1443ኛው የኢድ አል አድሀ ዐረፋ በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው – ኢድ ሙባረክ! ሰላም ፣ ፍቅር ፣ አንድነት!

1443ኛው የኢድ አል አድሀ ዐረፋ በዓል በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በልዮ ልዮ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች እየተከበረ ነው።
በድሬዳዋ አየር መንገድ አካባቢ በሚገኘው የኢድ መስገጃ ሜዳ እየተከበረ በሚገኘው የአረፋ በአል ላይ በብዙ ሺ የሚገመቱ የገጠርና የከተማ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተካፋይ ሆነዋል ።
በበአሉ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ ወርሰሜ እና የካቢኔ አባላት፣ የየመስጅዱ ኢማሞች፣ኡላማዎች፣ሼኾች ተሳታፊ ሆነዋል።
የድሬደዋ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ መሐመድ አብደላ በራርቲ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በአሉን የተቸገሩትን በመርዳት ፣ የተራቆቱ እና ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን በመርዳት እንዲሁም የታመሙትን በመጠየቅ ማክበር ይገባል ብለዋል ።
ይበልጥኑ ህዝበ መስሊሙ አንድነቱን በመጠበቅ በአገር ዘላቂ ሰላም እና ልማት ላይ እያበረከተ የሚገኘውን አስተዋጽኦ ማጠናከር እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
በስግደት ስነ ስርአት ላይ የተሳተፉት የድሬደዋ አላማዎች ምክር ቤት ተወካይ እና በከተማው ነዋሪ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅ የሆኑት ሼኽ አሚን ኢብሮ የአገሪቱን ሰላም ዕድገት መጠበቅ እና ማሳደግ የመላው የአገሪቱ ሙስሊሞች ግዴታ እና ኃላፊነት መሆኑን አሳስበዋል ።
ህዝበ ሙስሊሙ አንድነቱን አፅንቶ ሊከፋፍሉት ከሚፈልጉ አካላት ራሱን በመጠበቅ የአገር ዘላቂ ሰላም መጠበቅ አለበት ብለዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ ወርሰሜ ለመላው የአገሪቱ የሙስሊም ማህበረሰብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለአገር ሰላም ፣ ልማት እና ዕድገት እያበረከተ የሚገኘው ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት እየጨመረ መምጣቱን ገልፀዋል ።
ይህን ተሳትፎ ይበልጥ በማሳደግ የፀረ ሰላም እና የፀረ ልማት አካትን እና ሽብርተኞች በመከላከል የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ በስኬት እንዲጠናቀቅ ርብርባቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል ።
በተመሳሳይም 1443ኛው ዒድ አል-አድሐ /ዐረፋ/ በዓል በጂንካ ከተማ እየተከበረ ነው።
በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠውና ህዝበ ሙስሊሙ በአንድነት ለፈጣሪ ፀሎት የሚያደርሱበት 1443ኛው ዓመተ-ሒጅራ የዒድ አል-አድሐ /ዐረፋ/ በዓል በጂንካ ከተማ የቀድሞው አየር ማረፊያ እየተከበረ ነው።
ኢዜአ
ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የተሳተፉበት ‘ኤችአር 6600’ ረቂቅ ሕግን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

2 Comments

  1. ይገርማል ሃጅ ሙፍቲ ከአማራው ክልል ስለሆኑ እነ አህመዲን ጀበል ገዝግዘው ጣሏቸው የኦሩሙማም አስተዳደር እገዛውን አደረገላቸው ማለት ነው? ሃይማኖትም ጎሳ ሆነ ማለት ነው? አህመዲን ጀበልን ኡለማ አድርጎ የአባይ ግድብን ማፍረስ ነው አሁን ነገሩ ግብጽ እንደምትፈልገው እየሄደ ነው፡፡ ደህና መሪ ቢኖር አህመዲን ጀበል በተለያየ ስም ሳያዞረው ጅማና አዲስ አበባ ያለውን ሃብቱን ከየት አመጣኸው ብሎ መጠየቅ በተገባ ነበር፡፡ ማን ይጠይቀው የቄሮ መሪ ነው እነ ሽመልስ ቢሮ ያለ ቀጠሮ የሚገባ የሃይማኖት ክንፍ ጓዳቸው ነው፡፡ እስቲ ይሁና ሃጅ ሙፍቲን የመሰሉ የረጉ አባት አባርሮ አህመዲን ጀበልን በተዘዋዋሪ ቦታው ላይ ማስቀመጥ፡፡ ለጊዜው የሰመረ ይመስላል ግን አይደለም፡፡

  2. ሴቶቹ የኢትዮጵያን ባንድራ ለብሰው እንዴት ይምራሉ ዘር ይውጣላችሁ እነ አቡበከር፤አቡሃይደር እናንተ አረብ እንጅ ኢትዮጵያዊ አይደላችሁም ሲሏችሁ ወግድ ብላችሁ እንዲህ ደምቃችሁ መምጣታችሁ ጥሩ አድርጋችኋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share