(የአውሮፕላኑ ጉዳይ) ምንድን ነው ኩራት?

ከሥርጉተ ሥላሴ (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

ዘጠና ደቂቃ በኢንተቤ በሚል እርስ በታዋቂው ጸሐፊ ማሞ ውድነህ የተተረጎመ አንድ የእውነት መጸሐፍ በልጅነቴ ማንበቤን አስታውሳለሁ። ግን በጣም በተደራጀና በርካታ ጉዳዮችም በቅንብር የተከወነበት ነበር። ዛሬ ደግሞ በአንድ ዕጣ ነፍስ ቀንበጥ እጅግ የተጠና የታቀደ የቀደመ ሥልጡን ተግባር ተከወነ። ትውልዱና ታሪኩ በአዲስ መልክ አዲስ ምዕራፍ ከፈቱ። ለእኔ ኩራት ማለት የወገንን ጥቃት በረቀቀ ግን በታቀደ በተረጋጋ መንፈስ የሚከወን ተግባርን ነው።
እርግጥ ሌትና ቀን ወያኔና አጃቢዎቹ ተደናብረዋል። የኢትዮጵያ አዬር መንገድ ክብር፤ ዝናና ታሪክ ጎደፈ ሲሉም ይደማጣሉ። ኩራትና ዘረፋ ቀረ አይነት። መጀመሪያ ነገር አይደለም የኢትዮጵያ አዬር መንገድ ኢትዮጵያ ከነሙሉ አካሏ አለችን? የትናንት የኩራት የነፃነት አንባ አይደለም ለእኛ ለጥቁር ህዝብ አርማ የነበረችው ሀገራችን ከነሙሉ ወርድና ቁመናዋ አሉን? ለእኔ የለችም ነው የምለው። ….. ይህቺ ናት እኮ ኢትዮጵያ ስንት ጊዜ ቀዶ ጥገና ያደረጋላት ወያኔ …. ያፈረሳት፤ እንደ ሰንጋ ለባዕዳን ያቀራመታት። ባህሏም፤ ታሪኳም፤ ጥሪቷም፤ ቅርሷም፤ የዕምነት ሥርዓተ ህግጋቷም፤ ህይወቷም ጠረናቸው የተበከለ ሆነው ከእኛነታችን ውስጥ እንዲፋቁ መርዝ የነሰነሰባት። ባዕዳን ሲገቡ ከነሁለመናቸው ነው። ለጆሮ ከሚዘገንኑ ልማዳቸው ጋር …. በቻይና ሃብታሞቹ ምን እንደሚበሉ ታውቃላችሁ? በልጅነታችሁ ሲተረትላችሁ የነበረውን የጭራቅ ታሪክ እሰቡት …. ይቀፋል ….

በወያኔ – ትራፊ በሰልፍ የሚጠበቅባት፤ ሚሊዮን የነገ ፍሬዎች ነገ ሳይመጣ ተስፋቸው ደርቆ እራብ እዬቆላቸው የሚያልቁባት። ሊለምኑ ያፈሩ ሚሊዮኖች እንደ ተዘጋባቸው የሚያልፉባት። ህጻናት እንደ አወጡ ለንግድ ጨረታ የወጡባት፤ ሴት ታዳጊ ወጣት ደመ ከልብ ሆነው አረብ ሀገር ተደፍረውና ተዋርደው የሚቀቀሉባት፤ ሀገር ውስጥ ያለው ወጣት በቤንዚን አርከፍክፎ እራሱን የሚያቃጥልባት፤ ታንቆ ወንዝ ገብቶ የሚሞትባት፤ በዘሩ በሃይማኖቶ እዬተለቀሙ ዕልፎች ከሥራ ገበታቸው የሚባረሩባት የዕንባ ባዕት … ለእለት ጉሮሮ፤ ለመጠለያና ለከፈን ያልተበቃባት።
አዬሩ የስጋት ዓውድ ያፈናት፤ ስደት ከሃይማኖት አባቶች ጀምሮ በፆም በጸሎት የሚናፈቅባት፤ ሰው በነፃ ቤቱ በሰላይ ታፍኖ የሚኖሩባት የረመጥ ሀገር እኮ ናት ኢትዮጵያ ዛሬ። መሬቷ ለነገ ሳይታሰብ ተሸጦ በኬሚካል የሚቃጠልባት ኖሪዎቿ እዬተፈናቀሉ ባለቤት አልባ የትም የሚበተኑባት፤ ህጻናት ወላጅ አልባ የሚቀሩባት እኮ ናት ዛሬ እናት ሀገር። የሰው ልጅ በአስተሳቡ የሰበውን ያለመውን እንዳይናገር ጉሮሮውን የተዘጋበት መንፈሱ የተቆለፈባት ወጥቶ ለመግባት ማስተማመኛ የሌለበት፤ የክትና የዘወትር የሚለይባት፤ ለዘመንተኞች ገነት ለብዙኃኑ ሲኦል የሆነች ሀገር እኮ ናት።
በደም በአጥንት በክብር የተከበረች ሀገር ለውጪ ኃይል ለገጸ በረከት የተሸለመች ሀገር ሆና … እንዴት ኩራት ይታሰባል?

ተጨማሪ ያንብቡ:  ደመቀ መኮንንና ተመስገን ጡሩነህ፤ የጭራቅ አሕመድ ክራንቻወች

ይህ ያንገፈገፈው የመረረው የዘገነነው ወጣት እንሆ ቆረጠ ወሰነ አደረገውም። ገድል ነው። ብቻውን ከሀገርም ሲዊዘርላንድ መረጠ – ረቂቅ። በተረጋጋ መንፈስ ሳይታወክ ፍላጎቱን በጥቂት ቃላት ብቻ ልብን እንደ ቅል አንጠልጥሎ ገለጸ። ምንም ዓይነት አይደለም የድርጊት የቃል እንኳን ግድፈት ሳይኖርበት። ምንም አይነት የቅድመ ሁኔታ ድርድር ሳይጠይቅ፤ እጅግ በቀደመ ጨዋነት ለሚሊዮኖች እራሱን ሰጠ። በቃ! ፍቅር ይሏችኋል ይህ ነው! ኩራትም ይሏችኋል ይህ ነው! ጀግንነትም ይሏችኋል ይህ ነው! የእናት ሀገር ጥሪ ከሰማያተ ሰማያት ፈቅዶ ተቀበለ። የተሳካ በፍጹም ሁኔታ የተሳካ ድርጊትም እንሆ ከወነ። በድርብ አንጎል። ሌላው ወያኔ ሊደበቅበት የሚገባው ጉዳይ ለኣለም ድንቅ ትምህርት ቤት የሆነው አዬር መንገዳችን የትውስት ዋና አብራሪ ሲኖረው ይህ ነው ታላቁ ውርዴት ለወያኔ … ይህን የመሰለ ጭንቅላት ያለው ወጣት ረዳት፤ ጣሊያናዊ አብራሪ ዋና …. ዓለም ከሃቅ ጋር እስኪ ይፋጠጥ ….

ትውልዱ ይህን ይመስላል ወያኔ ቢማርበት። 40 ዓመት የደከመበት መና ከንቱ መቅረቱን። ዛሬም እናት ጀግና ትወልዳለች። ዛሬም ኢትዮጵያዊነት ግብግብ ቅጥል ርምጥምጥ የሚያደረገው አርበኛ እንዲህ በልበ ሙሉነት ሙያ በልብን ከውኖ ገዢ መሬቱን ካለምንም ብክነት የሚቆጣጠር ቀንዲል ትወልዳለች አምላኳ አልረሳትም እና።
ዓለም ፊቱን አዞረ፤ ሰንደቃቸውን እንደ ለሰበሱ በትቢተኛው ሳውዲ አደባባይ ወገኖቻችን ደማቸው ሲንዶለዶል ሚዲያው ሁሉ ዘጋን፤ እኮ ታምረኛውን አምላክ አዘጋጅቶ ኖሮ ዛሬ አንደበታቸውን አስከፈተ። ጀግናው አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ተገኘ በክፉ ቀኗ ለእናት ሀገሩ የተገኘ የቁርጥ ቀን ልጅ። ሥሙ እራሱ ሥም ነው።
እኛ ስለ እስራቱ፣ ስለነገ ህይወቱ ተጨንቀን ይሆናል። እሱ ግን ሁሉንም ዓይነት መስዋዕትነት ለመቀበል አውቆ የቆረጠ የወሰነ ምርጥ ዘር ነው። ቀደምቶቹ – አብርኃም ደቦጭ፤ ሞገስ አስገዶም፤ አብዲሳ አጋ፤ ኃይለማርያም ማሞ፤ በላይ ዘላቀ፤ ዘርአይ ደረስ – ተፈጠሩ። ዳግም ተነሱ። የትንሳኤ መግቢያ ዋዜማ …..
በተጓዦች ዘንድ አንድም የመንፈስ ቅንጣት ጭንቀት ሳይፈጠረ፤ በረቀቀ ጥበብ በአውሮፕላኑ ድንበር ወስጥ ሳይሆን ከዛ ውጪ በሆነ ሁኔታ በመስኮት የላቀ ትዕይንት …. ፈጸመ። በሰለጠነው አለም ቢሆን ስንት ኪኖ ያሰራ ይሆን ይህ ታዕምር? …. ይህን የዘመናችን አዲስ ትውልድ እኮ ለመተርጎም የሰማይ ጸጋ ይጠይቃል አባቶቼ ያመሳጥሩት እኔስ አቅም የለኝም።
አጓጒ ሂደቱ ልብን እንደ አንጠለጠለ ይቀጥላል። የተረጋጋችውም ሲዊዝም ሰከን ብላ ለየት ባሉ ህጎቿና ተፍጥሯዋ ትንሽ በትንሽ እያቃመሰች የኢትዮጵያን መከራ ፈተና ስቃይና ዕንባ በዓለም አደባባይ ታስፈትሻለች ….
በጀግናው ፊት ለፊት በጎኑ በስተኋላው ያለው ነፃነት የናፈቃት እናት ሀገሩና የፈጠረው አምላኩ ደግሞ ከመቼውም በላይ ጥበቃቸው አይለዩትም። ሲፈጠር የተቀባበትን ጸጋ ነው የፈጸመው አትርፏል። ትርፉ 150% ነው። እነሱ ዋስ ጠበቃ ይሆኑታል። በእኛ በኩል ደግሞ ለዚህ ለላቀ መስዋዕትነቱ እኛ ነፍስ ያለው ጠበቃ አቁመን መሟገት። የጠነከረ ተከታታይነት ያለው የሎቢ ተግባር መሰራት። ለምናውቃቸው ሁሉ የኢትዮጵያን መከራና ሰቀቀን እስካሁን ድረስ በኣለም ዐቀፍ ሰብዕዊ መብት ድርጅቶች የተዘገቡትን ሪፖርቶችን ሊንኮችን እያሰባሰብን መላክ። ከጎኖ መቆም ያስፈልጋል። አብሶ በእንግሊዘኛ ቋንቋ አጫጭር ጹሑፎች በምልሰት በደሎች እዬተቃኙ ማቅረብለወቅቱ ተስማሚዎች ይመስሉኛል።
ዜግነት እንዲህ ሲያምርበት፤ እንዲህ በድርጊት በጥበብ ልቆ ባለማዕረግ ሲሆን ከማዬት በላይ ምን ሐሴት አለ?! የጉዞ አቅጣጫ ካለምንም የሰው ህይወት ጥፋትና ንብረት እንዲሁም ወድምት መሆኑስ አይገርምም! በሌላ በኩል ብልሹውን የወያኔን ሴራ ከመሰረቱ ተተራመሰ። የዘመኑ ምርጥ ወጣት ታላቅ ተጋድሎ …. ሳይ በህይወት መኖሬን ዛሬ ወደድኩት። ለእኔስ ኩራቴ ወጣት ኃይለመድህን አበራ ተገኘ። የኢትዮጵያዊነት ሚስጢሩም ተዚህ ላይ ተገኘ። እግዚአብሄር ይስጥልን የ እኛ ብቁ የተስፋ ቡቃያ! እናመሰግንኃለን፤ እናከብርህምአለን። እንወድህምአለን። ታሪክ-በትውልድ፤ ትውፊት -በድርጊት፤ አደራ – በጀግነነት በልበ ሙሉነት ተፈጸመ። ተመስገን!

ተጨማሪ ያንብቡ:  አንድ አፍታ ከኢትዮጵያውያን ወታደሮች ጋር በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል… በዲ/ን ተረፈ ወርቁ

ኢትዮጵያን በልጆቿ መስዋዕትነት ከዘላለማዊ ክብሯ ጋር አምላካችን ያኑርልን። አሜን።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

8 Comments

  1. This is a very important Observation and Keep it up. This Shows that there are great lessons to be learned from this hero. He has shown a different way of transmitting a good message to the world. the way medias involve themselves in the struggle could be revisited and become more proactive to ensure that there exists proper knowledge on how to deal with the Problem the Country faces today.

    He is an ethiopian Edward snowden.

  2. I don’t want to rush and forward comment pro or against Hailemedhin… At least I shall wait and hear his real concern first…

    But for Christ sake why did you remove the family call?…
    Drear Henok, would you do this if he was your brother… Don’t you think that this will worsen the pain of his beloved family… I’m so sad… Pray for me to long more for the better media outlet and responsible journalism for the desperate Ethiopia…
    God bless Ethiopia!

  3. Let me give u the answer for yellow shaded area or ? Area that is on the hand of the owner of that land it’s belong for Eritrean not for Amhara or tegaru it’s out land and we have it if u do not understand or want to try to have it we will give u ur price.

  4. **********************************************!
    አያት ቅድም አያቱ ጠላት ሲማርኩ ሲያስሩ
    ሴት አያቶቹ ስንቅ ሲያቀብሉ እርሻ ሲሰማሩ
    ባለሟል አክሰቶች ፈትለው ኩታ ሰሩ
    የመጥለፍን ጉዳይ ለትውልድ ሊያስተምሩ
    ልጅን አስትምረው ጥንታዊ ታሪክን
    ቁጭትና ጥልፈት የሰላም የድል ዘዴን
    የድሮ ጠላቱን ገልጋይ በሌለበት በሰማይ አገኘና
    ከፊቱ አብርሮ ከውስጥ ቆለፈና
    አንክበክቦት ሄደ ሰው በአይነት ጫነና
    ድሮም ያውቃሉና የጎበዝን ሀገር የጥቁር ቤት ዝና
    ሐበሽ ከፊት ሳቀ ጥልያን አለቀሰ ሽንት ቤት ገባና!
    ምን አሉ አንግሊዞች አሜሪካ ፈረንሳይ ሮማንያ ያየናቸው
    ቆሟል እንዳይሉ በመሄድ ላይ ናቸው
    ወረድን አይሉ በአየር ላይ ናቸው
    ጥሊያን ላይ ሲያስቡ ሲውዘርላንድ ናቸው
    ብቻውን ዘወረው ያ ጥልፍ አዋቂ አበሻ ኀይለመድህን
    ተክኖታልና መጫንም ማውረድም መንዳትን መምራትን
    ሰርቶ አሳያቸው ምን አሉ ነጮቹ ሲገቡ ሀገራቸው!
    እኛ ነን አይሉ እጅ ወደ ላይ አርገው ሲጮሁ አየናቸው
    ማረክን አይሉ በሩን ዘግቶባቸው በገመድ ወረደው
    ፀብ ነበር አይሉ ፍቅርን የአበራ ሰላማዊ ሰው ነው
    ያ! ሁሉ የዜጋ ዓይነት ለመጪው ትውልድ ምሥክር ነው
    ምን የሀገር ቅርስ መጎብኘት ታሪክ ማንበብ ብቻ ነው
    ታሪክ ያበስራሉ ስለ ኢትዮጵያዊነት ሲገቡ ሀገራቸው!?
    _______++++++++++++_____!!

  5. God bless you, Sirgut. We are standing by his side and we are trying our best to let the world know what has been going on in Ethiopia under EPRDF/TPLF Machievillian ruling. I take off my hat to you

  6. Sirgute Silasie: Good remark! But do you think your opinion is relatively better than others who are in power for the one who eats once in day, unlike you who lives in better environment?? Just wondering…

  7. SERGUTE SELASAY, Semen Melak yawetawal yembalwe ewnet Ekonew. Yanayheit enQwan Ethiopiawe honku endhel tesefaa betefabet bezhe seat tesfaa yalwen negeger yemtasemee Yemeserach Beyashalhu esaya enQwan Noreshelen bewenet kelebay Gonbese beyaleshalhu, TesefaaNeshe yawegenocheshe kurat endhoneshe yanureshe.EWDESHALHU,endanche ayentwan geta degagemo yesetn.AMEN.

Comments are closed.

Share