በስጋትና በግራ መጋባት መካከል የሚገኙት ኢትዮጵያዉያን በዩክሬይን

አቶ በፈቃዱ ጥላሁን በዩክሬይን ሃርከፍ ሲኖሩ ሲኖሩ ከ 36 ዓመት በላይ ሆኗቸዋል። የ29 ዓመትና የ17 ዓመት ወንዶች ልጆች አሏቸዉ።ቤት ገንብተዉ በንግድ እየተዳደሩ ነበር። የሚኖሩበት ከተማ ከሩስያ ድንበር 36 ኪሎሜትር ብቻ በመራቁ ሁኔታዉ አሳሳቢ ሆኖባቸዋል። የከተማዉ ህዝብም ከሩስያ ጋር መቀላቀል ይፈልጋል። ወዲህም ዩክሬንን ይወዳል ይላሉ።

በሮኬት እና ቦንብ ፍዳታ በምትታመሰዉ ዩክሬይን ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎች ብሎም ትዳር ይዘዉ ልጆች ወልደዉ ኑሮአቸዉን መስርተዉ በዩክሬን ከ30 ዓመታት በላይ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በዩክሬይን ይቆዩ ከዩክሬን ይዉጡ ግራ ተጋብረዋል። ሳምንቱን የደፈነዉ  ሩስያ በዩክሬን ላይ የጀመረችዉ ወረራን ሸሽተዉ ከዩክሬይን የወጡ ኢትዮጵያዉያን አብዛኞቹ ለትምህርት የመጡ ወጣት ኢትዮጵያዊያን ነበሩ። በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ዘመን የትምህርት እድል አግኘተዉ ወደ ተለያየ የአሁንዋ ዩክሬን ግዛት ትምህርታቸዉን ይከታተሉ ከነበሩት አብዛኛ ተማሪዎች መካከል፤ እዝያዉ ትዳር ይዘዉ ልጆች ወልደዉ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ቁጥር ግን ቀላል አይደለም። ዶክተር ግርማ እንዳለ ከባለቤታቸዉ ከወይዘሮ እቴቱ ጋር በዩክሬይን ሲኖሩ ከ 36 ዓመታት በላይ ሆንዋቸዋል። ሦስት ሴት ልጆችን ወልደዉ፤ ልጆቻቸዉ ከአንዷ በቀር ሁለቱ የከፍተኛ ትምህርታቸዉን አጠናቀዋል። የመጨረሻዋ ልጃቸዉም ቢሆን በጋዜጠኝነት ትምህርት ዘንድሮ መመረቅ ነበረባት። ይጦርነቱ መጣና ትምህርቱ ተቋረጠ እንጂ። ዶ/ር ግርማ በሃርከፍ ከተማ የቆዳ እና የአባላዘር በሽታ ህክምና በመስጠት ይተዳደሩ ነበር። ባለቤታቸዉ ደግሞ የከብት ህክምና ባለሞያ ናቸዉ። ዶ/ር ግርማን ለሊት በስልክ ያገኘናቸዉ በሃርክፍ ከተማ ከሚሳይል ድብደባ ለማምለጥ እንደ ከተሜዉ ሰዉ በመከላከያ ጉድጓድ ዉስጥ ተሸሽገዉ ነዉ።

እዝያዉ በሃርከፍ ከተማ ነዋሪ የሆኑት እና አነስተኛ የልብስ ስፊት ድርጅት ከፍተዉ አስር የዩክሬን ዜጎችን ቀጥረዉ በጨርቃ ጨርቅ ሽያጭና በልብስ ስፌት ይተዳደሩ የነበሩት አቶ ከፍያለዉ ኃይሉ ፤ ከ 16 ዓመት ወንድ ልጃቸዉ ጋር ብቻቸዉን እቤት ተቀምጠዉ የሚያደርጉት ነገር ጠፍቶአቸዋል። ልጃቸዉ ሌላ ሃገር መሄድ እና እንደ አዲስ የሌላ ሃገርን ህይወት መጀመር አስግቶታል። ብንሄድም ብንቀመጥም ችግሩ ያዉ ነዉ ባይ ነዉ። ስለዚህም በሮኬት በምትደበደበዉ ከተማ ሃርከፍ መቆየትን መርጦአል። የአቶ ከፍያለዉ ባለቤት በፖላንድ የከፍተኛ ትምህርቷን ለመከታተል የሄደችዉን ልጃቸዉን ለመጠየቅ ወደ ፖላንድ እንደሄዱ ነዉ ጦርነቱ ተቀስቅሶ ፤ ከልጃቸዉ እና ከባለቤታቸዉ የተነጠሉት።

Ukraine Krise zerstörtes Wohngebäude in Irpin

ሌላዋ የዩክሬይን ነዋሪ ኢትዮጵያዊት ወ/ሮ ዉዴ ተሰማ ገላ ይባላሉ። የመዲና ኪይቭ ነዋሪ ናቸዉ። የአስራ አምስት ዓመት ወንድ ልጅ እናት ናቸዉ። ወ/ሮ ዉዴ ባለቤታቸዉን ዩክሬናዊ ባለቤታቸዉን የተዋወቁት በባህርዳር ከተማ ነዉ። ባለቤታቸዉ  የባህርዳር ፖሊቴክኒክ አስተማሪ ነበሩ። ኢትዮጵያ ዉስጥም በትዳር ባህርዳር ላይ አብረዉ ኖረዋል። መዲና ኪይቭ ደሞ መኖር ከጀመሩ አስራ ስድስት ዓመት ሆንዋቸዋል።  ባለቤቴን እና ልጄን ትቼ አልወጣም ብዩ ተቀምጫለሁ። ልጄም አባቴን ጥዬ አልወጣም ብሎአል። እኔም ባለቤቴንም ልጄንም ጥዬ የትም አልሄድም ብለዉ ኪይቭ ከተማ ተቀምጠዋል። እንደ ሮ/ሮ ዉዴ የሚበላ ምግብ እያለቀ ነዉ። ለሊት ለሊት ከፍተኛ ፍንዳታ ይሰማል። ሁኔታዉ እጅግ አሳሳቢ እና አስፈሪ ሆንዋል።  ሁኔታዉ ግን እጅግ አስፈሪ እንደሆን ነዉ

ተጨማሪ ያንብቡ:  የወልድያ ከተማ ነዋሪዎች የመንግሥትን አፋጣኝ እርምጃ ጠየቁ (ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን)

አቶ በፈቃዱ ጥላሁን ከ  በዩክሬይን ሃርከፍ ሲኖሩ ሲኖሩ ከ 36 ዓመት በላይ ሆንዋቸዋል። አንድ የ 29 ዓመት እና የ 17 ዓመት ወንድ ልጆች አልዋቸዉ። ቤት ገንብተዉ በንግድ እየተዳደሩ ነበር የሚኖሩት። የሚኖሩበት ከተማ ከሩስያ ድንበር 36 ኪሎሜትር ብቻ በመራቁ ሁኔታዉ አሳሳቢ ሆኖባቸዋል። የከተማዉ ህዝብም ከሩስያ ጋር መቀላቀል ይፈልጋል። ወዲህም ዩክሬንን ይወዳል። ግራገብቶታል ባይ ናቸዉ። አቶ በፈቃዱ በዩክሬን ሲኖሩ ባለ ሦስት ፎቅ ቤት ገንብተዋል። አፓርታማ ዉስጥብ የግላቸዉ ቤቶች አልዋቸዉ። አሁን ዩክሬንን ጥለዉ እንደ አዲስ በሌላ አገር ህይወት መጀመርና ስደተኛ መሆን ያስፈራቸዋል።

ቤተልሄም ግርማ ከኢትዮጵያዉያን እናት እና አባት ሃርከፍ ከተማ የተወለደች በዩክሬይን ታዋቂ ሙዚቀኛ ናት አማርኛ ትንሽ ትንሽ ነዉ የምችለዉ ስትል ሁኔታዋን በኢንጊሊዘኛ ታስረዳን ጀመረች ። ኪይቭ ከተማን ጥላ ወደ ኦዲሳ ከተማ ከከተመች ቀናት ተቆጥረዋል።

Ukraine Kiew | Ukrainische Soldaten passieren eine zerstörte Brücke

«በድንጋጤና በፍርሃት ልቤ እየመታ ነዉ፤ በላያችን ላይ ሮኬት እየዘነበብ ነዉ። እኔ በተወለድኩበት እህቶቼ እንዲሁም እናት እና አባቴ በሚኖሩበት በሃርከፍ ከተማ ከፍተኛ ጥቃት ሲጣል እና ሲወድም ማየቱ ልብ ይሰብራል። ሃርከፍ ከተማ ለራሽያ ቅርብ ከተማ ነዉ። በከተማዉ ከፍተኛ ዉድመት ደርሶአል። ቀንም ለሊትም የምንሰማዉ የቦንብ እና የሮኬት ፍንዳታ ብቻ ነዉ። ሮኬት ብቻ። በጣም ያስፈራል። እየገደሉ ያሉት ሲቢል ማኅበረሰቡን ነዉ። ከመኖርያ ቤት ነጭ ባንዲራ እየያዙ ሰዎች ሰላማዊነትን ቢያሳዩም ወታደሮች ሲቢሉን ሲገድሉ ታይቶአል። ይህ የማወራዉ እዉነቴን ነዉ፤ የቪዲዮ የፎቶ ማስረጃ አለኝ። ዓለም ዝም ሊል አይገባም። እንዲ አይነት ጭካኔን በህይወቴ አይቼ አላዉቅም።  ሁኔታዉ የሁለተኛዉን የዓለም ጦርነት ታሪክን ነዉ የሚያስታዉሰኝ።»

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዐማራው በፈጣሪውና በራሱ ብቻ ተማምኖ ኅልውናውን እና ማንነቱን ለማስጠበቅ በአፋጣኝ በአንድነት መቆምና መደራጅት ያስፈልገዋል!

ቤተልሄምን ድንበር ላይ አፍሪቃዉያን ስደተኞች በቆዳ ቀለም ምክንያት መድሎ ሲደረግ ታይቶአል የተባለዉስ ነገር ስንል ጠየቅናት።

«እኔ ዘረኝነት ታይቶአል የሚባለዉ ነገር አላምንም። ምክንያቱም ዩክሬኖች ባቡር ላይ ሲያሳፍሩ የነበረዉ መጀመርያ ህጻን ልጅ የያዙ ሴቶችን አረጋዉያንን ከዝያ ደግሞ ብቻቸዉን ያሉ ሴቶችን ነዉ ። እንዲህ አይነት ነገር ታይቶ አይታወቅም።  ህጻን አዋቂዉ በጣም ተረብሾአል። ምን መያዝ እንዳለበት፤ የት መደበቅ እንዳለበት ምን መስራት እንዳለበት አያዉቅም። ዘረኝነት የተባለ የሚወራዉም ነገር ሃሰት ነዉ።   እርግጥ ነዉ በጭራሽ ዘረኝነት ዩክሬን ዉስጥ የለም ማለቴ አይደለም። አሁን ግን ሃገሪቷዋ ተወራለች። ሁሉ ቦታ ጦርነት ነዉ። ዩክሬኖች ብዙ የዉጭ ሃገር ሰዎችን በፍቅር እና በእንክብካቤ ነዉ የያዙት። አሁን ግን እነሱም ችግር ላይ ወድቀዋል። አንዲት ጥቁር ሴት እምድር ዉስጥ ባለ ባቡር ዉስጥ ህጻን ልጅ ተገላግላለች። ዩክሬኖች ሲረድዋት ሲንከባከቡዋት ነበር። ይህን በአይኔ አይቻለሁ።»

Ukraine Krise Explosion in Borodyanka

ቤተልሄም ዩክሬይንን ወክላ የዛሬ አንድ አመት ከመንፈቅ በታዋቂዉ የአዉሮጳ የሙዚቃ ዉድድር ተካፍላለች።

«የዘፈን ግጥም እና የሙዚቃ ደራሲ እንዲሁም ዘፋኝ ነኝ ። በዩክሬይን በጣም ታዋቂ ነኝ። ከሌሎች ሁለት እህቶቼ ጋር «ፎ ሾ» የተባለ ባንድ መስርተን በዩክሬይን የሙዚቃ መድረኮች ዘፈን በማቅረባችን እንታወቃለን።  በጎርጎረሳዉያኑ 2020 የአዉሮጳ ሃገራት የሙዚቃ ዉድድር  «Eurovision Song Contest» ላይ ዩክሬንን ወክለን ተወዳድረናል። አሁን ያ ሁሉ የለም ። ፑቲን ሃገሪቱን በሮኬት እያወደማት ነዉ።

«ማስተላለፍ የምፈልገዉ ነገር አለ። ፑቲን በዩክሬይን ላይ ሮኬት እንዳያዘንብ የአዉሮጳ ኅብረት እና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ሃገራት « ኔቶ » የዩክሬይንን የአየር ክልል እንዲዘጉ ጥሪ ማስተላለፍ እፈልጋለሁ። ንገሩልን።»

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዶ/ር አብይ አህመድ እና ለማ መገርሳ ም ዕራብ ወለጋ ተገኙ

በጦርነት መፍትሄ አይገኝም ጦርነት አዉዳሚ ነዉ። በዉይይት ችግርን መፍታት ደግሞ  አዋቂነት ነዉ። ስትል ቤተልሄም ተናግራለች ሃገርዋ ዩክሬይንን ከጠላት ለመከላከል ግን ቤተልሄም ግርማ ብረት ማንሳትዋን ተናግራለች። ሰላም ያምጣ።

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ

DW

2 Comments

  1. አጼ ሐይለ ስላሴ ዛሬ በኛ ላይ የተጀመረው እሳት ነገ እናንተ ላይ ይሄዳል ያሉት ዳግም እውነት ሊሆን ነው ማለት ነው?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share