ወላሂ ኢትዮጵያን ከልቤ እወዳታለሁ – የአፋሯ ልዩ ኃይል ሐዋ መሀመድ

”ወላሂ አሁንም ኢትዮጵያን ከልቤ እወዳታለሁ፣ በጦርነት ወቅት በደረሰብኝ ጉዳት ምክንያት አልፎ አልፎ ይጥለኛል፣ አይኔም እንደቀደመው ማየት ተስኖታል“
የአፋሯ ልዩ ኃይል ሐዋ መሀመድ
ኢትዮጵያ ”ወላሂ ኢትዮጵያን እወዳታለሁ“ የሚለው ንግግሯ በሁላችንም ልብ ታትሟል፡፡ የአፋርን ልዩ ኃይል ስትቀላቀል ስምንተኛ ክፍለ ነበረች፡፡ ህዋኃት አፋርን ሲወር ከሀገር በላይ ምንም የለም በማለት ደብተሯን አስቀምጣ፣ ጠመንጃ በመያዝ ህወኃትን ፊት ለፊት ተጋፍጣለች ፣ የአፋሯ ልዩ ኃይል ሐዋ መሀመድ ፡፡
ሀዋ ካደገችበት ቀየዋ ብቻ በአሸባሪው ህዋሃት 58 ሰዎች ተገድለዋል፣ከመቶ በላይ ደግሞ ቆስለዋል፡፡ ሀዘኑ ገና ከልቧ ባይወጣም ህዋሃትን ለመታገል ግን አሁንም ቁርጠኛ ነኝ
ትላለች፡፡
”ኢትዮጵያን ከልቤ እወዳታለሁ፣ አሁንም ቢሆን መስዋእት ለመክፈል ዝግጁ ነኝ“ የምትለው ጀግናዋ የአፋር ልዩ ኃይል በጦርነት ወቅት በደረሰባት ጉዳት አልፎ አልፎ ይጥላታል፡፡
”አይኔም እንደቀደመው ማየት ተስኖታል“ ትላለች ፡፡ ትናንት ለብዙዎች ነጻነት የተዋደችው ሐዋ፤ ከህመሟ አገግማ ትምህርቷን መቀጠል እና ኢንጅነር መሆን የወደፊት ህልሟ ነው፡፡ ሐዋ የእኛን ህመም ነው የታመመችው ፡፡ የደማችውም፣ የቆሰለችውም ለእኛ ነጻነት ነው፡፡ ስለሆነም በቃል ሳይሆን በተግባር ኢትዮጵያን እንወዳለን የምንል ሁሉ ከጀግናዋ የአፋር ልዩ ኃይል ሐዋ መሀመድን ጎን በመቆም አለኝታነታችንን እናረጋግጥ፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:  ጎጃም ተጋድሎው ተቀጣጥሏል | በአማራ በበርካታ ቦታዎች ውጊያዎች እየተደረጉ ነው፥ ትልልቅ ከተሞች በፋኖ እጅ ገብተዋል፥ የአምኒስቲ ሪፖርት፥ ኮሬ ነጌኛ፥ ሀዋሳ ሀዘን ላይ ናት

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share