በሸዋሮቢት በንፁሃን ላይ የመንግሥት ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ የተሰው ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ ነው

 ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሰባት ሰዎች መሰዋታቸው ይፋ ሆኗል።
ከጤና ተቋማት እየወጡ ያሉ ምስጢራዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ደግሞ፣ የሟቾች ቁጥር ወደ 12 ከፍ ሊል ይችላል። ከሃያ በላይ ቁስለኞችም በመታከም ላይ ናቸው።
“የመንግሥት ታጣቂዎች ቁስለኛ ለማሳከም የሄደን ሰው ሁሉ በጥይት ገድለዋል። ባጃጅ ውስጥ ነው የገደሏቸው። ሕዝቡ እያለቀሰ ነው” ብለዋል ያነጋገርናቸው የዓይን ምስክር።
“መንግሥት መምራት አቅቶታል። የሕዝቡን ጥያቄ መመለስ ባይችል እንኳን፣ ማወያያት ሲገባው በንፁሃን ላይ ተኮሰ። የመንግሥት እንቅስቃሴ ከዕለት ወደ ዕለት የሕዝቡን ቁጣ እየጨመረው ነው” በማለትም ያነጋገርናቸው የመረጃ ምንጭ ጨምረዋል።
አገዛዙ በሸዋሮቢት ተኩሶ የገደላቸውን ሰዎች ለመደበቅና ቁጥሩን ለማሳነስ እየሞከረም ይገኛል።
ዘገባው—-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ
ተጨማሪ ያንብቡ:  መነኩሴ ዘር የለውምና እኚህን አባት ለማመስገን ማንም ኢትዮጵያዊ ሊሳቀቅ አይገባውም!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share