ባምንስቲ ላይ መወሰድ ያለበት ቀጣይ እርምጃ

አምንስቲ ኢንተርናሽናል (Amnesty International) በወልቃይት ላይ ያቀረበው ከወያኔወች የበለጠ ወያኔያዊ አጭቤ ዘገባ (fake report) የአማራን ሕዝብ ክፉኛ እንዳስቆጣ ተገንዝቧል፡፡  ስለዚህም፣ ዓላማውን ሳይሆን ዘዴውን ይለውጣል፡፡  የአንግሊዝን መሠሪነት በደንብ ማወቅ የሚገባው እዚህ ላይ ነው፡፡  እንግሊዝ ኃይል ስታሳየው የሚጥመለመል፣ የተዳከምክ ስትመስለው የሚናደፍ ዕባብ ነው፡፡

የእንግሊዙ አምንስቲ ኢንተርናሽናል፣ በዘገባው የተቆጣውን የአማራ ሕዝብ ለመደለል ሲል ወያኔና ኦነግ በአማራ ሕዝብ ላይ ስለፈጸሙት ወንጀል በገደምዳሜ የሚጠቅስ ዘገባ ቢጤ በቅርብ ቀን ውስጥ እንደሚያወጣ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡  ይህ የሚያደርገው ግን በአማራ ሕዝብ ላይ ስለተፈጸመው ዘርተኮር ጭፍጨፋ ለማውሳት አስቦ ሳይሆን፣ ሚዛናዊ በመምሰል በወልቃይት ላይ ያወጣውን ዘገባ የበለጠ ክብደት ለመስጠት ነው፡፡

ስለዚህም የአማራ ክልል አመራሮች፣ ለአማራ ሕዝብ ብለው ሳይሆን፣ ለራሳቸው ቆዳ ሲሉ የአምንስቲን ቀጣይ ሴራ ከወዲሁ ማክሸፍ አለባቸው፡፡  በአማራ ላይ ስለተፈጸሙ ጥቃቶች መረጃወችን ስጡኝ ሲላቸው፣ እኛ የራሳችን የሰብኣዊ መብት ድርጅት አለን፣ አንተ ምን ቤት ነህ፣ የአፍሪቃውያን የሰብኣዊ መብት ጠበቃ አድርጎ የሾመህ ማነው፣ …. በማለት አብጠልጥለው መመለስ አለባቸው፡፡  (ይህን ስል ግን የአምንስቲን ፀራማራ ዓላማ ለማክሸፍ እንጅ፣ ኦነጋውያን በበላይነት የሚቆጣጠሩትን የጦቢያን ሰብዓዊ መብት ድርጅት በማመን እንዳልሆነ አንባቢ እንዲረዳልኝ እፈልጋለሁ፡፡)

አምንስቲ እና አምንስቲን የመሰሉ በሰበኣዊ መብትና በዲሞክራሲ ሰበብ የምዕራባውያንን አጀንዳ ለማራመድ የተቋቋሙ ድርጅቶች የሚያቀርቧቸው ዘገባወች ተዓማኒነት ሊኖራቸው የቻለው፣ መዋሸት በሚፈልጉት ውሸት ላይ ከአፍሪቃውያን መንግሥታት የሚያገኟቸውን መረጃወች እዚህም እዚያም ጣል፣ ጣል በማድረግ ውሸታቸውን ወደ ግማሽ ውነት (half-truth) ስለሚለውጡት ነው፡፡  ስለዚህም እነዚህን መሠሪ ድርጅቶች እርቃናቸውን ማውጣት የሚቻለው ከነሱ ጋር አለመተባበር ብቻ ሳይሆን ጭራሹንም አናውቃችሁም በማለት ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትላልቆች ታናናሾችን ያስተምሩ፣ ሁላችንም ለሕዝባዊ ውይይት እንነሳ!! - ከበየነ ከበደ

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

2 Comments

  1. Well, it is the right thing to challenge the report and the recommendation of the organization that may be thought that it has a wrong and misleading elements in it with a substantive and defendable way of doing things !!!
    However, I reasonably and strongly want to argue that 1) Any one or any entity that might involved in doing some sort of criminal or inhuman act must be responsible and accountable regardless of its ethnic or political identity!
    2) I also want to reasonably and strongly argue that standing against the report but not also against the very notoriously criminal ruling circle of our own is totally and embarrassingly absurd !!! It sounds just like saying that nobody or no entity should be concerned about our political elites who have killed and keep killing the generation !! Absolutely absurd if not disgraceful !!!

  2. Mesfin Arega we thank you for your relentless contribution to your country. It is also advisable Ethiopian loving individuals and organizations to march to Amnesty’s office to ashame them for thier partisan report.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share