March 28, 2022
2 mins read

በሱማሌ ክልል በ‹‹ቦምባስ›› ከተማ በተፈጠረው ግጭት አፋጣኝ ፍትህ እንዲሰጥ (ኢዜማ)

ezema 1 2
ezemaመጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)የሰው ህይወት መጥፋቱንና በዜጎች ላይም የአካል ጉዳት ማጋጠሙን ታማኝ ከሆኑ ምንጮች መረጃ ደርሶናል፡፡
በቦምባስ ከተማ ሊካሄድ በነበረው የአኪሾ የጎሳ መሪ ምርጫ ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት የፀጥታ ኃይሎች ተመጣጣኝ ያልሆነ ኃይል በመጠቀማቸው የሰው ህይወት የጠፋ ሲሆን፤ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

በክልሉ በተለያዩ ጊዜ ማኅበረሰቡን ያሳተፈ የጎሳ ምርጫ የሚደረግ ሲኾን በቅርቡ ሊደረግ የነበረው የአኪሾ ጎሳ መሪ ምርጫ ድብቅ የፖለቲካ አላማ ያላቸው አካላት ፍላጎታቸውን ለማሳካት ባደረጉት ጥረት በጸጥታ አካላትና በሕዝቡ መሀከል ግጭት እንዲነሳ በዛም ደግሞ ንጹሃንን ተጎጂ ያደረገ ጉዳት ደርሷል፡፡

በሱማሌ ክልል በተለያየ ጊዜ የሰውና የመንግሥትን ንብረት ያወደመ፣ የሰውን ሕይወት የቀጠፈ ግጭት ከተፈጠረ በኋላ የግጭቱ መነሻ ምን እንደሆነ ሳይጣራ፣ አጥፊዎች ተለይተው ለህግ ሳይቀርቡ፣ የፍትህ ሥርዓቱ አስተማሪ የሆነ ቅጣት ሳያስተላልፍ በመንግሥት ኃላፊዎች እገዛ ጭምር ግልፅ ያልሆነ የእርቅ ሂደት መከናወኑ ግጭቶች እንዲደጋገሙ መንገድ ከመክፈቱ በተጨማሪ የክልሉን ሰላም ከቀን ወደ ቀን አስተማማኝ እንዳይሆን እያደረገው ይገኛል፡፡

የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከዚህ ድርጊት በስተጀርባ እጃቸው ያለበትና የሚመለከታቸውን አካላት ማንነት በማጣራት አፋጣኝ ፍትህ እንዲሰጥ እናሳስባለን፡፡ ግጭቱን ተከትሎ የቆሰሉ አካላት ተገቢ ሕክምና እንዲያገኙ፣ የሟች ቤተሰቦችም ተገቢውን ካሳ እንዲያገኙ እንጠይቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
መጋቢት 19 ቀን 2014 ዓ.ም

1 Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Abiy Ahymed
Previous Story

ሙሲባው አብይና የመጅሊሱ ችግር – ቢቢኤን

277538683 273424684980994 2024413168374354966 n
Next Story

‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎቹን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ ተካሄደ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop