April 3, 2013
6 mins read

የኢህኣዴግ ኣጀንዳና የኣማራ ተወላጆች መፈናቀል …..! (አብርሃ ደስታ፣ መቀሌ)

(አብርሃ ደስታ፣ መቀሌ)

አብርሃ ደስታ
የኢህኣዴግ ኣጀንዳና የኣማራ ተወላጆች መፈናቀል …..! (አብርሃ ደስታ፣ መቀሌ) 1

ህወሓት/ኢህኣዴግ ከሚከተለው ‘ኣብዮታዊ ዴሞክራሲ’ የተሰኘ የፖለቲካ ኣቅጣጫ (እነሱ ‘ርእዮተ ዓለም’ ይሉታል) ኣንፃር ‘የቡድን መብት’ ከ’ግል መብት’ ይቀድማል። በቡድን መብት እሳቤ መሰረት (በኣንቀፅ 39 የ’እስከመገንጠል መብት’ ታግዞ) ብሄሮች በየክልላቸው ያለ ሃብት (ለምሳሌ መሬት) በዋናነት እንዲቆጣጠሩ ያስችላል።

በዚ መሰረትም ‘የሌላ’ ክልል ተወላጆች በ’ሌላ ክልል’ መሬት የማግኘት መብታቸው ሲነፈጉ ይታያል። የኣማራ ተወላጆች ብዙ ግዜ ኑሮኣቸው ከመሰረቱበት ቀያቸው በኃልና በግፍ ሲፈናቀሉ እያየን ነው። በቡድን መብት መሰረት የኢትዮዽያ ሕጋዊ ዜጎች በገዛ ሀገራቸው መኖርያ መሬት ሲከለከሉ ማየት እጅግ ያሳዝናል። በሌላ በኩል በስልጣን ያለ ድርጅት (የራሱን ዜጎች እያፈናቀለ) መሬ ታችን ተቀባይነት በሌለው መንገድ ለዉጭ ዜጎች ሲቸረችር ይታያል። ዜጎቻችን በገዛ መሬታቸው ባዕድ ሁነዋል ። የሚገርመው ደግሞ ‘መሬት ኣይሸጥም ኣይለወጥም’ ከሚል ግራ የተጋባ ፍልስፍና መሬታችን ለውጭ ዜጎች የሚሰጠው በነፃ ሊባል በሚችል ሁኔታ መሆኑ ነው። (በነፃ የሚሰጥበት ምክንያት መሬት ተሸጠ እንዳይባል ነው)። የኣማራ ተወላጆች ከቀያቸው መፈናቀል የገዢው ፓርቲ የተሳሳተ ፖሊሲና ለህዝብ ያለው ንቀት የሚያሳይ ነው። ዜጎችን በማባረር (‘ሕጋዊ ያልሆኑ ኗሪዎች’ በሚል ስም) መሬት ለውጭ ዜጎች ሲሰጥ እነዚህ የሌላ ሀገር ዜጎች እንዴት ‘ሕጋዊ’ ሆኑ???

ሰዎች ከቀያቸው በሃይል (በግፍ በዘርሓረጋቸው እየተለዩ) ሲፈናቀሉ (ሲባረሩ) የከፋ የሰብኣዊ መብት ጥሰት ነው። ዜጎቻችን (ወገኖቻችን) ሲፈናቀሉ የሚደርሳቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊና ስነልቦናዊ ቀውስ (Helplessness) መገመት ኣይከብድም። ሁሉም ኢትዮዽያ ሊተባበራቸው ይገባል፤ መንግስት ይህን ተግባሩ እንዲያቆም ተፅዕኖ ማድረግ ኣለብን።
እኛም እየተፈናቀሉ ካሉ ሰዎች ጎን መሰለፍ ያለብን ይመስለኛል። ምክንያቱም (1) ወገኖቻችን ናቸው። እኛ ኢትዮዽያውያን ያልደረስንላቸው ማን መጥቶ ይረዳቸዋል? (2) ዛሬ በኣማራ ተወላጆች እየተፈፀመ ያለው ግፍ (ኣሁንኑ ካልቆመ) ነገ በእያንዳንዳችን እንደሚፈፀም ማወቅ ይኖርብናል። (3) የማፈናቀል ተግባሩ የብሄር ፖለቲካ ችግር ኣባብሶ የጥላቻ ፖለቲካ ስር ሰዶ የኢትዮዽያ ሀገራችን ኣንድነት የሚፈታተን ይሆናል።
የስርዓቱ ደጋፊዎች ይህንን ችግር ተረድታቹ በገዢው ፓርቲ Pressure ፍጠሩ ፤ ኣለበለዝያ ግን ችግሩ ሁሉም ዜጋ ይነካል። በተለይ የትግራይ ተወላጆች በግልፅ ተቃውሞኣችንን ማሰማት ኣለብን። ህወሓት /ኢህኣዴግ ከተግባሩ እንዲቆጠብ ማድረግ ወይ ተግባሩ እንዲያቆም በመቃወም ከነዚህ ተፈናቃዮች ጎን መሰለፍ ኣለብን። ምክንያቱም እነዚህ ተፈናቃዮች ብዙ ችግር እንደሚደርስባቸው የታወቀ ነው። ቂም መያዛቸው (በገዢው ፓርቲ ቅር መሰኘታቸው) ኣይቀርም። ገዢው ፓርቲ (ኢህኣዴግ) የህወሓት ስራ መሆኑ ይታወቃል። ህወሓት ስልጣን መያዝ የቻለው በትግራይ ህዝብ ትግል ነው (ህወሓት ህዝቦች ማፈናቀል ወይ መጨቆን እንዲችል ለማብቃት ባይሆንም)።
ስለዚ የኣማራ ተፈናቃዮች በህወሓት ተግባር ምክንያት በትግራይ ህዝብ ቅር ሊሰኙ ይችላሉ። እንዲህ ከሆነ ደግሞ ዛሬ በኣማራ ህዝብ እየተፈፀመ ያለው ግፍ ነገ በትግራይ ህዝብ መደረጉ ኣይቀርም። ግለሰዎች በስልጣን ለማቆየት ሲባል በሰለማዊና ንፁህ ዜጎች ግፍ እየተፈፀመ ዝም ብሎ መመልከት ተገቢ ኣይደለም።
ስለዚ ተቃውማችን ማሰማት ኣለብን። ደሞ የትግራይ ተወላጆች በኣማራ ክልል የሉም? የደቡብ ክልል ወይ ኦሮምያ ወይ ሌላ ክልል ተወላጆች በኣማራ ክልል የሚኖሩ የሉም ? የማፈናቀሉ ተግባር ካልቆመ መጨረሻው ምን ሊሆን ነው? ስለ ሌሎች ስናስብ ስለራሳችን እያሰብን ነው፤ ሌሎችን ስንተባበር ራሳችን እየተባበርን ነው። ተግባራችን ስንቃችን ነው።
ለዜጎች ቅድምያ እንስጥ!

 

 

Latest from Blog

የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው እና አሁን ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የሁለተኛ (ተፈራ ) ክፍለጦር ሰብሳቢ የነበረው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በክብር ተሰዋ። የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህሎና አደጋ ለመቀልበስ ያለ

ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል !

January 22, 2025
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

Go toTop