February 27, 2022
11 mins read

ዐብይ አሕመድና የኦነግ አራጅ ሠራዊት – መስፍን አረጋ

ከጦርነት ዝግጅቶች ውስጥ አንዱና ዋናው ጠላትህን ጭራቅ አድርገህ በመሳል፣ ተዋጊወችህ የሚዋጉት ከሰው ጋር ሳይሆን ከጭራቅ ጋር እንደሆነ፣ የሚገድሉትም ሰው ሳይሆን ጭራቅ እንደሆነ እንዲያስቡ በማድረግ፣ በጠላታቸው ላይ ማናቸውንም ዓይነት ጭካኔ ቢፈጽሙ ምንም ዓይነት የህሊና ወቀሳ እንዳይሰማቸው ማድረግ ነው፡፡    የወያኔና የኦነግ  አመራሮች መሠረታዊ ጠላታችን ነው ብለው ጦርነት ባወጁበት በአማራ ሕዝብ ላይ ያደረጉትም ይሄንኑ ነው፡፡

shene 1የኦነግ ወንበዴወች አማራ ሲያርዱ ምንም አይሰማቸውም፣ ምክኒያቱም በነሱ እይታ መሠረት የሚያርዱት ሰው ሳይሆን አማራ ነውና፡፡  የኦነግ ሽፍቶች የአማራን ሕጻናት ጎጆ ውስጥ ሰብስበው ሲያንጨረጭሩ ምንም አዘኔታ አይሰማቸውም፣  ምክኒያቱም በነሱ እይታ መሠረት የሚያንጨረጭሩት ሕጻናትን ሳይሆን የአማራ ሕጻናትን ነውና፡፡  የኦነግ ቄሮወች ከአማራ አስከሬኖች በተቆረጡ እጆና እግሮች ሲጨፍሩ ደስታውን አይችሉትም፣ ምክኒያቱም በነሱ እይታ መሠረት እነዚህ እጆችና እግሮች የሰው ሳይሆኑ የአማራ እጆችና እግሮች ናቸውና፡፡  የኦነግ አክራሪወች የአማራ ሬሳወችን በሞተር ሳይክል ሲገትቱ ምንም አይሰቀጥጣቸውም፣ ምክኒያቱም በነሱ እይታ መሠረት ሬሳወቹ የሰው ሳይሆኑ የአማራ ናቸውና፡፡  የኦነግ ታጣቂወች የአማራ ነፍሰጡሮችን ማሕጸኖች ሲዘረክቱ ድሪቶ የቀደዱ አይመስላቸውም፣ ምክኒያቱም በነሱ እይታ መሠረት የሚዘረክቱት የሰው ነፍሰጡሮችን ሳይሆን፣ የአማራ ነፍሰጡሮችን ነውና፡፡

ባጠቃላይ አነጋገር የአነግና የወያኔ አመራሮች በአማራ ሕዝብ ላይ ማናቸውንም ዓይነት ጭፍጨፋና ውድመት ሲፈጽሙና ሲያስፈጽሙ ደስታውን አይችሉትም፣ ምክኒያትም በነሱ እይታ መሠረት የሚጨፈጭፉትና የሚያወድሙት ሰውን ሳይሆን አማራን ነውና፡፡  ዐብይ አሕመድ ደግሞ ከነዚህ ዓይነት የኦነግና የወያኔ አመራሮች ጉያ ሥር የአማራን ጥላቻ እየተጋተ ያደገ የኦነግና የወያኔ ዲቃላ ነው፡፡  አወ፣ ዐብይ አሕመድ አማራን በጭራቅ አምሳል እንዲመለከት ተደርጎ የተቀረጸ የኦነግና የወያኔ ቅጥቅጥ ነው፡፡  አማራ ጭራቅ አድርጎ እንዲመለከት ስለተደረገ ደግሞ እጅጉን ይጠላዋል፣ በዚያው ልክ ደግሞ አጅጉን ይፈራዋል፡፡

በወለጋ አማሮች ላይ የሚካሄደው ዘግናኝ ጨፍጨፋ ለዐብይ አሕመድ ዴንታ አይሰጠውም፣ ምክኒያቱም በዐብይ አሕመድ እይታ መሠረት የሚጨፈጨፉት ሰወች ሳይሆኑ አማሮች ናቸውና፡፡  ለዚህ ነው በጭፍጨፋው ማዘኑን ለይምሰል ያህል እንኳን አንድም ጊዜ ያልገለጸው፡፡  በተቃራኒው ግን በጭፍጨፋው ዕለት ወይም ማግስት ሕንጻ እየመረቀ ወይም አበባ እየተከለ በጭፍጨፋው መደሰቱን በተግባር ይናገራል፡፡

ዐብይ አሕመድ የአማራን ሕዝብ በምን ዓይን እንደሚመለከት ፍንትው አድርጋ የምታሳየው ግን የኦነግ ጨፍጫፊወችን የወለጋ አርሶ አደሮች ለምን ይደግፏቸዋል ብለን መጠየቅ አለብን በማለት በፓርላማ ውስጥ እንደዋዛ የተናገራት ንግግር ናት፡፡  በዚች ንግግሩ ዐብይ አሕመድ ለማለት የፈለገው የአማራ ሕዝብ በዘግናኝ ሁኔታ በኦሮምያና በመከተል የሚጨፈጨፈው፣ በዘግናኝ ሁኔታ እንዲጨፈጨፍ የሚያበቁትን ወንጀሎች ስለሠራ ነው ነው፡፡  በሌላ አባባል በዐብይ አሕመድ እሳቤ መሠረት ኦነጋውያን አማራን የሚጨፈጨፉት ምክኒያት ስላላቸው ስለሆነ፣ ጥፋተኞቹ ተጨፍጫፊወቹ እንጅ ጨፍጫፊወቹ አይደሉም፡፡

ከሱማሌ ክልል ‹‹ተፈናቀሉ›› በሚል ሰበብ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ኦሮሞወችን አዲስ አበባ ላይ ኮንዶሚኒየም እየሰጠ በማስፈሩ ተኩራርቶ የተናገረው ዐብይ አሕመድ፣ ከኦነግ ጭፍጨፋ የተረፉትን የአማራ ተፈናቃዮች (በተለይም ደግሞ ሕጻናትንና አረጋውያንን) ግን በረኻ ለበረኻ እያንከራተተ በጠኔ እየጨረሳቸው ነው፡፡  ምክኒያቱም በሱ እይታ መሠረት ተፈናቃዮቹ ሰወች ሳይሆኑ አማሮች ናቸውና፡፡

ዐብይ አሕመድ ተራ ኦነጋዊ ቢሆን ኖሮ፣ በከረረ (chronic) የስነልቦና በሽታ የሚሰቃይ በሽተኛ ነው ተብሎ ተንቆ ይተው ነበር፡፡  ዐብይ አሕመድ ግን የጦቢያን በትረ መንግሥት የጨበጠ፣ አፉና ምግባሩ ሐራምና ቆቦ የሆነ፣ የኦነግ ኦቦ ነው፡፡  የአማራ ሕልውና ጥያቄ ውስጥ የገባው ደግሞ ይህ የአማራን ሕዝብ እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ጭራቅ የሚመለከት፣ የአኖሌን ሐውልት ለማስገንባት ከፍተኛ ሚና የተጫወተ፣ ኦነጋዊ አውሬ የጦቢያ መሪ በመሆኑ ነው፡፡

ስለዚህም የአማራ ሕዝብ ሕልውናውን ማስቀጠል የሚችለው ከዚህ ኦነጋዊ አውሬ ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቆ አውሬውን ከጫንቃው ላይ ካወረደ ብቻና ብቻ ነው፡፡  የአማራ ሕዝብ ዐብይ አሕመድን ከጫንቃው ላይ ካወረደ ደግሞ፣ ዐብይ አሕመድ ያዘላቸው ኦነግና ወያኔ አብረው ስለሚፈጠፈጡ፣ ባንድ ዲንጋ ሦስት ወፎች ያረግፋል፡፡

የአማራ ሕዝብ የሕልውናው ዋናው ጠላት ከሆነው ከዐብይ አሕመድ ጋር የሞት ሽረት ትግል የሚያደርገው ግን የሕልውናው ዋና ጠላት እሱና እሱ ብቻ መሆኑን ያለ ምንም ጥርጥር ተገንዝቦ፣ ውጉዝ ከመ አርዮስ እያለ፣ በጽኑ ሲያወግዘው ነው፡፡  በጽኑ ያላወገዝከውን በጽኑ አትታገለውም፡፡

ስለዚህም ለአማራ ሕልውና በጽኑ እየታገላችሁ ያላችሁ የሚዲያ ሰወች እባካችሁ ይሄን ጽኑ ጉዳይ በጽኑ አስቡበት፡፡  ለአማራ ሕዝብ አርዮስ የሆነውን ዐብይ አሕመድን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ዶክተር፣ እርስወ እያላችሁ በማይገባው ከበሬታ በመጥራት የሰውነት ባሕሪ እየሰጣችሁ፣ የአማራ ሕዝብ በዚህ አርዮስ ላይ ጨርሶ እንዳይቆርጥበት አታድርጉት፡፡

የአማራ ሕዝብ ዋና የሕልውና ጠላት በዐብይ አሕመድ ላይ የቆሙት ኦነግና ወያኔ ሳይሆኑ ራሱ ዐብይ አሕመድ መሆኑን የአማራ ሕዝብ ከገጠመኙ ቢያውቅም፣ እናንተ የሚዲያ ሰወች ስታንቆለጳጵሱት ግን ጥርጣሬ እንዲገባበትና ዋና ትኩረቱን ከዐብይ አሐመድ ላይ እንዲያዞር ታደርጋላችሁ፡፡  ዐብይ አሕመድ ደግሞ ሲዞሩበት እየትጥመለመለ ሲዞሩለት የሚናደፍ መሠሪ ዕባብ ስለሆነ፣ ፊቱን ወደ መናኛ ጠላቶቹ ያዞረውን የአማራን ሕዝብ ከጀርባው እየነደፈ መጨረሱን ይቀጥላል፡፡

በሕልውና ጦርነት ላይ ጨዋነት ትርጉም የለውም፣ ለዚያውም ደግሞ ጨዋ የሚለው ቃል በቋንቋው ውስጥ ስለሌለ ጨዋነትን ከፈሪነት ለሚቆጥር ኦነግንና ወያኔን ለመሰለ የሕልውና ጠላት፡፡  ዐብይ አሕመድ መጠራት ያለበት በተቀመጠበት መንበር ሳይሆን በግብሩ ነው፡፡  አይሁዶች የናዚ ጨፍጫፊወችን የሚጠሯቸው የኦሽዊትዝ አራጅ (the butcher of auschwitz)፣ የምንትሴ ቀርዳጅ እያሉ በስማቸው ሳይሆን በግብራቸው እንደሆነ ሁሉ፣ አነጋዊው ናዚ ዐብይ አሕመድም መጠራት ያለበት የወለጋው አራጅ፣ የመተከሉ አወራራጅ እየተባለ ነው፡፡  ኢትዮ360ወችና አዲስ ድምጾች ሰማችሁኝ?

 

መስፍን አረጋ

[email protected]

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop