April 21, 2022
33 mins read

የፋኖ ሦስተኛ ተገዳዳሪ ኃይል ሆኖ መውጣት፣ ለመላ ኢትዮጵያ አንድነት ኃይሎች ታላቅ የምሥራች ነው

ኢት-ኢኮኖሚ  /ET- ECONOMY
ፀ/ት ፂዮን ዘማሪያም (ኢት-ኢኮኖሚ

et990cf0

‹‹በኢትዮጵያ ግማሽ ሚሊዮን ወጣቶች በማያባራ ጦርነት ያስጨረሰው የአብይ መንግሥት አገዛዝ  በቃ!!!››…የኢትዮጵያ ህዝብ ከኦህዴድ ብልፅግና ከኦነግ ሸኔ የኦሮሙማ ስልቀጣ ለመዳን በህብረት መታገል ጊዜው አሁን ነው!!!…ኢትዮጵያን ለመታደግ ‹‹የሽግግር መንግሥት መመስረቻ ጊዜው አሁን ነው!!!››

  • ‹‹እኔ አልመለስም፡፡ ሻማው ተለኩሶላችኃል ሻማው እንዳይጠፋ!!!›› ፕሮፌስር አስራት ወልደየስ
  • ‹‹የአማራ ጥያቄ የዴሞክራሲና እና የህልውና ነው፡፡ አማራ በክልሉ ውስጥ ሆኖ የህልውና ችግሮች አሉብን!!!››ብ/ጀ አሳምነው ፅጌ
  • ‹‹የአሸባሪው ህወሓት መመታት ለኢትዮጵያ የሠላም ዋስትና ነው!!!›› ብ/ጀ ተፈራ ማሞ
  • ‹‹ህወሓት በወልቃይት ተቀበረ!!!››…‹‹ለፌዴራል መንግሥቱ እጅ አልሰጥም!!!››ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ
  • ‹‹ከኮሮና ከሱዳን ሠራዊት በላይ ፋኖ እንዴት አሰጋ!!!›› መሣፍንት ተስፉ
  • ‹‹የአማራ ህዝብ ታሞ ኢትዮጵያ ጤናማ ልትሆን አትችልም!!!››…..‹‹ከዚህ በኃላ ማንም ዱላ የያዘ ሁሉ እንደ ከብት አይነዳንም!!!››…ዘመነ ካሴ
  • ‹‹በአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተው ዘመቻ በአስቸኳይ ይቁም!!!›› ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ
  • ‹‹ከጦርነቱ በኃላስ ተስፋና ስጋቶች›› ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው
  • ‹‹ከሽብርተኛው ትህነግ ጋር ድርድር በምን ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ይደረጋል? ›› ዶክተር አክሎክ ቢራራ
  • ‹‹የሽግግር መንግሥት መመስረቻ ጊዜው አሁን ነው!!!››….‹‹ዋና ትግላችን ከአክራሪ የኦሮሞ ብሔርተኞች ጋር ነው!!!›› እስክንድር ነጋ
  • ‹‹የትኛዋ ሴት ሚንስትር ናት ስለ እነዚህ ሴቶች በአደባባይ የጠየቀችው›› ቀለብ ስዩም
  • ‹‹መሰረታዊው ጉዳይ አማራን ማህበራዊ እረፍት መንሳት ነው!!!›› ዶክተር  ሲሳይ መንግስቴ
  • ‹‹ኢትዮጵያ መንግስቱን፣መለስን፣ኃይለማርያምን አስተናግዳለች እንዲህ ዓይነት አጭበርባሪ ግን አይታ አታውቅም!!!›› አቻምየለህ ታምሩ
  • ‹‹››የዘውግ ፌዴራሊዝም ችግሮችና የደቀነው አደጋ!!!›› ዶክተር ሰማኸኝ ጋሹ

ህርማን ኮህን፣ ሌንጮ ለታ (ኦነግ)፣ ኢሣያስ አፈወርቂ (ሻብያ)፣ መለስ ዜናዊ (ህወሓት)፣ ኢትዮጵያን ተደራዳሪ ተስፋዬ ዲንቃ፣ አሻግሬ ይግለጡ  የአሜሪካ መራሹ የ1983ዓ/ም የሎንዶን የሠላም ኮንፍረንስ አደራዳሪ ህርማን ኮህን በአደባባይ የኢትዮጵያን ልዑካኖችን የዛሬ ሠላሳ አንድ አመት ለሠላሳ  ዲናር ከድተው ሸጦቸው፡፡  አይበገሬው ተደራዳሪ- ተስፋዬ ዲንቃ …አንድ ለእናቱ!!! የአሜሪካኖቹን ክህደት በፕሬስ ኮንፍረንስ አጋልጦቸው እንደነበር በታሪክ ይታወሳል፡፡ ኢትዮጵያና ሦስቱ የሽምቅ ተዋጊዎች ቡድን ለዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ መራሽ የሰላም ድርድር!!! ኤርትራን ያስገነጠለውና ወያኔን ለሃያ ሰባት አመታት በስልጣን መንበሩ እንዲፈናጠጥ ያደረገው የአሜሪካ መንግሥት ሴራ ነበር፡፡  ዛሬም  ዳግሞ የአብይ አህመድን የኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት ከደብረፂዮን የህወሓትና ኦነግ ሸኔ  ጋር የሠላም ድርድር አድርጎ የአማራና አፋር ግዛቶችን ለህወሓት ወደ ትግራይ ለማካለል አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት አዲስ የፖለቲካ ሴራ ነድፈዋል፡፡ ፋኖ የአማራ መከላከያ ኃይል ህዝባዊ የታጠቀ ኃይል በመሆን ሦስተኛ ተገዳዳሪ ኃይል በመሆን የአማራን ህዝብ ወክሎ ይህ የሠላም ድርድር በመቃብሬ ላይ ብሎል፡፡

የአማራ ህዝብ ወኪል በሌለበት ‹‹የኢትዮጵያ ህገ-መንግሥት›› ረቆ መፅደቁ ልብ ይበሉ፡፡ በኢትዮጵያ የሚካሄድ ማንኛውም ድርድር  ፋኖ የአማራ መከላከያ ኃይል የአማራ ክልልን በመወከል ተደራዳሪ ሆኖል፡፡ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ብልፅግና ሹማምንቶችና ካድሬዎች ከህዝብ ጋር እንዲወግኑ የመጨረሻ እድል በመስጠት፣ በፋኖ ላይ የሚያካሂዱት የትጥቅ ማስፈታትና አፈና ዳግም ከተከናወነ ግን በፋኖና ህዝባዊ ኃይል ተይዘው በወንድማዊ አያያዝ ማረፍያ ቤት እንዲቆዩ ወይም በቤታቸው እንዲቆዩ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ  ልዑክ የሚመራ የሠላም ድርድር ኢትዮጵያን በተመለከተ ኦህዴድ ብልፅግና፣ ህወሓት፣ ኦነግ ሸኔ፣ ለማደራደር የሚደረግ የሠላም ድርድር የአማራና የአፋር ክልል ህዝብ ተጠሪዎችን ሳይጨምር የሚታሰብ አይደለም!!! የሠላም ድርድሩ ፍህታዊና ዘለቄታዊ እንዲሆን የሁሉም ተሳትፎ ያስፈልጋል፡፡

{1} የፋኖ የአማራ መከላከያ ኃይል የጦርነት ትርፍ፡- ጀነራል አሳምነው ፅጌ አንድ ጊዜ አምስት ሽህ የአማራ ፖሊስ ሠራዊት ባስመረቀ ጊዜ አብይ አህመድ ለሠላሳ ጊዜ በላይ የኦሮሞ ፖሊስ ሠራዊት አሰልጥኖ ነበር፡፡አብይ የአማራን ክልል ባጀታችሁን ሠራዊት በማሠልጠን ነው የምትጨርሱት በማለት አብይ ተቆጥቶ ነበር፡፡ የአሳምነው ደም በከንቱ ፈሶ አልቀረም!!! የወያኔው ደብረፂዮንና የኦህዴድ ብልፅግናው አብይ የማያባራ ጦርነት በሃገሪቱ አቀጣጠሉ፡፡ የአብይ መንግሥት ወያኔ፣ የአማራና አፋርን ክልሎች ተቆጣጥሮ ወደ አዲሰ አበባ በገሠገሠ ጊዜ የአማራ ህዝብና ወጣቶች የወያኔን ጦር  እንዲመክቱ  የማረኩትንም እንዲወስድ በቴሌቪዚን በሬዲዬ ዶክተር አብይ አወጀ፣ተማፀነ፣ ጥሪውንም   የአማራ ወጣቶች በመቀበል ወደ ማሠልጠኛ ተቆማት ተመሙ፡፡ በጦርነቱም ወቅት በህወሓት ተይዘው የነበሩ የአማራ መሬቶች ወልቃይት፣ ጠለምት፣ ጠገዴ፣ ራያ ወዘተ አስለቀቁ፡፡ የአብይ አህመድንም በትረ ሥልጣን ከአፋፍ ላይ ቆመው ታደጉ፡፡ የአማራ ወጣቶች ዳግም እየሠለጠኑና እየታጠቁ የጀነራል አሣምነው ፅጌን ጦር  ገነቡ፡፡ የአማራ ልዩ የፖሊስ ኃይልና ፋኖ እንዳይሠለጥኑና እንዳይታጠቁ የነበረው ሴራ ከሸፈ፡፡

የአማራ ወጣቶች ፋኖ ይሄን ወርቃማ ጊዜ በአግባቡ በመጠቀም ከአሸባሪዎች ትጥቅና ስንቅ በመማረክ፣ እራሱን አስታጠቀ ብዙ ሽዎች ክላሸን ኮቭ፣ መትረየሶች፣ መድፎች፣ ዲሽቃዎች፣ ወዘተ በመማረክ ራሱን አስታጥቆ፣ የአማራን የህልው ትግልና በህይወት የመኖር መብቶች ለማስከበር ቆርጦ ለአንዴና ለሁሌ በሃገሪቱ ተገዳዳሪ ኃይል ሆኖ በመውጣት ለአማራ ህዝብ ፋኖ የጦርነቱ ትርፉ ሆኖ በታሪክ ተመዝግቦለታል፡፡ ተወደደም ተጠላ፣ አሁን በሃገሪቱ ሥስት የኃይሎች አሠላለፍ ሲኖር እነሱም የህወሓት የታጠቀ ኃይል፣ ኦህዴድ ብልፅግ መንግሥትና የኦነግ ሸኔ  የታጠቀ ኃይል፣ የፍኖ ተዋጊ የታጠቀ ኃይሎች ሆነዋል፡፡ የኦነግ ሸኜ አሸባሪ ኃይል ከኦህዴድ  ብልጽግና ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያገኝ የአደባባይ ሚስጢር ሆኖል፡፡  የፋኖ የአማራ መከላከያ ኃይል ከወያኔ፣ ከኦነግ ሸኔና ኦህዴድ ብልፅግና ጋር ለማይቀረው ጦርነት መዘጋጀት ይጠበቅበታል፡፡ ፋኖ በአንድ መዕከል ሥር ሆኖ መመራትና ከሻብያ ጋር መርህ ላይ የተመሠረተ ግንኙነት ማድረግ ይጠበቅበታል እንላለን፡፡ ፋኖ በደሙ ከፍሎ የታጠቀውን ትጥቅ ለማስፈታት የሚደረግ የዝናር በቅፊዎች ጥቃት ከምርኮ ሌላ ፋይዳ አይኖረውም፡፡ የፋኖ ትጥቅ ልቡ ላይ ነውና!!!

የፋኖ ሦስተኛ ተገዳዳሪ ኃይል ሆኖ መውጣት ለመላ ኢትዮጵያ አንድነት ኃይሎች ታላቅ የምሥራች ነው፡፡ ፋኖ የአንድነት ኃይሉን በማጠናከር በዙሪያው የአፋር ኃይልን፣ የሱማሌን፣ ጋምቤላን፣ ደቡብ ክልልን፣ ሲዳማን፣ ሃረሪን፣ ወዘተ ክልሎች ጥቃትን አብሮ በመመከት አጋርነቱን በተግባር በመግለፅ የኢትዮጵያን አንድነት ማስጠበቅ ታሪክ የጣለበት አደራ ነው፡፡ ከኦህዴድ ብልፅግና ኦነግ ሸኔ የኦሮሙማ ስልቀጣ ለመዳን በህብረት መታገል ጊዜው አሁን ነው!!!…‹‹የሽግግር መንግሥት መመስረቻ ጊዜው አሁን ነው!!!›› አራጁ ኦነግ  የኦሮሞ ህዝብን በስብዓዊ ጋሻነት አፍኖ በግፍ በመግዛት ላይ ይገኛል፡፡ የኦሮሞ ፓርቲዎች የዶክተር መረራ ጉዲና ኦፌኮ፣ የአብይ ኦህዴድ ብልፅግና ስለ አማራና ኦሮሞ ህዝቡ መታረድ አንድ ቀንም ድምፃቸውን  አሰምተው አያውቁም!!!

{2} የሻብያ የጦር አበጋዞች የጦርነት ትርፍ፣ በሻብያ ላይ ተነጣጥረው የነበሩ ሚሳኤሎችና፣ ላውንቸሮች፣በወያኔ ላይ ሆኑ፡፡ በሻብያ ላይ ያለሙ የታንኮቹ አፈሙዝ ላንቃ በህወሓት ላይ ተሰበቁ፡፡ በሻብያ ላይ የተደገኑ መድፎች፣ቢአሮች፣ቢኤምዎች በትህነግ ላይ ዞሩ፣ ዓለም ተሸዓተ ሆነ!!! ሻብያ ለሃያ አመታት ሽንፈቱን ውጦ ከተኛበት ተነሳና  ወያኔንም ኢትዮጵያንም አሸነፈ፡፡  የቀይ ባህሩ ቌጥኝ ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራን ለአረቦች ይሸጣል ሲባል እንዲያው የሃኒሽ ደሴት ይገባኛል እያለ ድንበር ሲያስፋፋ ተያዘ፣ ኢሳያስ ለኤርትራዊያን ነፃነትን በባርነት፣ ዴሞክራሲን በአንባገነንነት፣ ተክቶ ለሦስት አሰርት ኤርትራን ገዛ፡፡ ወዲ ኢሳያስ ኦቦ አቢቹን አግዞ ጦርነቱን ሲቀላቀል፣ የወያኔ እንጥሉ ወረደ፣ ቡአ ወረደው ፡፡  ሻብያ በትግራይ ከሚገኙ መቶ በላይ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ባንኮች ውስጥ በብዙ ቢሊዮን ብር የሚቆጠር የኢትዮጵያን ገንዘብ ዘርፎል፡፡ ሻብያ ከወያኔ ላይ ብዙ ታንኮች፣ የጦር መኪኖችና የጦር መሣሪያዎች መጋዘኖች ዘርፎ ወደ ኤርትራ ጭኖ ወስዶል፡፡ ሻብያ ልዩ ልዩ መኪኖች ሎቤዶች፣ ትራክተሮች፣ የጭነት መኪኖች፣ ወታደራዊ መኪኖች፣  ስርቆ ‹‹ተዘወሪ መኪና›› እያለ ነድቶ አስመራ ወስዶል፡፡ የአልሜዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ በኤርትራ ወታደራዊ ኃይል ተዘርፎ ወድሞል፡፡ የመሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ተዘርፎል እቃዎቹ ወደ ኤርትራ ተጭኖ ተወስዶል፡፡ በአብይና ኢሳያስ ጣምራ ጦር አዲስ መድሐኒት ፋብሪካ፣ የጎዳ ብርጭቆ ፋብሪካና የስኳር ፋብሪካ ተዘርፈው ወድመዋል፡፡ የትራንስ ኢትዮጵያ መቶ ሰባ ዘጠኝ የጭነት ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ኤርትራ ተዘርፈው ተወስደዋል፡፡ በትግራይ ይገኙ የነበሩ የጤና አገልግሎት ሆስፒታል፣ ክሊኒኮች፣ ጤና ጣቢያዎችና ጤና ኬላዎች  ሰባ በመቶ ወድሞል፡፡ የሆስፒታሎች መድሓኒት ቤቶች፣ የህክምና እቃዎችና የላብራቶሪ እቃዎች፣ ተፈትተው ተወስደዋል፡ የዩኒቨርሲቲ ቤተመፅሃፍቶች፣ የላብራቶሪ እቃዎች፣ የመብራት ኃይል ትራንስፎርመሮች፣ ጀነሬተሮች፣ ስብ እስቴሽኖች ተዘርፈዋል፡፡ የቴሌኮሙኒኬሽን ውድ እቃዎች ተዘርፈዋል፡፡ ሻብያ በጦርነቱ ያገኘው የዘረፋ ትርፍ ይህን ይመስላል፡፡ ከመንግሥትና ከግል ነጋዴዎች የተለያዩ መጋዘኖች እህል፣ ሲሚንቶ፣ ብረታ ብረት፣ የግንባታ እቃዎች፣ ወዘተ ተዘርፈዋል፡፡ከህዝብና ግለሰቦች  ላይ የተዘረፉ ወርቅ፣ ገንዘብ፣ ሞባይል ስልኮች፣ ልዩ ልዩ ኮንፒውተሮች ወዘተ ላይ በግፍ የተዘረፈውን ቤቱ ይቁጠረው፡፡ የሲቪሊያን ሰላማዊ ሰዎች ግድያና የሴቶች አስገድዶ መድፈር  ወንጀል ከሁሉም አስቃቂ የወንጅል ድርጊት ነበር፡፡ በአብይና ኢሳያስ ጣምራ ጦር የትግራይ የመሠረተ-ልማቶች ውድመት መልሶ ለመገንባት መቶ ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ተገምቷል፡፡ ኢሳያስና አብይ ፒኮሎ መቐለን ወደ በሻሻነት ቀየርናት!!!›› አለ፡፡ ‹‹The United States imposed sanctions on Eritrea’s army chief, Filipos Woldeyohannes, over human rights abuses in the Tigray region. A US Treasury Department statement said Eritrean Defense Forces (EDF) troops had raped, tortured, and executed civilians as well as destroying property and ransacking businesses. The allegations were angrily rejected in Addis Ababa, who have also rejected US claims that it has blocked aid into Tigray.›› የትግራይ ህዝብ በጨላማ ውስጥ እንዲኖር ተፈረደበት፣ ያለ ውኃ፣ ያለ ስልክ፣ ያለ ኢንተርኔት፣ ያለ ባንክ፣ ያለበጀት፣ያለደሞዝ፣ የኮነሬል አብይ አህመድ የአራት አመት አገዛዝ ዘመኑ  በጦርነቱ ግማሽ ሚሊዮን ወጣቶች አለቁ፣ አከል ጉዳተኛ ሆኑ፣ ሴቶች ተደፈሩ፣ በርሃብ ቸነፈር ህፃናት አለቁ፣ ህዘብ ቀየውን ለቆ ተሰደደ፡፡ የአብይ ግፍ ሞልቶ ፈሰሰ! የደብረፂዮን ግፍ ሞልቶ ፈሰሰ!!! ከትግራይ በብዙ ሽህ የሚቆጠር ህዝብ ወደ አማራና፣ አፋር ክልሎች ተሰዶ ገብቶል፣ ህዝቡም ‹‹ቤት ለእንቦሳ!!!›› ብሎ ተቀብሎቸዋል፡፡ ጦርነቱ የእብድ መሪዎቻችን ጠብ እንጂ የህዝብ ጠብ አለመሆኑ ተመሠከረ፡፡

Warehouses containing aid in northern Ethiopia have been looted by both sides in the country’s civil war, the head of a U.S. agency said. State-run TV had initially aired an interview in which Sean Jones, who heads the U.S. Agency for International Development (USAID) in Ethiopia, said fighters for the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) had looted every camp in the Amhara region as they made military advances. But a transcript subsequently released by the U.S. Embassy showed that Jones also accused government troops and Eritreans of raiding aid warehouses in the region in past months.

More than nine million people in northern Ethiopia are in need of critical food supplies, the UN says………………….(1)

Rebels in Ethiopia’s war-torn Tigray region have been looting aid warehouses, the US aid agency said on Tuesday, calling the alleged thefts a “great concern for humanitarians”. “We know for a fact… that the TPLF (Tigray People’s Liberation Front), every town they’ve gone into they looted the warehouses, they’ve looted trucks, they’ve caused a great deal of destruction in all the villages they visited and it’s a great concern for humanitarians,” Sean Jones, head of the USAID mission in Ethiopia, told Ethiopian state television EBC.,……………………………………………….(2)

{3} የወያኔ የጦር አበጋዞች የጦርነት ትርፍ፣ የወያኔ ኃይል በአማራና አፋር ክልሎች ወርሮ  ቦታዎች በያዘበት ሥፍራ ሁሉ የዩኤስኤድ የእህል መጋዘኖችን ዘርፎል፡፡የብልፅግና መንግሥትና የኤርትራ መንግሥት በዝርፍያው ተሳታፊ ነበሩ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ለዘጠኝ ሚሊዮን ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልግ አስስቦ ነበር፡፡ የዓለም የምግብ ድርጅት በሰሜን ኢትዮጵያ ሁለት የምግብ እርዳታ ማከፋፈያ እንዲዘጉ ያደረገው በህወሓት የታጠቁ ኃይሎች ብዛት ያለው እህል፣ የህጻናት አልሚ ምግብ፣ ከእህል መጋዘኑን በመዝረፋቸው የተነሳ ነበር፡፡ ነዋሪዎች ለኤኤፍፒ በገለፁት መሠረት ባንኮች፣ የመንግሥታዊ መስሪያ ቤቶች፣ አየር ማረፍያ፣ ሆስፒታል በወያኔ መዘረፉን ገልፀዋል፡፡ ‹‹The World Food Programme (WFP) has suspended distribution of food aid in two northern Ethiopian towns after gunmen looted its warehouses. Looters from rebel Tigrayan forces held aid staff at gunpoint in the town of Kombolcha, the United Nations said. They stole large quantities of essential food supplies – including some for malnourished children.….Residents told AFP news agency that banks, government offices, the airport and hospital had been looted by rebels››…………………..(3)

 

የወያኔ የጦር አበጋዞች በአማራና በአፋር ክልሎች ወረራ በመፈጸም መሠረተ-ልማቶች በመዝረፍና በማውደም ድርጊት ተሳትፈዋል፡፡ ሆስፒታል፣ የትምህርት ቤት፣ የቴሌኮም እቃዎቸ፣ የመብራት ኃይል እቃዎች፣ የውኃ፣ ውድ እቃዎች ፈተው ጭነው ወስደዋል፡፡ ወያኔ ሁለት መቶ ሰማንያ ስድስት ባንኮች ዘርፎል ከደሴ ባንክ ብቻ ስድስት ቢሊዮን ብር ዘርፎል፡፡ ከፌዴራል መንግሥት የተላከ አዲስ ብር የተቀየረ ጊዜ፤ ወያኔ ከመቐለ ኤርፖርት ሦስት ቢሊዮን ብር  ዘርፎ ወስዶል፡፡ ወያኔ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰሜን እዝ መምሪያ ከባባድ የጦር መሣሪያዎች፣ ታንኮች፣ መድፎች፣ ሚሳኤሎች፣ ወዘተ ዘርፎ ወስዶል፡፡ በአማራና አፋር ሠላማዊ ህዝብን ጨፍጭፎል፣ አስሮል፣ ሴች ደፍሮል፣ ንብረትና ኃብት ዘርፎል፡፡ ወያኔ የጦር አበጋዞች የጦርነት ትርፍ ለናሙና ይሄን ይመስላል፡፡ ህወሓት የጦርአበጋዝ ሠራዊት ተገዳዳሪ ኃይል ሆኖ ቀጥሎል፡፡ የዶክተር አብይ አህመድ የፌዴራል መንግሥት የትግራይን ክልል አያስተዳድርም፡፡ ህወሓት ሓይል በአማራና አፋር ክልሎች ውስጥ ተጨማሪ ቦታዎች እንደያዙ ይገኛሉ፡፡

{4} የብልፅግና የጦር አበጋዞች የጦርነት ትርፍ፣ የኮነሬል አብይ አህመድ የብልፅግና መንግሥት ከሰሜኑ ጦርነት ያገኘው ትርፍ ከኪሳራው ጋር ሲነፃፀር አተርፍ ባይ አጉዳይ አድርጎታል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሃያ ስምንት የረድኤት ሠራተኞች ተገድለዋል፡ በዚህም ሃገሪቱ ለስብዓዊ እርዳታ ስርጭትና ለሠራተኞች በጣም አስቸጋሪነት ሥፍራ ሆኖ ተመዝግቦል፡፡ የፌዴራል መንግሥት መከላከያ ሠራዊት ከትግራይን ክልል ሙሉ በሙሉ ለቆ ወጥቶል፡፡ የአብይ አስተዳደርና ግዛት ከትግራይ መለስ ሆኖ ሰላም አውርዶ ተደራድሮ ለመግዛት ቆምጦል፡፡ ወያኔ በመስፋፋት የአማራና የአፋር ግዛቶችን ይዞ እያለ ጦርነቱ አልቆል ማለቱ በቀሪው ህዝብ የአብይ ጦር መንበርከኩ ለአማራና አፋር ህዝብ አልተዋጠላቸውም፡፡ ‹‹This is yet another example of the dangerous environment humanitarian workers have to operate under in Ethiopia. Since the beginning of the conflict a year ago, 28 humanitarians have been killed, making the country one of the most dangerous for aid workers, according to the UN››…………………….(4)

የኮነሬል አብይ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ውስጥ  የሚገኙ ከሠላሳ እስከ አርባ በመቶ የሚሆነውን ግዛቶች እንደማያስተዳድር ይታወቃል፡፡ የአብይ መንግሥት በህወሓት የተያዘችውን ትግራይ ግዛት፣ በኤርትራ የተያዘውን ግዛት፣ በኦነግ ሸኔ የተያዘውን የኦሮሚያ ግዛት፣ በሱዳን የተያዘውን የአማራ ግዛት አስረክቦ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተንበረከከ መንግሥት ለመሆን ችሎል፡፡

 

{5} የኦነግ ሸኔ የጦር አበጋዞች የጦርነት ትርፍ፤- ኦህዴድ ብልፅግና ከኦነግ ሸኔ ጋር በነደፉት የፖለቲካ ሴራ በሁሉም ክልሎች ላይ ጦርነት ከፍተዋል በአማራ ፣ በአፋር፣ በሱማሌ፣ በሲዳማ፣ በቤኒሻንጉል፣ በጋምቤላ፣ ወዘተ የኦሮሙማ ስልቀጣን ለማስፋፋት  ጦርነት ከፍተዋል፡፡ ህወሓትና ኦነግ ሸኔ በጋራ በመሆን የተቀነባበረ ጦርነት ከፍተዋል፡፡ ከዚህ የአሸባሪዎች የፖለቲካ ሴራን ለመበጣጠስ ዋናው ተገዳዳሪ ኃይል ሆኖ የወጣው  የፋኖ የአማራ መከላከያ ሠራዊት ታሪካዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡ ከፋኖ ጋር በማበር ህወሓትን፣ ኦነግ ሸኔንና ኦህዴድ ብልፅግናን በህብረት መታገል ጊዜው አሁን ነው!!!

 

ኦነግ ሸኔ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሃያ ሦስት ባንኮች ዘርፎል፡፡ የእርዳታ እህልና የማዳበሪያ መጋዘኖች የዘረፈው ኦነግ ሸኔ ኡሪያና ዳፕ ከአራት እሰከ አምስት ሽህ ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡ ኦነግ ሸኔ ከህዝብ ላይ የተዘረፉ መኪኖች፣ ባጃጆች፣ ወርቅ፣ ገንዘብ ፣ ሞባይል ስልኮች፣ ልዩ ልዩ ኮንፒውተሮች ይዘርፋል፡፡ ኦነግ ሸኔ ሰዎች እያገቱ ብዙ ገንዘብ ይጠይቃሉ፡፡ ኦነግ ሸኔ ብዙ ከተሞችን አቃጥሎል ሻሸመኔ ከተማ፣ አጣዬ ከተማ፣ በአርሲ፣ በጅማ፣ በወለጋ ፣ በሰሜን ሸዋ የብዙ ሽህ ገበሬዎች ቤትን ዘርፎ አቃጥሎል፡፡ ኦነግ ሸኔ ከፌዴራል መንግሥቱ ኦህዴድ ብልፅግና ከመከላከያ ሠራዊቱ  ጋር በህብረት በመሥራት የህዝብ ንብረትና ኃብት በማውደም ላይ የሚገኝ አሸባሪ የኦሮሙማ ብድን ነው፡፡

የሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ የጦር አበጋዞች የጦርነት ኪሳራ ከግማሽ ሚሊዮን ወጣቶች በጦርነቱ ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ብዙ ሽህዎች አካል ጉዳተኞች ሆነዋል፣ ብዙ ሽህ ሴቶች ተደፍረዋል የሥነልቦና ችግር ተዳርገዋል፣ በብዙ ሚሊዮኖች ከቀያቸው ተፈናቅለው ተሰደዋል፣ የእርዳታ ጠባቂ ሆነዋል፡፡ በዚህም ሥራቸው አንድ ቀን በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ተጠያቂ ሆነው ለፍርድ ይቀርባሉ፡፡ የጦርነቱ ሰለባ ህዝቡ የመብራት፣ የውሃ፣ የስልክ፣ የኢንተርኔት፣ የትራንስፖርት፣  የባንክ አገልግሎቶች  ለብዙ ወራቶች አጥተዋል፡፡

የሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ የጦር አበጋዞች የጦርነት ትርፍ

  • በጦርነቱ ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከባድና ቀላል የጦር መሣሪያዎች፣ የጦር መጋዘኖች በሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ ተዘርፈዋል፣ ለእነሱ  የጦርነት ትርፍ ለእኛ ኪሳራ ተመዝግቦል፡፡
  • በጦርነቱ ወቅት ከእርዳታ ማስተባበሪያ የእህል መጋዘኖችና ከተለያዩ የነጋዴ መጋዘኞች የዘረፎቸውን እህል፣ ስኳር፣ ፓስታ፣ መኮረኒ፣ ዱቄት ወዘተ እንዲሁም የኮንስትራክሽን እቃዎች ብረታብረት፣ ጀነሬተር፣ ትራንስፎርመር፣ የትራንስፖርት መገልገያ መኪኖች፣ ባጃጆች ወዘተ ተዘርፈው ለህዝብ በከፍተኛ ዋጋ ተቸብችቦል፡፡
  • የትግራይ፣ የአማራና የአፋር አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በቡዙ መቶ ሽህዎች የቀንድ ከብቶቻቸውን፣ የጋማ ከብቶቻቸውን ታርደው ተበልተዋል፣ ተዘርፈዋል፣ ተሸጠዋል፡፡
  • የጦርነቱ ተዋናዬች በቤንዚን ህገወጥ ንግድና ሽያጭ አንድ ሊትር ቤንዚን ከ300 እስከ 400 ብር በክልል ድንበሮች በኩል በብዙ እጥፍ ትርፍ በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡
  • የህክምና መድኃኒቶች በጦርነት ቀጠና ባሉባቸው የክልል ድንበሮች በኩል በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡ በከፍተኛ ጉዳት አደጋ የደረሰባቸው ግለሰቦች ለግሎኮስ መግዣ እስከ ሠላሳ ሽህ ብር እንደሚገዙ ታውቆል፡፡
  • የቴሌኮም ሥራና የባንክ ሥራ በጦርነቱ ወቅት ወደ ግለሰቦች የንግድ ሥራነት ተቀይሮ ከውጭ ሃገራት ለዘመዶቻቸው ገንዘብ ማስተላለፍ የሚፈልጉ ሰዎችንና ዘመዶቻቸውን የሚያገናኙ የኮሚሽን ኤጀንቶች ከሚላከው ገንዘብ ከሠላሳ እስከ አርባ በመቶ ኮሚሽን እየወሰዱ ቢዝነስ ይሠራሉ፡፡
  • ወያኔ በመቀሌ ከአማራና አፍር ክልሎች የተዘረፉ ልዩ ልዩ እቃዎች በመቀሌ ገበያ በወያኔ ካድሬዎች ይሸጣሉ፣ የቤት ቁሳቁሶች ቴሌቪዝን፣ ፍሪጅ፣ ስቶቨ ባጃጆች ወዘተ ይሸጣሉ፡፡
  • ‹‹የሽግግር መንግሥት መመስረቻ ጊዜው አሁን ነው!!!››

 

ምንጭ፡-

(1) Govt troops, Eritreans and Tigray looted aid supplies: US agency/BY GERMAN PRESS AGENCY – DPA/ NAIROBI SEP 01, 2021 – 5:07 PM GMT+3/ Ethiopia war: UN halts food aid in two towns after warehouses looted/9 December 2021

(2) Ethiopia’s Tigray rebels looting aid supplies: US agency/ 31/08/2021 – Nairobi (AFP) –

(3) Ethiopia war: UN halts food aid in two towns after warehouses looted – BBC News

(4) Aid suspension deepens a worsening crisis/By Emmanuel Igunza, BBC News, Nairobi

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop