ሙሽሮቹ በሰርግ ቀናቸው ቂሊንጦ ወህኒ ቤት በማምራት እስረኞችን ጠየቁ

ዳዊት ሰለሞን በፌስቡክ ገጹ እንዳሠፈረው፦

በሰርግ ስነ ስርዓት ወቅት የሙሽሮችን አእምሮ ወጥረው የሚይዙ ብዙ ነገሮች ይኖራሉ፡፡ ከቤተሰብ መነጠልና አዲስ ህይወት የመጀመር ፍርሃት ዋናዎቹ ተብለው ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡

በሰርግ ቀን ስሜትን የሚቆነጥጥ፣ድባቡን በሀዘን እንዲዋጥ የሚያደርግ ነገር ማድረግን አልያም ማየትን ማንም አይፈልግም፡፡በዚህ ፎቶ ላይ የምትመለከቷቸው ሙሽሮች በመንፈስና በልባቸው ወደ ቂሊንጦ ወህኒ ቤት በማምራት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን አስበዋል፡፡ ሰርጋችንን ያደረግነው በሙሉ ደስታ አይደለም በማለትም ሁለት እጆቻቸውን በማመሳቀል እኛም ታስረናል ብለዋል፡፡

ህዝቡ የፍርሃት ጠርሙሱን በመስበር በሁሉም ቦታ እምነቱን፣ተቃውሞውን እየገለጸ ይገኛል፡፡እነዚህ ሙሽሮችም ለዚህ አይነተኛ ማስረጃ በመሆናቸው በድርጊታቸው ሊወደሱ ይገባቸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በናይጄሪያ እዚህ መድረስ የብሄራዊ ቡድናችንን ብቃት መለካት ይችላል?
Share