ሙሲባው አብይና የመጅሊሱ ችግር – ቢቢኤን

March 27, 2022
Abiy Ahymed
ህወሃት መዳፍ ስር የነበረው መጅሊስ ህዝባዊ እንዲሆንና የመንግስት ጣልቃ ገብነት እንዲያበቃ የተቻለንን ሁሉ አድርገናል። ያኔ በዘመነ ህወሃት ከመንግስት ጋር በመተባበር ሙስሊሙን ሲያስመቱ የነበሩ ሁሉ «የብስራት ዜና ተሰማ» የሚል መውጫ ቀዳዳ ተሰጣቸው።ለሐጢዓታቸው ማስተስረያ «እርቅ» ላይ መሰረት ያደረግ አንድነት እውን ይሆን ዘንድ ይሰራሉ ተብሎ ሲጠበቅ ‹የለመዱት ልማድ ያሳድዳል ከማእድ› ሆነና ነገሩ በኢህአዴግ ቁጥር ሁለት (ብልጽግና) እየታገዙ ሙስሊሙን ማሀረሰብ ማተራመሱን ቀጠሉ።
ችግሩን መሸፋፈንና በአንድ አዛውንት ላይ መጫኑ አያዋጣም።ችግሩ የመዝሃብ ጉዳይ አይድለም።ችግሩ የድሜ ባለጸጋ የሆኑ ግለሰብ (ግለሰቦች) በብቃት የሚተውኑት አይደለም።ችግሩ ሙስሊሙን ማህበረሰብ ለዘመናት በማሽመድመድ እንደ ብዙኋንነቱ በአገሩ ሁለንተናዊ የዲሞክራሲ መዋቅር ውስጥ ተጠቃሚ እንዳይሆን የሚፈተል ሴራ መሆኑ ነው።ችግሩ ሲሶ መንግስትን ተቀራምተው የነበሩ የቢሮክራሲው አካላት ዛሬም ሁለተኛ ዜጋን ለመፍጠር የሚያደርጉት መፍጨርጨር ነው። ሙስሊሞች በበዙባቸው ክልሎች በውጭ እርዳታ መስፋፋት የሚሹ ሐይሎችና ይህንን ለማስፈጸም የሙስሊሙ ማህበረሰብ አካላትን ተባባሪ (Trojan horse) በማድረግ እየተቅለሰለሰ የሚሰራው Abiy Ahmed Ali ነው ችግሩ።
ወደ ስልጣን ከመጣበት ግዜ ጀምሮ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ለማናገር ፈቃደኛ ያልነበረው አብይ «ድምጻችን ይሰማ» የሚለውን ቃል ከአፉ ያወጣው ዘንድ ብዙ ትችት ደርሶበታል።ዱባይ ላይ «ሱኒ ሰለፊ» ብሎ ከቀላቀለ በሗላ ስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ሔዶ «ድምጻችን ይሰማ» የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ግዜ መተንፈሱ የሚዘነጋ አይደለም።( https://tinyurl.com/52uxmz7s ) ብልጽግና በዘንድሮው ጉባኤው ላይ ለውጡን አስመልክቶ ሲዘግብ ለትግሎች ሁሉ መሰረት የሆነውን «ድምጻችን ይሰማን» ነጥሎ መተው ምንን ያሳያል?
ሙሲባው አብይ አህመድ አለም በአድናቆት የሚዘክረውን የሙስሊሙ ትግል አምኖ ከሚቀበል የሙስሊሙን ትግል ሲመሩ ከነበሩ የመስዋ እትነት ተምሳሌቶች ጋር ከፊት ለፊት እየተቅለሰለሰና እየተቃቀፈ ከኋላ በጩቤ ቢወጋ ይመርጣል።ስለዚህ የመጅሊስን ችግር ስናስብ አብይ አህመድ ተልእኮውን ለማስፈጸም የሚጠቀምባቸውን የዋሃን እናስተውል።ችግሩን ለእድሜ ባለጸጎች ትከሻ ላይ መቆለል ሳይሆን እነዚህን የእድሜ ባለጸጎች መጠቀሚያ በማድረግ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ መከፋፈል የሚፈጥረውን
የትላንትናውን ሙስሊም ተጠያቂ ማድረጉ ግድ ይላል።
አብይ አህመድ የፈተለውን ማሰሪያ ገመድ በአንድ የስልክ ጥሪ ወይም በመልእክተኛ ይፈታዋል።ግን አብይ የመጅሊስን ጉዳይ ከሚፈታ፣ድምጻችን ይሰማን አምኖ ከሚቀበል የፎቶ አጋጣሚ የሚፈጥርለትን ማንኛውንም ትርኢት ከመተግበር ወደ ኋላ አይልም።ምን አልባትም የሸረባቸው ሴራዎች ሁሉ ካልሰሩለት የመጅሊሱን ችግር የፈታ መስሎ «የብስራት ዜና ተሰማ ቁጥር ሁለትን» ከመተወን ወደኋላ የማይል አይን አውጣ መሆኑን ልብ እንበል።ነገሮች አህያውን ፈርቶ ዳውላውን እንዳይመስሉ ጣቶች ወደ ሙሲባው አብይ አህመድ ይጠቆሙ።
ልብ ያለው ልብ ይበል!

ቢቢኤን የናንተው ድምፅ

1 Comment

  1. አህመዲን ጀበል ነህ? እስላም ያላገኘው ምንድነው የሚያስፈልገውስ ምንድነው? በሀጅ ሙፍቲ ቦታ አስቀምጠውህ ካልዘረፍክ ነብስህ እረፍት አታገኝም። እስቲ ይሄን ህዝብ ለቀቅ አድርገው ድምጽህ ካልተሰማ ጥሩ ማይክራፎን ከሳውዲ አስመጣ። አረብ አገር በአንተ ዘመዶች የሚሰቃዩትን ወገኖቻችንም አስባቸው ጤና ነሳኸን ሰውም ጠላህ መጨረሻህ አያምርም እንደ ተስፋዬ ገአብ መሆንህ አይቀርም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

277548572 3114325085553191 6439083434222111162 n
Previous Story

ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ዐማራ ጨቋኝ ነው አለች (ዘ-መቀጣዋ)

ezema 1 2
Next Story

በሱማሌ ክልል በ‹‹ቦምባስ›› ከተማ በተፈጠረው ግጭት አፋጣኝ ፍትህ እንዲሰጥ (ኢዜማ)

Latest from Blog

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት

የኢካን ዓላማ በኔዘርላንድ የሚኖረውን ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና ኢትዮጵያውያንን ኮምዩኒቲይ የማሰባሰብ ሳይሆን የመከፋፋልና የማዳከም ተልኮን ያነገበ ነው።

አገር ! ለየአንድ ሠው ቋንቋው፣ ልማዱ፣ ባሕሉ፣ እምነቱ፣ አስተሳሰቡ፣ ወጉና በአጠቃላይ እሱነቱና ማንነቱ የሚከበርበት ብቸኛ ሥፍራ ነው። ኢትዮጵያውያንም በስደት በሚኖሩባቸው አገራት ሁሉ እነኝህን በስደት ያጧቸውን የግልና የጋራ ማንነቶቻቸውን በአንድ ላይ ሆነው ለመዘከር
Go toTop