June 30, 2022
3 mins read

የኢትዮ ሱዳን የድንበር ፍጥጫ ወዴት?

289400592 5722414181124964 5269612006251504988 n
289400592 5722414181124964 5269612006251504988 n
የሱዳን ጦር በአርማጭሆ ወረዳ በኩል ከርቀት የመድፍ እና ከባድ ጦር መሣሪያ ጥቃት እየሰነዘረ ነው መባሉ ድንበር ላይ ውጥረት አንግሷል። ጦሩ ኢትዮጵያውያን ባሉበት አቅጣጫ ጥቃት ሰንዝሮ በአካባቢው ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች እና ነጋዴዎች ከተባረረ በኋላ የኢትዮጵያ ጦር ወደ አካባቢው መምጣቱን ነዋሪዎች ማክሰኞ ዕለት ለዶይቸ ቬለ ተናግረው ነበር። የወረዳው የሰላምና ደህንነት ኃላፊ አቶ አብራራው ተስፋ በበኩላቸው፦ የሱዳን ጦር ከርቀት መድፍ እየተኮሰ መሆኑን ረቡዕ ዕለት ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል፡፡ አንድ የአካባቢው ነዋሪም የሱዳን ጦር ትንኮሳውን በአካባቢው ቀጥሎ እንደነበር አስረድተዋል፡፡
በድንበር ይገባኛል የሚወዛገቡት ኢትዮጵያ እና ሱዳን በሰሞኑ ግጭት የተነሳ የዲፕሎማሲያዊ እሰጥ አገባ ውስጥ የገቡም ይመስላል። ሱዳን አዲስ አበባ የሚገኙ አምባሳደሯን ወደ ካርቱም ጠርታለች። የኢትዮጵያ መከላከያም አስፈላጊ ከኾነ ምላሽ ለመዝጠት በጥሩ አቋም ላይ እንደሚገኝ ዐስታውቆ አስጠንቅቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሱዳን ጦር ከአወዛጋቢዉ የኢትዮ-ሱዳን ድንበር አጠገብ የሚገኘዉን ጀበል ካላ አል-ለበን የተባለዉን ሥፍራ መቆጣጠሩን ማሳወቁን ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዘግቧል። ኢትዮጵያ በውስጣዊ የፖለቲካ ውጥረት፤ ግጭት እና የበርካቶችን ሕይወት በቀጠፉ ጥቃቶች ተሰቅዛ ባለችበት ወቅት የሱዳን ሠራዊት ጥቃት ሰነዘረ መባሉ ምንን ያመለክታል? ውስጣዊ የፖለቲካ አጣብቂኝ ውስጥ የምትገኘው ሱዳን በራሷ በተለያየ ጊዜ በተቃውሞ ሰልፎች ትታመሳለች። ሱዳን ውስጥ ለዛሬ መጠነ ሰፊ የተቃውሞ ሰልፍ የተጠራ ሲሆን፤ በዋና ከተማዪቱ ካርቱም የኢንተርኔት አገልግሎት መዘጋቱን ሮይተርስ ዘግቧል።
የሱዳን ሠራዊት ኢትዮጵያ ላይ ጥቃት የሰነዘረው ውስጣዊ ውጥረቱን ለማርገብ እና ከተለያዩ ቡድኖች ጋር በመቀናጀት ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር ነው የሚሉ አሉ። የ«ታላቁ ሕዳሴ ግድብ» ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት ሰአታት ስለቀሩትም ጊዜ ጠብቆ የተሰነዘረ ነው የሚሉ አስተያየቶችም ተሰጥተዋል። በእናንተ ዕይታ የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ድንበር ላይ ወረራ እና ጥቃቱን ዳግም ያጠናከረበት ምክንያቱ ምንድን ነው ትላላችሁ?
አስተያየታችሁን ፃፉልን።
DW

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Lisan
Previous Story

አሜሪካ መንግሥት በወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ላይ የያዘውን የተዛባ አቋም አጥብቀን እንቃወማለን!

289659386 10159901026834393 7717595044600991369 n 1
Next Story

የአስራ አምስት ቀን ህፃን! – በላይነህ አባተ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop