በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ በመንግሥት ኃይሎች መካከል ግጭቶች መፈጠራቸውን፤ ሕይወት መጥፋቱን ተገለፀ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ከትናንት ጀምሮ በታጣቂዎች እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ግጭቶች መፈጠራቸውን፤ ሕይወት መጥፋቱን እና ንብረት መውደሙን የአካባቢው ነዋሪ ለዶይቼ ቬሌ ማምሻውን ተናገሩ። ታጣቂዎቹ በወረዳው ሞላሌ ወደምትባል መንደር ገብተው መውጣታቸውንና አሁን ወደ ሌሎች ቀበሌዎች መሸሻቸውንም እኚሁ የዓይን እማኝ አመልክተዋል። ግጭቱ የተከሰተው ከአጣዬ ከተማ በቅርብ ርቀት ባሉ ቀበሌዎች ነው። የአካባበው ነዋሪዎች ጥቃቱን የከፈተው መንግሥት «ኦነግ ሸኔ» የሚለው ታጣቂ ኃይል ነው ይላሉ። የባሕር ዳር ዘጋቢያችን ዓለምነው መኮንን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ ወረዳው አስተዳዳሪም ሆነ ወደ ዞኑ ፀጥታ ኃላፊ ስልክ ቢደውልም እንዳልተሳካለት አመልክቷል።

DW


#ሰበር —- አጣዬ
/
በመንግስት ኃይሎች የሚደገፈው ኦነግ/ሸኔ በአጣዬ እና አካባቢዋ ከፍተኛ ውድመትና ግድያ ዛሬ ፈፅሟል። አራት ቀበሌወች ወድመዋል።
ኦነግ/ሸኔ ከጠዋት ጀምሮ በከፈተው ተኩስ፣ በቁጥር ማወቅ ያልተቻለ በርካታ አማራዎች መገደላቸውንና መቁሰላቸውን ከቦታው ምንጮች አድርሰውናል።
——ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ
/
ከዚህ በታች ያለው ደግሞ፣ የአማራ ሚዲያ ማዕከል ከቦታው ያደረሰው ዝርዝር ዘገባ ነው።
(© አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ)
በኤፍራታ እና ግድም ወረዳ አጣዬ ዙሪያ ከኦሮሚያ ልዩ ዞን የመንግስት አካላት ድጋፍ ይደረግላቸዋል የተባሉ የኦነግ እና የትሕነግ አሸባሪ ቡድን አባላት በሁለት ቀበሌዎች ላይ ወረራ በመፈጸም በርካታ አማራዎችን በመግደል ከ4 በላይ መንደሮችን አቃጥለዋል፤ ወረራቸውን አጠናክረው ቀጥለውበታል ተብሏል።
በኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን በበጤ ፈጫ ቀበሌ ብቻ 38 የሚሆኑ የትሕነግ የሽብር ቡድን አባላት ጽንፈኛ እና ተስፋፊ ኦነጋዊያንን እያሰለጠኑ ነው በሚል መረጃው ከዞን እስከ ክልል የደረሰ ቢሆንም ጀሮ ሰጥቶ ያዳመጠው እንደሌለ ከጥቃት የተረፉት ይናገራሉ።
“በአስቸኳይ ድረሱልን!” በሚል ጥሪ እያቀረቡ ያሉ ነዋሪዎች እንደገለጹት የተቀናጀ እና የቡድን መሳሪያ የታጠቀ ወራሪ ኃይል ሀምሌ 3/2014 ለመጨፍጨፍ የያዘውን እቅድ ለማስቀጠል በመጀመሪያ በአርሶ አምባ ማኛ ቀበሌ በገበሬዎች አዝመራ ላይ ከብቶችን በመልቀቅ ማሳቸውን አስበልቷል።
ከብቶችን ለማባረር ሲሯሯጡ በነበሩ ገበሬዎች ላይ ጦርነቱን በማስጀመር በዙሪያው ለወረራ አዘጋጅቶት ሲያሰለጥነው የከረመውን የኦነግ እና የትሕነግ ኃይል ከበጤ በኩል እያመላለሰ በማስገባት ሀምሌ 3/2014 ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ ከፍተኛ ተኩስ ከፍቶ ውሎ አድሯል።
በዚህም አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ያነጋገራቸው የአርሶ አምባ ማኛ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ማሞ ማስረሻ እንዳረጋገጡት የተቀናጀው እና መንግስታዊ ድጋፍ ያለው የአካባቢው አርሶ አደሮችን በማካተት ወራሪው ቡድን ዋጌና እና በርሃ የተባሉ ሁለት ጎጦችን በማቃጠል ተቆጣጥሯል።
እስካሁን ባለው መረጃ በአርሶ አምባ ማኛ ቀበሌ ብቻ 7 ሰው ተገድሏል፤ 9 ሰዎች ቆስለዋል፤ ከ150 በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ ከ176 በላይ ገበሬዎችን የቀንድ ከብቶች እና የጋማ ከብቶችን በቀላል ግምት ከ10 ሚሊዮን በላይ ንብረት ተዘርፏል።
በስናይፐር እና በብሬን የጀመሩት ግልጽ የወረራ ጦርነቱ ቀጥሏል የሚሉት አቶ ማሞ ሀምሌ 4/2014 ከጠዋቱ ጀምሮ ከአርሶ አምባ ማኛ ቀበሌ በተጨማሪ በመንተኬ ሸረፋ ቀበሌ ላይም ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ ሙሉቀን ሲወሩ እና ሲጨፈጭፉ ውለዋል።
በቀጠለው ግልጽ ወረራ እስካሁን ከተቃጠሉ መንደሮች መካከል:_
1) ከአርሶ አምባ ማኛ ቀበሌ:_
ሀ) ዋጌና እና
ለ) በርሃ የተባሉት ሰፈሮች እንዲሁም
2) ከመንተኬ ሸረፋ ቀበሌም:_
ሀ) ስረጌ፣
ለ) መዲና እና
ሌሎች መንደሮች ይገኙበታል።
በመንተኬ ሸረፋ ቀበሌ ጂሌ አምባ፣ሼህ ኡስማን እና ጃለሌ በሚባሉ መንደሮችም ቃጠሎ እንዳለ
ተነግሯል።
የመንተኬ ሸረፋ ቀበሌ ዋና ከተማን ብርቂቶን ለመቆጣጠር በቅርብ ርቀት ያሉትን ስረጌ እና መዲናን አቃጥለው እየቀጠሉ ይገኛሉ ተብሏል።
ሀምሌ 4/2014 ከረፋዱ 4 ሰዓት ላይ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ቀይ ባንዴራ ይዘው ከፌደራል ለማረጋጋት ነው የመጣን በሚል በመኪና የገባው ተጨማሪ ኃይል ነዋሪዎችና ልዩ ኃይሉን በማዘናጋት ነው ጭፍጨፋውን የፈጸመው።
ሀምሌ 3/2014 ምሽት ገብቶ ከነበረው የአማራ ልዩ ኃይልም በርካቶች መገደላቸውን የአሚማ ምንጮች እየተናገሩ ነው።
አንድ የዐይን እማኝ ሁለት ልዩ ኃይሎች ተመተው ሲወድቁ እና መሳሪያቸውን ገፈው ሲወስዱባቸው ተመልክቻለሁ ብለዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞንም ሆነ የአማራ ክልል መንግስት በከሚሴ እና በአካባቢው ማን የት ላይ እንደሚሰለጥን፣ የያዘውን ትጥቅ ጭምር እያወቀ በዝምታ ከመመልከቱም በላይ ለሁለት ቀናት ያህል ግልጽ ወረራ እና ጦርነት ሲከፈትበት ተጨማሪ ኃይል ለማስገባት አለመድፈሩ በእጅጉ እንዳሳዘናቸውና ከነገሩ እጁ እንዳለበት ያመለክታል ብለዋል።
ዘገባው የአማራ ሚዲያ ሴንተር ነው።


# የቴዲ አፍሮ አድናቂዎች ደም እንዳይለግሱ ተከለከሉ!!
/
‘ወደ ፍቅር’ የተሰኘው የክብር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አድናቂዎች ማህበር በብሔራዊ ደም ባንክ በኩል ደም እንዳይለግስ ተከልክሏል።
“ሺህ ሆነን የሺህዎችን ህይዎት እንታደግ” በሚል መርህ ትናንት፣ እሁድ ፣ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ.ም. ሊደረግ የታሰበው የደም ልገሳ የተከለከለው ‘ከበላይ አካል በመጣ ትዕዛዝ ነው’ መባሉን ማህበሩ አስታውቋል።
“ከየትኛውም ነገድ እና የፖለቲካ እስቤ ነፃ መሆን ከሚጠበቅባቸው እና የሰብዓዊነት ሥራ ብቻ ይሰራባቸዋል ተብለው ከሚታሰቡት አንዱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ደም ባንክ ሆኖ ሳለ፣ እንዲህ ዓይነት ግዙፍ ተቋም ላይ ይህን ዓይነት የፖለቲከኞች ፍላጎት ማስፈፀሚያ ሆኖ መገኘቱ ቅር የሚያሰኝ እና የሰብዓዊ ስራዎች ላይ ለተሰማሩትም እንቅፋት መሆን እጅግ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን። ለወደፊትም እንዲህ ዓይነት ተግባሮች ተቋሙ ከተቋቋመበትም ከቆመለትም ዓላማ እና እሳቤ ውጪ ያፈነገጠ በመሆኑ፣ በቶሎ ሊታረም እና ሊደገምም የማይገባው ነው ብለን በፅኑ እናምናለን” ብሏል ወይ ፍቅር ማህበር።
ለደም ልገሳው ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱንም ገልጿል።
/

ተጨማሪ ያንብቡ:  “የፕሬዝደንት ትረምፕ ጉዳይ መሄድ ያለበት ወደ ኖቤል ሽልማት ኮሚቴ ነው" ጠ/ሚር አብይ አህመድ

Balderas ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ 


#ሰበር # በአጣዬ ኦነግ/ሸኔ ከፍተኛ ተኩስ ከፈተ!!
ሰኞ፣ ሐምሌ 4 ፣2014 ዓ.ም.
/
ኦነግ/ሸኔ፣በሰሜን ሸዋ፣ አጣዬ ከተማ፣ ልዩ ቦታዋ በጤ በምትባል አካባቢ፣ ዛሬ ጠዋት ጀምሮ ከፍተኛ የተኩስ ድብደባ እያደረገ መሆኑን ተሰማ።
በአሁኑ ሰዓት በጤ በምትባለው አካባቢ የአማራ ልዩ ኃይል ከኦነግ/ሸኒ ጋር የተኩስ ልወውጥ እያደረገ ይገኛል።በተኩስ ልውውጡም ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች መቁሰላቸውን ምንጮች ከቦታው መረጃ አድርሰውናል።
በአሁኑ ሰዓት ኦነግ/ሸኔ ከፍተኛ የሆነ ኃይል በመያዝ ወደ አጣዬ እያመራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።አነግ/ሽኔ በዐማራ ላይ ጄኖሳይድ እየፈፀመ የሚገኝ አሸባሪ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል።
ተጨማሪ መረጃ እናደርሳለን።
/

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share