አዲስ አበባ ያለው የኦነግ ቢሮ በኦነግ ሸኔ ላይ እየተወሰደ ነው ያለው ወታደራዊ እርምጃ እንዲቆም ጠየቀ

July 3, 2022

OLFየአማራ እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንቶች በቅርቡ የኦሮሞ ነጻነት ጦር የተባለውን ታጣቂ ቡድን “ለማጥፋት” ይወሰዳል ያሉት እርምጃ እንዲቆም የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጠየቀ። ኦነግ ባወጣው መግለጫ ግጭቱ በሰላም እንዲፈታ ጥሪ አቅርቧል።

የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል መሪዎች የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ ሹማምንት በተገኙበት በባሕር ዳር ከተማ ባለፈው ሰኔ 21 ቀን 2014 በሰጡት መግለጫ በታጣቂ ቡድኑ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀው ነበር። ባለሥልጣናቱ መግለጫውን የሰጡት ሰኔ 11 ቀን 2014 በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ አሰቃቂ ጥቃት ተፈጽሞ በርካታ ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ነው።

የኦሮሞ ነጻነት ጦር በኦሮሚያ ክልል ደምቢዶሎ እና ጊምቢ ከተሞች እንዲሁም በጋምቤላ ጥቃቶች ፈጽሟል።በጥቃቶቹ በበርካታ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች፣ የጸጥታ አስከባሪዎች እና የአማጺ ቡድኑ አባላት ተገድለዋል። ባለሥልጣናቱ ከሰጡት መግለጫ በኋላ ኦነግ እንደሚለው በኃይል የታጠቁ ወታደሮች የጫነ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቅፍለት ከአማራ ክልል በኩል በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል ገብቷል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ባወጣው መግለጫ ግን ቀውሱ በኃይል ይፈታል ብሎ እንደማያምን አስጠንቅቋል። “ለሚፈጠረው ተጨማሪ የደም መፋሰስ ተጠያቂ በመሪዎቹ ትከሻ ላይ እንደሚወድቅ” የገለጸው ኦነግ ሌሎች ክልሎች እጃቸውን እንዳያስገቡ ጠይቋል።

ምንሊክ ሳልሳዊ

2 Comments

  1. ይሄ ነው የአብይ ሹመኛ ከምንም በላይ ታምኖ ሚኒስቴር የተደረገው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ይህ ሰው ይህን አስተያየት ከመስጠቱ በፊት አስቀድሞ ስራውን መልቀቅ ነበረበት የሆነ ሁኖ አብይም ኦነግ ሸኔ ስለሆን ችግር የለውም፡፡ ቀጥሎ አዳነች አቤቤ፤ዳውድ ኢብሳ፤ሺመልስ አዱኛ፤ታየ ደንዳ፤ጁዋር መሃመድ፤ታከለ ኡማ ኦነጋችንን አትንኩብን ይሉናል መጠበቅ ነው፡፡ ተወልደ ገ/ማርያም የትግሬዎችን ሰልፍ ሲያስተባብር አየሁት ለበል?

  2. እንዲህ ነች ፓለቲካ! በመንግስት ስልጣን ላይ ሆኖ ዘረኝነትን ማጋጋል። ሲጀመር ያለፉት 50 ዓመታት የኢትዪጵያ ፓለቲካ ተገን ያረገው በአማራ ጥላቻ ላይ ነው። እንዲህም ብሎም ፓለቲከኝነት የለም። ሻቢያ አናፍሶት ወያኔ ንፋስ እንደ መታው ድቄት በየቦታው የበተነው ይህ የአማራ የጥላቻ ፓለቲካ ዛሬ በኦነግ ባቀጣጠጠለው ተንኮልና ሴራ አማራውን እየመረጠ በማውደም ላይ ይገኛል። በሰላሙ ጥሪ ሃገር የገቡት የታጠቁም ሆነ ትጥቅ ያልነበራቸው ተቃራኒ ሃይሎች አሁንም በበጎች መካከል ተኩላ ሆነው አፍራሽና ከፋፋይ ሥራ እየሰሩ እንደሆነ ተግባራቸውና ቃላቸው ያመለክታል።
    ኦነግ ቢሮ ውስጥ አዲስ አበባ ተቀምጦ ኡኡታ ማሰማቱ በኦሮሞ ደም አፍሳሾች የተገደሉትን አማሮች ከቁጥር ያላስገባ ለራሱ ሲቆርስ የማያሳንስ ወልጋዳ ፓለቲካ ነው። እንዲህ አይነቱ መርጦ ማልቀስ ነው ሃገሪቱን ዛሬ ላለችበት መተላለቅ የዳረጋት። የማንም ብሄር ተወካይና እንባ ጠባቂ ነኝ የሚሉ ሁሉ ሰውን ሁሉ በሰውኛ እይታ ብቻ ማየት እስካልቻሉ ድረስ በጎጥና በክልል ፓለቲካ ዋይታ ስናሰማ ዓለም ሁሉ ጥሎን ይጓዛል። ያው እንደ ተለመደው ተራብን ተጠማን ድረሱልን እንላለን የተከመረ የእህል ክምር ራሳችን እያቃጠልና አርሰው የሚያበሉን ገበሬዎችን በዘር ፓለቲካ በመጨፍጨፍ። ወያኔ መቀሌ ላይ ሆኖ መሬት ተወስዶብኝ፤ አማራ ከቦኛል፤ ኤርትራ ወራኛለች፤ የዶ/ር አብይ መንግስት ይህን ያን ሴራ አረገብኝ ይላል። በሌላው ላይ የሚያደርገው ወያኒያዊ ሴራ ግን ለራሱ አይታየውም። እየገደሉ፤ ሞተብኝ፤ እየዘረፉ፤ ተዘረፍኩ፤ ሴቶችን እየደፈሩ ተደፈርኩ፤ ኸረ ስንቱ አታድርስ ነው። የውስልትና ፓለቲካ መቋጫ የለውም። ግራም ነፈሰ ቀኝ ይህ የኦሮሞ እንባ ጠባቂ ጠባብ ብሄርተኛም ሆነ ሌሎችን ብሄሮች እንወክላለን የሚሉ ሙታኖች እይታቸው ሃገራዊና አህጉራዊ አልፎ ተርፎም አለም አቀፋዊነትን እስካልተላበሰ ድረስ የራሳቸውን ትንፋሽ አዙረው ሲተነፍሱ ራሳቸውንም ሆነ እናስብለታለን የሚሉትንም ህዝብ እንዳታለሉ ዝንተ ዓለም እንደሚያንቀላፉ እውን ነው። ይህ ደግሞ በእጅጉ ያሳዝናል። ክፉ እንደሸረቡ አፈር መግባት። ሌላው ዓለም በሰላም እንደሚኖረው ሁሉ እኛ በህብረትና በመከባበር ለመኖር እንታገል። የኦሮሞ እንባና ደም የሁሉም፤ የትግራይ እናቶች ሰቆቃና ጭኽት የሃገር ሁሉ ሰው የአማራው ደም መፍሰስ የሁላችንም ይሁን። ያኔ ብቻ ሰው ሆነን ስለ ሰው እናስባለን። የተናጠሉ እንባ የአዞ እንባ ነው። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

291897445 619922073032385 8076187310552108346 n
Previous Story

በሸዋሮቢት በንፁሃን ላይ የመንግሥት ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ የተሰው ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ ነው

Bnalf Kuku
Next Story

“የብሄር ግጭት ተነሳ የሚባለው እርባና ቢስ ወሬ ነው። ከብልፅግና የሚጠበቀው በፅናት በመቆም ወደፊት መግፋት ብቻ ነው” – አቶ ብናልፍ አንዱአለም

Latest from Blog

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት

የኢካን ዓላማ በኔዘርላንድ የሚኖረውን ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና ኢትዮጵያውያንን ኮምዩኒቲይ የማሰባሰብ ሳይሆን የመከፋፋልና የማዳከም ተልኮን ያነገበ ነው።

አገር ! ለየአንድ ሠው ቋንቋው፣ ልማዱ፣ ባሕሉ፣ እምነቱ፣ አስተሳሰቡ፣ ወጉና በአጠቃላይ እሱነቱና ማንነቱ የሚከበርበት ብቸኛ ሥፍራ ነው። ኢትዮጵያውያንም በስደት በሚኖሩባቸው አገራት ሁሉ እነኝህን በስደት ያጧቸውን የግልና የጋራ ማንነቶቻቸውን በአንድ ላይ ሆነው ለመዘከር

ፋኖ ምሽጉን ደረመሰው ድል ተሰማ | ” ስልጣን እለቃለሁ ” ፕረዚዳንቷ | ህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ | “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ

-966+9-የኦህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ – ስልኩ ተጠለፈ “እኛ የምን’ዘጋጀው ለፋኖ ሳይሆን ለኤር-ትራ ነው” አበባው|”በጊዜ ቦታ አዘጋጁልኝ” አረጋ

አንድ በኢኮኖሚና በሌሎች ነገሮች ወደ ኋላ የቀረች አገር አንድን ኃያል መንግስት በመተማመንና ጥገኛ በመሆን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ማምጣትና የተሟላ ነፃነትን መቀዳጀት ትችላለች ወይ?

ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ሰኔ 4፣ 2016 (ሰኔ 11፣ 2024)   በዚህ አርዕስት ላይ እንድጽፍ የገፋፋኝ ዋናው ምክንያት ሰሞኑኑ ዶ/ር ዮናስ ብሩ የቻይንንም ሆነ የቬትናምን በኢኮኖሚ ማደግ አስመልክቶ ሁለቱ አገሮች እዚህ ዐይነቱ የዕድገት ደረጃ ላይ ሊደርሱ የቻሉት ከአሜሪካ ጋር

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት አብይና ዳንኤል ክብረት ጉድ አሰሙ-|ጀነራሉ በቁ*ጣ ተናገሩ-‘ህዝቡ ጉድ ሰራን’-|“ብልፅግናን ራ*ቁቱን አስቀርተነዋል”-|ታዳሚው ባለስልጣናቱን አፋጠጠ
Go toTop