“የኦነግ ጭፍጨፋ ተብለው ከሚጠቀሱ ትራጄዲዎች መካከል አብዛኛዎቹ በኦነግ የተፈጸሙ አልነበሩም” – ከአፈንዲ ሙተቂ

ከአፈንዲ ሙተቂ

——
“ዳውድ ኢብሳ ሲሞት ጥሩኝ” በሚል ርዕስ በለጠፍኩት አነስተኛ ሐተታ ላይ ሁለት ዓይነት ተቃውሞዎች ቀርበውብኛል፡፡ አንደኛው “ኦነግ በአማራው ላይ የሰራውን ሴራ እና ሸፍጥ እያወቅክ ጥብቅና ቆመህለታል” የሚለው ሲሆን ሁለተኛው “የኦፒዲኦን ድርጅታዊ ህልውና አንኳሰስክ፤ አቶ አለማየሁንም ረገጥክ” የሚል ነው፡፡ ስለ ኦፒዲኦ የጻፍኩት አዲስ ነገር አይደለም፡፡ የድርጅቱ አባላት እራሳቸው በየአጋጣሚው የሚናገሩትን ነው በፌስቡክ የደገምኩት፡፡ በተለይ ደግሞ አባላቱ ከስራቸው ሲባረሩ፣ ወይ ደግሞ ከድርጅቱ ከድተው ወደ ውጪ ሀገር ሲኮበልሉ “ኦፒዲኦ የኦሮሞን ህዝብ ለማጭበርበር ሆን ተብሎ የተፈጠረ ድርጅት ነው” የሚል ጩኸት በማሰማት ነው የሚታወቁት፡፡ እነ ዮናታን ዲቢሳ፣ ዱባለ ጃሌ፣ ኢብራሂም መልካ ሲያደርጉት የነበረው ይህንኑ ነው፡፡ ነገር ግን እኔ የነርሱን ፈለግ በመከተል አይደለም እንዲያ ብዬ የጻፍኩት፡፡ ከነርሱ በፊትም እንደዚያ ስል ነበር፡፡
——
ኦነግን ለመጀመሪያ ጊዜ ካየሁበት ግንቦት 1983 ጀምሮ የድርጅቱን የፖለቲካ መስመር ስደግፍ ቆይቻለሁ፡፡ ዩኒቨርሲቲ ስገባ ግን ድርጅቱ በሚያራምደው ርዕዮተ ዓለምና በፖለቲካ ፕሮግራሙ ላይ ጥያቄዎች ማንሳት ጀመርኩ፡፡ በዋነኛነትም “የመገንጠል ፖለቲካው የኦሮሞን ጥያቄ የትም አያደርሰውም” የሚል ሀሳብ አነሳሁ፡፡ እንዲሁም የሚከተላቸው ስትራቴጂዎቹ ፍጹም ሊዋጡልኝ አልቻሉም፡፡ በዚህም ከኦሮሞ ወንድሞቼ ጋር ብዙ ጊዜ እነታረክ ነበር፡፡ በተለይም በዚያ ጊዜ ኦነግን መተቸት Taboo ተደርጎ ይቆጠር ስለነበር ከቅርብ ጓደኞቼ ጭምር እስከመጣላት ደርሰናል፡፡ እናም ከ1990 ጀምሮ የድርጅቱ ተቃራኒ እንጂ ደጋፊ አይደለሁም፡፡

እንዲህ በመሆኑ ግን ድርጅቱን በሐሰት መክሰስ ያለብኝ አይመስለኝም፡፡ ድርጅቱን በሰራው ጥፋት ብወቅሰው ማለፊያ ነው፡፡ ባልሰራው ወንጀል መክሰስ ግን ለማንም የሚበጅ አይሆንም፡፡ እንደምሳሌም ኦነግ የሚከሰስባቸውን ጭፍጨፋዎች እንመልከት፡፡ በደኖ፣ አርባ ጉጉ፣ ወተር፣ አረካ፣ አሰቦት ገዳም ወዘተ…

እነዚህ ጭፍጨፋዎች መከሰታቸው ሁላችንንም ያሳዝነናል፡፡ አንድ ቀን እውነቱን ፈልፍለን የማውጣት ግዴታም ተጥሎብናል፡፡፡ ነገር ግን በርካታ ሰዎች በሁሉም ጭፍጨፋዎች ኦነግን ተጠያቂ ሲያደርጉ በጣም እገረማለሁ፡፡ በተለይም ዛሬ በህትመት ላይ የሌሉ ሁለት የግል ጋዜጦች ይህንን ፕሮፓጋንዳ እየደጋገሙ ሲያስተጋቡት ሳይ “ስለ የትኛው ሀገር ነው የሚያወሩት” እያልኩ እደነቅባቸው ነበር፡፡ እንዲህ የምለው ጋዜጦቹ የመረጃ እጥረት የነበራቸው መሆኑን በማወቄ ብቻ አይደለም፤ የጂኦግራፊ እውቀትም ያጠራቸው ስለሚመስለኝም ጭምር ነው፡፡ ለምሳሌ “አረካ”ን እንውሰድ፡፡ ይህቺ ከተማ የት ነው ያለችው? ኦሮሚያ ውስጥ ነው? ወይስ ሌላ ቦታ?

ይገርማል! አረካ ማለት በደቡብ ክልል በወላይታ አውራጃ ከሶዶ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ያለች ከተማ ናት፡፡ እኔ እስከማውቀው ድረስ ኦነግ እዚያ ድረስ ሄዶ ሀገር አላስተዳደረም፡፡ “አረካ የኦሮሚያ ግዛት ናት” ብሎ የሚያውቅም አይመስለኝም፡፡ እናም ጂኦግራፊን በትክክል የሚያውቅ ጋዜጠኛ የአረካውን ግጭትና ጭፍጨፋ ለኦነግ አይሰጥም ነበር፡፡ በተጨማሪም የአረካው ግጭት የደረሰው ኦነግ የሽግግር መንግሥቱን ለቆ ከወጣና በእጁ የነበሩት መሬቶች በሙሉ በኢህአዴግ ቁጥጥር ስር ከወደቁ በኋላ ነው፡፡

የአረካው ግጭት በሽግግሩ ዘመን ለነበረው የተወካዮች ምክር ቤት የውይይት አጀንዳ ሆኖ እንደቀረበ ይታወሳል፡፡ በከተማዋ ያለቁት የ31 ሰዎች ግድያ በመከላከያ ሰራዊቱ እንደተፈጸመ መንግሥቱ በይፋ አምኗል፡፡ ዳሩ ግን ለግድያው የተሰጠው ምክንያት በጣም አነጋጋሪ ነበር፡፡ መንግሥት ያቀረበው ምክንያት “ሰልፈኞቹ የተገደሉት ቦንብ በመወርወራቸው ሳቢያ የመከላከያ ሰራዊቱ ራሱን ለመከላከል በወሰደው እርምጃ ነው” የሚል ነው፡፡ ይሁንና ይህንን ምክንያት ብዙዎች አልተቀበሉትም፡፡ ብዙዎች እንደተጠራጠሩት እስከ ዛሬ ድረስ ቆይቷል፡፡ በነገራችን ላይ በአረካ የሞቱት የቀድሞ መንግሥት ወታደሮች ነበሩ፡፡ እነዚያ ወታደሮች “የጡረታ መብታችን ይከበርልን” በማለት የተቃውሞ ሰልፍ በማድረጋቸው ነው ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር የተጋጩት፡፡
——–
በሚያዚያ ወር 1984 በወተር ከተማ በተካሄደ ጭፍጨፋ የሞቱትም በተመሳሳይ መልኩ በመከላከያ ሰራዊቱ እንደተገደሉ የሽግግር መንግሥቱ በወቅቱ አምኗል፡፡ ይሁን እንጂ በወተር የተገደሉት 230 ሰዎች በሙሉ ኦሮሞዎች እንጂ አማራዎች አልነበሩም፡፡ እነዚያ ሰዎች የተገደሉት ኢህአዴግ ከከተማቸው ወጥቶ ኦነግ ወደ ከተማዋ እንዲመለስ በመጠየቃቸው ነው (ወተር ለአንድ ዓመት ያህል በኦነግ ቁጥጥር ስር ነበረች፤ ኦነግ ከከተማዋ ሲወጣ ኢህአዴግ ገብቶባታል፤ ነዋሪዎቹ “እንደ ቀድሞው ጊዜያችን ኦነግ ወደ ከተማዋ ይመለስ” በማለታቸው ነው ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር የተጋጩት)፡፡ ጋዜጦቹ ግን “ኦነግ አማራዎችን ጨፈጨፈ” እያሉ ነበር የሚዘግቡት፡፡
——-
በ1984 (ወሩን አላስታውሰውም) በአሰቦት ገዳም በተካሄደ ግድያ ሰባት መነኮሳት ሞተዋል፡፡ ይህንን ግድያ የፈጸሙትም በወቅቱ የአሰቦት ከተማን ለትንሽ ጊዜ ተቆጣጥሮ የነበረው የኦሮሞ ነጻነት እስላማዊ ግንባር (IFLO) ታጣቂዎች ነበሩ፡፡ ግድያው ስር ሳይሰድ በአፋጣኝ ያስቆሙት ደግሞ ኢህአዴግና ኦነግ ነበሩ፡፡ ሁለቱ ድርጅቶች አንድ ጥምር ኮሚቴ በማቋቋም በወሰኑት ውሳኔ መሰረት IFLO ከከተማው ተባርሮ አካባቢው በኢህአዴግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል፡፡
——
በአርባ ጉጉ የተፈጸመው እልቂት በሁለት ተጎራባች መንደሮች መካከል በተካሄደ ግጭት ነበር የተለኮሰው፡፡ እያደር ግን መርቲ ጀጁ እና አሰኮ የሚባሉ የአርባ ጉጉ ወረዳዎችን አዳርሷል፡፡ በግጭቱ የኦሮሞ እና የአማራ ተወላጆች በእኩል ደረጃ ተጎድተዋል፡፡

በአርባ ጉጉ ግጭት የራሳቸውን የፖለቲካ ትርፍ ለማጋበስ የፈለጉ ወገኖች እጃቸውን አስገብተውበታል ይባላል፡፡ በመሆኑም በውጤቱ ከሁሉም ግጭቶች የከፋ ሊሆን ችሏል፡፡ በዚህ ግጭት ከሁለቱም ወገን እስከ ስድስት መቶ ያህል ሰዎች መሞታቸው ይነገራል፡፡ ከመቶ ሺህ ያላነሰ ሰው ወደ ሀረርጌና ሸዋ ክፍለ ሀገሮች ተፈናቅሏል፡፡ ሆኖም ኦነግ በዚህ ግጭት ውስጥ እጁን ማስገባቱን የሚያረጋግጥ ፍንጭ እስከ አሁን ድረስ የለም፡፡ ኦነግ በወቅቱ በአርባ ጉጉ አውራጃ ምንም ይዞታ አልነበረውም፡፡ የመላው አማራ ህዝብ ድርጅትም ቢሆን በግጭቱ የከሰሰው ኦህዴድን (OPDO) እንጂ ኦነግን አልነበረም፡፡ በተለይም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የምዕራብ ሸዋ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ የነበረው ኮሎኔል ዲማ ጉርሜሳ ከግጭቱ ጋር ተያይዞ ስሙ በሰፊው ይነሳ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ በዚያን ጊዜ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ሐሰን ዓሊ ከእፎይታ መጽሔት ጋር (ግንቦት 1985) ባደረጉት ቃለ-ምልልስ “አቶ ዲማ ጉርሜሳ ንጹሕ ነው” በማለት ከመከላከላቸውም በላይ ለግጭቱ ዋነኛ ተጠያቂ ያደረጉት መአሕድን እንጂ ኦነግን አልነበረም፡፡

የግል ጋዜጦች ግን ነገሩን አራግበው በኦነግ ላይ አላከኩት፡፡ ነገሩን ሳያውቁት ቀርተው የተደረገ አይመስለኝም፡፡ አንዳንድ ጋዜጦች -ተከፍሎአቸው እንዲህ እንደሚያደርጉ በደንብ እናውቃለን፡፡
——–
የበደኖ ጭፍጨፋ! አዎን! ኦነግ ሊጠየቅበት የሚገባው ብቸኛው ትራጄዲ ይህኛው ነው፡፡ በርግጥም እልቂቱ በተፈጸመበት ወቅት በደኖ በኦነግ ቁጥጥር ስር ነበረች፡፡ የሞቱት ሀምሳ ያህል ሰዎች ለምን እንደተገደሉ ባይታወቅም አድራጎቱ በኦነግ ወታደሮች እንደተፈጸመ ድርጅቱ ራሱ አምኗል፡፡ ኦነግ በወቅቱ በወታደሮቹና በአዛዦቹ ላይ እርምጃ ወስጃለሁ ቢልም የተወሰደውን እርምጃ ምንነት አልገለጸም፡፡ በነገራችን ላይ በዚህኛውም እልቂት ከሞቱት መካከል ግማሽ ያህሉ ኦሮሞዎች ነበሩ፡፡
—–
ከላይ በዝርዝር እንዳስረዳሁት የኦነግ ጭፍጨፋ ተብለው ከሚጠቀሱ ትራጄዲዎች መካከል አብዛኛዎቹ በኦነግ የተፈጸሙ አልነበሩም፡፡ ኦነግ ሊጠየቅበት የሚገባው ብቸኛው ድርጊት በበደኖ የተፈጸመው ነው፡፡ የእውነት ቀን ሲመጣ ያንን ፋይል ማውጣታችንም አይቀሬ ነው፡፡ ይሁንና በኦነግ ያልተፈጸመውን ከርሱ ጋር አያይዞ መጻፍ ጥቅሙ ምን እንደሆነ ሊገባኝ አይችልም፡፡ እንዲያውም የያኔዎቹ የግል ጋዜጦች የሚያራግቡት ወሬ በተወሰነ መልኩ የኦነግ ጨካኝነትን ከመግለጽ ይልቅ “ኦሮሞ ጨካኝ ነው” የሚል እድምታ ለመፍጠር የታለመ ነበር የሚመስለው፡፡

እርግጥ የኦነግ ወታደሮች በብዙ አጋጣሚዎች ልዩ ልዩ የጭካኔ ተግባራትን ሲፈጽሙ ተስተውለዋል፡፡ እርሱን አንክድም፡፡ የነርሱ ገፈት ቀማሽ ሆኖ የዘለቀው ግን በአብዛኛው ኦሮሞው ነው እንጂ የሌላ ብሄረሰብ ተወላጅ አልነበረም፡፡ በተለይ አንዳንዶቹ የኦነግ ወታደሮች “ጎበና፤ ቢተምቱ.፤ ወዘተ..” ለሚሏቸው ግለሰቦች ምህረት አልነበራቸውም፡፡ እንዲሁም ተጻራሪ ድርጅት ሊያቋቁሙ ነው በሚል ፍርሃት አባላቶቻቸውን ጭምር እስከ መግደል ይደርሱ ነበር (የኦነግ የሀረር ቢሮ ሃላፊ የነበሩትን አቶ አራርሶ ወዳይን እና በመቻራ ከተማ የተገደለውን የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ካሊድ ሃጂ ኑራን መጥቀሱ ይበቃል)፡፡ ሆኖም ጋዜጦቻችን ድርጅቱ የፈጸመውን ማውራት ይተውና ድርጅቱ ያልፈጸመውን ወንጀል ይነግሩን ነበር! ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ማለት ይህ ነው፡፡

ለማጠቃለል ያህል እኔ ለኦነግ አልተከላከልኩለትም፡፡ አንዳች ጥብቅና አልቆምኩለትም፡፡ የጻፍኩት የማውቀውን ሐቅና የማምንበትን አቋሜን ነው፡፡ ይሁንና ይህ አባባሌ ኦነግን ከመፍራት እንዳይወሰድብኝ አደራ እላለሁ! አስፈላጊ ከሆነ በኦነግም የተፈጸሙ ስህተቶችና ጥፋቶችን አንድ በአንድ መዘርዘር እችላለሁ፡፡

ሰናይ ቀን ይሁንላችሁ!!

16 Comments

 1. Note: the below comment does not refer to the current OLF faction led by the patriotic Ethiopian G. Kemal Geltchu.
  Mr. Afendi, OLF/ODF anti Amhara sentiment is the same as its ideology god’s fathers shabiya and woayne. You skipped Assosa, but the first mass murder on ethnic Amharas started from there before the fall of Mengistu’s regime. It was orchestrated by OLF and shabiya accessing through Sudan under the blessing of the Sudanese. People were burnt to ash locked in a school. The following many killings parallels that brutality, including throwing people off cliff alive. That anti Amhara campaign is still on full fledge as we are witnessing on the pro OLF/ODF paltak rooms, Facebook pages and different blogs. I myself possess more than 200 hours voice recordings and screen shots from pro OLF/ODF Paltalk rooms targeting ethnic Amharas that reminds many of us the cold blooded murders of those days. We heard in a broad day light pro OLF/ODF scholars preaching for division, bloodshed and even denouncing intermarriages.
  Mr Afendi, you are trying to defend the indefensible. OLF/ODF never tried to refute these claims. They never produce any evidence to counter the video documented woayne claims. WHY??…..by the way, there are many living witnesses who escaped that brutality and all fingers point to OLF/ODF. Woyane was video recording it when OLF/OLF murders. Woyane never tried to stop it since both are Anti Mahara and anti Ethiopian unity entities. However, later woayne used the evidences to knock out OLF and forced it to surrender more than 30, 000 of its rag tagarmy without a single shot in one day operation. That effectively breaks OLF’s back bone and now the same folks are trying to play different game under different jerseys like ODF. However, we Ethiopians are aware of all these games and always out there to neutralize it. The spilled blood of innocent ethnic Amahras is crying for justice. Justice will be served soon or later!!!!….God bless Ethiopia….dooms day is near for criminals and haters!!!

 2. Dear Afendi,

  I think you forget to mention the Assosa Massacre which was perpetrated by OLF being driven by EPLF/TPLF from behind. Do not forget to include the Assosa genocide in the list of OLF hate led crimes.

 3. My Answer To Afebdi MuteQi

  አፈንዲ ሙተቂ “የኦነግ ጭፍጨፋ ተብለው ከሚጠቀሱ ትራጂዲዎች መካከል አብዛኞቹ በኦነግ የተፈጸሙ አለበሩም “።
  በሚል ርእስ ዘሃበሻ ላይ ላቀረበው ጽሁፍ የተሰጠ መልስ ።።https://zehabesha.info/archives/13572

  መልሱን ያዘጋጀሁት ቆራጡ የተማረው አስተዋዩ መሪያችን ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ በእጁ ከጻፈው ነው ።

  እንዲህ ሲል ይቀጥላል ።
  “አሁን በመቀጠል ላይ ያለው ጭፍጨፋ መንስዔ የሆነው የዐውራጃው የኦህዴድ ተወካይ የዐቶ ዲማ ጉርሜሳ የጭፍጨፋ ስልት በሚከተለው ሁኔታ እንደነበር ተገልጿል ።

  ፩ ፣ 1 , የዐውራጃው የኦህዴድ ተወካይ አቶ ዲማ ጉርሜሳ ግንቦት ፪፮፨፩፱፰፬ [26 1984] በአበምሳ ከተማና በኣካባቢው የሚኖሩትን የኦሮሞ ተወላጆችን ስብሰባ ከጠሩ በሆላ ኣሼ ፥ ኦዴ ፥ ዒመና ፥ ኣቡሌ በሚባሉ መንደሮች የሚኖሩ አማሮች ይገደሉ ብላችሁ ፈርሙ በማለት ትዕዛዝ ይሰጣሉ ከተሰበሰቡት የኦሮሞ ተወላጅ መካከል ሀጅ ቃሲም የተባሉ እጃቼውን አውጥተው ዕለረጅም ግዜ ኣብረን የኖርን እና የተዋለድን ስለሆን አንፈርምም ፥ የአማራ ህዝብ አይመታም መመታት ያለበት ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ነው የሚል አስተያየት በማቅረባቼው የኦህዴዱ ተወካይ በመናደዱ ሽጉጡን ኣውጥቶ የነፍጠኛ እረዳት ነህ በማለት ማስፈራራት ሲጀምሩ ስብሰባው የሀጅ ቃሲምን ሀሳብ በመከተል ተበተነ ።

  ፪ ፣ 2 , በማግስቱ በግንቦት ፪፯ ፩፱፰፬ [27 1984 ] አቡሌ የተባለው የዐማራ ተወላጆች መንደር በኦህዴድ የታጠቀ ሰራዊት ተኩስ ከተከፈተበት ቡሗላ መንደሩ በላውንቸር መደብደብና መነደሩ መቃጠል ሲጀምር ህዝብ ሂወቱን ለማዳን በየዐቅጣጫው መሸሽ ጀመረ ፤ ከሚሸሹትም መካከል ሀያ የሚሆኑ ህጻናት ሴቶችና አረጋውያን በዐቅራቢያቸው ከሚገኘው ቤተክርስቲያን አጥር ግቢ እንደተጠጉ በኦሮሞ ዘላን [ olf lemalet new ] እንዲከበቡ ተደርጎ ሁሉም እንዲታረዱ ተደረገ ፤ የገባንበትም ቤተክርስቲያን ከካህናቱ ጋር እንዲቃጠል ተደረገ በዐጠቃላይ የዐማራ መንደር የሆነው መንደር ሁሉ እንዲቃጠልና እንዲወድም ተደረገ በግምት ከ ፩፶ በላይ የሚሆኑ ቤቶች ተቃጥለዋል ።

  ፫ ፣ 3, የኦህዴድ ተወካይና የዐውራጃው የሽግ ግር መንግስት ተወካይ የሆኑት አቶ ዲማ ጉርሜሳም በመሪነታቸው ለወራሪው ሰራዊት “አማራን መጨረስ ዛሬ ነው” የሚል መሪ መፈክር በማሰማት ለዐውራጃው ትእዛዝ በመስጠት አበሳ የሚባለው የዐማሮች መንደር በዘላኑ እንዲከበብ አድርገው ህዝብ ከቤት መንደሩ እንዲቃጠል ተደረገ በዚህ መንደር ከነሂወታቸው በቤት ውስጥ እንዳለ የሞቱትን ሰወች ቁጥር ለማወቅ ባይቻልም በጠቅላላው ከ ፻ [100] ቤቶች በላይ ሲወድሙ ከቃጠሎው የተረፉት ፶ [50] የሚሆኑ ሰወች ተይዘው በጥይት እንዲረሸኑ ተደርጓል ።

  ፬ ፣ 4 , የዐቡሌ መደር ወሰንተኛ በሆነው አሼ በተባለው መንደር የሚኖረው አማራም በዐካባቢው የሚፈጸመውን ሰቆቃ እየተመለከተ መሸሻ በማጣቱ እየተጨነቀ የመንግስት ሀይል ይደርስልኛል እያለ በመንደሩ ሆኖ በመጠባበቅ ላይ እንዳለ የኦህዴድ ሰራዊት ደርሶ መንደሩን ከከበበ ቡሗላ የዐማራውን ትጥቅ በማስፈታት ከመካከላቸው ፪፭ [25 ] ሰወችን ረሽኖ የኦህዴድ ጦር ተከታታይ የሆነው ዘላን ጦር በዐቡሌ መንደር እንደፈጸመው ሁሉ በዐሸም መንደር የፈለገውን ጭፍጨፋ እንዲያካሂድ ለቆለት ሄዷል ። በዐሁኑ ጊዜ የዚህ መንደር እልቂት ውጤት ሪፖርት ባይመጣልንም የኦህዴድ ሰራዊት በቀዳሚነት አማራውን እየከበበና እየረሸነ ትጥቅ ሲያስፈታ እሱን የሚከተለው ዘላንም[olf] ማረድ ማቃጠል ነፍሰጡሮችን እየመረጠ ጽንስን ማግኘት መስለብና ሞራቸውን እያወጣ ማየት ስለሆነ ከዚህ የባሰ ድርጊት እንደማይፈጸም እናምናለን ።

  ፭ ፣ 5 , ከላይ የተገለጸው በዐንድ ቀን በዐቶ ዲማ ጉርሜሳ መሪነት በዐቦምሳ ፣ በዐቡሌ ፣ በዐበሳና አሸ በተባለው መነደር የተፈጸመውን ብቻ ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታ ይትባረክ በተባለው የኦህዴድ ተወካይ የሚመራው ጦር በተመሳሳይ እለት ግንቦት ፪፯ ፩፱፰፬ [27 1984] በሚከተሉት መንደሮች የሚከተለውን እልቂት ፈጽሟል ።

  ፭ ፣ ፩ ፣ 5,1 በጉና ወረዳ ሰርቢዩ አዲስ አለም ከተባለው ቦታ ፩፶ [150] ቤቶችን ሲያቃጥል ሁለት የታወቁ ሽማግሌወችን እጅ እግራቸውን አስሮ በዕሳት ውስጥ በመጨመር ከነሂወታቸው ተቃጥለው እንዲሞቱ ተደርጓል ።
  ፭፣ ፪ ፣5,2 በዚሁ ወረዳ ዋቂንትራ ከተባለው መንደር ፻ [100] ቤቶች ሲያቃጥል ከነሂወታቸው የተቃጠሉ ሰወች አይታወቅም ። ”

  የእኔ አስተያየት ሲቀጥል
  ____________
  ወንድሜ አፈንዲ ኦነግን መውቀስ እንደ ታቡ ይቆጠር ነበር ሲል ይጀምራል ። ከሰባት ወረ በላይ የሆኑ ነፍሰጡሮችን እየመረጠ ሽል እየሰለበ ለድርጊቱ ደግሞ ከእብደቱ የሚስቅን [ፕሮፌሰሩ በእጁ ከጻፈው እንዳነበባችሑት] ኦነግ መውቀስ አሁንም ትክክል ነው ብየ ነው የማምነው ።

  ሌላው ወያኔ የጻፈው ; ያወራው መረጃ ሳያስፈልገን ኦነግ በዐማሮች ላይ የፈጸመው ድርጊት በራሱ የተጋነነና የሰው ልጅ ሊገምተው ከሚችለው አረመኒያዊ ድርጊቶች የራቀ ነው ። ወያኔ በተለያዩ ቦታወች ላይ አማሮች ሲጨፈጨፉ ወያኔ በራሱምም ሲጨፈጭፍ ሌሎች ጎሳወችም [በጎሳ የተደራጁ የጎሳ መሪወች ያስታተቋቸው] ሲጨፈጭፉ አነግ ነው እያለ ያቀርብ ነበር ። ያን ሁሉ አንፈልገውም የመረጃ እጥረት ሳይሆን የሰሚ እጥረት ብቻ ነው ያለን ።

  አፈንዲ አረካ የሚባል ሰምቼው የማላቅ የቦታ ስም ጠቅሶ ያ ውሸት እንደሆነ ኦነግ ባካባቢው እንዳልነበረ ይናገርና ውትርን አርባጉጉን በደኖን ወዘተ ብሎ ባጭሩ ይዘጋዋል ።
  ይቀጥልና አፈንዲ ትልቁን ስተት ሲሳሳት እንዲህ ይላል ውትር ውስጥ የተገደሉት 230 ኦሮሞች ኦነግን በመፈለጋቸውና ወያኔን በመጥላታቸው ወያኔ የፈጸመባቸው ነው ሲል አቅርቦታል እኔም ሲደንቀኝ እዚያው አካባቢ አፍንጫቸው የተፎነኑ ፣ ብልታቸው የተሰለቡ ፣ ጆሯቸው የተቀረጡ ሂወታቸውንም ያጡ አማራወች ነበሩ ። ከነዚህ ተቀማጭነቱን በሆላንድ ሀገር ያደረገው ዶክተር አሰፋ ነጋሽ ከቤተሰቦቹ የዚህ ሰላባ የሆኑ ሰወች አልሉ ። እና አፈንዲ ዶክተር አሰፋን ኦሮሞ ነው ሊለኝ ነው ። ?? ወይንስ እነኛ “አማርቲቲን ነማሚቲ ” [አማሮች ሰው አይደሉም ] በሚለው የኦነግ መፈክር ሰው አይደሉም ብለን እንስማማ ። ??

  አርባጉጉን ሲገልጸው እንዲህ ይለናል አማሮችም ኦሮሞችም የተጨፈጨፉት እኩል ነው ይለናል ። ጭፍጨፋ ጣሊያንም መቶ ጨፍጭፎናል ብዙወችንም አማሮች መጥፎወች ናቸው ሲል በጥላቻ ይሰብክ ነበር ። አርባጉጉ ላይ ኦነግ አስተዳዳሪ ስላልነበር በጊዜው ተጠያቂ አይደለም ይለናል ፕሮፌሰሩ በወቅቱ የጻፍትን ስናይ አሁን በሂወት ያሉ ሰወችን ስንጠይቅ ወያኔ ትጥቅ ሲያስፈታና አሉ የትባሉ ህዝብን ያደራጃሉ ተነስ ይላሉ የተባሉ ሰወችን መርጦ ከረሸነ ቡሗላ ለኦነግ ነበር ትቶለት የሚሄደው ። ኦነግም የዛሩን እናቶችን ሽላቸውን እየሸለበ ያሽካካ ነበር ።
  አፈንዲ የማያውቀው ነገር ኦነጎች በፓልቶካቸው ስም እየጠሩ “እንዲህ አደረግናት ገደል ጣልናት እከሌን እንዲህ አደረግነው ” እያሉ ከዐመታት በፊት በግልጽ ነበር የሚናገሩት ይህ ድምጽ ደግሞ ከዶክተር አሰፋ ነጋሽ እጅ በዐሁኑ ሰዐት ይገኛል ።
  በደኖን ሲዳስሳት በዐንድ ሌሊት ብቻ ከ 150 በላይ አማሮች እንደታረዱ አባኒቆዲሞስን ጨምሮ ሌሎችም ነግረውናል ምንም እንኳ አፈንዲ ወደ 50 አውርዶ ከህሊና ዳኝነት ውጭ ወጥቶ ከ 50 ወቹ ግማሹ ኦሮሞወች ናቸው ሲለን ለመስማት ብንበቃም ። ኦሮሞወች ተገለው ሊሆን ይችላል ለምሳሌ በዐርባጉጉ ገደል ላይ የተጣሉት ኦሮሞወች ብቻ 36 ይደርሳሉ ። ይህም የዐማራ ባህልና ሃይማኖት የነበራቸው ከጉለሌ የሄዱ ኦሮሞዎች ናቸው የተጨፈቸፉትም በኦነግ ነው ። ይህ ማለት ግን ወያኔ ኦሮሞወችን አልጨፈጨፈም ማለት አይደለም ። የብሄር ግጭት እንደነበርም ለማስቀመጥ ተሞክሯል የብሄር ግጭትም አለነበረም የነበረው ስር የሰደደ ብሄርተኝነት ብቻ ነበር ። የብሄር ግጭት የሚባለው አንድ ኦሮሞና አማራ ስለተጋደሉ አይደለም ።

  በመጨረሻ የተጠቀመው ታክቲክ የፕሮፍፌሰር አስራትን ንግ ግር አምታቶ ማቅረብ ነበር ይሄም ድርጅታቸው ተጠያቂ ያደሬገው ኦህዴድን ነው ስለዚህ ኦነግ በዐርባጉጉ ላይ ተጠያቂ አይደለም እሳቸው እንዲህ ካሉ ወደሚል ድምዳሜ ነው ሲያሸጋሽገው የታየው ። እኔ እንዲህ እላለሁ ፕሮፌሰሩ ኦህዴድ የወያኔ አካል ስለሆነ ትጥቅ ያስፈታቸው ይሄን ነገር ሲፈጸም ዝም ብሎ ማየቱና በዐካባቢው ያሉ አሉ የተባሉ ሰወችን ገሎ ለኦነግ ለዘላኑ ቡድን አስርክቦ በመሄዱ ዋናው የወያኔ እጅ አለበት ዋናው ተዋናኝም እሱ ነው እንጅ ያሉት ኦነግ አልገደለም አላሉም እንደውም ሽል ሰላቢው ኦነግ እንደሆነ በግልጽ ያስቀመጡልን ነገር ነው ።

  ይሄን መከራከሪያ ካደረክ ሰው ግደል ብሎኝ ነው የገደልኩት እና እኔ ከደሙ ነጻ ነኝ ስትል ህግ ከለቀቀህ ኦነግ ባርባጉጉ ላይ ተጠያቂ አይደለም የሚለው መከራከሪያህ ይሰራ ይሆናል ይህም የሚሆነው እብዶች ዳኛ የሆኑ ለት ብቻ ነው ።

 4. Dear Afendi
  With all respect, i am not sure if OLF has pure hands as far as the rest genosides you listed above, if not the town in SNNP. he one i personally knew and lost several family and friends in Arsi was clearly the making of OLF. Or you have to convince me that, that time OPDO and OLF were closely working together. Otherwise, all these leaders of the killings and displacing were those who carry the mission of OLF, such as this is our OROMIA, leave OROMIA, you didnot belong here—you neftegna, you Amhara, regardless of you are gurage, or amhara, —-that was and is what OLF is known for. I tell you those killings started down there in Arba Gugu and stretched to Arsi highlands somehow up to Adama was coordinated by OLF as that of the one in Bedeno. In fact, even Meles said, OPDO is OLF! —sitifaku—-hence, my friend Afendi, i know you are faithfull and geniun, but believe me OLF has to be one who come first as far as these 20 years genocides in Ethiopia. As Meles and the lost Gambela guy are the one to take the genocide in Gambela. In fact, meles is everywhere–his hand is there after every killing.

 5. Your truth has no foundation. You denied all the worng doings of the savage OLF. (What do you say about Assosa? Horogudru?)

 6. This is author is one of the many idiots who are preparing Ethinc Amharas for another round of persecution by blood thirsty and mad OLFites who are clearing the road to Genocide against poor Amharas by teaching their followers false and fabricated history written by sick and mad OLFites dude don’t make a mistake TPLFites are brutal killers but they kill using bullets they don’t cut people throat and cut women breasts only OLFites are capable of doing such kind of brutality
  Oh I forgot that OLFites always accuse Amharas for cutting women breasts kkk it is only the culture of ARSI and GUJI Oromos who are known for cutting breasts and Pennis now modern day mad OLF historian gave their own barbarism to AMHARA who never had even killing the culture of killing Women
  We will not be fooled by people like u and give another chance for people like JAWAR who are waiting to wage genocide on Amharas when they get the chance

 7. Afendi muteki.thank you for your honest information you share with us.i think you will continue to tell us all the truth in your coming articles.and Esat radio and tv need to work thier assignment to show the truth about the weyane genocide commited on the poor Ethiopians.

 8. አፈንዲ ምንነካህ! በሐረርና አካባቢዋ ተወልደው ያደጉና በግብርና ሚ/ ር ተቀጥረው አገልግሎት የሚሰጡ ልጆች ላይ የተፈጸመውን ግድያ ማን ፈጸመው ልትለኝ ነው? ለኦነግ ጥብቅና መቆሙን ለጊዜው ተወት ብታደርገውና ጊዜው ሲመጣ ይህንን የምስክርነትህን ቃል ትሰጣለህ። ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ጠቢቡ ሰለሞን ወይም ሱሌይማን በዐረብኛው፤ እስከዚያው ድረስ ሆድ ይፍጀው ማለቱ ይቀላል። በተረፈ ሃሳብህን የምታውቀው ድረስ መግለጽህ አይከፋም፤ ጥሩ ነው። ችግሩ ግን ጥፋትን ለመሸፈን የሚደረግ ሩጫ ፤ ደስ አይልም። አበቃሁ! አፈንዲ ደግ ማለፊያ ነው። ብዕርህ ሁልጊዜ ወደ እውነት አድረጋት፤ ወደ ውሸት ካዘነበለች ልፋትህም ዋጋ ታጣለች። ለምኑ ብለህ ኦቦ አፈንዲ! ሺህ ዓመት አይኖር።

 9. Compared to 5 million massacared by Minilik and breat and hand cutting, OLF is very generous. I have never seen and heard any OLF doing any crime. instead any oromo that counted to 10,000 killed slowly by the current regime in the name of OLF. We struggle for freedom and TPLF and EPRP will die its natural death with its pity propoganda

 10. We Ethiopians never forgot what happend in weter be
  deno,asossa, etc. believe me time will come for justice, by the way OLF,Opdo, Tplf,Eplf all r the same to attack Ethiopia/Amhara

 11. For those who talked Assosa Assosa here is the fact…the thing was happened in “Gojam Sefer”- a village between Assosa & Kobor/Begi and the victims were Oromo merchants. Begi, Kobor, Gaba Dafino are well known in coffee, Teff & other cereals. Those merchants used to take these agri products to neighbouring towns like Assosa, Bambasi & Mendi using horses or donkeys. And most of the time their properties were confiscated at Gojam Sefer & forced to return back. The tragedy happened in 1981 E.C was different from usual ones. They were not only robbed but imprisoned in school for days & later Niguse Fanta ordered to burn them alive. That was reality. No single Amhara was killed! The killing was an extension of Anole massacre committed by DERGU.

 12. From GETACHEW REDA (Editor Ethiopian Semay)

  To the Habesha Editor

  To brother Patriot

  First to brother Patriot:- Please patriot, can you send me your comments on my email? It is hard to copy anything from this website (especially form the commentary pages)

  To Habesha Editor or to anyone who can help us the trick how to copy and paste important views posted on the Habesha commentary pages? It is difficult to copy anything from the commentary page/. If readers are restricted from copying educational views for educational or for record, what is the use of commentary page? Please, the Habesha lift the restriction. It is very strange. Other websites never restricted such.

  Besides , we can’t even find any pass archives/files. That means any writer’s article are only good for three days. Then they disappear/unavailable.
  Thanks Getachew Reda

 13. You said you are not agreeing with OLF idea anymore but telling us they killed only 50. When it comes human life even killing one person is still crime. OLF killed the 50 just because of their ethnic background, being Amharas, and it is still genocide. However, OLF’s history is not as you are trying to cover up; trust me they did vicious genocide on Amharas (I am one of live witnesses). When OLF start doing crime openly on Amhara, the first mass murder happened in South West Ethiopia, on settlers came from Northern Ethiopia due to draught. OLF rebels/soldiers, started shooting at night, while the villagers were sleeping, and got a chance to kill many. Many who tried to escape were caught on shooting, those who jumped to the river and washed away by the river water; other ones hidden in jungle were eaten by wild animals. The worst scenario was also women, kids, and elderly have been roasted inside their houses (Gojo), locked the door behind them. It sounds horrific movie but it is a sad truth and I will leave the rest for others. It’s a shame, just because time is still on OLF and Woyane’s side, many are bothered to reveal the fact that happened to Amhara by then. Only one person raised question why throughout 23 years, for the sake of truth and being human being, Dr. Asrat Woldeyes (may his soul rest in peace). Just because time is on your side, and Amhara does not have any protection for the time being, you can write any good image about OLF. Many cry same as “Burka Zimita” being with you. I believe there will be one historic moment that Amhara will free of being killed; will let us read historic books written by their children saying, “Never Again”. Trust me it will happen; it is a matter of time.

 14. For those who talked Assosa Assosa here is the fact…the thing was happened in “Gojam Sefer”- a village between Assosa & Kobor/Begi and the victims were Oromo merchants. Begi, Kobor, Gaba Dafino are well known in coffee, Teff & other cereals. Those merchants used to take these agri products to neighbouring towns like Assosa, Bambasi & Mendi using horses or donkeys. And most of the time their properties were confiscated at Gojam Sefer & forced to return back. The tragedy happened in 1981 E.C was different from usual ones. They were not only robbed but imprisoned in school for days & later Niguse Fanta ordered to burn them alive. That was reality. No single Amhara was killed! The killing was an extension of Anole massacre committed by DERGU.

 15. afendi tanks for ur information,i know ur best our writer but some of ur info not balanced,indeed above 100 oromo killed by olf east harege around gole re’e and mojo burn zeir house on them but around bedeno above 200 amaras throuwen 2 in z hole called hinqufetu,

 16. @Babekir,
  What kind of lier are u? If u ask any body around Asosa u will be told that all non-Amharas were carefully selected and ordered to leave the house. Then the OLF roasted the Amharas only. By the way SHABIA and OLF has cheated the farming-Amharas as if they were looking for them to discuss important security issues…otherwise it would have been a different scenario.By that time poeple in Assosa called OLF the scavenger becuase they used to eat only after the Shabia soldiers have eaten. OLF maferia yetilachicha kimir yalebachew, ye-Oromo jegininet yaltelabesu emotional animals neberu. I have been in Assosa and knows every thing. Babekir if u are Oromo do not talk about OLF, If u are Shabia or TPLF OLF IS IMPORTANT FOR U AND U CAN PRAISE IT.

Comments are closed.

Kidney stone
Previous Story

Health: ስለ ኩላሊት ጠጠር ሊያውቁ የሚገባዎት 5 ነገሮች

Next Story

ያረጋገጥነው የምግብ ኢዋስትናን (ዋስትና አላልኩም) ነው።

Latest from Blog

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ | አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ | አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል | ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ\  አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

ከመጠምጠም መማርን እናስቀድም!

;በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) አብዛኛው አንባቢ ተገንዝቧል ብዬ እንደምገምተው ሕዝብ ለቡና ቲራቲም፣ ለግብዣ፣ ለበዓል፣ ለሰረግ፣ ለሐዘን፣ ለእድር፣ ለእቁብ ለውይይትና ለሌሎችም ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ሲገናኝ የሚበዛው አድማጭ ሳይሆን ተናጋሪ  ወይም ደግሞ ለመናገር  መቀመጫውን ከወንበር ወይም
Go toTop