“የብሄር ግጭት ተነሳ የሚባለው እርባና ቢስ ወሬ ነው። ከብልፅግና የሚጠበቀው በፅናት በመቆም ወደፊት መግፋት ብቻ ነው” – አቶ ብናልፍ አንዱአለም

የብልፅግና ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሠባ ላይ የተናገረው

ሠላም በሌለበት ሀገር የሠላም ሚኒስትር የሆኑት አቶ ብናልፍ ሠሞኑን ሲካሄድ በቆየው የብልፅግና ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሠባ ላይ የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ሂዴት በአግባቡ መረዳት የተሣናቸው ወገኖች ተጠባቂ የሆኑ ክስተቶችን እያነሡ የብሄር ግጭት ተነሣ ሠው ሞተ አያሉ ሲያብጠለጥሉ መሰማታቸው የሚጠበቅ ነው ብለዋል።
የብሄር ግጭት ተነሳ የሚባለውን እርባና ቢስ ወሬ በመስማት ከአላማችን ማፈግፈግ ሳይሆን ከብልፅግና የሚጠበቀው በፅናት በመቆም ወደፊት መግፋት ነው በማለት እየተካሄደ ያለውን የዘር ማፅዳት፣ ማፈንና ማሠር ፓርቲያቸው አጠናክሮ ሊቀጥልበት እንደሚገባ በአፅንኦት መክረዋል።
አቶ ብናልፍ በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ብልፅግናን በመወከል በጃቢ ጠና ወረዳ ለፓርላማ ተወዳድረው የነበረ ሲሆን የራሣቸው የብልፅግና መዋቅራቸው ሣይቀር መመረጥ የለባቸውም ብሎ ተቃውሟቸው ነበር።
ተቃውሞውን ወደ ጎን በማለት በግድ እንዲወዳደሩ ከተደረገ በኋላ ህዝቡም እሱን አንመርጥም ብሎ አቋም መውሠዱ ከተገመገመ በኋላ አቶ በላይነህ ክንዴ የሚባለው ባለ ሃብት ብናልፍ ወደቀ ማለት ጎጃም እንደ ወደቀ ነው የሚቆጠረው እያለ ለምርጫ ተወዳዳሪዎቹና ድምፅ ለሚሠጡ ሠዎች መደለያ አስራ ሁለት ሚሊዮን ብር መድቦ አከፋፍሎለት ተወዳድሯል።
ያሜ ሆኖ እንኳን ህዝቡ ሳይመርጠው ቀርቶ 183 ድምፅ ከተቃዋሚ ተወዳዳሪዎቹ በገንዘብ ድምፅ ገዝቶ በምርጫ ውድድሩ አልፏል ተብሎ ከአንድ ሣምንት በኋላ ተለጠፈለት።
በአካባቢው ህዝብ ዘንድ አንድ የሚታወቅ እና ሁሉም ሠው የሚግባባበት ሙድ ተይዛለች፤ 183 ከተባለ ብናልፍ አንዱአለም እንደማለት ነው።
እንዲህ አይነት ታሪክ ያለው ሠው በአብይ አህመድ ዘንድ እንደ አዋቂና ተንታኝ ተቆጥሮ ብናልፍ አንዳለው አየተባለ የትክክለኛነት ምሣሌ ተደርጎ ስትሠማ አይ ሀገር፣ አይ አማራ ከማለት ውጭ ምን ይባላል?

ፈለገ ግዮን

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጀነራሉን አብይ አሶገደው ኮረኔሉ በአጃቢዎቹ ተገደለ ጎጃም ባህርዳር ደፈጣ | ህውሀት ጦርነት ከፈተች | የክልሉ መሪዎች በአሜሪካ ኢምባሲ፣

1 Comment

  1. ብናልፍ አንዱ አለም አሁን ሽመልስ አብዲሳ አንተን እንደ ብልጽግና አካል የሚቆጥርህ ይመስልሃል? እውነቱን ከፈለግህ እንደ ማሟያና የአማራውን መምቻ ነው የሚያደርግህ፡፡ አይንህ ፈጥጦ ነብስህ እየቃተተች ለየትኛው እድሜህ ነው እራስህን እንዲህ ለውርደት የምትዳርገው? ያች ህጻን ወላሂ ማሩኝ ካሁን በኋላ አማራ አልሆንም ያለችው እንዳንተ አይነት በግድ ካልወከልናችሁ ብላችሁ እንዲህ መላ ቀጡ የጠፋ መግለጫ የምሰጡ ሆድ አደሮች በመብዛታችሁ ነው፡፡ በረከት ስሞን ሁለመናችሁን ቀይሮ ግኡዝ አድርጓችኋል እንዲሁ ህወአት ሲመጣ የሰረቃችሁትን ይዛችሁ መፈርጠጥ ነው ለመብላት ከታደላችሁ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share