ለወልቃይት፤ ሐምሌ-05 ምስክር ትሁን!
በሙሉዓለም ገ/መድኀን
የሐበሻዋ ፓሪስ እማማ ጎንደር ሐምሌ 05 ልዩ ቀኗ ነው። ጀግና መውለድ የማያቆም ማህጸን እንዳላት ያስመሰከረችበት አሸናፊነቷን ያጸናችበት ልዩ ቀኗ ነው!
ይህን ተጋድሎ ከታሪክና ከዛሬ ሁነቶች አስተሳስረው ያጤኑ ጉልሃን፣ የጎንደር መነሳት የአማራም የኢትዮጵያም መነሳት ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
ስለሐበሻዊቷ ፓሪስ አንድ ለመንገድ
“Through the pages of their accounts, one can get a glimpse of the splendour that was Gondar. The most exuberant of them all were Ferrent and Gallinier. After pointing out the commercial importance of Gondar and the pride of Gondarines as the FASHION-SETTERS of the empire, they conclude: ‘GONDAR IS INDEED THE PARIS OF ABBYSSINIA.’ “
(Bahiru Zewde 1988, Gondär In the Early Twentieth Century: A Preliminary Investigation of a 1930/31 Census)
ተዛማጅ ትርጉም
“ከትረካዎቻቸው ገጾች ጸዳላማ የነበረችውን ጎንደር በጨረፍታ ማየት ይቻላል። ከእነርሱም መካከል ይልቁን የለመለመው (ትረካ) የ ፌረንት እና ጋሊኒየር ነበር። ጎንደር በንግድ የነበራትን ትልቅ ቦታ እና ጎንደሬዎች ለዐፄው ግዛት የፋሽን መሠረቶች በመኾናቸው የነበራቸውን ኩራት ከጠቆሙ በኋላ፣ “ጎንደር በርግጥም የሐበሻዋ ፓሪስ ነች፣” ሲሉ ይደመድማሉ።”
***
ጎንደር፥ በኢትዮጵያ ሀገረ-መንግስት ውስጥ የገዘፈ ታሪክና ተፅእኖ ያለው አካባቢ ነው:: በአማራ ሕዝብ ላይ የተቃጡ አብዛኛዎቹ የጥፋት ዘመቻዎች ሁሉ የተመከቱት ጎንደር ላይ ነው:: የዛሬዋ ኢትዮጵያም ዳግም ከጎንደር ማህፀን የተወለደች ነች:: የዳግም ውልደቷን አብሳሪም ‘ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ቴዎድሮስ ዘ ኢትዮጵያ’ በሚል ታሪክ መዝግቦታል።
ሌላው ቀርቶ ኢትዮጵያዊነትን የሚያቀነቅኑ አብዛኛዎቹ የአማርኛ ቋንቋ ዘፈኖች የዜማ ምታቸው በይበልጥ ጎንደርኛ ስለመሆኑ ጀሮ ያለው ሁሉ የሚያረጋግጠው ሀቅ ነው:: ታደሠ “ብሔር ብሔረሰቦች” የሚለውን ተወዳጅ ነጠላ ዜማውን የሚደመድመው በጎንደርኛ ምት ነው። ይህ ያለ ምክንያት አልሆነም።
ጎንደር ጎንደር
የአንዲት ኢትዮጵያ ዋልታና ማገር!
ማዕከላዊ መንግስቱ ወደ ሸዋ ከዞረ ወዲያ የጎንደር ተፅእኖ የቀዘቀዘ ቢመስልም “ጎንደር ምን አለ?” የሚለው የመንግስታት ስጋትና ጥያቄ ግን ቀጥሏል:: ጎንደር ሲያምፅ አልጋው ይረበሻል:: ኢትዮጵያ የቆመችው በጎንደር የሀገረ-መንግስት የአስተሳሰብ እርሾ ላይ ነው ብንል ማጋነን አይሆንብንም:: ይህ የታሪክ ‘ሀሁ ነው’ የመናገሻዋን ታሪክ ገለጥ ገለጥ ያደረገ ሁሉ የሚያውቀው እውነታ ነው።
የበጌምድር ሕዝብ ከፋሽስት ጣሊያን ጋር ተናንቋል:: የቱ ተነስቶ የቱ ሊተው? በጠረፍ አካባቢው የነበረውን ፀረ-ፋሽስት ትግል እንኳ ብናይ ለሰማይ ለምድር በከበዱ ጀግኖች የሚመራ ነበር:: በእነ ራስ አሞራው ውብነህ፣ ቢተወደድ አዳነ መኮንን፣ ደጃዝማች እንግዳው ተሰማ፣ ፊታውራሪ ኃይሉ ፋሪስ፣ የቀኛዝማች ዓባይ ወ/ማርያም፣ የቀኛዝማች መስፍን ረዳ የቀኛዝማች ገብሩ ገ/መስቀል የሚመሩት የጠረፍ ቀጠናው ተዋጊዎች ጣሊያንን ተስፋ ያስቆረጡ ነበር:: የታሪካችን ተራኪ አርበኛ ገሪማ ታፈረ “ጎንደር ጠላቱን አሳፈረው” ሲል በገድለ አርበኛ (ጎንደሬ በጋሻው) መጽሐፉ ደጋግሞ ይገልፀዋል።
ፀረ-ወያኔ ትግል ከጠዋቱ የጀረው ቢሆንም፣ በአዲስ የትግል ምዕራፍ 2008 ዓ.ም. የተቀጣጠለው አብዮት እንዲህ ነበር የጀመረው፦
ሰኔ 2/3 ቀን 2008 ዓ.ም.
ዳባት ከተማ ላይ ህዝቡ ሳያውቅ ጀኔረተር ጭነው ሊሄዱ ሲሉ ጀግናው የወልቃይት እናት ወገራ፣ የዳጃዝማች አያሌው ብሩ መቀመጫ ዳባት፣ ሕዝቡ ግልብጥ ብሎ ወጣ:: ጀኔሬተሩን በኃይል ከመኪና አወረደ:: ለመጫን የመጣውን መኪና አወደመ:: በአደባባይ አስፈሪ ቁጣውን ገለፅ:: ቅድመ-ሐምሌ 05 የጎንደርን ሞራል ከፍ ያደረገ ተቃውሞ ነበር::
የመጨረሻው መጀመሪያ፤
ሐምሌ 5/2008 እና ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ..
ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የወልቃይት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነበር:: አሁን ደግሞ Commandor of The Tekeze Guards ነው፡፡ ይህ ሰው የትግሉ ማርሽ ቀያሪ ነው፡፡ ወደ ሐምሌ 5 ቀን 2008 እንመለስ። … እብሪተኛዋ ወያኔ፣ የአማራ ክልል መንግሥት ሳያውቅ የሰለጠኑ ኮማንዶ አፋኞችን በመላክ በሌሊት አፍና ለመውሰድ ሞከረች:: “እጅህን ካልሰጠህ እስከቤተሰብህ እንገልሃለን” ብለው ተኩስ ከፈቱበት:: ጀግናው ባለቤቱና ልጆቹን ረክዞ በመጡበት ቋንቋ አናገራቸው:: የገዳይ ቡድኑን በሩ ላይ አነባበረው:: አንበሳው ግዳይ ጣለ። እነ ሲሳይ ታከለ፣ ጎቤ መልኬ፣ ሻለቃ ደጀኔ፣ ሙሀቤን የመሰሉ… አያሌ ጀግኖች
“አትሙት እኔ አልወድም
ጎንደሬ አይደለም ወይ ከፊት የሚቀድም”
ተብሎ እንደተዜመለት እነዚህ ጀግኖች ከቅርብም ከሩቅም ሲገሰግሱ ደረሱለት::
በተጨማሪ ኃይል እየተጠናከረ የነበረውን አፋኝ ቡድን ዶግ አመድ አደረጉት:: በማግስቱ ኮሎኔል ደመቀ በጎንደር ህዝብና ሺህ ትጥቅ አሳማሪ ግዳይ ጣይ ጀግኖች ታጅቦ ከቤቱ በክብር ወጣ:: ያኔ የሆነው ሁሉ የአማራን ህዝብ አንገት ያቃና ሆነ:: ተጋድሎው ተቀጣጠለ።
አውሬው ላይድን ቆሰለ። ያ ቁስል እያመረቀዘ ከመሀል አገር ለመነቀሉ መንስዔ ሆነ።
ሐምሌ 12 ቀን 2008…
የጎንደር ከተማው ተጋድሎ ወደ ስሜናዊቷ መናገሻ ደባርቅ ተስፋፋ:: ደባርቅና አካባቢው ተንቀጠቀጠ:: ተጋድሎው አድማሱን አሰፋ:: የእምቢተኝነት መልኩም ብረትን ከሰላማዊ ትግል ጋር የቀላቀለ ነበር።
ሐምሌ 24 ቀን 2008 ዓ.ም
በታላቋ የፋሲል ከተማ መናገሻ_ጎንደር ላይ መሬት አርድ የሕዝብ ድምፅ ተሰማ። ይህ የተቃውሞ ሰልፍ የወያኔ የማህበራዊ ሚዲያ ካድሬዎች እነ Daniel Berhane ሳይቀር እጅ የሰጡለት፣ ግዝፈት የነሳ ለጎንደር ታሪክ የሚመጥን የሕዝብ ድምፅ የተሰማበት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ሆኖ ተመዘገበ። ህንፃዎች ላይ በተጠመዱ ስናይፐሮች ስር መቶ ሽዎች ተርመሰመሱ:: ዛሬም ድረስ ተፅዕኗቸው እጅግ የጎሉ የፖለቲካ መልእክቶች ተላለፉ:: ወልቃይት እንደማትረሳ ቃል ተገባላት:: ወያኔ ተረግማ ፍፃሜዋ እንደቀረበ ተነገራት:: ኢትዮጵያ እንደማትፈርስ ታወጀ:: አማራነት ከፍ አለ:: የአማራ ፍትሐዊ ጥያቄዎችና ኢትዮጵያዊነት መሳ ለመሳ ታወጁ:: የህዝቦች ወንድማማችነትና ተቆርቋሪነት በደማቁ ተፅፎ ለአለም ተገለጠ::
የጎንደር ፍላጎት ወያኔና የጭቆና ሥርዓቱ ተሸንፈው፤ የአማራ ክብር በተሟላ ሁኔታ ተጠብቆ ሌሎች ወንድም ህዝቦችም መብታቸው ተከብሮ በነፃነትና በእኩልነት በኢትዮጵያ ሰማይ ስር በአንድነት መኖር መሆኑ ለአለም ተገለጠ::
እንደ ነገሥታቱ ዘመን ከዳር ዳር “ጎንደር ምን አለ?” ተባለ። ኦህዴድ እና ብዓዴን “ኦሮማራ”ን ለማወጅ የወዲያው ገፊ ምክንያታቸው ሐምሌ 24/2008 ነበር።
ሐምሌ 30/2008 ዓ.ም
ጎንደር ከዳር ዳር አሁንም በተቃውሞ መናጧን ቀጥላለች፣ ማማው ደብረታቦር መሪነቱን ተረክቧል። በተከታዮቹ ቀናት ደግሞ ተቃውሞው ንፋስ መውጫ ዘልቆ “በዓይኔ አሳየኝ ጋይት ሲያስወጣ አጋንንት” የተባለለት ተጋድሎ ሊመዘገብ ችሏል።
ሐምሌ 30/2008 ዓ. ም ጎንደር_ደብረታቦር ወያኔን በአደባባይ ከመጋፈጥ ባለፈ፣ የሰው ሕይወት የተገበረበት ዕለት ነበር። በወያኔ ታሪክ ውስጥ በጥቁር መዝገብ የሰፈረው የጉና ጦርነትን ያካሄደው ፅኑ ሕዝብ መገኛ ማማው ደብረታቦር፣ ወልቃይ ወገንና ወሰናችን ወደእናት ግዛታቸው በጌምድር_ጎንደር ይመለስ፣ በአማራ ማንነት ላይ ያነጣጠረው ጥቃት ይቁም ብለው አደባባይ በመውጣት ንፁሃንን ገብረው ሥርዓቱን በማንኮታኮት ሂደት ማማው ደብረታቦር ታሪክ ፃፈ።
በዕለቱ አንድ ወጣት ይህንን ዘመን ተሻጋሪ ንግግር የሰንደቅ ዓላማ መስቀያ ፖል ላይ ሆኖ ጮኾ ተናገረ…”አንድ የአማራ ወጣት ቢፈራ ፀያፍና ነውር ነው” አለ። ሰልፈኛው በጩኸት አደመቀው። ይህ ወጣት ዛሬም በህይወት አለ። ሆኖም ይህንን ሰልፍ ካስተባበሩት ውስጥ ሁለቱ ተሰው። ያ ሰላማዊ ሰልፍም ወደ አመፅ ተቀይሮ ከልዩ ሀይልና ከመከላከያም ጭምር ሞት ተመዘገበ። ያኔ ባህርዳር ላይ የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ የነበረው ፍስሀ ኪዳኑ (ማንጁስ) በድንጋጤ ሂሊኮፍተር አስነስቶ አዳሩን ወደ ደብረዘይት በረረ።
ጎንደር በአንድ በኩል የወያኔን የበላይነት በማውገዝ አገዛዙን ስታንኮታኩት በሌላ በኩል ደግሞ በልጆቿ ሐዘን ተዋጠች። ቢሆንም ግን “ያለደም ሥርየት የለም” በሚለው የትግል ዓላማ እንደፀናች ትግሉን አሻግራ አባይ ማዶ አዘለቀችው።
የኦሮሞ አመፅ ታክቲክ ለውጥ….
በወቅቱ በኦሮሚያ አካባቢ በአንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሲደረግ የነበረው አመፅ በልጆች ትርጉም የለሽ ተደጋጋሚ ሞት የተነሳ ተስፋ ቆርጠው አመፁን ወደ ማቆም በመሄድ ላይ ከነበሩት የኦሮሞ አመፅ መሪዎች አንዱ የሆነው ጃዋር መሃመድ የጎንደሩን ሰልፍና ተጋድሎ ካስተዋለ በኋላ “This is strategic masterpiece” በማለት አድናቆቱን በአደባባይ ገለፆል:: ጃዋር ከዚያ በኋላ የጎንደርን ልምድ እየተከተለ የኦሮሞን አመፅ እንደ አዲስ አቀጣጥሏል:: አሁናዊ ሁኔታው ቢቀየርም ቅሉ
በፀረ-ወያኔ ትግሉ የሁለቱ ሕዝብ አዲሱ ትውልድ የጋራ ትግል ትልቁ እርሾ በዚህ ቀን ነበር እውን የሆነው።
የሽምቅ ተጋድሎ (Insurgency)…
የጎንደሩ የአማራ ተጋድሎ ወደ ባህርዳር ከተማ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፣ አዊና ሰሜን ወሎ ዞኖች አድማሱን አስፋፍቶ የወያኔን የአፈና መዋቅር በታትኖታል::
ይህ ተጋድሎ በከተማ አመፅ ብቻ የተወሰነ አልነበረም:: በጎንደር እነ ዋዋ ጎቤ እነ ሙሃቤን፣ ቃቁ፣ ሞላ፣ አጋየን ይዞ በአርማጭሆ ከፋኝ ሕዝባዊ የጦር ኃይል ተመሰረተ::
አርበኛ መሳፍንት ጦሩን ይዞ በወገራ እንቃሽ፣ አጅሬና ቀሪውን የቋላ ወገራ መሬት አስፍቶ ትግሉን ቀጠል::
አርበኛ አረጋ ጦሩን ይዞ በሊቦ፣ እብናትና በለሳ ዱር ቤቴ አለ::
መቶ አለቃ ደጀኔ መንግስቱ ጦሩን ይዞ በመተማ፣ ሽንፋና ቋራ ትግሉን ቀጠለ:: ሌላው በእያካባቢው ዱር ቤቴን አለ::
የወያኔና የባንዳዎች ሙከራ…
ወያኔ የመከላከያና ደህንነት እዙን ወደ ጎንደር አዘዋወረ:: ጀኔራል ሳሞራ በቦታው ሆኖ ለመምራት ወደ አዘዞ መከላከያ ዕዝ ተመላለሰ:: ልዩ ኮማንዶ ወደ አርማጭሆ፣ ወገራ፣ ቋራና ሊቦ ተላኩ::
ግና፣ በዙዎች ሬሳቸው ገደል ውስጥ ገብቶ የአሞራ እራት ሆነው ሊመለሱ አልቻሉም:: ወያኔ ተደጋጋሚ ዘመቻዎችን አደረገ:: ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፉ በጎንደር ጀግኖች ተለቀሙ:: ወያኔ ማገገም አልቻለም::
…እንደምንም ብለው ዋዋን በባንዳ አስገደሉት:: ጎንደር ህመሟ በረታ! ያም ሆኖ ቁጭቱ ለአርበኞቹ ስንቅ ሆናቸው። በሽምቅ ስልት ግዳይ መጣሉ የዕለት ዜና ሆነ። ግንቦት ሰባት ሳይቀር በዕለት ዜናው ነገደበት! ኢሣት ላይ ከሚናው በላይ ሸለለበት። ይሁን ‘እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል’ እንዲሉ የወዲያው ስኬቱ የጠላት ሁለንተናዊ አቅም መዛሉ ነበር የሚፈለገው፤ ፕሮፖጋንዳም ዋጋ አለው በሚል ጀግኖች ግዳይ ከመጣል፣ ጩልሌዎችም ድሉን በጊዜዊነት እንዲነጥቁ ባላየ ታለፉ። ኦራል ሙሉ ኮማንዶ በቅፅበት የደፈጣ ውጊያ እየረገፈባት የተቸገረችው ወያኔ በቀሉን በእጥፍ አሳደገችው።
የወያኔ በቀል….
ወያኔ ጎንደርን በጦር ማንበርከክ አልቻለችም:: ድሮም ያን ቀጠና መድፈሩ ‘ቆንጆዎቹ’ እስኪወለዱ ድረስ ነበር። ወያኔ በሽምቅ ውጊያ ኪሳራ ሲበዛባት፣ የደካሞችን መንገድ መረጠች:: ሽብርን::
ከ2008 መጨረሻ ጀምሮ ሰላዮችን በእጥፍ አብዝታ አሰማራች:: ብዙ የገበያ አደራሾችንና ንግድ ቤቶች በእሳት አቃጠለች:: በያዝ ለቀቅ ትረዳው የነበረውን የቅማንት ኮሚቴን በሙሉ በጀት አስልጥናና አስታጥቃ ጎንደርን አጋደለች:: በውክልና ደማችን አፈሰሰች:: ያም ሆኖ ጎንደር አልተንበረከከም ይህን መክቶ በክብር አንገቱን ቀና ማድረግ ቻለ::
ጥቅምት 24 ቀን 2013
ከትግሉ ትይዩ ጎንደር አስቀድማ እንደተነበየችው ወያኔ ከማዕከላዊ መንግሥቱ በትረ-ሥልጣኗ ተነቅላ መቀሌ ከከተመች በኋላ በውክልና ጦርነት ወደሥልጣን ለመመለስ ብትሞክርም አልሆን አላት።
ቀድሞ በአገዛዝ ዘመኗ፣ በአማራ መቃብር ላይ የሚያብብ የትግራይ ሪፐብሊክ አልማ ‹ሶፍት› እና ‹ሀርድ› ፓወሩን ተጠቅማ ነበር፡፡ ከትግራይ ሪፐብሊክ በፊት አማራን መቅበር የምንግዜም ግቧ አድርጋ በወሎ በኩል ኮረም፣ አላማጣ፣ ኦፍላ አበርገሌን፤ ጎንደር በኩል ወልቃይት ጠገዴ ጠለምትን ከመውረሯ ባሻገር ተጨማሪ ግዛት የማስፋት፣ ነባሩን ሕዝብ ሲስተማቲካሊ የማጥፋት (መፍጀት፣ ማፅዳትና ማሟሟት) ግብ ይዛ ዓለማቀፍ ወንጀል ፈፅማለች፡፡
ወያኔ ከሸዋ ወደ መቀሌ ከሸሸች በኋላ ደግሞ የጦር ኃይሏን በማደራጀት ተጠምዳ ነበር፡፡ ግራንድ ስትራቴጂ አድርጋ የወሰደችው የትግሬን ጦር ማደራጀት ሲሆን፤ ለዚህ ተግባሯ በመከላከያ ሠራዊትና በፌዴራል ፖሊስ ተቋማት ውስጥ ያሉ የትግሬ ወታደራዊ መኮንኖችን አቅም ተጠቅማለች፡፡
የልዩ ኃይል፣ ሚሊሺ፣ መደበኛ ፖሊስ አደረጃጀቶቿን በማሻሻል በክፍለ ጦር ደረጃ አዋቅራ ነበር፡፡ በዚህ ሳትወሰን የኮማንዶና ልዩ ኦፕሬሽን ሰልጣኞችን በሬጅመንት ደረጃ እስከማደራጀት ደርሳ ነበር፡፡ ቀደም ሲል (በአገዛዝ ዘመኗ) የኢትዮጵያን አቅም ለትግራይ ልዩነት መፍጠሪያ ስትጠቀም የነበረ በመሆኑ ከመከላከያ ሠራዊት ካዝና ካሸሸችው የጦር መሳሪያ ክምችቷ በላይ ከሱዳን፣ ሊቢያና የመን በርካታ የጦር መሳሪያ ግዥ ፈጽማ እንደነበር ዘግይተው የወጡ መረጃዎች ያስረግጣሉ፡፡
ይህ ሁሉ ዝግጁቷ አማራን የማጥፋት ፕሮጀክቷን ወደልዩ ምዕራፍ ለማሳደግ ነበር፡፡ ለዚህ ዓላማዋ ጥቅምት 24 ሰሜን ዕዝን በማጥቃት የጀመረችው ልዩ የጥፋት ምዕራፍ፣ አማራን በስድስት አቅጣጫ በመውጋት ነበር የጀመረችው፡፡
ከእነዚህ ውስጥ አራቱ ግንባሮች በጎንደር በኩል ነበር የተከፈቱት። እነዚሁ ግንባሮች ፦ቅራቅር፣ ሶረቃ፣ አብደራፊ (ምድረ-ገነት)፣ ጠለምት ሲሆኑ፤ አራቱም Grand Front ናቸው። በወያኔ በኩል ጦርነቱ የተጀመረው ቀጥተኛ ወረራ በመክፈት ነበር።
ያ ኹሉ ቅድመ ዝግጅት የተደረገበት የጦርነት ድግስ ከቅራቅር ተራራ አናት ፈቀቅ ማለት አልቻለም። የጎንደር ሚሊሻ፣ የገበሬ ጦርና ፋኖ የአማራ ልዩ ኃይል ክንድ፤ ከጀርባው ለተወጋው የሀገር መከላከያ ሠራዊት አለኝታ ሆኖ ተገኘ። በአራቱም ግንባር ጠላትን እያሳደደ ለቀመው። በሬሳ ክምር የሚራመዱት የመይሳው ልጆች የትግሬ ወራሪ መፈጠሩን እስኪጠላ በደም አበላ አጠቡት።
የወልቃይት አናብስት መውጫ በሮችን፣ አንገት የውጊያ ቦታዎችን ይዘው በጠላት የሬሳ ክምር ተጨማሪ ምሽግ ሰሩ። የአባ ደፋር አገር ወልቃይት ጠገዴ ለወራሪዎቹ ረመጥ ሆነ። ጥቅምት 24 ውጊያው በጀመረ በቅፅበት ውስጥ ነገሮች ተቀያየሩ፤ በብርሃን- በጭለማ ወለቃይት ለጠላት መሸሸጊያ ስንዝር መሬት ነፈገች። ለጠላት ብቸኛው አማራጭ ሽሽት ነበር። በርካታ የጠላት ከጀርባው ተመትቶ ሞተ። በጀግኖች ፊት የፈሪ መጨረሻ ይኼው ነው።
በአንድ ሳምንት ውጊያ ወያኔ ተከዜን ተሻግራ በሁለት አቅጣጫ ፈረጠጠች። ወደትግራይና ወደሱዳን። በዚህ ሽሽቷ የፈሪ ዱላ ማይካድራ ላይ ከ1,600 በላይ ንፁሃንን መጨፍጨፏ ይታወሳል። ይህ ግን ሞትን የማይፈሩ የተከዜ ዘቦችን እንድንፈጥር በቁጭት አነሳሳን እንጅ አንገታችንን አላስደፋንም።
***
እነሆ ዛሬ ወልቃይት ከባርነት ከከፋው የወያኔ አፓርታይዳዋ አገዛዝ ነፃ ወጥታለች። ወያኔ “በአፍሪካ የሽምቅ ውጊያ ታሪክ አቻ አይገኝልም” ስትል እንዳልነበረ ዛሬ ከ26 ጊዜ በላይ የወረራ ሙከራ አድርጋ አንዱም ሳይሳካላት ቀርቷል። ‘የቆጡን አወርድ ብላ…’ እንዲሉ በዚህ ጦርነት >400K ገብራ በካናዳ ስንዴ እየተጠገነች ለዳግም ጦርነት ራሷን እያዘጋጀች ነው። ትሞክረው በቀጣዩ ፍልሚያ ከምትነዳው መንጋ ጋር ወደ permanent minority እንቀይራታለን።
ዛሬ ወልቃይት ነፃ ነው። ነፃነት በነፃ አይገኝምና ጀግኖችን ገብረን ነው ተከዜን ያስከበርነው።
አንዳንድ የፖለቲካ ድሃዎች በበጀት የሚቀየር ማንነት ያለ መስሏቸው ብዙ ሲሉ እንሰማቸዋለን። በጌምድር ወልቃይት ይሰጣል እንጅ አይለምንም።
አገራችን ጎንደር ወንዛችን ተከዜ
ምንይመጣብናል እምቢ ያል ጊዜ
በለው!
በነገራችን ላይ የወልቃት ሕዝብ ከፍ ሲል ኢትዮጵያዊ ዝቅ ሲል በጌምድሬ ስለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በአደባባይ የመሰከሩት እውነታ ነው።
ወደትፋቱ የሚመለስ ውሻ ብቻ ነው።
የወልቃይት ጉዳይ በደም የተዘጋ ፋይል ነው። ይቅርና መላ አማራ፣ ጎንደር ብቻ በትንሹ ሦስት ሚሊየን የታጠቀ ኃይል አለ። ይህ ብቻ አይደለም ለወልቃይት የእናቱ ሆድ ውስጥ ካለ ፅንስ በስተቀር፣ ሁሉም ለመፋለም ዝግጁ ነው።
ማንነት የራስ ምርጫ እንጅ በሌሎች ይሁንታ የሚሰጥ አይደለም፡፡ ደማችን እንደተከዜ ወንዝ ይፈሳል እንጂ የሰማዕታት አደራ አይታጠፍም! ለበጀት አሳልፈን የምንሰጠው ማንነት የለም!
ለወልቃይት፤ ሐምሌ 05 ምስክር ትሁን!!
ለሐምሌ 05 በጀግንነት እንኳን አደረሰን! አደረሳችሁ!!