2 የአዳነች አበቤ ካቢኔ አባላት በኮንደሚኒየም እጣ ማጭበርበር ተጠርጥረው ታሰሩ

ሁለት የአዳነች አበቤ የካቢኔ አባላት፣ አቶ ሙሉቀን እና የቤቶች ልማት ቢሮ ወ/ሮ ያስሚን፣ ከኮንዶሚኒየም እጣ ጋር በተያያዘ ለማጭበርበር ሞክረዋል ተብለው ትላንት ማታ ታስረዋል።
እንደሚታወቀው፣ ይህ የባልደራስ የፌስቡክ ገፅ፣ እጣው ከወጣ ቦኃላ ውጤቱ እንዳይነገር ከተደረገበት ግዜ አንስቶ ቀዳሚውን ተቃውሞ ከማንሳቱም ባሻገር፣ ጥቆማ እየተቀበለ ሸፍጥ እየተሰራ መሆኑን ቀድሞ አጋልጧል። በዚህ እንቅስቃሴውም፣”ኦሮሞ ጠል ነው” ተብሎ ተተቸቷል።
ይህ ገፅ ቀደም ብሎ ባወጣው ዘገባ፣ “የኦሕዴድ ካድሬዎች በልዩ ሁኔታ ኮንዶሚኒየም እንዲሰጣቸው በተቀመጠው አሰራር ፈፅሞ እንዳልረኩ ታውቋል። በግልፅ ይደረጋል የተባለው የባለ እድለኞች እጣ አወጣጥ፣ ከመጋረጃ ጀርባ አሁንም በተረኞች ተጠልፎ ውዝግብ እና ቅሬታ እያስነሳ ይገኛል። ማሽኑ ያወጣው ዕጣ ለሕዝብ ይፋ ከመሆኑ በፊት በሰዎች ሳንሱር እየተደረገ ይገኛል” ብሎ ነበር።
በዚህ ሂደት ሁለት ሰዎች አሁን ለእስር የተዳረጉ ቢሆንም፣ በከንቲባዋ አቀናባሪነት የሚመራው ዋነኛው የኦህዴድ/ ብልፅግና የተረኞች ቡድን ገና ለህግ አልቀረበም። ከሸፍጡ በስተጀርባ ያለው ዋናው ይህ ቡድን ነው።
በዚህ ቡድን ቁጥጥር ስር ያለው የአዲስ አበባ አሰተዳደር ትላንት ምሽት ተገዶ ባወጣው መግለጫ፣ “ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው፣ የኦዲት ሥራ ስንጀምር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነቶች ተግኝተዋል፡፡
በመሆኑም፣ በእስካሁኑ የማጠራት ስራ ላልቆጠቡ ሰዎች እጣ መውጣትን ጨምሮ፣ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች ታይተዋል፡፡ በጉዳዩ የተጠረጠሩ ባለሙያዎች እና አመራር በቁጥጥር ሥር ሆነው ምርመራ እየተደረገ ይገኛል፡” ብሏል።
ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁት ይህን ዜና ከሰሙ ቦኃላ በሰጡት አስተያየት፣ ከንቲባዋስ? ብለው ጠይቀዋል።
ቀጣይ ዘገባዎችን ይዘን እንመለሳለን።
ዘገባው—-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ
ተጨማሪ ያንብቡ:  የአዲስ አበባ ክልልነት ድምጽ ተሰማ፣ የአማራ ብልጽግና የዛሬው ውሎ፣ ከሸኔ ጋር በከባድ መሳሪያ ውጊያ ተጀመረ፣ የፈረሱት መስጊዶች 13 ደረሰ

1 Comment

  1. የወ/ሮ አዳነች አቤቤ የ50ሚሊዮን ዶላር ወድ አካውንታቸው የገባው በኦሮምያ ስብሰባ የተገመገሙበት ጉዳይ ከመን ደረሰ?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share