የኢትዮጵያ ቋሚ ታሪካዊ ጠላቶች ኢትዮጵያዊነት እና ኢትዮጵያ የጥላቻ መነሻ እና መድረሻ ማድረጋቸዉ የሚገርም ነዉ ፡፡
የሚያሳዝነዉ ግን የክፋታቸዉን ክርፋት እና ጥቃት ለብሄራዊ ዉድቀት እና ሞት የደስታቸዉ ምንጭ ሆኖ ቀጥሏል ፡፡
ትናንት ኤርትራ ከእናት አገር እንዳትለይ እና ሁለቱም ህዝቦች ከጥላቻ ይልቅ የፍቅር አቻ ፤ከመለያየት አንድነት ቢከተሉ መልካም መሆኑን ህዝብ ቢናገሩም ሰሚ አጥተዉ የኤርትራን ኢትዮጵያዊነት የሚሻ መንገዱን ጨርቅ አሉን …አለን የኢትዮጵያ እና ህዝቦች ጠላት የነበሩ ፤ያሉ እና የነበር፡፡
ኢትዮጵያ የብዙኃን አገር የባህር በር ማጣት የለባትም ቢያምስ አሰብ ሲባል ፉፁም ፀረ ኢትዮጵያ እና ህዝቦች አሰብን መርቆ የግመል መፈንጫ ነዉ በሚል የኢትዮጵያን ጉዳይ ለሞኝ ያብቃችሁ ብሏል የእኛዉ አሊባባ መሪ የነበረዉ ፡፡
ቀጠለ እና በሴራ የበሬ ግንባር በማትኃል አንድ አይዉል ባድሜ ላይ የሴራ ፖለቲካ ለማስቀጠል ሲባል በኢትዮጵያ ታሪክ ሆኖ ማይታወቅ የዜጎች ሞት ይህም ከሰባ ሽ አስከ መቶ ሽ በአንድ ዓመት የወንድማማቾች ሞት እና ዕልቂት ምክነያት ሆኗል ፡፡
ይህ በነበረበት ሁነት ከአራ ዘጠኝ መቶ ሠባዎች ጀምሮ አስከ ዛሬ በጉልበት እና በማን አለበኝነት በዉስጥ እና ዉጭ ኢትዮጵያ ጠላቶች ለእነርሱ ትልቅ ለኢትዮጵያ እና ለዓማራ ህዝብ ምንም የሚሉትን የወልቃይት ፣ራዕያ እና መተከል ምንም ያልሆነ እንዲያዉም የብቀላ መሳሪያ በማድረግ ቀጥለዉበታል፡፡
የሀምሌ ፭ ቀን ሁለት ሽ ስምንት ዓመተ ምህረት የማንነት እና የህልዉና ንቅናቄ ግለት ለማዳፈን ጥልቅ ተሀድሶ በሚል ሰበብ በሁለት ሽ ዘጠኝ ክረምት ወራት መጨረሻ ጥልቅ ተሀድሶ ስም የማዕከላዊ እና አዲስ አበባ ቅጥር ሠራተኞች ጋር ከፍተኛ ግብግብ የነበረበት የሁለት ሳምንት ስብሰባ ሲካሄድ የማንነት እና የድንበር ወሰን ጥያቄ ቅወቧል፡፡
ትናንት የነበሩት እና ዛሬም ኢትዮጵያ ጠል ፖለቲከኞች እንደዛሬዉ ያኔ ጎንደር ሲባል ጎንደር ለሀረር ምኑ ነዉ ሲሉ ፤ ወልቃይት ፣ራያ እና መተከል የሞት ቀጠና የመሆናቸዉ የፍትህ እና የህልዉና ጉፋይ ሲባሉ የሚሰጡት መልስ ኢትዮጵያዊነት እና ህዝባዊነት የጎደለዉ የምን አገባኝ እና ምን አለብኝ የድፈረት እና የንቀት ምላሽ ነበር ፡፡
ይህ አልበቃ ብሎ ዛሬም በታሪክ በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የደረሰዉን ዉርደት ፣ ጥቃት ፣ስደት እና ሞት ለኢትዮጵያ ጠሎች የስልጣን ጊዜ ማራዘሚያ የሚደረግ ገፀ በረከት የሆነ አስከሚመስላቸዉ በኢትዮጵያ ህዝብ መቃብር ላይ ይፏልላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ በማንነቱ(ኢትዮጵያዊነት) ከሶስት አስርተ ዓመታት በላይ የደረሰበትን እና እየደረሰበት ያለዉን ሁለንተናዊ ጀምላ መገለል እና መገደል እያሳነሱ በህዝብ ቁስል መርዝ የሚነሰንሱ ትናንት በጎጃም ጉዳይ ጎንደር ፤ በኢትዮጵያ ጉዳይ ኢትዮጵያዊ አያገባዉም ባዮች ዛሬ በህዝብ ነፃነት እና ማንነት ተጋድሎ ቢያላግጡ ምን ይገርማል፡፡
የሚገርመዉስ ትናንት አገር እና ህዝብ ክደናል ፤ በጥቅም እና በከንቱ ዉዳሴ የአገራችንን ጥቅም አሳልፈን ሰጥተናል ብለዉ ተፀፅተዉ ይቅር ብለዉ ካሳ ለመክፈል ከህዝብ ፊት ሲንበረከከኩ ነበር ፡፡
በዓማራ እና የኢትዮጵያ የዘመናት የማንነት እና ሉዓላዊነት ጥያቄ ላይ ትናንት ኤርትራን፣ የባህር በር፣ የኢትዮ-ሱዳን ድንበርን፣ የዓማራ ህዝብ የህዝብ ጠላት በማለት ኢትዮጵያዊ መሰርት ለማናጋት ከዚያ አስከ ዛሬ ተግተዉ ከሚሰሩት በጥላቻ እና በከንቱ አቻ በሽታ ከሚሰቃዩት ፍትህ መጠየቅ ታሪክን እና የኋላ ማንነትን አለማወቅ ነዉ ፡፡
የሚያሳዝነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ዓማራ የህልዉና ፣ የማንነት ፣ የግዛት አንድነት እና የግለሰብ ነፃነት አስቀድሞ ከታሪክ እና ከህግ ማዕቀፍ ዉጭ ጥላቻ እና የበታችነት ትብታብ በወረሰዉ ዱለታ/ሴራ በቁሙ ገድለዉ ከቀሙት ዛሬም ነፃነት ማለቱ ነዉ ፡፡
ነፃነት በዉሳኔ ለዚያዉም ከጠላት ሳይሆን በህብረት እና በፅኑ ዓላማ ማስተዋል ባለበት ኃይል እና ኃይል ነዉ ፡፡
ለዚህም ነዉ አንድነት ኃይል ነዉ ኃይልም የጠላት መንበርከኪያ አለት ነዉ ፡፡ የኃይል ሚዛን ሲያጋድል ጠላት ቀርቶ ወዳጂ ጠላት ሊሆን ይንሸራተታል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በህይወት ቤዛ፣ በአጥንት ክስካሽ ፤ በደም ፍሳሽ በጎንደር እና ወሎ የተገኘዉን የነፃነት ጭላንጭል ዕዉቀና፣ የስራ ማስኪያጃ ገንዘብ…….ብሎ ርምጃን መግታት ወደፊት የሚደረገዉን የህልዉና እና ዕድገት ጉዞ ለአፍታም ሊያዘናጋ አይገባም ፡፡
የማንኛዉም ሀብት ምንጭ ህዝብ ነዉ በመደበኛ ሆነ በሌላ መንገድ ከግብር ፣ቀረጥ…የሚገኝ የአንድ አገር ወይም አካባቢ ገንዘብ ምንጭ ህዝብ አስከ ሆነ በተለይም እንደ ወልቃይት እና ራያ አካባቢ ያሉትን ለማልማት ከሌላ አካል መጠበቅ የተገኘዉን ነፃነት መፋቅ ነዉ ፡፡
እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ነኝ ባይ በቀን አምስት ብር ለዕድገት ቢመድብ ኢትዮጵያን አይደለም አፍሪካን መለወጥ ይቻላል፡፡
እኮ እንዴት ነዉ ጎመን ከዉጭ የምታስገባ ኢትዮጵያ ሁመራ ፣ራያ፣ መተከል…..የመሳሰሉ ጠፍ መሬት በበጀት መኖር ፤አለመኖር እየተባለ ጦም ማደር ለማን ይበጂ ይሆን ፡፡
አገር የሚለማዉ በሰዉ ለዚያዉም በራሱ ዜጎች እንጂ በጠላትም ሆነ ጠላትነቱ በማይነገር ወዳጂ ፤ጎረቤት አለመሆኑን አዉቀን ለረሳችን ህልዉና እና ዕድገት እንደ ሰንሰል ተጋምደን ለእኛ እና እኛ ዘብ እንቁም፡፡
ኢትዮጵያን መስርተዉ ሰርተዉ ያቆዩን ኢትዮጵያዉያን እንጂ ጠላትም ሆነ መንግስታት አልነበሩም ፤አይደሉም ፡፡
እናም እኛ እንደ ህዝብ ከባርነት እና ድህነት ቀንበር ጫንቃችን የሚላቀቀዉ በህብረት እና አንድነት መስራት እንጂ ለህልዉና ጠንቅ ከሆኑ ጠላቶች ነፃነት መጠበቅ የጥልቅ ድንቁርና ቁራኛነት ነዉ ፡፡
“የየትኛዉም አገር እና ህዝብ የዕድገት እና ስልጣኔ ምንጭ ህዝብ ብቻ ነዉ ፡፡”
“አንድነት ኃይል ነዉ ”
ማላጂ