ኢትዮጵያ እንደ አገር የመቀጠል አደጋ ከተጋረጠባት ቅድመ እና ድህረ ኢሀዴግ ጭለማ ዘመን ዜጎች በማንነታቸዉ እና ኢትዮጵያ በመሆናቸዉ ብቻ ሲገለሉ እና ሲገደሉ በሞት እና በስደት ለሚናወጠዉ ዜጋ ሰቃይ መሳለቅ የተለያ ስያሜ በመስጠት ግጭት ማለት የዘመናችን ክህደት ነዉ ፡፡
በቀጥታ እና በግልፅ ብሄራዊ አንድነትን በማዳከም ለመቀራመት ኢትዮጵያ ትዉደም ፤ዓማራ ይክሰም ብሎ አስቦ እና አቅዶ በአገር እና ህዝብ ላይ ክህደት ለግማሽ ክ/ዘመን እየፈፀመ የሚገኝ ጠላት የሚያደርገዉን ጅምላ ፍጂት ኢትዮጵያን ለመበታተን የሚደረግ ሂደት መሆኑ እየታወቀ ግጭት ማለት ለአገር ቀርቶ ለግል ቁም ነገር አይበቃም፡፡
ኢትዮጵያ ያለችን አንድ አገር ሆና ሳለ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ኢትዮጵያ ጠል ጠላቶች ቅንጂት በዘመናት ሆኖ እና ተስምቶ የማይታወቅ ግፍ በህዝብ ላይ መድረሱን ግጭት እያሉ ችግርን ማቅለል የኢትዮጵያን ዉድቀት እና የህዝቦች ዕልቂት የሚገታ ሳይሆን የሚያበረታታ ነዉ ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ግጭት እና ክህደት ምን እንደሆነ አሳምሮ የኖረዉ እና የሚያዉቀዉ መሆኑን የሚመለከታቸዉ መገናኛ ብዙኃን እና ይመለከተናል ባይ አካላት ያስተዛዝባል እና እባካችሁ ዕዉነት ካላወቀችሁ ፤ዕዉነት መናገር አትችሉም እና ዝም በሉ ፡፡
ድፍን አለም እና አበሻ የሚመሰክሩት የገሀዱ ዓለም ዕዉነት ግን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የ “Eric Arthur” ጥቅስ “አንድን ህዝብ ለማጥፋት የራሱን ታሪክ ፣ወግ እና ማንነት ንፈገዉ/አሳጣዉ ”( The most effective way to destroy people is to obliterate & deny their understanding of their own history. የሚለዉን መሰረት ያደረገ የአጥፍቶ ጠፊዎች የጥፋት ቃለ መኃላ (ማንፌስቶ) ከ1968 ዓ.ም. አስከ ዛሬ በተጨባጭ መታየቱ ከክህደት በላይ መገለጫ ቢኖር ያንሳል እንጂ አይበዛም፡፡
የጨዉ ክምር ሲናድ ሞኝ ይስቃል ፤ ብልህ ያለቅሳል እንዲሉ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ጠላት ህብረት ፈጥሮ ሲማስን ግጭት እያሉ ማደባበስ የት እንደሚያደርስ የሚያይ ያየዋል፡፡
ለእኛ ኢትዮጵያዉያን ጠላት ፊት ለፊት የሚመታ ሳይሆን ከጎን አለሁ ባይ በማሳሳት እና በአድር ባይነት ዕዉነትን የሚሸጥ የህዝብ ጠላት እና የግጭት አትራፊ ደላላ ብቻ ነዉ ፡፡
አገር የሚፀናዉ በተግባር እንጂ በንግግር አለመሆኑን አዉቀን በሁለም አገሪቷ ወሰን አገር ለማፍረስ እንደ አሸን የሚርመሰመሰዉን ጠላት ፀረ -ኢትዮጵያ ከኃዲ መሆኑን በመካድ ማለባበስ የኢትዮጵያን ሠላም፣ አንድነት እና የዜጎችን መከራ ጊዜ ከማራዘም ዉጭ የሚያስገኘዉ መፍትሄ ባለመኖሩ “በሽታን የደበቀ…..” እንዲሉ ፵( አርባ ) ዓመት ማድበስበስ ከቁም መበስበስ አይለይም፡፡
“አንድነት ኃይል ነዉ ”