አታካብዱ ! “የዝንጀሮ ኩፍኝ“ እንጂ “የዝንጀሮ  ፈንጣጣ“ አይደለም ፣ አውሮፖን የናጣት ወረርሺኝ::

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ( ኤክሰፐርት ክሊኒካል ነርስ )

Monkeypox is a rare disease that is caused by infection with monkeypox virus. – CDC

የዝንጀሮ  ኩፍኝ በመባል የሚታወቀውን እና በመላ ሰውነት ላይ የተቀቀለ ማሽላ የመሠሉ ሆኖም ከማሽላ ተለቅ የሚሉ እባጮችን የሚፈጥረውን    ቫይረስ  በእንሥሣት ላይ በቸደረገ ምርምር ለሠጀመሪያ ጋዜ የተረጋገጠው በመካከለኛውና በምእራብ አፍሪካ በ1958 ዓ/ም እጎአ ነው ። በሽታው በሰው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተው ግን በቀድሞዋ ዛየር በአሁኖ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ፤ በ1970 ዓ/ም እጎአ  መሆኑ በዓለም የበሽታ ድርሳን ውሥጥ ተመዝግቧል ። ያውም በቀይ ቀለም ። …

ይኸው በዓለም የበሽታ ድርሳን ውሥጥ በቀይ ቀለም የተመዘገበው ሰበቡ ቫይረሥ የሆነው ህመም እንሆ ዛሬ ግንቦት 7/2022 ዓ/ም በኢንግላንድ  ተከስቶ መላ አውሮፓን እና አሜሪካን እያሥፈራራ ነው ።

ይህ ኩፍኝ መሠል ሆኖም ከኩፍኝ መጠናቸው የጎላ እብጠቶችን በሰውነት በሙሉ ና በብዛት ደግሞ በፊት ገፅ  ላይ የሚፈጥረው እና በትኩሳት ፣ በማንቀጥቀጥ ፣በራሥ ምታት ፣ በጀርባ ህመም ፣ በጡንቻ ህመም ና በጉሮሮ ህመም ፣ ሥሜት የሚታወቀው ወረርሺኝ ይኼን ያህል አሥጊና ለመቆጣጠርም የሚያዳግት መድሃኒት አልባ አይደለም ። ማንም ሰው እውቀትን በእውነት ሊገነዘብ የገባልና ይኽ በወረርሺኝ መልክ የተከሰተው በሽታ ከፈንጣጣ  ጋርም የማይመሣሠል ነው ። ፈንጣጣ ወይም “ አንትራክስ “ በባክቴሪያ የሚመጣ ገዳይ በሽታ ነው ። ሃያላኑ አገሮች በላብራቶሪ አባዝተው  በባዮሎጂ ጦር መሣሪያነት  አከማችተው እንደያዙትም በውሥጥ አዋቂዎች እና በጠርጣሪዎች ይወራል ። እናም ይኽ ፀሐፊ የዝንጀሮ ፈንጣጣ የሚባለው ጩኸት ይቆም ዘንድ አበክሮ ይጠይቃል ። ጫማና ኩፍያ የሆነ ፈፅሞ ከእውነት የራቀ ትርጉም ነውና ።

ይኽ የዝንጀሮ ኩፍኝ በተጨማሪ ፣ ዛሬ እና አሁን አሜሪካ፣ ሲውዲን እሥፔን ፣ ፖርቹጋል እና ኢጣሊያ መከሰቱ ታውቋል ። በድንገት  የወረርሽኙ ተጠቂዎች በተጠቀሱት አገሮች በመከሰቱ ፣ አገራቱ ህመምተኞቹን በየሆሥፒታሎቻቸው አግለው እያከሟቸው ነው ። በሌሎች  የአውሮፓ አገሮችም ወረርሽኙ እንደገባ ይወራል  ።

የወረርሽኙ ዛሬ በአውሮፖና በአሜሪካ መግባት በእግዳነት የሚታይና የሚያሥደነግጥም አይደለም ። ከላይ እንደገለፅኩት ይኽ የዝንጀሮ ኩፍኝ ( Monkey pox ) በማለት ሥም የተሠጠው ወረርሽኝ በ2003 በአሜሪካ ተከስቶ እንደንደነበር ይታወቃል  ። በወቅቱ ከ70 የማይበልጡ ሰዎችንም ይኽ መንኪ  ፖክስ ይዞ ነበር ።

እናም ፣  ይኽ በቫይረሥ የሚመጣ ኩፍኝ መሠል በሽታ በቀላሉ በፀረ ቫይረሥ መድሃኒቶች መታከም የሚችል መሆኑ ጥንትም ይታወቃል ። ( ጥንቃቄ አድርጉ እንጂ ፈንጣጣ በማለት ሐሠተኛ ትርጉም በመሥጠት አታካብዱ )

በቅጡ ለመገንዘብም የዩቲዩቡን ዜና እና የነቢቢሲን ዘገባ መርምሩ ። ይኽ በቫይረስ የሚመጣ ኩፍኝ መሠል  በሽታ ነው ።በቃ ። በዋነኝነት የሚተላለፈው በአይጥ ፣ በአይጠ መጎጥ ና በፍልፈልና በመሣሠሉት እንጂ  በዝንጀሮ አይደለም ። ዝንጀሮ ዋንኛ አሥተላላፊ አይደለም ። ሆኖም የዝንጀሮ ዘመድ አዝማድ ሁሉ  በበሽታው ይያዛል ። ያኔም እርሱ ነበር በ1958 ዓ/ም ጥናት የተካሄደበት ።

” በተያዘ ሰው ላይ ጥናት አልተካሄደምን ? ” በማለት ጥያቄ መጠየቅ ተገቢ ነው ። እንካችሁ መልሱን ።

በዝንጀሮ ኩፍኝ  የተያዘ ሰው ከ 5 እሥከ 21 ቀናት በበሽታው መያዙ ሊረጋገጥ ይችላል ። ወይም የበሽታዎቹ ሥሜቶች በነዚህ ቀናት ይታዩበታል ። በበሽታው መያዙ ከታወቀ በኋላ ከበሽታው ለመዳን እሥከ አራት ሣምንት ሊፈጅበት ይችላል ።

በዝንጀሮ ኩፍኝ የተያዘ ሰው ይኽንን ቫይረሥ በሚያሥነጥስ እና በሚያሥል ጊዜ ሊያሥተላልፍ ይችላል ። ከህመምተኛው የተቀቀለ ማሽላ  ከመሠሉ ፣ ችምችም ካሉ እባጮቸ ጋር መነካካትም በሽታውን ያሥተላልፋል ።  በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜም በሽታው ወደጤነኛ ሰው ይተላለፋል ።

ይኽ እንግሊዝና እሥፔንን ጭምር ያዳረሰው የዝንጀሮ ኩፍኝ ” አይነተኛው ቫይረስ ” ምንጩ ፣ በመካከለኛውና በምዕራብ አፍሪካ ነው ። ቢባልም ፣ በእንግሊዝ በወረርሽኙ ከተያዙት  8 ቱ ወደ ካናዳ እንጂ ወደ አፍሪካ ተጉዘው የማያውቁ መሆናቸው ታውቋል ።

እናም ወደፊት ሣይንቲሥቶቹ ተመራምረው የዚህ ቫይረሥ ምንጭ ፣ የአውሮፖና የአሜሪካ ምሥጢራዊ ላብራቶሪ ነው ። ባይሉንም እኛ ሰው ነን እና መጠርጠራችን አይቀርም ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ራስዎን በሁለት ቦታ የማስገኘት ጥበብ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share