እና ለዘመናት አገሪቷ እና ህዝቦች የደከሙለት የአገር አለኝታ ጦር ያለምንም ቅድ ሁኔታ በጥላቻ እና ክህደት ተበተነ ፡፡

ይህም የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና የህዝቦች ደህንነት ጥበቃ ዋስትና አከተመለት ፡፡ ህዝባዊ ፤ ኢትዮጵያዊ  ስም እና መልክ ያለዉ ተቋም ፈርሶ የፓርቲ ጦር ( ህዉኃት/ኢህዴግ ጦር) ተመሰረተ ፡፡

ይህ አልበቃ ብሎ ለግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የነበረ የሉዓላዊት ኢትዮጵያ ህዝባዊ ጦር ያለምንም በባዶ ተክዶ አገር ለማፍረስ ሲሰራ የነበር ኃይል ከ15 ዓመት ወደ ኋላ ሂዶ ጥቅማጥቅም ፣ጡረታ……እንዲከፈል ተደርጓል ፤ሆኗል፡፡

ይህ ብቻ አይደለም በተለያየ ምክነያት የህዝብ ተቋማት እና አገልጋዮች እንዲከስሙ እና እንዲወድሙ ተደርጎ የፖለቲካ ጥቅም እና ስም እንዲይዙ ተደርጓል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሚሳናቸው የለም

ይህን በቁም ያዩት ዐስራት የዓማራ ህዝብ በሰበብ አስባብ መገፋት እና ሞት የኢትዮጵያ የዉድቀት እና ጥፋት ዋዜማ መሆኑን አስቀድመዉ የተረዱ ባለብሩህ ፤ቅን ልቡና ስለነበሩ ህዝቡን እና አገሪቷን ለመታደግ ቆርጠዉ ተነሱ ፣አነሳሱ ፣ታገሉ ፡፡

ትግላቸዉም ተቀጣጥሎ የነጻነት እና የህልዉና ፋና ወጊነታቸዉ  ታሪክ  የደመቀ ዘውዱን አፅንቶ ሀምሌ ፭ ቀን ሁለት ሽ ስምንት ደፍቷል፡፡

ከነዚህ የቅርብ ጊዜ የነፃነት እና የዕምቢ ባይነት ጀግኖች የትዉልድ ፈርጦች  የታሪክ ማህደር የምንማረዉ የአንድ ሠዉም ሆነ ማህበረሰብ መብት ፣ነፃነት እና ህልዎት የሚገኘዉ ፣የሚረጋገጠዉ እና ህያዉ የሚሆነዉ በራሱ አንድነት እና ህብረት እንጂ በጠላቶች ምኞት እና ይሁንታነት ዓለመሆኑን አስተምረዉናል ፤ ኖረዉ አሳይተዉናል፡፡

ለዚህም ነዉ የጥፋት እና የሞት መነገድ ስምምነት -ህገ-ኢህዴግ እና የአገሪቷ የቀደመዉ የግዛት አንድነት በሚቃረን የክልል ዉቅር ዉስጥ ሆኖ የኢትዮጵያን አንድነት እና የዜጎችን ሉዓላዊነት እንዲሁም የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት አስኳል  -ዓማራን የማያካትት ሁለ ነገር ባለበት  የኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያዉን እና ዓማራ  ነፃነት እና ህልዉና ማሰብ ቅዠት ሳይሆን በስራ የማይገለጥ ዕምነት እና ኃይማኖት መከተል ነዉ ፡፡

እናም የፀረ-ኢትዮጵያዉያን ወጥመድ( ህገ-ኢህአዴግ) እና ጉድጓድ( የክልል አወቃቀር) አስካለ ሁሉም ነገር በጥፋት እና ሞት ወሬ እየታደሰ (ጥልቅ እና  ብቅ መታደስ ) የሚቀጥል ስለሚሆን የማንነት ፣የነፃነት እና በህይወት የመኖር የህልዉና ተጋድሎ ወጥመዱን ከመበጣጠስ ፤ ጉድጓዱን ከማፍረስ  አስከ ሠባዊ ክብር አስከ ማስመለስ   መሆን አለበት ፡፡

ከጠላት ወዳጂነት ፣ይቅር ባይነት እና አሸናፊነትን እንጂ ነፃነትን እና ህልዉናን እንዲሰጥ የሚጠብቅ ራሱ የወዳጂ ጠላት ወይም የጠላት ወዳጂ  ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አገርን የማያጸና ህገ መንግስት - ገብረ አማኑኤል

“ሠዉ አገር ሲሆን ያለ ሠዉ ኦና ምድር እንጂ አገር አይሆንም ፡፡ ” አንታርቲካ በረዷማ ቦታ እንጂ አገር አይደለም ፡፡

“ ህልዉና ነፃነት በአኃዝ መግለጥ ባርነት እና ሞት የመለማመድ መጥፎ አዝማሚያ ነዉ  ፡፡”

“ነፃነት እና ህልዉና አይለካም ፤ማንም ለክቶ እንዲሰጥ አንጠብቅም ”

አንድነት እና ህብረት የበላይነትን በማስቀረት ዕኩልነትን ለማስፈን  ፤ የኃይል ሚዛንን ለማስጠበቅ ነዉ ፡፡

 

አንድነት ኃይል ነዉ ፤

NEILOSS –Amber

1 Comment

  1. This needs to be inscribed in gold letters.

    “እናም የፀረ-ኢትዮጵያዉያን ወጥመድ( ህገ-ኢህአዴግ) እና ጉድጓድ( የክልል አወቃቀር) አስካለ ሁሉም ነገር በጥፋት እና ሞት ወሬ እየታደሰ (ጥልቅ እና ብቅ መታደስ ) የሚቀጥል ስለሚሆን የማንነት ፣የነፃነት እና በህይወት የመኖር የህልዉና ተጋድሎ ወጥመዱን ከመበጣጠስ ፤ ጉድጓዱን ከማፍረስ አስከ ሠባዊ ክብር አስከ ማስመለስ መሆን አለበት ፡፡”

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share