ሕወሓት በኢሳያስ አፈወርቂና በተስፋፊ አማራ ልሂቃን ላይ እርምጃ ይወስዳል ሲሉ ዶ/ር ደብረጺዮን ተናገሩ

(ምንሊክ ሳልሳዊ)

የትግራይ ቴሌቭዥን ባወጣው ዘገባ መሰረት የትግራይ መንግስት ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የአማራ ሊሂቃን ከወራሪው አምባገነኑ ኢሳያስ ጋር በመወገን ያሳዩት ተግባር የባንዳነት ሚናቸው ያረጋገጠ ነው አሉ። ብሏል። ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከትግራይ ቴሌቪዝን ጋር በነበራቸው ቆይታ የአገሪቱን ነፃነት ለአምባገነኑ አሳልፈው የሰጡ የፖለቲካ ሃይሎች ዋነኛ ተጠያቂዎች ናቸው ብለዋል።

 የትግራይ ህዝብ ትግራይን ሙሉ በሙሉ ነፃ እስክትወጣ ድረስ ከወራሪው የአምባገነኑ ኢሳያስ ሆነው የባንዳነት ሚና እየፈፀመ ካለው ተስፋፊው የአማራ ሃይል የሚያደርገው ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የትግራይ መንግስት ፕሬዚዳንት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል እንደገለፁት ተስፋፊው የአማራ ሊሂቅ ከአምባገነኑ የኢሳይስ መንግስት ጋር ሆኖ በትግራይ እየፈፀመው ካለው ወረራ ባልተናነሰ የአምባገነኑ ኢሳያስ በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች እንደፈለገ ፈላጭ ቆራጭ ሲሆን አብዛኞቹ የፖለቲካ ሃይሎች ዝም ብለዋል፤ ከፊሎቹም ከአምባገነኑ ጋር ተባባሪ ሆነዋል፤ የሃገሪቱ ነፃነትን አሳልፈው የሰጡ የፖለቲካ ሃይሎች ዋነኛ ተጠያቂ ናቸው ብለዋል።

በዚህ ረገድ ተስፋፊው የአማራ ሊሂቅ በልዩ ሁኔታ ባንዳነቱን ያስመሰከረበት ጊዜ ላይ ነን ያለነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ ድርጊቱ ለሺ አመታት ነፃነትዋን ያስጠበቀች ሃገር የሚለውን አባባል ያፈረሰ መሆኑን ተግባር ገልፀዋል።

በአሁኑ ሰዓት ሁለቱም ተቃርኖ ያላቸው አካላት ህገ-መንግስትንና የፌደራል-ስርአቱን በማፍረስ እንቅፋት ይሆነናል ያሉትን የትግራይ ህዝብ ላይ ዘር የማጥፋት ወንጀል ከመፈፀም አልፈው በሕገ-ወጥ መንገድ የሃገሪቱ መሰረታዊ ጉዳዮች ለአምባገነኑ ኢሳያስ አሳልፈው በመስጠት አምባገነኑ በሀገሪቱ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ፈላጭ ቆራጭ እስከመሆን መድረሱን ገልፀዋል።

ቁልፍ ተቋማት በአምባገነኑ ስር መውደቃቸው፤ ወሰኔ ቀይ ባህር ነው የሚል አቋም የሚያራምደው ተስፋፊው የአማራ ሃይል ህገ- መንግስትንና የፌደራል-ስርአትን በማፍረስ አሃዳዊ ስርአትን ለመመለስ ኢትዮጵያን ለማዳከምና ለማፈራረስ እየሰራ ካለው አምባገነኑ ኢሳያስ ጋር በጥምረት እየሰሩ ነው ብለዋል ዶ/ር ደብረፅዩን ገ/ሚካኤል፤ ይሁንና ሁለቱም ሃይሎች የትግራይን ህዝብ ለማጥፋት ካላቸው ፍላጎትና ህገ-መንግስቱንና የፌደራል ስርአቱን በማፍረስ በሀገሪቱ አሃዳዊ አገዛዝን ለማስፈን በጥምረት ቢሰሩም በመካከላቸው ካለው መሰረታዊ ቅራኔ ቁርኝታቸው ዘለቂ እንደማይሆንና ሄዶ ሄዶ በግጭት እንደሚጠናቀቅ የሚታወቅ ነው ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ስለ የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያዊው ቅጂ ሙዚቃ ከቴዲ አፍሮ የተሰጠ መግለጫ፡ "ጉዞው ይቀጥላል!"

ተስፋፊው የአማራ ሊሂቅ በዚህ ወቅት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ቆርጦ ከተነሳው አምባገነኑ የኢሳያስ መንግስት ተቀናጅቶ በመንቀሳቀሱ ተባባሪ ከመሆን አልፎ ራሱ ገዳይና ጨፍጫፊ ሆኖ በትግራይ ህዝብ ላይ ወንጀሎች እየፈፀመ መሆኑንም ተናግረዋል።

በኤርትራ ይህ ነው የሚባል ስራ ያልሰራው አምባገነኑ የኢሳያስ መንግስትና የባንዴራ ፍቅር አለኝ እያለ ሃገሪቱን ለውጪ ወራሪ አሳልፎ የሚሰጥና ተባባሪ የሆነው የአማራ ሊሂቅ ተመሳሳይ የፖለቲካ ባህርይ እንዳላቸው ፕሬዚዳንቱ አብራርተዋል።

የትግራይ መንግስት ፕሬዚዳንት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካአኤል እንደገለፁት የትግራይ ህዝብ ድሮም ለወራሪዎች ተንበርክኮ አያውቅም አሁንም ወራሪዎች በሰላም ከትግራይ ጠቅልለው እስካልወጡ ድረስ ጠላቶቹን እያሳደደ የጀመረው ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል።

ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችም ከራሳቸው መሰረታዊ ጥቅም ተነስተው አምባገነኑን ኢሳይስ መዋጋት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የትግራይ መንግስት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ዓለም አቀፍ ማህበረ-ሰብ የአፍሪካ ቀንድን በማተራመስ የሚገኘውን አምባገነኑ የኢሳያስ ቡድን ላይ ተገቢውን እርምጃ ሊወሰድበት እንደሚገባ አሳሰቡ።

ኤርትራ ነፃ ሃገር ከሆነችበት ጊዜ ጀምሮ ጦርነትና ግጭት በመንቀሳቀስ የሚታወቀው አምባገነኑ የኢሳያስ መንግስት አከባቢውን በመበጥበጥ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር እየሰራ መሆኑን ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ገልፀዋል።

አምባገነኑ ኢሳያስ ከኤርትራ ህዝብ ጋር የማይመጣጠን ሰራዊት ገንብቶ ዋና ስራው ጦርነትና ግጭት አድርጎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም ተናግረዋል።

ይህ አምባገነን መሪ በሶማሊያ ከሚንቀሳቀሱ አሸባሪዎች ግንኝነት እንዳለው የጠቀሱት ዶ/ር ደብረፅዮን በሱዳን፣ በየመንና በኢትዮጵያ ችግር ፈጣሪ የሆኑ በድኖችን በማደራጀት በማስልጠንና በማስታጠቅ ግጭቶቹን ሲመራ መቆየቱ አስታውሰዋል፡፡

አያይዘውም ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ላይ ወረራ በማካሄዱ የተሸነፈው አምባገነኑ ኢሳያስ በተሸነፈበት አገር መጥቶ እንዳሻው ጦሩን የሚያዝ፣ የሚያዋጋ፣ ጦሩን ወደ ፈለገበት ቦታ የሚያሰማራ ኢኮኖሚው ላይ ጣልቃ እየገባ እንደፈለገ በሚያደርግበት ደረጃ ላይ መድረሱን ገልፀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኃይለማርያም “ኢትዮጵያዊነት ደምቋል” አሉ (VOA)

አምባገነኑ የኤርትራን ህዝብ ከማደህየት ውጭ ምንም እንዳልፈየደው የጠቆሙት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከኤርትራ አልፎ በትግራይ ባካሄደው ዘር የማጥፋት ወንጀል በተለያዩ የኢትዮጵያ አከባቢዎችም ሆነ በቀጠናው እያደረገ ባለው አተራማሽ ተግባር አለም አቀፍ ማህበረሰብ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ሁሌም ከጦርነት ውጪ መኖር የማይችለው አምባገነኑ ኢሳያስ ቀደም ሲል በፈፀመው የወረራ ተግባር ማእቀብ ተጥሎበት የነበረና አሁንም በአሜሪካ የተጣለበት ሆኖ ሳለ ማእቀብ አልፈራም በማለት የኢትዮጵያ መንግስትም ወደ ሰላም እንዳይመጣ ተግቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

ይህ ለኤርትራ ህዝብም፣ ለትግራይና ለኢትዮጵያ ህዝቦች የሰላምና የደህንነት ስጋት የሆነው አምባገነን መንግስትን በመታገል ረገድ የኤርትራ ህዝብ ቀዳሚውን ድርሻ እንዲያበረክት ጥሪ አድርገዋል።

የትግራይ ህዝብ ላይ ጀኖሳይድ የፈፀመውን የአምባገነኑ ኢሳያስ ወራሪ ሰራዊት ከቦታው እስካልለቀቀ ድረስ የትግራይ ህዝብ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።

1 Comment

  1. ምን ታደርግ አብይ ተባባሪህ በመሆኑ እንቅልፍ የጣላቸውን የኢትዮጵያ ልጆችን ማረድህን ረስተኸዋል። አማራ ምን ያድርግህ የኢትዮጵያን ወታደር ካረድክ በሗላ በሳምሪ አማካይነት አማራውን አርደህ በላኸው ከዚህ በላይ ምን ፈሉግህ? የምን ተስፋፊን አመጣህ? አገኘሁ ተሻገርን የመሰሉ ሰካራሞች አለችሎታቸው እላይ ቁጭ ብለው አማራን መጫወቻ አድርገውታል እንደዚህ ግን ሊቀጥል አይችልም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share