በሱዳን ስደተኛ ካምፕ የትህነግ ወታደራዊ ምልመላ ቀጥሏል! (በጌታቸው ሽፈራው)

ትህነግ ላለፈው አንድ ወር በሱዳን የሚገኙ የትግሬ ተወላጆችንና ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በግዳጅ ወደ ማሰልጠኛ ጣቢያ እያስገባ ይገኛል። ወደ ጦር ሜዳ ላለመሄድ የወሰኑት ስደተኞች መካከል የቻሉት ወደ ሊቢያ፣ እድል ያልቀናቸው ከስደተኛ ካምፕ ውጭ ጠፍተው ወደ ሱዳን ከተሞች ሸሽተዋል። ይሁንና ግብፅና ሱዳን ለቀጣዩ ጦርነት መሳርያ እንዲገባለት ከማገዛቸው በተጨማሪ የሱዳን ፀጥታ ኃይሎች የሚጠፉትን ስደተኞች ለህወሃት አሳልፈው እየሰጡ ነው። መዝመት አንፈልግም ያሉ ከ1600 በላይ ስደተኞች ታስረዋል። ከስደተኛ ጣቢያ ውጭ ያሉና ኑሯቸውን ሱዳን ውስጥ ያደረጉ የትግሬ ተወላጆችና ሌሎች ኢትዮጵያውያንም ለጦርነት በግዳጅ ወደ ማሰልጠና እየገቡ ነው።

የህወሃት አመራሮች ስደተኛ ካምፕ ውስጥ ስብሰባና ምልመላ ሲያደርጉ የሚጠይቃቸው አካል የለም። በተመድ የሚመራው የስደተኛ ካምፕ ውስጥ የሚሰሩት የህክምና ባለሙያዎች የትህነግ አባላትን የድንገተኛ አደጋ ህክምና እንዲያሰለጥኑ ግዴታ ተጥሎባቸዋል። ፈቃደኛ ያልሆኑ የገንዘብ ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ይህን የትህነግ ድርጊት የሚቃወም ኃላፊ አልተገኘም።

የስደተኛ ካምፕ ውስጥ ወታደር መመልመልም ሆነ ሌላ ፖለቲካ አላማ ማራመድ ወንጀል ነው። ለትህነግ ግን ተፈቅዶለት እየሰራበት ነው። በየሳምንቱ ምልምሎች ከስደተኛ ካምፕ ተጭነው ወደ ወታደራዊ ካምፕ ይወሰዳሉ።

ባለፈው ሳምንት የሙዚቃ ድግስ ተደርጎላቸው ወደ ካምፕ ተሸኝተዋል። በዚህ ሽኝት ወቅት የህወሃት አመራሮች በካምፑ ተገኝተዋል። በፎቶው የሚታዩት አምራኩባ ስደተኛ ካምፕ ሲሆን የአካባቢው ደጋፊ የሆነ የሱዳን ተወላጅ ካምፕ ውስጥ ለእርድ የሚሆን እንሰሳ አምጥቶ ሲሰጣቸውም የሚያሳይ ነው። ስደተኛ ክምፑን እንደ ራሳቸው ካምፕ እየተጠቀሙበት ነው።

ቅዳሜ በተደረገ ድግስ በዚህ ክረምት ጠላታችን እናጠፋለን እያሉ በካምፑ ውስጥ ሲፎክሩ ውለዋል። ወልቃይትን ለእኛ፣ አርማጭሆን ለሱዳን እያሉ ሲጨፍሩ ውለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኦሮሚያ ክልል በጎሀ ፅዮን ከተማ የሚኖሩ በቁጥር 30 የሚሆኑ ዐማሮችና በኦነግ ሸኔ አማካኝነት መታረዳቸው ተነግሯል

የኢትዮጵያ መንግስት ሱዳን ስደተኛ ካምፖች ውስጥ የሚደረጉትን ወንጀሎች ያውቃል። ስደተኞች ለውትድርና እየተመለመሉ መሆናቸውን መረጃ አለው። ትህነግ በሀሰት መረጃ ኢትዮጵያን እየወጋ የኢትዮጵያ መንግስት ግን ዓለም አቀፍ ተቋማት ከትህነግ ጋር ሆነው እየፈፀሙት ያለውን ወንጀል እንኳን ማጋለጥ አልቻለም።

በፎቶው መመልከት እንደሚቻለው የትህነግ መልማዮች በስደተኛ ካምፑ ውስጥ ነው እየሰበሰቡ፣ እየመለመሉ ያሉት።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share