ለአቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ፍትሃትና ሽኝት ሲባል ቅዳሴ መቋረጡ ምዕመናኑን አሳዘነ

(ዘ-ሐበሻ) የኦህአዴድ ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የሆኑት ዓለማየሁ አቶምሳ የቀብር ስነ ሥነ ሥርዓት በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ዛሬ ተፈጸመ። የርሳቸውን ሞት ተከትሎም ዛሬ 5 ኪሎ በሚገኘው ቅድስተ ማርያም ቤተክርስቲያን የክልሉ ፕሬዚዳንትን ፍትሃትና በአዲስ አበባ ስታዲየም የተደረገውን የሽኝት መርሃ ግብር ምክንያት በማድረግ ከጠዋቱ 8:30- (2:30) እስከ 9፡00 0 (3:00)ሰዓት ማለቅ የነበረበት ቅዳሴ ተቋርጦ በጠዋቱ 7 ሰዓት(1:00) ላይ መፈጸሙ ምዕመናኑን ማስቆጣቱን ለዘ-ሐበሻ የደረሱት መረጃዎች ያመለክታሉ።

ለአቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ስንብት በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲደረግ ቅርብ ቤተሰቦቻቸው፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የተለያዩ ክልሎች የስራ ሃላፊዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ጀምሮ እንዳጀቧቸው የገለጹት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደ የስንብት መርሃ ግብር ላይ ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም “አቶ ዓለማየሁ ደርግን ለመጣል የነበረውን ትግል በወጣትነታእው ጀምሮ ተቀላቅለው በተለይ ለኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲና ፍትህ ማግኘት የታገሉ፤ እስከ ሕልፈታቸው ድረስም ታግለው የተሰዉ ታላቅ ሰው ናቸው። እነ አቶ ዓለማሁ ቢሰውም ያፈሯቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች ትግሉን ያስቀጥላልይ፤ በመሰዋታቸው ለቁጭትና ለላቀ ትግል የሚያነሳሳን ነው” ሲሉ አወድሰዋቸዋል።

የኢሕአዴግ መንግስት ሕገመንግስቱን በጣሰ ሁኔታ ፓርላማው ሳይሰበሰብ የሶስት ቀን ብሔራዊ ሐዘንና ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ በመላው ሃገሪቱ ማወጁ አነጋጋሪ በሆነበት ሰዓት በሃይማኖት ተቋማት ውስጥም መዋቅር በመዘርጋት ቅዳሴ እስከማቋረጥ መድረሱ ብዙዎችን አስቆጥቷል። “በዚህ ታላቅ ጾም ወቅት ልጆቻችንን ለማቁረብ በፓትሪያሪኩ መቀመጫ በቅድስተ ማርያም ቤተክርስቲያን ተገኝተን እያስቀደስን ባለንበት ወቅት ልጆቻችንን እንዳናቆርብ የአቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ፍትሃትና ሽኝት አለብን በሚል ቅዳሴው 7 ሰዓት (1:00) ላይ እንዲቋረጥ መደረጉ አስቆጥቶኛል” ሲል አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ምዕመን ለዘ-ሐበሻ ገልጿል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ተወዳድሮ ማሸነፍ የሚችለው ሰማያዊ ብቻ መሆኑ ተረጋገጠ

በቅድስተ ማርያም ቤ/ክ የተገኙት ምእመናን “ባለስልጣኑ ሕይወታቸው በማለፉ እናዝናለን፤ እግዚአብሔር ገነትን ያውርሳቸው፤ ሆኖም ግን እኩለ ቀን ላይ ለሚደረግ ቀብር የእኛን መብት ጥሶ ቅዳሴውን ማቋረጥ አግባብ አይደለም” የሚል አቋም ያለቸው ምዕመናን “ይህ የሚያሳየው የመንግስትን በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ መግባትን ነው” ብለዋል።

“በባለስልጣኑ ፍትሃት እና ሽኝት ላይ ቤተክርስቲያን ሰው ወክላ መላክ ትችላለች፤ በዚህ ዓብይ ጾም ወቅት ልጆቻችንን ሳናቆርብ ቅዳሴ ማቋረጥ ግፍ ነው” ሲሉ ሌላው አስተያየት ሰጪ ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ተናግረዋል።

አቶ አለማየሁ አቶምሳ በታይላንድ ባንኮክ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ45 አመታቸው የካቲት 26 ቀን 2006 ዓመተ ምህረት ነው ያረፉት። በምስራቅ ወለጋ ቢሎ ቦሼ ወረዳ ከአባታቸው አቶ አቶምሳ ሚጃ እና ከእናታቸው ወይዘሮ አየለች ብሩ በ1961 ዓ.ም መወለዳቸውን ከዚህ ቀደም መዘገባችን አይዘነጋም።

7 Comments

  1. Very sad. I do not get why you are bothered by lowering the flag for 3 days. The guy is a national leader, even though he is not TPLF.

    What’s the so called KIDASE anyway? I am glad I am not a member of this Orthodox cult.

    Henok, I am sure this article is not written by you.

    • በመጀመሪያ ደረጃ ዘጋቢው የሰአት አቆጣጠርህ አጠቃቀም ልክ አይደለም። እየዘገብክ ያለህው ለአማርኛ አንባቢዎች እስከሆነ ድረስ የነጮችን አስቀድመህ የኛን በቅንፍ ውስጥ ማድረግህ ምን ለማስተላለፍ ፈልገህ ነው።
      ሌላው ነጥብ ብዙዎችን ያስቆጣው ለፍታት ተብሎ ቅዳሴ መቃረጡ ነው። አንዱ ስሙ አንዳይጠቀስ ፈልጎ መቆጣቱን ግን ገልጻል። መለስ የሞተ ጊዜ በቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን በር ላይ ለረጂም ጊዜ ምስሉ ተስቅሎ አልነበረም ወይ ? ቅዳሴ ማቃረጥ አሁን ነው ወይ የትጀመረው? ቤተክርስቲያና የተደፈረችው እኮ አሁን አይደለም። ቆይታል በጣም ቆይታል ።
      ስለዚህ የቤተ ክርስቲያናን ክብር ለማስጠበቅ መእመናን ተቃውሞአቸውን በግልጽ ማሰማት መቻል አለባቸው ።ያ ካልሆነ ግን ቀድሞ በነጮቹ አሁን ደግሞ በወያኔዎች ይህቺን ቤተ ክርስቲያን በረጂም ጊዜ እቅድ እያለች የለችም እያሰኙ ጳጳሳትን ካድሬ እየሾሙ ለማጥፋት ታቅዶ እቅዳቸውንም እያሳኩ ነው ስለዚህ ለቤተ-ክርስቲያን እንቆረቆራለን የምንል ሁሉ ድምጻችንን ማሰማት ለነገ የማይባል ጉዳይ ነው።
      ገዥዎቻችን ከኛም አልፎ እግዚአብሄርንም ለመዳፈር ወደ ሃላ ያላሉ እኩይ የዘመናችን የሰይጣን ስራ አስፈጻሚዎች ናቸው።

  2. I don’t think this is a big issue to be mentioned. Remember that the person is the president of the Oromia Region, a one who somehow represent 30 millions of Ethiopia. Oromia is the home of millions of orthodox church and the church is very much welcomed in the region. But what we as oromos receive from the church in return is disappointing. Alemayehu desrve national mourning and it is fine that the flag is lowered. I have already gave up on habasha including the habasha website. The disrespect the habasha has for oromos is too much and that is why we are saying that we are not part of Ethiopia. After reading this you may decide not to post it, I don’t care good you read it.

  3. TG:you must be angry not to be orthodox!!!aske your friends about Orthodox
    I think you are not an Ethiopian becouse … You now that
    Ethiopia is holy land of next to israel!!!!

  4. For TG
    Because u have complex with orthodox and Ethiopia on the top of that u don’t have religion. So alemayhu or u or opdo r the enemy of Ethiopia
    Belive me we punish u soon. Tebtaba

  5. even if he is respected man he is equal from any person infront of GOD i am sad realy i doesn’t understand job of sinodose! please GOD bless ethiopia

  6. For Motii
    Please don’t speak on behalf of the great Ethiopian Oromo people. Tell as ur dream, u can be Madagascar , or Kenyan Oromo or other. I think u confused I’m sorry

Comments are closed.

Share